Amanuel mabru ugamo

Amanuel mabru ugamo

Share

ለነገ አትጨነቅ ነገ ለራሱ ይጨነቅ

06/04/2026

ነገ መልካም ይሆናል።

07/07/2025

ክቡርነትዎ ስትሰርቁ ለጎሳ አላካፈላችሁም ስትያዙ ምስክን ጎሳን መሰብሰብ ትንሽ አይዛንዛቦትም🙄?

26/06/2025

እግዚአብሔር አለ🙌

16/06/2025

ለአንዳንዶች ህይወት የተለየ ትርጉም አላት። ከጸሃይ መውጣት መግባት ባሻገር፤ ከክረምት በጋ መፈራረቅ ባሻገር፤ ህይወት የሆነ የተለየ ትርጉም አላት።

እኝህ ሰዎች ለአቅማቸው ግድብ አያበጁም፤ ታላቅ ለመሆን የሌሎች ሰዎችን ፈቃድ አይጠይቁም፤ የተፈጠሩት ለሆነ አላማ እንደሆነ ያምናሉ።

የተቀበረውን ችሎታቸውን ለማውጣት ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይጥራሉ። መውደቅ ማለት የአላማቸው ማክተም ሳይሆን፤ ይበልጥ የሚጠነክሩበት እና ገዝፈው የሚመጡብት እድል ነው።

አመንም አላመንም ታላቅነት በሁላችንም ውስጥ ያለ ነገር ነው። ደስተኛ በሆኑት እና ባልሆኑት፤ ስኬታማ በሆኑት እና ባልሆኑት፤ በአሸናፊዎች እና በተሸናፊዎች መካከል ያለው ልዩነት የአስተሳሰብ ልዩነት ብቻ እንደሆነ የተረጋገጠ እውነታ ነው።

ስለዚህ ተስፋ አትቁረጡ፥ ተበደልን ብላችሁ ከእቅዳችሁ ፈቀቅ አትበሉ ፥ ያላችሁን አቅም አሟጣችሁ ተጠቅማችሁ እንደምትችሉ አሳዩአቸው።

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው!!
አሜን 🙏🙏

04/10/2024

አንዲት ሴት ብዙ አመታት ስሟን አጥታ በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ምንም ብርሃን በሌለበት ጨለማ ውስጥ ተዘፍቃ ቆይታ ነበረች። ፈጣር ይሄንን ጉስቁልናዋን አይቶ ይሄንን ደሳሳ ጎጆዋን ልያነሳ አሰበላትና ታላቅ አውሎ ንፋስ ነፈሰ።

ደሳሳ ጎጆዋን ጠራርጎ ይዞ ይሄዳል ይህች ሴትዮ ተስፋ ቆረጠችና ወደ ፈጣር እንባ እያፈሰሰች መቼ ነው ከጎሮቤቶቸ ጋር እኩል የሚሆነው ፣መቼ ነው ለብሼ ተውበ የሚሄደው ብላ መራራ ለቅሶ አለቀሰች።
ይህ እንባ በፈጣሪ ዘንድ ደርሶ ዘመን መጣላት።

ታዲያ ለዚህች ሴትዮ ያማረ ቤት ፣የተመቻቸ ኑሮ እንድትኖር ፣ ከጉስቁልና አለም የሚያወጣትን አንድ ታላቅ ሰው ተፈለገ። ከብዙ ፍለጋ በኃላ ተገኘ።

ያንን ሰው ገዥው ጠርቶት እንድህ አለው ይህችን ሴትዮ ካለችበት ጉስቁልና ማውጣት የሚትችለው አንተ ብቻ ነህ ስለዚህ አድናት ብሎ አጥብቆ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ይህ ሰው ግራ ተጋባ እኔ እንዴት ነው ከዚህ ሁሉ ነገር የሚያወጣት ብሎ በውስጡ ተረበሸ።

በመጨረሻ ላይ አንድ ነገር ታየው ፈጣር ከእኔ ጋር ከሆነ ይህችን ሴት ከራሷ አልፎ ለልጆቿ እሆንላታለው ብሎ ለራሱ ቃል ገባ።

ከዛ በኃላ ለፈጣሪ ፀሎት አነሳ ጌታ ሆይ ለዚህች ሴት ቤቷን እና ህይወቷን፣ የተመቻቸ ኑሮ ላኖራት ትዕዛዝ ተላልፎብኛል እኔም ደግሞ በአንተ አምኜ ቃል ገብቻለሁና እርዳኝ ብሎ ወደ ፈጣር በታላቅ ድምፅ ጮሄ።

ፈጣርም ጩሄቱን ሰምቶ ምድርቱን ጨለምለም አደረገ በሰማይ ላይ ከባድ ድምፅ ተሰማ ሃይለኛ ዝናብ ዘነበ። ጎርፉ አሸዋ እና ድንጋይ ይዞ መጣ፣ ያ ሰው አሸዋን ጠራርጎ በድንጋይ የማይፈርስ ቤት ሰራላት።

ሴትየዋ ነገሩ (መብረቅ) ሆኖባት (ተመስገን) ከእኔም አልፎ ለልጆቸ (ተረፈ) አለች።

መብረቅ ተመስገን ተረፈ❤❤

ወ/ገነት እንደ ስሟ ገነት ሆና ትልማ።

አማኑኤል ነኝ ከወንዶ ገነት

14/07/2024

#አንዳንድ ጊዜ ከምታስበው ውጪ ማሰብ ልመድ። ተመሳሳይ የሆነ የህይወት ዘይቤን አትከተል። እቅድ ስታወጣ አንዳንድ ጊዜ የእብድ እቅድ አውጣ። ብዙዎች እንደሚያቅዱት አታቅድ።
። እስቲ አይምሮህ ምን መፍጠር እንደሚችል እየው። ካንት እቅድ ውጣ ከዛም የህይወትን እቅድ አቅድ።

#ሚስጥሩ ያለው ቀላሉን ያንተን የህይወት እቅድ ትተህ አስቸጋሪ እና ከባድ ነው የሚባለውን ትክክለኛ የህይወት እቅድ አውጣ። እሾህ ድንጋይ ምናምን እንዲያቆምህ አትፍቀድ። ሁለት ሰዎች ከመሬት ግራቪቲ በላይ አይሮፕላን የሠሩት አይደፈርም የተባለውን የፊዚክስ ህግ ደፍረው ነው። ስለዚህ ደፋር ሆነህ የደፋር እቅድ አውጣ።

#በዘመንህ የቅጥር ሰራተኛ የሚባለውን ሀሳብ ሰርዘው። አይምሮህን ለፈጠራ ተጠቀምበት። የትም አደርስም ያሉህን የህይወት ስኬት ላይ ደርሰህ አስደንግጣቸው።

#ይሄን ፅሁፍ ምታነበው አንተ በራስህ ላይ እምነት ከሌለህ፤እኔ ባንተ ላይ እምነት አለኝ። አንተ እራስህን ከምታምነው በላይ እኔ ባንተ እምነት አለኝ። አሁን ጊዜው ነው ተነስና አስብ።

#ጉልበትህን ሳይሆን አይምሮህን ተጠቀም። አመሠግናለሁ🙏🙏🙏

25/03/2024

Loonsohu lophanno tewaantannireno afiranno. Konni beetti haja illacha tunge la'nannite.

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa