Arada Subcity Health Offic

Arada Subcity Health Offic

Share

Holistic ,Unversal and equitable Health Service

22/01/2026
Photos from Arada Subcity Health Offic's post 30/01/2024

ብሔራዊ ገዥ ትርክት ልክ እንደ ዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ በተሰናሰለ የብሔር-ብሔረሰቦች ላብ እና ደም ድምር ዉጤት የተገነባችና በወል ጥረቶቻቸው የምትበለጽግ ሀገር ናት ማለታችን ነዉ።

Photos from Arada Subcity Health Offic's post 28/01/2024

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ አቅጣጫ፣ የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሪፎርም እና ስታንዳርድ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ረቂቅ ማዕቀፍ ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
___________

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ አቅጣጫ፣ የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሪፎርም እና ስታንዳርድ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ረቂቅ ማዕቀፍ ላይ የጤና ሙያ ማህበራት፣ አጋር ድርጅቶች ፣ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ የተካሄደው በብቃትና ምዘና ሪፎርም ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲሆን በተቋሙ የተዘጋጀውን የጤናው ዘርፍ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ረቂቅ ማዕቀፍ ላይ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑ ታውቋል።

በጤና ሚኒስቴር የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ደምሴ መድረኩን ባስጀመሩ ጊዜ እንደተናገሩት መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም እንደ አንድ አጀንዳ ይዞ እየሠራ ነው። ከሪፎርሙ ሰባት ምሶሶዎች መካከል አንዱ የሆነውን የሲቪል ሰርቪስ የብቃት ማረጋገጫ ሪፎርም፣ ተወዳዳሪና ብቁ የሆነ ሠራተኛ በተገቢው ቦታ ተመድቦ የሚፈለገው ዓይነት አገልግሎት መሥጠት እንዲችል እንዲሁም ሠራተኛውን የማብቃት አላማ ያደረገ ነው።

አቶ ሀብታሙ የጤና ዘርፍ የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕቀፍ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በመድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ መድረክ የጤና ሙያ ማህበራት፣ አጋር ድርጅቶች፣ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እንዲሁም የስራና ክህሎት ሚኒስትር በማዕቀፉ ዙርያ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲይዙ እና የሚሰጡትን ግብዕት በመሰብሠብ የማዕቀፍ ሠነዱን ለማዳበር ታስቦ መድረኩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

አቶ ሀብታሙ የባለድርሻ አካላቱ የጋራ ግንዛቤ በመጨበጥ ለረቂቅ ማእቀፉ ግብአት የሚሆኑ አስተያየቶች እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሠራተኞች ብቃትና ምዘና ስራ አመራር ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ይማነ ሀይሉ ከተሳታፊዎች በተነሱ ሃሳቦች ላይ ማብራሪያ በሠጡበት ጊዜ እንደተናገሩት የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሪፎርም ጉዳይ በፈተና የመውደቅና የማለፍ ጉዳይ ሳይሆን የመፈጸም አቅም ጉዳይ ነው። የፈጻሚውን የብቃት ክፍተት የመለየት፣ በአፈጻጸም የሚታይ ክፍተትን በስልጠና የመሙላት አላማ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ አቅጣጫ፣ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ሪፎርም እና ስታንዳርድ እንዲሁም በጤናው ዘርፍ የሰው ሀብት ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ረቂቅ ማዕቀፍ በመድረኩ የቀረቡ ሠነዶች ሲሆኑ ሠፋ ያለ ውይይት ተደርጓባቸዋል።

Photos from Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን's post 04/01/2024
30/12/2023

የወል ትርክት ለወል ሀገር!

ብልፅግና ፓርቲ ነጠላ ትርክቶች በመሀላቸው ያለውን የሀሳብ ክፍተት ከመሙላት ይልቅ የበለጠ የሀሳብ ልዩነት እንዲፈጠር ሰበብ አስባብ የሚፈልጉ እንደመሆናቸው መጠን ለወል ሀገር ግንባታ መሰናክል ናቸው ብሎ ያምናል። በመሆኑም ብሄራዊነት የተሰኘ አሰባሳቢ ሀገራዊ ትርክት ይዞ የተነሳ ፓርቲ ነው።

ይህ ታላቁ ትርክት መከፋፈልና መገፋፋትን በመሻገር ትብብርና መሰባሰብን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ከፖለቲካ ፓርቲ የተሻገረ ሀገራዊ ጠቀሜታ አለው።

ኢትዮጵያ ከአንድ ፖለቲካ አመለካከት በላይ የሆነች የተከበረች ሀገራችን ነች። የፖለቲካ አመለካከት የፖሊሲ አማራጭ ጉዳይ ስለሆነ በፖለቲካ ፓርቲ የተደራጁ ሀይሎች በሚያራምዱት የፖሊሲ አማራጭ የተለያዩ ቢሆኑም በሀገር ሉአላዊነትና ብሄራዊ ጥቅም በትብብር መስራት እንዳለባቸው ብልፅግና ፓርቲ በፅኑ ያምናል።

ከዚህ የፀና እምነቱ የተነሳ ነው ብልፅግና ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የመንግሥት ስልጣን መቆጣጠር የሚያስችል የህዝብ ይሁንታ አግኝተው ሲያበቃ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደረጃ የተለያዩ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግስት ውስጥ ገብተው ሀገራቸውን ማገልገል እንዲችሉ ዕድል የሰጣቸው።

የሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ብሄራዊነት የተሰኘ አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንስራ።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa
00000