Jems awol

Jems awol

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jems awol, al Rawda, Al Ain.

ከቁርአን እና ሱና የተቀየሩ እውነተኛ የእስልምና ትምህርቶችን፣ ሀዲቶችን፣ አውዶችን እና ታሪኮችን እናቀርባለን። በእምነት እና እውቀት አብረን እንድንድግ ተቀላቀሉ።نشارككم المعرفة الإسلامية الصحيحة من القرآن والسنة، مع تذكيرات يومية، أحاديث، آيات، وتاريخ إسلامي. انضموا إلينا لننمو معاً في الإيمان والعلم.

07/04/2026

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ አውጭዎች ትራምፕ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠየቁ

የአሜሪካ ህግ አውጪዎች የትራምፕ አስተዳደር አባላት ፕሬዚዳንቱ ማንሳት ካልቻሉ የስልጣን ሽግግር የሚደነግገውን 25ኛውን የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ በማድረግ ከስልጣን እንዲያነሱት እየጠየቁ ይገኛል፡፡

የአሪዞና ኮንግረስ አባል የሆነችዉ ያሳሚን አንሳሪ 25ኛው ማሻሻያ በትራምፕ ላይ እንዲተገበር ጥሪ ካቀረቡት ባለስልጣን መካከል ናቸዉ፡

" ትራምፕ አስከፊ፣ ህገወጥ ጦርነት እያባባሱ ነው፣ ግዙፍ የጦር ወንጀሎችን እያስፈራሩ እና በኢራን ውስጥ የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ኢላማ አድርገዋል ብላለች።

ባለፉት 48 ሰአታት ውስጥ ብቻ ትራምፕ ያስተላለፉት ንግግር ሁሉንም መስመር አልፏል" በማለት አንሳሪ በኤክስ ገጿ ላይ አስፍራለች፡፡

የሚኒሶታዋ የኮንግረስት ሴት ኢልሃን ኦማርም ትራምፕ በኢራን ውስጥ ባሉ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ለሰነዘሩት ዛቻ በሰጡት አስተያየት፣ “ይህ ያልተነካ እብድ ከስልጣን መወገድ አለበት” ብለዋል።

የኒው ሜክሲኮ ግዛት ኮንግረስ አባል የሆነችዉ ሜላኒ ስታንስበሪ የስልጣን ሽግግር የሚደነግገውን 25ኛውን የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ ተግባራዊ መሆን ያለበት አሁን ነዉ፤ ኮንግረሱ እና ካቢኔው እርምጃ መውሰድ አለባቸው ብላለች።

የኢሊኖው የቀድሞ የሪፐብሊካን ኮንግረስ አባል ጆ ዋልሽ ስለ ትራምፕም ባሰፈሩት መልዕክት “በዚች ሀገር ላይ ለዘላለም ጉድፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

የዲሞክራቲክ ሴኔት አባል የሆኑት ክሪስ መርፊ በኤክስ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “እኔ በትራምፕ ካቢኔ ውስጥ ብሆን ኖሮ የስልጣን ሽግግር የሚደነግገውን 25ኛውን የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ የሕገ መንግሥት ጠበቆችን በመጥራት ይህን ዉሳኔ አሳልፋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።
💞
:
Ibnuali Al Alyu

07/04/2026

የቀይ ባሕር የብስራት ዜና!

የቀይ ባሕር አዲሱ ምዕራፍ፦ አካታችነት፣ የኢትዮጵያ ሚና እና የቀጠናው የጋራ ህልውና፣

በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ዙሪያ "አካታችነትና ትብብር ለጋራ ጥቅም" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የምክክር መድረክ፣ በቀጠናው ለዘመናት የቆየውን "የባሕር ዳርቻ አገራት ብቻ ባለቤትነት" ትረካ የሚቀይር ታሪካዊ እርምጃ ነው።

ይህ መድረክ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የማይተካ ሚና እና የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄዋን ከግል ፍላጎት ባለፈ ለቀጠናው ሰላም ዋስትና መሆኑን በይፋ ያረጋገጠ ነው።

ይህ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አስተዳደር ዙሪያ የተጀመረውን ሰፊ የምክክር መድረክ መነሻ በማድረግ፣ የኢትዮጵያን ስልታዊ ፍላጎቶችና ቀጠናዊ ፋይዳዋን የሚመረምር የ MS NEWS ልዩ ስትራቴጂያዊ ትንታኔ ነው፦

# ከአግላይነት ወደ አካታችነት፦
ላለፉት ረጅም ዓመታት የቀይ ባሕር አስተዳደር ጥቂት የባሕር ዳርቻ አገራት ላይ ብቻ ተወስኖ መቆየቱ፣ ቀጠናውን ለውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ለደኅንነት ስጋቶች ተጋላጭ አድርጎታል።

አሁን የተጀመረው ውይይት እንደሚያሳየው፣ ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ የሚታሰብ ማንኛውም የቀይ ባሕር ስምምነት ዘላቂ ሰላምን ሊያመጣ አይችልም።

ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላት ግዙፍ የሕዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣው ኢኮኖሚዋ እና ወታደራዊ አቅሟ በቀይ ባሕር አስተዳደር ውስጥ "ባለድርሻ" እንድትሆን ተፈጥሯዊ ግዴታ ይጥላል።

# የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ፦
ኢትዮጵያ ሉዓላዊ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ተራ የንግድ መውጫ ፍለጋ ሳይሆን፣ የሀገርን ሕልውና የማረጋገጥና ታሪካዊ ፍትሕን የመመለስ ጉዳይ ነው።

# ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ጋር የተሳሰረውን ራዕይ ስንመለከት፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከአህጉራዊው የ2063 አጀንዳ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም ነው።

አጀንዳው "የተቀናጀች፣ የበለጸገችና ሰላማዊት አፍሪካን" ለመገንባት በሚያልመው መሠረት፣ የውስጥ ለውስጥ የንግድ ትስስርን (AfCFTA) ለማሳለጥ የኢትዮጵያ ወደብ ባለቤት መሆን ወሳኝ ሞተር ነው።

ይህ ጥረት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣ ለጎረቤት አገራትም አዲስ የንግድ አማራጭና የጋራ ብልጽግናን ይዞ የሚመጣ ነው።

# የ MS NEWS ማጠቃለያ፣
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የጀመሩት የባሕር በር የማግኘት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አሁን ፍሬ እያፈራ ይገኛል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና የቀጠናው አገራት የኢትዮጵያን አስፈላጊነት መረዳታቸው ትልቅ ድል ነው።

# ለዲፕሎማቶቻችን፦ ብልሃት የተሞላበትና "ሰጥቶ መቀበልን" መሠረት ያደረገ ድርድራችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ፤ መንገዱ ቀልሏል።

# ለሕዝባችን፦ ይህ የታሪክ አጋጣሚ የትውልድ ዕዳን የምንከፍልበት በመሆኑ፣ በአንድነትና በጽናት መቆም ይገባናል።

በጥቅሉ ቀይ ባሕር የጥቂቶች የግል ንብረት ሳይሆን፣ የሁላችንም የጋራ ሀብትና የሰላም ድልድይ ሊሆን ይገባዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ተፈጥሯዊ የባሕር በሯ መመለሷ በቀጠናው ላይ አዲስ የብልጽግና ብርሃን ይፈነጥቃል።

ውድ አንባቢዎቼ የእርስዎ አስተያየት፦
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አስተዳደር ውስጥ ያላት ተሳትፎ መጠናከሩ ለጎረቤት አገራት የሚኖረው ፋይዳ ምንድን ነው ይላሉ?

"የቀይ ባሕር ጸጥታ ያለ ኢትዮጵያ ሙሉ አይሆንም!"

"MS NEWS" - ከመረጃ ባሻገር!
🌐 www.mechal.org.et

በመሐመድ ስራጅ
(ጋዜጠኛ፣ የጂኦ-ፖለቲካና የማኅበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ)

Photos from Jems awol's post 07/04/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እንድሁም ሞዴል መንደር ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ተጠናክረው ቀጥሏል።

‎በዛሬው ዕለት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በዛላ ቀበሌ በመንደር 39 ለሚገኙ ነዋሪዎች የእንቁላል ዶሮ ስርጭት ተደርጓል።

‎ በየቤቱ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የቤተሰብ ብልጽግናንና የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ስራ ትልቅ ሚና እንዳለዉ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ በዶሮ ስርጭት ወቅት ተገኝተው አስገንዝበዋል።

‎የተሰራጩት ዶሮዎች የታለመላቸውን ግብ እያሳኩ መሆኑን በየጊዜው በዘርፉ ባለሙያዎች ክትትልና ድጋፍ መደረግ እንዳለበትም አቶ አ/መጅድ አሳስቧል።

‎ በሌሎች የሌማት ትሩፋት ዘርፎች እንደ ወተትና ማር ምርት እንድሁም የጓሮ አትክልት ያሉ ስራዎችንም በተመሳሳይ መልኩ ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መላኩ ወ/ኪዳንና ሌሎች የከተማ አስተዳደር አመራሮችና ና ባለሙያዎች በስርጭት መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ.ጽ.ቤት

07/04/2026

ሰበር ዜና አሁን ስዓት ኢራን ዝግጁ እያደረገች ያለው ኢራን የደብቀችዉን ከ4000 ኪሎሜትር ፦ 5500 ኪሎሜትር እና እስከ አሰር ሺህ ኪሎሜትሮች በሰኮንድ ውስጥ ወደ ገሀነም የሚቀይሩ ማርሽ ቀያር ሚሳኤሎች ለመጠቀም የአሜሪካ ጥቃት እየተጠባበቁ ይገኛሉ ።🇮🇷🇮🇷 ጋር አላህ ይሁን 🇮🇷🇮🇷
Salih

Photos from Jems awol's post 07/04/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ቀበሌ የ2018 ዓ.ም ምርት ዘመን በመደበኛ በልግ የበቆሎ ዘር ተዘራ

መጋቢት፣29/2018 በዌራ ዲጆ ወረዳ ኡዳና ጮሎቅሳ ቀበሌ የ2018 ዓ.ም ምርት ዘመን በመደበኛ በልግ የበቆሎ ዘር የመዝራት ተጠናክረው ቀጥሎዋል !!

05/04/2026

📌48 ሰዓት እንደገና‼️

📌በደቡባዊ ኢራን ሰማይ ላይ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች መመታታቸውን ተከትሎ ቀውሱ ይበልጥ ተባብሷል። ኢራን አንዱን ኤፍ-15 ኢ (F-15E) የተባለ ተዋጊ ጄት መትታ የጣለች ሲሆን አብራሪው ቢድንም የጦር መሣሪያ መኮንኑ እስካሁን አልተገኘም። እሱን ለመፈለግ የተሰማራ ሌላ ኤ-10 (A-10) የጦር አውሮፕላንም በተመሳሳይ ተመትቶ ወድቋል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በጠፋው ወታደር ዙሪያ ፍለጋ እያደረጉ ሲሆን ኢራን ወታደሩን በሕይወት ላገኘ አካል ከፍተኛ ሽልማት እንደምትሰጥ በማወጅ የስነ-ልቦና ጫና ለመፍጠር እየሞከረች ትገኛለች።

📌በፖለቲካው ረገድ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኢራን የ48 ሰዓት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ኢራን ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የነዳጅ ማስተላለፊያ ሰርጥ በአስቸኳይ ካልከፈተች ወይም የሰላም ስምምነት ላይ ካልደረሰች አሜሪካ እጅግ አስከፊ ጥቃት እንደምትሰነዝር ዝተዋል። ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ገና ዋናውን ጥቃት እንዳልጀመረች በመግለጽ የኢራንን የነዳጅ ሀብት የመቆጣጠር ፍላጎት እንዳላቸውም በግልጽ ተናግረዋል። ይህ የ48 ሰዓት ገደብ የሚያበቃው April 6 ቀን ይሆናል።

📌በሌላ በኩል የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በኢራን የኢንዱስትሪ እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው። በቡሸር የኑክሌር ጣቢያ አቅራቢያ በደረሰ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ኢራንም በበኩሏ በእስራኤል ከተሞች ላይ የአጸፋ ሚሳይል ጥቃቶችን ሰንዝራለች።

©SMN

26/03/2026

Bizabee - Create Landing Pages in Seconds 23/03/2026

https://buzland.co/l/jemal-online-store

Bizabee - Create Landing Pages in Seconds Bizabee - AI-powered landing page builder. Create beautiful, professional landing pages in seconds. No coding, no templates, just describe what you need.

17/02/2026

#رمضان

26/08/2025

🎊🎈🍾

ግድብ እውን ሆኗል

ይድረስ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ!

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሰላም መጠናቀቁን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

ለዘመናት የቆየው የትውልድ ህልም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ውሳኔና አንድነት ውጤት የሆነው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት፣ አሁን በታሪክ ማህደር ውስጥ ስሙን አስፍሯል።

ይህ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት ብቻ አይደለም። የብዙሃን ኢትዮጵያውያንን ላብ፣ ደም እና ህይወት ዋጋ የተቀመጠበት፣ በጋራ መቆም እና መቻል የሚለውን መርህ ያስመሰከረ የድል አድራጊነት ማሳያ ነው።

በቅርቡ ከሀገራችን ወዳጆች ጋር በመሆን በደማቅ ስነ-ስርዓት የሚመረቅ ሲሆን፣ የግድቡ ግንባታ ማሽነሪዎች ደግሞ ወደ አዲስ የአባይ ፕሮጀክት እየተጓዙ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህ የህዳሴው ዘመን የአርበኝነት ታሪክ፣ ለመጪው ትውልድ ትልቅ ትምህርት እና የኩራት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ታሪካዊ ክስተት ነው።

እንኳን ደስ አለን በድጋሚ

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

04/07/2025

ሲደክምሺ እፍ አትበይ
አልሐምዱሊላህ በይ
አመስጋኝ ባሪያ ሁኝ!!
ሙስሊም ጌታውን አመስጋኝ ባሪያ ነው።

ሙዕሚን ቢደክመው፣ ቢርበው ፣ችግር ቢደርስበት
ፈተናወች ቢደራረቡበት አላህን አመስጋኝ ነው!!
ሙስሊሞች ምንም ይድረስባቸው ሰው ሲጠይቃቸው የመጀመሪያ ምላሻቸው አል-ሐምዱሊላህ ነው ምናልባት ከዛ በኋላ ችግራቸውን ሊናገሩ ይችላሉ!!
«አልሐምዱሊላህ አላኩሊሀል!!

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Al Ain?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Al Rawda
Al Ain