The Alkhamis
Sport and Ethiopia
16/10/2022
ድል በድል ሆነናል።
በሆላንድ በተካሄደ የአመስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና በመጀመሪያ ማራትኗ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል አሸንፏለች። ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ ፀሀይ ገመቹ ሶስተኛ ወጥታለች።
በሕንድ ቬዳንታ ዴልሂ ግ/ማራቶን በተካሄደ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በወንዶቹ ምድብ ጫላ ረጋሳ በ1:00.30 ቀዳሚ ሲሆን በሴቶቹ ዳዊት ስዩም 1:08.02 በሆነ ጊዜ 2ኛ ሆናለች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት የቦታውን ሰዓት በማሻሻል አሸነፈች!!
ደብብ አፍሪካ በተካሄደ የኬፕታዎን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መሰረት ድንቄ 2:24:02 በመሮጥ አሸንፏለች። በወንዶች
ደቡብ አፍሪካዊው አትሌት ሲያሸንፍ
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል።
01/10/2022
በዘንድሮው የውድድር ዘመን በ1500 ሜትር የሴቶች ከፍተኛ 10 ሯጮች አምስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች ተካትተውበታል።
🇪🇹ጉዳፍ ጸጋዮ 3፡54:21
🇪🇹ድርቤ ወልተጂ 3፡56:91
🇪🇹ፍሬወይኒ ኃይሉ 3፡56:94
🇪🇹ሂሩት መሸሻ 3፡57:30
🇪🇹አክሱማዊት እምባዬ 3፡58:80
26/09/2022
🇪🇹 በበርሊን! ትግስት አሰፋ በሴቶች 2፡15፡3 በመግባት አሸንፋለች።
👉 በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ትግስት አሰፋ በሁለተኛው ማራቶን 2፡15፡37 በማሸነፍ ብሪጊድ ኮስጌን እና ፓውላ ራድክሊፍን በመከተል በማራቶን 3ተኛዋ ፈጣን ሴት ሆናለች። ባለፈው ሚያዚያ በሀምቡርግ ባስመዘገበችው የኢትዮጵያ ሪከርድ 1፡46 ቀንሳዋለች።
1. ትዕግስት አሰፋ 2፡15:37
3. ትዕግስት አበየው 2፡18፡03፣
4. ወርቅነሽ ኢዴሳ 2፡18፡51፣
5. መሰረት ጎላ 2:20:58,
ሁለተኛውን ደረጃ ኬንያዊቷ ዋንጅሩ ስትወስደው ከአንድ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
06/08/2022
በመጨረሻም Ethiopian athletics final result in Mexico u20 2022
25/07/2022
በመጨረሻም እንዲህ ሆነ።
24/07/2022
የሌሊት ደስታ በሰንበት
ጉደፍ ጸጋዬ በ5000ሜ የወርቅ ሜዳሊያ ስታሸንፍ ዳዊት ስዩም የነሐስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።
ለዚህ ውጤት የለተሰንበት ሚና በጣም ከፍተኛ ሆኗል።
በአለሻምፒዮናው ታሪክ በ5000ሜ ሴቶች ወርቅ ካስመዘገቡት ጥሩነሽ ዲባባ - መሰረት ደፋር እና አልማዝ አያና ጋር ጉዳፍ በክብር ስሟ ተፅፏል::
22/07/2022
በእርሷ የደም ስር ውስጥ የሚዘዋወረው ደም ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል ውሃ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ሳትጠራ ያሳለፈችው ጊዜ ያለ አይመስለኝም። በሳንባዋ የሚቀያየረው ኦክስጅን ኢትዮጵያ የሚል ነው። እርሷ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ተለክፋለች። ለሃይማኗቷ ለሀገሯ ልዮ ናት። ወላጆቿ ማርያም የሚለውን ቃልና ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በእንጀራ ፍትፍት እያጎረሱ ያሳደጓት ይመስለኛል።
የዘንድሮውን የኦሪጎንን አትሌቲክስ ስመለከት የሩጫ ዘመን ቢገታትም እህት ወንድሞቿን አሰልፋ የሀገሯን ሰንደቅ ከፍ ለማድረግ አብዝታ ደክማለች። እናም የጠበቀችሁ ሆነ። ደጋግማ ልምዷን ያካፈለቻቸው ልጆቿ የድል ሸማውን እየሰነጣጠቁት መጡ። ከእነርሱ ማሸነፍ በላይ የዚህች ጀግና ስሜት ቀልቤን ሰቅዞ ያዘኝ። ቀይ ቢጫና አረንጓዴ የሰንደቅ መለያቸውን ይዘው ሲያውለበለሰቡ ስትመለከት ራሷን መቆጣጠር አልቻለችም። የእንባ ሲቃ ተናነቃት።
በፊቷ ላይ የሚታየው የደስታ ስሜት ወደኋላ ቀትዝታ ጎተተኝ። በፈረንጆቹ ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ጀግነዋ አትሌት ራሷ የተሳተፈችበትና የድል ዋንጫ የተቀዳጀችበት የባርሴሎና ኦሎምፒክ 10000 ሜትር ፍጻሜ። የደቡብ አፍሪካዋን ኢሊና ሜየርና አሜሪካዊቷን ሊይን ጀኒንገስ አስከትላ ስታሸንፍ ያሳየችው ስሜት ትዝ አለኝ።
በድጋሜ በአወስትራሊያ ልዩ ከተማ ሲድኒ በፈረንጆቹ ሚሊኒየም የሀገሯን ልጅ የማራቶኗን ልእልት ጌጤ ዋሜን እስከትላ ባሸነፈችበት ድል የወርቅ ሜዳሊያዋን ለማጥለቅ የወርቅ ደረጃ ከፍ ተደርጎ ወደተሠራው መሠላል ወጣች።
አብሯት የበቀለ በሚመስለው ትህትና በስታዲየም ውስጥና በቲቪ መስኮት ያለው ተመለካች ሰላምታ ሰጠች። የድካም ውጤቷ የሆነው የወርቅ ሜዳሊያ በአንገቷ ላይ አረፈ። ስሜት በወረረው ፈገግታ ጥርሷን ገለጠች።
ወደሰሜን አቅጣጫ ዙሩ ተባለ። የሀራችን መዝሙር ሊዘመር ባንዲራው ከፍ ብሎ ሊውለበለብ በተጠንቀቅ ቆሙ። መዝሙሩ በክላሲካል ታጅቦ የኢትዮጵያ ባንዲራ በነፋስ እየተውለበለበ ከፍ ከፍ እያለ ነው። የደራርቱ ስሜት ተለወጣ። በሀገር ፍቅር የሚቃጠለው ልቧ ከሲድኒ ኢትዮጵያ ትቷት መንኗል። ስሜቷን ለመደበቅ ሞከረች። ግን አልቻለችም። የሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ ደስታ ትዝ አላት። የበረዶ ግግር የመሠለ ነጭ እንባ ከሁለት ዐይኗ እንደ ጎርፍ እየተቀዳ በአፍንጫዋ ላይ እየዘለለ መውረድ ጀመረ። በለበሰችው መለዮ ጠረገችው። ሊቆም አልቻለም። ሰውነቷ ላይ የመንቀጥቀጥ ስሜት ታየበት። የእርሷ ስሜት ተጋባብኝ። የምወድዳት ባንዲራ ከፍ ብላ እየተውለበለበች እርሷ ሲድኒ እኔ ቴሌቪዥን መሥኮት ፊት ለፊት ቆሜ አብሬያት አለቀስኩ። ደስታየ ወደር አጣ።
በኦሪጎን 2022 እርሷ ከአትሌቶቻችን የማሸነፍ ጀርባ የእርሷ የደስታ እንባ ውስጤን ረበሸው። ደስታ ለራቀው ሕሊናየ ረፍት ሰጠችው። በኢትዮጵያዊይነት ፍቅር አቃጠለችኝ።
ለዘለዓለም ኑሪ። የኢትዮጵያዊነትን ማማ ከመሪዎች ይልቅ በእናንተ ቡድን ውስጥ አይቻለሁና አንችንና መሰሎችሽን ያብዛልን።
በሚከተሉት ገጾች ቤተሰብ እንሁን መረጃ እንለዋወጥ እንማማር።
ቴሌግራም
https://t.me/+Vtbo0QcfYephNTM0
page
https://www.facebook.com/dgtw1982/
Group
https://www.facebook.com/groups/933175270511611/?ref=share
Youtube
https://youtube.com/channel/UCA3ubZpjpYSHAXfXbnB8tMA
21/07/2022
ኢትዮጵያ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል በወርቅ ውሃ ጌታቸውና በመቅደስ አበበ የብርና ነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።
18/07/2022
ማራቶን ወደክብሩ ተመለሰ
እንኳን ደስ አላችሁ
ማራቶን በባዶ እግራቸው ሩጠው ወደሳከበሩት ኢትዮጵያውያን ዐይኑን አዙሯል።
ጀግኒት ጎይቶም ገብረ ሥላሴ ባለ ማኅተቧ በማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዐዲስ ክበረ ወሰን አስመዝግባ አሸንፋለች።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጀግኖቹ ባለ ማኅተቦቹ በማራቶን ክበረ ወሰን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
17/07/2022
ጀግኖቻችን ዛሬም ውድ ሀገራችን አኩርተዋል።
ወርቅና ብር በማራቶን ።
ጀግናው ታምራት ቶላ
ጀግናው ሞስነት ገረመው
ኦሪጎን 2022
Click here to claim your Sponsored Listing.