Solomon Shiferaw
YouTube
ዓይን ያወጣ ጥንቆላ እዩልኝ ብቻ
14/12/2022
ቤተክርስቲያን በህግ ውርጋጥ ፓስተሮችን እንደምትጠይቅ ተገለጠ። በህግ የማይጠቁ ከሆነ አባቶች ኦርቶዶክሳዊያን አንገታችሁን ለመስጠት ተዘጋጁ ብለዋል። አንገት ሲሰጥ አንገት ይዞ መውደቅ እንዳለም በአጽንኦት አስገንዝበዋል። በቦታው የተገኙ አቦታችና ምዕምናን ስሜታቸውን በእምባ ገልጠዋል።
ፈታ በሉ
በአንድ ሳምንት የሚያስወልድ ፓስተር። ዶሮ እንኳ ታቅፋ ለመፈልፈል ሦስት ሳምንት ትፈጃለች።ማይሰማ ጉድ እንደሆን የለም።
አስተማሪና አዝናኚ ቪዲዮ
እናስተውል
የዚህን ሰውዬ አካሄድ ተመልከቱልኝ። በኢንተርኔት ከሲዖል ነፍሳትን አወጣሁ እያለ ራሱን እንዴት እንደሚክብ። ፌስቡኬ ላይ እንዳልፖስት ስለተከለከልኩ ይህን ፔጅ ቤተሰብ ሁኑ።
እጅግ በጣም አንጀት የሚበላ የሰቆቃ ጥሪ። የእኚህን አባት ተማጽኖ ስሰማ አንጀቴ ተላወሰ።ወንድ ልጅ እንዲህ እዬዬ ሲል ያማል።
ወሎ ገራገሩ
እጅግ ልብ የሚነካ ህፃን። በቤተክርስቲያን በር ላይ ተንበርክኮ ፈጣሪን ሲለምን። ቆይ አሁን ይህ ብላቴና ምን አሳስቦት ይሆን እንዲህ ፈጣሪን የሚማጸነው?
ማይሰማ የለም።
12/04/2022
ደጉ ባላገሩን ተውት
እጃቸው አመድ አፋሽ ሆኖ እንጂ በአጎረሱ አይነከሱም ነበር። ሰው አእምሮውን ካልሳተ በቀር የበላበትን ወጭት አይሰብርም። ልጄ ዘጠኝ ወር በአረገዝኩህ ማህፀኔ፣ በተሸከምኩክ ጀርባዬ እየተባለ ሰይፍ በእናቶቹ ላይ አይመዝም ነበር።ወዳጄ ሰላም፣ ፍቅር፣ መልካምነት፣ ትህትና እና ደግነትን የምታገኘው ከገራገሩ መንደር ከባላገሩ ነው። አራሹን ገበሬ ገፍተንና ጠልተን በቆሸሸ ፖለቲካችን እንደ በግ በየ ቀኑ ደሙን እያፈሰስን ተቅበዝባዥ እየሆንን ነው።ከትላንቱ ዛሬ ይሻላል ብንል የባሰ እየመጣ መከራችንና ሰቆቃችን እየጨመረ ነው። ደጉ ገበሬ መዳበሪያ እንኳ እንዳይደርሰው ተከልክሏል። አምና ከሚገዛበት ዘንድሮ አምስት እጥፍ ጨምሯል። አምና 1000ብር የሚገዛውን ዘንድሮ 5000 ብር ግዛ ተብሏል። አስቡት ሁለት ሦስት ቁንጣ ማዳበሪያ የሚገዛ ገበሬን። ምን 10,000 እና ከዛ በላይ ለማዳበሪያ ካወጣ ምን ያገኛል? ምክኛቱም ተጨማሪ ልፋት አለበት፣ የአረም መድኃኒት አለበት፣ የዘር አለበት። ይህን የማቅረብ የመንግስት ግዴታ ሆኖ ሳለ ለፖለቲካ ፍጆታ የተመረጡ ጥቂት ሄክታሮች ላይ የተተከሉና የተዘሩትን እህሎች እያሳዩ በኩታ ገጠም ይህን ያህል አመረትን ቢሉ እውነትና ፀሐይ እያደር ይጠራል እንደሚባለው ቀጣይ አመት የሚፈጠረውን ታዩታላችሁ። ይህን ስላችሁ ዝም ብዬ አይደለም። ለምሳሌ እኔ ሰፊ የእርሻ መሬት ነበረኝ። የእኩል ሰጥቼ እያሰራሁ ነበር። አሁን ላይ የእኩል የሚሰሩት አንፈልግም መሬቱን ተረከበን ነው ያሉኝ። ምነው ስላቸው ይህን ያህል ወጪ አውጥተን በጣም ቢለማ ራሱ ዋናችንን አይመልስም በዛ ላይ ቢጠፋ ደግሞ አስበው አሉኝ። በእነሱ ቦታ ሆኜ ሳስበው ስጋታቸውን ተረዳሁት። የገበሬውን ጭንቀት ተመለከትኩ። ለመጀመሪያ ጊዜ ደጉ ባላገሩ ተስፋ ወደ መቁረጥ ሲያመራ አይቼ አዘንኩ። በጣም እጅግ በጣም ምስኪኑ የዋሁ ገበሬ ተጎሳቁሏል። እንኳን ለሰው እንሰሳትን ጡታቸውን አጥብተው ተንከባክበው የሚያሳድጉት ዛሬ በቆሸሸ ፖለቲካ ለችግር ተጋልጠዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
0000