Addis Guday
Addis Guday tv
23/04/2026
23/04/2026
በ3.5 ሚሊዮን ብር ሸልማት የታጀበው ''የመድን Grand Fight Night" ሊካሄድ ነዉ!
በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት የውጊያ ስፖርቶችን በአንድ መድረክ ላይ የሚያገናኘው "የመድን Grand Fight Night I" የተሰኘው ዘመናዊ የውድድር መድረክ የፋታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም እንደሚካሄድ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ዝግጅቱን ስዌት ቦክስ ጂም፣ ሸጋ ኤቨንትስ እና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የዝግጅቱ ዋነኛ ስፖንሰር (Title Sponsor) በመሆን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ከዚህም ባሻገር ውድድሩ የጡንቻ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ የስፖርተኞችን ስነ-ምግባር፣ ታታሪነትና ትዕግስት የሚፈተንበት መድረክ እንደሚሆን ታውቋል። ስፖርቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድልና መደበኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን ለማስቻልም ሰፊ ጥረት ተደርጓል።
ለዚህ ውድድር በአሸናፊነት ለሚወጡ ስፖርተኞች በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ስፖርተኞች በዘርፉ ተስፋ እንዲኖራቸውና ራሳቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ማበረታቻ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡
ውድድሩ በዕለቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን፣ ታዋቂ ድምፃውያን የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን በማቅረብ ዝግጅቱን እንደሚያደምቁትም ተገልጿል።
Guday
23/04/2026
በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ
በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም ኤግዚቢሽን ተከፍቷል
የኤግዘቢሽኑ ከዛሬ ሚያዚያ 15 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 18 የሚቆይ ሲሆን ዋና አላማው ሻጭ እና ገዢ ማገናኘት፣የግንባታ ግብአት አቅራቢዎች እና ተጠቃማዎችን እንዲገናኙ ለማድረግ፤ የአህጉሪቱን አልሚዎችና ባለሀብቶች በማገናኘት የንግድ ትስስርን ማጠናከር ፣ የሴከተሩ የጥናት ውጤቶችን ማቅረብና ለዘርፉ ችግሮች መፍትሄ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በዚህ የማህበሩ አባላት ብቻ በተሳትፉበት ልዩ ኤግዚቢሽን ላይ የሪል ስቴት አልሚዎች የተለያዩ ፕሮጀከቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ በመሆኑ ቤት እና ሰቅ ፈላጊ ማህበረሰብ አማራጮችን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።
በዚህ በ4ቱ ቀናት በሚካሄደው ኤክስፖ ከ5000 በላይ ጎብኝዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል::
በተጨማሪም የፋይናንስ ተቋማት፣ የኮንስትራክሽን እና ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶች በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉ በመሆኑ ለዘርፉ እድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተነግሯል።
23/04/2026
" አንድ መኪና አሸዋ 12ዐ፣ 130 ሺሕ ገብቷል። በቅርቡ 85 ፣ 90 ሺሕ፤ ከዛ በፊት ደግሞ 70 ሺሕ ነበር " - ህንፃ ገንቢዎች
➡ " የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ብር ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል" - ማህበሩ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ ፈታኝ ከሆነው የነዳጅ ችግር ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ግብዓት ዋጋ ከ20 እስከ 40 ሺሕ በላይ መጨመሩን ህንፃ ገንቢዎች እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሃብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ከ60 እስከ 70 ሺሕ ብር ይሸጥ የነበረው አንድ መኪና አሸዋ አሁን ከ12ዐ ሺሕ እስከ 130 ሺሕ ብር መግባቱን ቲክቫህ ኢትየያ ከህንፃ ገንቢዎች ገለጻ ተረድቷል።
ከአሸዋ ባሻገር፣ ከወራት በፊት 60 ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረው አንድ መኪና ጠጠር አሁን ከ85 ሺሕ ብር በላይ መሆኑ ታውቋል።
የግንባታ ድንጋይ ደግሞ፣ በሺዎች የሚቆጠር ጭማሪ አሳይቷል። የሲሚንቶ ዋጋም እስከ ሦስት እጥፍ ጨምሯል።
ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሀብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይለማርያም ገቢሳ፣ " በትክክል ጭማሪ አለ። የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል " ብለዋል።
ለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ንረት " የነዳጅም፣ የቢሮ ክራሲም ሰንሰለት " ችግርን እንደ መንስኤ ጠቅሰው፣ እነዚህ ነገሮች ተደምረው አምራች ላልሆኑትም ዋጋ እንዲጨምሩ መንስኤ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።
" ለምሳሌ እኛ አሸዋ እናመርታለን። ከሞጆ እና ከዚያም በታች የሚያመጡም በእንዲህ አይነት ዋጋ መሸጥ ግዴታ ሆኖባቸዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ለጭማሪው የተለያዩ ችግሮች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ በትራንስፖርቴሽን መንገድ ላይ ዝም ብለው ሚዛን ይጨምሩብሃል፤ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉሃል። 16 ሜትርኩዩብ መጫን ያለበትን መኪና 10፣ 9 ሜትር ኩዩብ መጫን አለብህ ብለው ያስቸግራሉ " ነው ያሉት።
" በዚህ፣ በዚህ ምክንያት ችግራችን እስከ ታች ድረስ ይወርዳል። ስለዚህ ሳንወድ በግድ ዋጋ እንጨምራለን " ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ " የሠራተኛው ደመወዝ መክፈል፤ ነዳጅ መግዛት፣ ለመንግስት ግብር መክፈል አንችልም " ሲሉም ምክንያት ያሉትን አስረድተዋል።
" ነዳጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጣ ጣጣ ነው። አሁን ወደ ዓለም አቀፍ ጉዳይ እየሄደ ነው። የነዳጅ ጉዳይ እኛን ብቻ አይደለም የሚመለከተው " ብለው፣ ነገር ግን በተለያዩ አቅጣጫ የመሰረተ ልማቱን ለማስፋት በተለይ " የጠጠር አምራች ባለሃብቶች ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል ብለን ነው አቤቱታ የምናቀርበው " ብለዋል።
" እነሱን መንግስት ይይልን፤ ከመመሪያ ውጭ አንሆንም፤ ግን በመመሪያ እንዲሆንልን ነው፤ የመንግስት መመሪያ፣ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አዋጅ ይከበር። በዛ መሰረት ሂደን ለመንግስት መክፈል የሚገባንን ዋጋ ከፍለን ወደ ሀገራችን ልማት እንግባ " ነው ያሉት።
23/04/2026
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪያዎችን በዘመናዊ ዳታቤዝ መመዝገብ ጀመረ
ፌደራል ፖሊስ በተቋሙ ግምጃ ቤትና በአባላቱ እጅ የሚገኙ የጦር መሣሪያዎች ላይ ምልክት የማድረግና ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት የማስገባት ሥራ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
አዲሱ አሠራር በሀገር አቀፍ ደረጃ የትኛው የጦር መሣሪያ የት እንደሚገኝ በቀላሉ ለማወቅና ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል።
ምልክት የማድረጉ ሥራ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት፣ የጠፉ መሣሪያዎችን ለመለየትና በጦር መሣሪያ የታገዙ ወንጀሎችን ለመመርመር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል።
የምዝገባ ሶፍትዌሩና የመረጃ ቋቱ በፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለፀገ መሆኑ ተመላክቷል።
በፌደራል ደረጃ የተጀመረው ይህ ምዝገባ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም
21/04/2026
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠያቂነትንና የአሰራር ግልፅነትን ለማጎልበት የተዘጋጀውን ደንብ አጸደቀ
- ሌሎች ውሳኔዎችንም አሳልፏል፣
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በሶስት ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ተፈጻሚ እንዲሆኑ አጽድቋል።
በስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ከተወያየ በኋላ ሶስት ረቂቅ ደንቦች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት:-
💢 የተሻሻለ የፋይናንስ አስተዳደርን ይበልጥ ለማዘመን፣ ተጠያቂነትንና የአሰራር ግልፀኝነትን ለማጎልበት የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ተፈጻሚ እንዲሆን፣
💢 በከተማዉ እየተገነባ ያለው ሰፊ የቤት ልማት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው፣ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሪፎርምን ለማጠናከር እና የማስፈፀም ብቃት ለማሳደግ የተዘጋጀዉን ረቂቅ ደንብም አፅድቋል።
💢 የመሬት ማስፋፊያ ለጠየቁ ተኪ ምርት ለሚያመርቱ ኢዱስትሪዎች፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል የፈጠሩ ፕሮጀክቶች፣ ሆቴሎች እንዲሁም፥ በከተማ አስተዳደሩ ከሐይማኖት ተቋማት ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የሚያስችል መሬት በምደባ ለማስተላለፍ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተፈፃሚ እንዲሆን በስብሰባው ወስኗል።
ምንጭ ከ #ድሬቲዩብ
21/04/2026
ላፍቶ ላይፍ ሌግዠሪ አፓርትመንት ዛሬ ሚያዚያ 13/2018 እስከ 17/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ኤክስፖ በላፍቶ ሞል ተዘጋጅታል አስተማማኝ እና ታዋቂ በሆነ ሪል እስቴት አልሚዎች የተመሰረት መሆኑ ላፍቶ ሞል እና ኒው ላይፍ ሪል እስቴት በጥምረት የሚገነባው መሆኑን በኤክስፖ መክፈቻው ላይ ተገልፁል።
21/03/2022
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ደራሲና ዳይሬክተር የሆነችው ሶሊያና አብዲ ጋር የተደረገ ቆይታ
07/08/2021
የዛሬው እንግዳዬ በጥርስ ህክምና ሙያ ላይ ከ10 ዓመት በላይ ልምድ ያካበቱት ዶ/ር እስማኤል ሙዜ ከዘመናዊ የጥርስ ህክምና እና ጥንታዊ ፅሁፎች ጋር በማቀናጀት እንዲሁም በሀገራችን ለጥርስ ደህንነት ከሰው ግንዛቤ ጋር በማጣጣም "የጥርስ ውበት" የተሰኘ መፀሐፍ ለህትመት አብቅተዋል ከዚህ ጋር በተያያዘ መጥፎ የአፍ ጠረን መፍትሄዎች እና የጥርስ ብሬስ ህክምና በስፔሻሊስት ሀኪሙ እንዴት ይገለፃል?
መጥፎ የአፍ ጠረን መፍትሄዎች እና የጥርስ ብሬስ ህክምና በስፔሻሊስት ሀኪሙ እንዴት ይገለፃል? ክፍል ሁለት subscribe to our channel to get all the latest videos
18/04/2021
የአድዋ ሽልማት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Website
Address
1621