Abubekr kedir

Abubekr kedir

Share

ኢስላማዊ አስተምህሮ የሚተላላፍበት።

23/08/2025

*የዱንያ ነገር!!*
~
ዐሊይ ብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–

"አምሳያ ያላገኘሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ደህይቶ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ሀብታም ሆኖ ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"

||

ሱብሓነላህ!!
ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣️ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣️ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣️ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍ .ጫፊ አረ .መኔ አለም ጠብባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

® ይቺው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣️ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣️ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)
"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ኢላሂ ልብ ስጠን!

18/03/2025

እስከ መቼ?!
~
★ በየቤቱ ብዙ የምግብ ብክነት አለ። በየጎዳናው ግን ብዙ የተራበ ወገን አለ።
★ በየሰፈሩ ብዙ ድግሶች አሉ። ብዙ ችግረኞች ግን ተጋባዥ ሳይሆኑ ትርፍራፊ የሚጠብቁ የሩቅ ተመልካች ናቸው።
★ በየቤታችን ብዙ የማንለብሳቸው ልብሶች አሉ። ብዙ በብርድ የሚቆራመቱ የታረዙ ወገኖች ግን ተረስተዋል።
★ በየጎዳናው ብዙ መኪኖች ባዶዋቸውን ይጓዛሉ። ብዙ ደካሞች ግን በእግር ይኳትናሉ።
★ በየአውቶቡሱ ብዙ ደካሞች ቆመው ይሄዳሉ። ብዙ ወጣቶች ግን ወንበር ይዘው ፀጉራቸውን ይፈትላሉ።
★ በሃገሩ ሰፋፊ መሬት አለን። ሰፊው ህዝባችን ግን ገዝቶ እንኳ የቤት ባለቤት የሚሆንበት እድል ጠባብ ነው።
★ በየ መስሪያ ቤቱ ብዙ ሹመኞች ወንበር ያሞቃሉ። ብዙ ባለጉዳዮች ግን ዘወትር ይጉላላሉ።
★ ለጎረቤት ሃገር የሚበቃ የመብራት አቅም አለን። ሰፊው ህዝባችን ግን ጨለማ ውስጥ ይኖራል።
★ ሀገሪቱ "የውሃ ጋን" ነው ስሟ። ህዝቧ ግን በውሃ ችግር ይማቅቃል።
★ በየ ከተማው ብዙ ሰባኪዎች አሉ። ብዙ ህዝብ ግን በዘረኝነት ይባልላል።
★ በዘመናችን ድንገተኛ ሞት እጅጉን በዝቷል። ብዙው ሰው ግን ከሞት ጭልጥ ብሎ ዘንግቷል።

መቼ ይሆን ከልብ ማሰብና መተሳሰብ ባህላችን የሚሆነው?

ኢብኑ ሙነወር

03/08/2024

ፂም እና ማጭበርበር :

ፂም የባህላችን ክፍል ሳይሆን የእምነታችን አካል ነው :: እምነቱን መሰረት በማድረግ ፂሙን ያሳደገ ሰው ሌሎች ነገሮችንም በእምነቱ መመሪያ ሊመለከታቸው ይገባል ...

የሰውን ሐቅ በውሸት መሃላ መብላት ፣ እያጭበረበሩ መሸጥና መግዛት ፣ መዋሸት ፣ የሰዎችን አማና መብላት የተወገዙ ቆሻሻ ምግባሮች ናቸዉ ። ፂምን አሳድጎ እንዲህ አይነት ነገር ውስጥ መግባት ደግሞ እጅግ አስነዋሪ ነው ...
አንዳንዱ
" ሰላትህን ስገድ ፣ ፆምህን ፁም ፣ ቁርአንህን ቅራ እንጂ የገንዘብ እና የንግድ ጉዳይ ላይ እንዳሻህ ብትሆን አትጠየቅም - በውሸት መክበር ያለ የነበረ ነውና አያሳስብህ " የተባለ ይመስላል ። ከነጺሙ ያጭበረብራል ፣ የሰው ኣማና ይበላል ፣ በውሸት ይምላል .... የገንዘብ ፍቅር ሌሎችን እንዳሰከረው የሱንም ጢምቢራ አዙሮታልና ቤት ለመገንባትና መኪና ለመግዛት የተከለከለን አሳፋሪ ምግባር ሁሉ ያለ ሐያእ ይገባበታል ! አላህ ፊት ቆሞ እንደሚጠየቅ ዘንግቷል !
እንዲህ አይነቱ ፂሙ ያደገ አጭበርባሪ ደግሞ በርካታ የሱና እና የተቅዋ ሰዎችን ያሰድባል ! በደካሞ እምነት ላይ ፈተናን ይጥላል ! ሰዎች ወደ ሐቅ እንዳይገቡ በርን ይዘጋል !

አላህ ይመልሰን !
Muhammed sirage

28/03/2024

የተራዊሕና ተሃጁድ አሰጋጆች ሆይ፥

🔹ለሰዎች የአላህን ቃል ማሰማትና የቁርኣንን መልዕክት ማድረስ መቻል ትልቅ ዕድልና ጸጋ መሆኑን አውቃችሁ በስራችሁ ተደሰቱ፤
ስራን አላህ ዘንድ ዋጋ ከሚያሳጡ ተግባራትና ኒያዎችም ተጠንቀቁ።

♦️ከኋላችሁ ካሉ ሰጋጆች (ደካማ መኽሉቆች) ይልቅ ከፊታችሁ ያለውን ኀያሉን አላህን እያሰባችሁ አሰግዱ። የማንንም አድናቆት አትከጅሉ፣ የማንንም ወቀሳ አትፍሩ።
♦️የቁርኣን ንባብ ላይ ድምጻችሁን ስታሳምሩ ኒያችሁን ቀድማችሁ አሳምሩ። ድምጹ ሲያምር እንዲባልለት ፈልጎ ድምጹን የሚያሳምር ሰው የጀሀነም ማገዶ ይሆናል!
ይልቅ የአላህን ቃል ባማረ ድምጽ ቀርቶ ሰዎች ይበልጥ የጌታቸውን ንግግር እንዲሰሙና እንዲመከሩበት ማሰብና መነየት ነው የሚገባው።
በቁርኣን ድምጽን በማሳመር ክብርና ዝና መፈለግ፣ ድምጽን የሚያሳምሩትን ያክል ስራና ስነምግባርን አለማሳመር ውጤቱ ነገ አላህ ዘንድ መክሰርና እያደረ ሰዎች ዘንድም ከክብር በኋላ መዋረድ፣ ከመወደድ በኋላ መጠላት ነው የሚሆነው::
♦️ የምታነቡትን ቁርኣን ተፍሲሩን ለማወቅ ጥረት አድርጉ፤ ሙሉ አቅሙ እንኳ ባይኖራችሁ አጫጭር የተፍሲር መጽሐፍትን አንብቡ፣ በሚገባችሁ ቋንቋ የተዘጋጁ ተፍሲሮችን አዳምጡ።
ልብ የሚገሰጸው የሚነበበውን ሲረዳ ነውና።
ከኋላችሁ ያሉ ሰጋጆችም ቀድሞ በሚያነበው አንቀጽ ከተገሰጸ ሰው አንደብት የሚወጣ ንባብ ይበልጥ ይገስጻቸዋል።
♦️ቀን ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግን በመተው በተደጋጋሚ ትልልቅ ስህተቶችን መሳሳት የተሰጠን አደራ በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር ሰጋጆች የልብ መረጋጋትን እንዲያጡ ያደርጋል።
ይህ እንዳይሆን ቀን ላይ በቂ ዝግጅት አድርጉ።
ይህን ከማድረጋችሁም ጋር ቁርኣን አሸናፊ ነውና ከተሳሳታችሁ ቆም ብላችሁ ለሚያርማችሁ ሰው ዕድል ስጡ! መሳሳት ነውር አይደለምና።
ይሳሳታል ላለመባል እየጣራችሁና እየደጋገማችሁ ሰዓት አታባክኑ!
♦️አትዋሹ! ሳል ሳይኖር ሲሳሳቱ ማሳልና ያልተሳሳቱ ለመምሰል መሞከር ተገቢ አይደልም!
♦️የሰላትና የአስጋጅነትን ህግጋት ጠንቅቃችሁ እወቁ። ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮችን፣ የሰላት መስፈርትና ማዕዘናትን፣ ከኢማም የሚጠበቁ ነገሮችን ሳያውቁ ቁርኣን በቃል ስለሸመደዱ፣ ወይም ጥሩ ድምጽ ስላለ ብቻ ወደ ሚሕራብ መግባት (አሰጋጅ መሆን) ትልቅ ስህተት ነው።
ኢማም ከኋላው ተከትለው በሚሰግዱ ሰዎች ሰላት መበላሸት ወይም መጉደል አላህ ዘንድ እንደሚጠየቅ ጠንቅቃችሁ እወቁ።

♦️ሚዛናዊ ሁኑ፤ ሩጫም ይሁን ዝግመት፣ ድምጽ ማነስም ይሁን መብዛት ሳይኖር (በይነ ዛለኪ) የሆነ አካሄድ ሂዱ።

አላህ ያግዛችሁ፤ ስራችሁንም ወዶ ይቀበላችሁ።

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረመዳን 16/ 1445ዓ.ሂ

05/02/2023

ለነፍሳችን እንድረስለት

ሰሌን ደህና ማረፊያ አይደለም ። አካልን ምቾት የሚነሳ መሻከር እንዳለበት የታወቀ ነው ….

ነብዩ ይሄው ሰሌን ላይ ይተኙ ነበር ። ሰሌኑም ጎናቸው ላይ ምልክትቱን ይጥል ነበር ።
ባልደረቦቻቸው “ ለምን የተሻለን ምንጣፍ አናደርግልህም ?” ሲሏቸው

ما لي وللدنيا؟ ما أنا في الدنيا إلا كراكب
استظل تحت شجرة، ثم راح وتركها

“ እኔና ዱንያ ምንና ምንድን ነን ? እኔ እኮ ዱንያ ውስጥ ዛፍ ስር ( ለማረፍ ) እንደተጠለለ አንድ ( መንገደኛ ) ጋላቢ ነኝ .. ከዚያም ሄደ ተዋትም ….

አንዳንዴ ቤታቸው ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ይጠፋ ነበር … በርግጥ ነው አንዳንዴ በርከት ያለ ነገር የነብዩ እጅ ውስጥ ይገባ ነበር ። ነገር ግን እጃቸው ውስጥ የገባውን ሪዝቅ በአላህ መንገድ ላይ ያከፋፍሉት ነበር ….

የነብዩ ባልደረቦች የሚለበስ በማጣት ተፈትነዋል ፣ ረሃብን አብዝተው አስተናግደዋል … ግባቸው የአላህን ውዴታ ማግኘት ነበርና ታገሱ ፣ ፈተናውን በአግባቡ ተወጡ … ግን ከነ ችግራቸው የደስታን ህይወት ገፍተዋል …

የኛ ነገርማ

ትልማችን አለማዊ ሆኗል ! ህልማችን የዱንያው ሸቀጥ ብቻ ሆኖ አኺራን ዘንግተናል … ወጋችን ባንክ ነው .. ሚዛናችን ሃብትና ዘር ነው - አላህ ያዘነት ሲቀር ጠፍተናል እየጠፋን ነው ።

ለነፍሳችን እንዘን ፣ ወደ አላህ መንገድ እንመለስ …

አላህ ይመልሰን !!

መሐመድ ሲራጅ

02/09/2022

ዋናው ልብና ስራ ነው❗

▪️ነቢያት የተላኩት፣ ቁርኣንና መሰል መጽሐፍትም የወረዱት የሰው ልጆችን ልብ ለማጽዳት፣ ስራና ስነምግባርን ለማስተካከል ነው።

▪️ያለንበት ዘመን ከመቼውም በላይ ሰዎች ውስጣቸውንና ከጌታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከማስተካከል ይልቅ ውጫቸውን በማሳመርና ለሰዎች እያስመሰሉ መኖር የበዛበት ዘመን ነው።

▪️አላህ ከሁሉም በፊት ከሰው ልጆች የሚያየው ልብና ስራን ነው።
▪️ልብ አላህን ከፈራና ንጹህ ከሆነ፣ ስራም መልካም ከሆነና ለአላህ ተብሎ ከተሰራ የሰው ልጅ አላህ ዘንድ ደረጃው ከፍ ይላል፤ ይከብራልም።
▪️ልብ ከቆሸሸና አላህ በሚጠላቸው ነገሮች ከተሞላ፣ አካላትም ለመጥፎ ስራዎች ከተንቀሳቀሱ የሰው ልጅ ጌታው ዘንድ ክብር ያጣል፤ ኣኺራውንም ይከስራል።

▪️ለሰዎች ማስመሰሉና የውጩ ብቻ ማማርም አላህ ዘንድ ምንም አይጠቅመውም።

▪️ሐዲሡም "አላህ መልክና ገጽታችሁንም ይሁን ሀብታችሁን አያይም።ይልቅ የሚያየው ልብና ስራችሁን ነው" ነው የሚለው።

✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ሀሙስ 04/2/1444 ዓ.ሂ

30/08/2022

:::::እውነተኛ ፍቅር :::::::

🌱ክፍል 5⃣
.. ከድጃም እንዲህ አለችው "ገንዘቡን ብናደባልቀው ይበዛል እንጂ አያንስም"፡፡ ወጣቱም በድጋሚ ምንም ሳይመልስላት ዝም አለ፡፡
#ከድጃም "በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚሰሩትን የሚያውቅና የሚያይ በሆነው ጌታዬ ይሁንብኝ በኔ በኩል ምንም የሚሸፍነው ነገር የለም፡፡ #ሁሉም #ነገር እውነት ነው በል አሁን ወደ ቤተሰቦችህ ሂድና አጎትህን ለጋብቻ እንዲጠይቁኝ ንገራቸው፡፡ ምናልባት አባቴ ብዙ ገንዘብ ለኒካህ ከጠየቃቸው የጠየቀውን በሙሉ እኔ እሰጥሀለው፡፡ #እኔ ያንተ ነኝ እኔው መረጥኩህ ከአንተ ሌላ ማንንም አልፈልግም፡፡ ልቀርብህ ሳስብ አትራቀኝ " አለችው ልመና በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡
#መሀመድ (ሰዐወ) ተነስቶ ከቤቷ ወጣ፡፡ ከድጃ መሀመድ (ሰዐወ) ከመምጣቱ በፊት ለወዳጅ ጓደኛዋ ለነፊሳ አጫውታት ነበር፡፡ ነፊሳም እሱን አሳምና ከምትወደው ሰው ጋር እንደምታጋባት ቃል ገብታላት ነበር፡፡ #ወጣቱ መሀመድና ነፊሳ ሲገናኙ ነፊሳ ስለታላቋ ሴት ስለ ከድጃ መልካም ባህሪና እንዲሁም እሱን ማግባት እንደምትፈልግ ከገንዘቧ እንደምታስበልጠው አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ ጥያቄዋን እንዲቀበልም አሳመነችው፡፡
#ታላቁ #ሰው አጎቱ ቤት ተመለሰ፡፡ አቡጣሊብን ከወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ቤት ቁጭ ብሎ አገኛቸው፡፡ አጎትዬው በፈገግታ ተቀበሉት ከዚያም "ከድጃ ከከባድ ስጦታ ጋር እንደላከችህ እገምታለው" አሉት፡፡ መሀመድም "አጎቴ ሆይ ግምትህ ትክክል ነው፡፡ #ከአንተ ጉዳይ አለኝ " አለ፡፡
#አቡጣሊብም "ከአንተ ጉዳይ ጀርባ ጌታህ አለ፡፡ ለመሆኑ ምንድናት ጉዳይዋ" አሉት፡፡
#መሀመድም "ሂዱና ከድጃን ለትዳር እንደምፈልጋት ቤተሰቧን ጠይቁና አምጡልኝ " አለ፡፡
የመሀመድ አጎቶች ተያዩ ከአቡጣሊብ በስተቀር ማንም ምንም መናገር አልፈለገም፡፡ #አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ ከድጃ እጅግ የተከበረችና በሰዎች ዘንድ የተወደደች ብዙ ሀብት ያላት ከአሁን በፊት ሁለት ሰዎች አግብታና በሞት የተለዩዋት ንብረታቸውን ወርሳ የምትኖር አሁን በቅርቡ ታላላቅ ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች ናት፡፡ አንተ የወንድሜ ልጅ ደግሞ ምንም ንግድ የለህም የርሷ ተቀጣሪ ነህ፡፡ ስለዚህ ራሷን አሳልፋ አትሰጥህም" አሉት፡፡
#ሙሀመድም (ሰዐወ) "አጎቴ ሆይ አሁን ያልከውን በሙሉ አውቀዋለሁ እረዳሀለው የጋብቻ ጥያቄው ግን ከራሷ ነው የመጣው፡፡ " አላቸውمنقول

29/08/2022

♻️ለአርባ ሺህ ሰዎች መስለም ሰበብ የሆነው አስደናቂ ውሻ ገድል!

☞የክርስትና እምነት ተከታዮች ሞንጎላዊያን ክርስትናን እንዲቀበሉ በመቋመጥ በሞንጎላዊያን ጎሳዎች መካከል ሰባኪዎቻቸውን ይልካሉ። ይህን መስመር ያመቻቸላቸው አረመኔው ሆላኮው አንዲት ዘፈር ኻቱን ከምትባል ክርስቲያን ሴት ጋር በትዳር በመቆራኘቱ ሰበብ ነበር።

♻️ከእለታት አንድ ቀን ታላላቅ የሚባሉ የክርስቲያን ቀሳውስት ከሞንጎላዊያን መሪዎች መካከል አንዱ ክርስትናን በመቀበሉ ሰበብ የተደገሰውን ታላቅ ድግስ ለመታደም ወደ ቦታው ተመሙ። በዚህም መሀል ከቀሳውስቱ መካከል አንዱ ተነስቶ የአላህ መልእክተኛን ሙሐመድን (صلى الله عليه وسلم) መሳደብ ጀመረ። እዛው ቦታ ላይ የአደን ስልጠናን በሚገባ የተማረ አደገኛ ውሻ ታስሮ ነበር። ይህ ክፉ መስቀለኛ ቄስ ረሱልን መሳደብ ሲጀምር ውሻው ማጉረምረም ጀመረ። ከዛም በእልህ እየጮኸ ቄሱ ላይ ዘሎ በሀይል ቧጨረው። ቦታው ላይ የታደሙ ሰዎች ቄሱን ከዚህ አደገኛ ውሻ በመከራ ገላገሉት።

♻️ይህን ክስተት እዛው ተጥደው የነበሩ ሰዎች "የሙሐመድን ክብር ስለነካህ ይሆናል ውሻው እንዲህ የቧጨረህ" አሉት።
ቄሱም "በፍፁም! ውሻው አደገኛ ስለሆነ በእጄ ወደ እሱ ሳመላክት ልመታው ያሰብኩ መስሎት ነው የዘለለብኝ" አለ።

♻️ከዚያም የአላህ መልእክተኛን በድጋሚ መወረፍና መሳደቡን ተያያዘው። የዚህ ግዜ ነበር ጉዱ ........
ውሻው የታሰረበትን ገመድ በጥሶ የቄሱ አንገት ላይ ዘሎ ደም ስሩን በጣጥሶ ወዲያውኑ ገደለው። እስትንፋሱን አሳጣው።

♻️ይህን አስደናቂ ትእይንት ሲመለከቱ የነበሩ ወደ አርባ ሺህ ሞንጎላዊያን ኢስላምን ተቀበሉ።

♻️አላሁ አክበር!


☞ይህን አስደናቃ ክስተት ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ ረጀብ (አላህ ይዘንለት) በዚህ ድርሳናቸው አፅድቀው ከትበውታል ▼▼▼▼▼▼

📚 [الدرر الكامنة (202)]

♻️እስኪ እኔን አንዴ አንብቡኝ!

☞የዚህን ውሻ አንድ አስረኛ እንኳን ለኢስላምና ለሱና መቆርቆር በቻልን አትሉም!

☞በህይወት ዘመንህ ቢያንስ አንድ ሰው በሰበብህ ወደ ኢስላም እንዲገባ ጥረት አርግ። ይህ ካቃተህ ከኢስላም እንዳይወጣ ታገል። ይህ ካቃተህ በአንተ ሰበብ ሰዎች ከኢስላም እንዳይወጡ ሞክር። ይህ ካቃተህ ውሻው ከአንተ ይሻላል ማለት ነው!

☞ውሻው ሰንሰለቱን ፈቶ ጠላት ላይ እንደዘለለው እኛም በስሜት ማነቆ የታሰርንበትን ዘለበት ፈተን ለኢስላም ዘብ እንቁም!

☞እንደ ውሻው መናከስ ባንችልም ሱናን ነክሰን እንያዝ!

☞እንደ ውሻው መጮህ ባንችልም ሱናን ለማስተማር በየቦታው ለሚጮኹ እውነተኛ ዳዒዎች ጆሮአችንና ልባችንን ለባጢልና ቢድዓ ደሞ ጀርባችንን እንስጥ!

☞አመት ጠብቀህ መልእክተኛውን እወዳለሁ እያልክ ከሴት ጋር ተቀላቅለህ እየጨፈር ከምትረብሽ ሱናቸው ሲረሳ ቢድዓ ሲነግስ ጀግና ሁን።

"إنا كفيناك المستهزئين"

(ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሀል)

📚[ሱረቱ'ል ሒጅር :(95)]

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

29/08/2022

::::::እውነተኛ ፍቅር::::::::

🍃:::::ክፍል 4⃣ት

ከሻም ጉዞ መልስ ከድጃ (ረዐ) #ለሙሀመድ (ሰዐወ) "ለአንተ እኔ ዘንድ ጥሩ ደስታና ስጦታ ተቀምጦልሀል ከሁሉም ሰራተኞች የበለጠ እጥፍ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፈልሀል" አለችው፡፡ #ሙሀመድም (ሰዐወ) ከጉዞ መልስ አጎቱ ጋር ተመለሰ፡፡ #አቡጣሊብም አባት ለልጅ አቀባበል ከሚያደርገው በላይ በደስታ ተቀበሉት፡፡ ከዚያም እንዲህ አሉት
" #ልጄ #ሆይ ከድጃ ከፈለችህ"
ሙሀመድም "ከውሉ በተጨማሪ ትርፍ ገንዘብ ጨምራ እንደምትሰጠኝ ቃል ገባችልኝ " አለ
#አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ የወላጆችህ አደራ አለብኝ እንደምታዬኝ አርጅቻለሁ የሞትም ምልክቱ እየታየብኝ ነው ስለዚህ አንተን ድሬ ወግ ማዕረግህን ማየት እፈልጋለሁኝ እናም ከቁረይሾች ጥሩ ሚስት ብፈልግልህና ብድርህስ " አሉ፡፡
#ሙሀመድም "አጎቴ ሆይ አንተ እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ እኔ ያንተን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ " አለ፡፡
ከሻም መልስ በሁለተኛው ቀን ታላቁ ሙሀመድ (ሰዐወ) ገላቸውን ታጥበው አቡጣሊብ በገዙላቸው ልብስ ተውበው ወደ ከድጃ ሄዱ፡፡ ከድጃም እውነተኛ ፣ ታማኝ ፣ ፍትሀዊ ፣ አዛኝ ፣ መልካም ሰሪን ታላቁን ወጣት በውበቱ ላይ አዲስ ልብስን ተጎናፅፎ ስታየው ተደነቀች ከዚያም " #እንዲህ #አምረህ የመጣኸው ከኔ አንድ ነገር ፈልገህ ሳይሆን አይቀርም ምን ልታዘዝ ሀጃህ ምንድነው?" አለችው፡፡
" #ከአንቺ ዘንድ ያለኝን ገንዘብ ፈልጌ ነው " አላት፡፡
" #መሀመድ ሆይ ይህ ውዐትና ገንዘብ ይዘህ በንደዚህ ሁኔታህ ምን ልትሰራበት ነው" አለችው፡፡
"አጎቴ ከቁረይሽ የሆነችን ሚስት እድርልሀለው ስላለኝ ተስማምቼ ነው የመጣሁት " አላት፡፡
" #ሚስት ልታገባ አስበህ ከሆነ እኔ እጅግ ቆንጆ የሆነች ገንዘብ ያላት ለዘርህ ቅርብ የሆነች ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች በሰዎች ዘንድ የተከበረች አዕምሮዋ የተረጋጋና የሞላ አንተን እንጂ ከአንተ ምንም የማትፈልግ ሚስት አዘጋጅቼልሀለው፡፡" አለችና #እንዲህ ስትል ቀጠለች "ከአንተ የማልደብቀው ሁለት ነውር አላት አንደኛው ነውሯ አግብታ ታውቃለች ሁለተኛው በዕድሜ ከአንተ ትበልጣለች " አለች፡፡
#መሀመድም "አንቺ ጥሩዋ ሴት ሆይ ማናት እሷ የትስ ነው ያለችው " አላት
"ያንተ ምርኮኛ ናት እዚሁ ቅርብ አጠገብህ ታያታለህ ስሟም ከድጃ ይባላል" አለችው፡፡
#መሀመድም ሁሉም ነገር በተገለጠለት ጊዜ ምንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡
ከድጃም "የእሺታ መልስ ስጠኝና ልቤን አሳርፈው" አለችው፡፡
አሁንም ከወጣቱ መልስ ስታጣ "አላህ ካለ እኔ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አንተንም በምንም አልወነጅልህም" አለች፡፡
#መሀመድም (ሰዐወ) "ከድጃ ሆይ አንቺ የተከበርሽና ባለብዙ ሀብት እኔ ደግሞ የአንቺ ተቀጣሪና ከምትሰጪኝ ገንዘብ ሌላ ምንም የለኝም እናም ገንዘብ የሌለው ፈልጎም ቢሆን ቢጤውን ያገባል" አላት፡፡منقول

29/08/2022

::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::::

🍃:::::ክፍል 3⃣

#የከድጃ ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ በውክልና እሷ ዘንድ በኮሚሽን መቀጠር ከቻሉ ሰዎች መካከል ሙሀመድ (ሰዐወ) አንዱ ነበር፡፡ ወጣቱ ትሁት ሰው አክባሪ የሰውን ገንዘብ ያለ ሀቁ የማይፈልግ ታታሪ ቸር ስራውን ወዳድ በመሆኑ ከድጃ ጋር #ከተቀጠረ ጀምሮ ከመካ ከተማ ርቆ በመሄድ እየነገደ ገንዘቧን በእጥፍ አሳደገው፡፡ በዚህም ከድጃ በወጣቱ ኮርታበታለች፡፡ #ሙሀመድ ከድጃ ጋር የተቀጠረው እንዲሁ በአጋጣሚ አልነበረም፡፡ የሚያሳድጉት አጎቱ ጥሪት አነስተኛ በመሆኑ እንጂ፡፡
የሙሀመድ አባት አብደላህ ገና ሳይወለዱ ነበር የሞቱት፡፡ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በ6 አመታቸው ነበር፡፡ ቢሆንም በአያቱ ዘንድ አደገ፡፡ አያቱ ሲሞቱ አጎቱ ተረከቧቸው፡፡
#መሀመድ አጎቱ ጋር መኖር ሲጀምር ፍየል በመጠበቅ ተግባር ተሰማራ፡፡ ግን ብዙም ሳይቆይ አጎትየው የገቢያቸውን መጠን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡
#አንድ #ቀን ከድጃ ወንዶችን ወደ ምድረ ሻም በመላክ እንደምታሰማራ ስላወቁ ነጋዴው ወደተባለው ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ሳሉ ሙሀመድን አስጠርተው ስለሁኔታው ሊነግሯቸው ወሰኑ፡፡
"የወንድሜ ልጅ ሆይ እንደምታውቀው አንዳች የሌለኝ ደሀ ነኝ ፤ ግዜው ደግሞ በድርቅ ተመቷል፡፡ ከድጃ ሰው ቀጥራ እንደምታስነግድ ሰምቻለው በርግጥ የምትከፍለው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ደስ አያሰኝም፡፡ #እናም ስለዚህ ጉዳይ እሷኑ ባነጋግርልህ " ሲሉ አቡጧሊብ ጥያቄ ለመሀመድ አቀረቡ፡፡ ሙሀመድም እንዲህ አላቸው "አጎቴ ሆይ እንዳሻህ ማድረግ ትችላለህ ሀሳብህ የኔም ሀሳብ ነው መጭው አለም ከዱንያ አለም በላጭ ነው" አሏቸው፡፡
#አቡጧሊብ ጊዜ ማጥፋት አልፈለጉም ወንድሞቻቸውን አስከትለው ወደ ኸድጃ ቤት አመሩ፡፡ እሷም ከሀር በተሰራ ባማረ ልብስ ተውባ በፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡
አቡጧሊብም "የተከበርሽው ከድጃ ሆይ እኛ የመጣነው ለጉዳይ ነው ሰዎችን ገንዘብ እየከፈልሽ እንደምታስነግጂ ሰምቻለው፡፡ ለሌሎች በምትከፊይው ላይ ጨምረሽ ተመሳሳይ ስራ እንዲሰራልሽ መሀመድን አትቀጥሪምን? " አሉ
ከድጃም "እንኳንስ ለሚወደድ ለቅርብ ዘመድ ለማይታወቀውም ቢሆን ጥያቄዎ በኔ ዘንድ ተቀባይነት አለው" በማለት አስደሳች መልስ ሰጠች፡፡
አቡጧሊብ አስደሳቹን ዜና ይዘው ወደ መሀመድ (ሰዐወ) ተመለሱ፡፡ ብስራቱን ከነገሩት በኋላ "ይህ ፈጣሪ ላንተ የላከው ሲሳይ ነው " አሉ፡፡
ሩህሩሁ አጎት መጪው ጊዜ ያረገዘውን ቢረዱ ይህ ለከድጃ ከሰማይ የወረደ ፀጋ ነው ባሉ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚህ መልካም ዜና በስተጀርባ የሚመጣውን የላቀ ዕጣ የሚያውቅ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እድለኛዋ ከድጃ አቡጧሊብ ያቀረቡትን ጥያቄ በደስታ ተቀበለች ፤ ይህም ሙሀመድ (ሰዐወ) እና ከድጃ (ረዐ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁበት አጋጣሚ ፈጠረ፡፡ ጉዳዩ በመካ ነዋሪዎች ዘንድ ተዳረሰ፡፡ በየአጋጣሚው የታላቁን ሰው መልካም ትሩፋት እውነተኛነት ዘረዘሩላቸው፡፡ ከድጃም ይበልጥ ደስ አላት፡፡ #መይሰራ ከተባለው አገልጋይ ጋር ወደ ሻም እንዲሄዱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታወቀች፡፡ ሙሀመድም የተሰጣቸውን አማና ተቀብለው ለንግድ ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም አመሩ፡፡

ይ-----ቀ-----ጥ---ላ------ል✍✍
منقول

28/08/2022

:::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::

ክፍል 2⃣

#የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ #ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ #ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ #እሷ #ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ #ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ #ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ #ሀብትና #ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
#አላህ #በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
#ከድጃ #ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ #የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ #ይህን #ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
#አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው #ስሙ #አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ #ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ #የተከበረችው #ከድጃ #ስትቀር

ይ...ቀ....ጥ.... ላ....ል ✍✍✍
منقول

28/08/2022

:::እውነተኛ ፍቅር::::::

🍃:::::::ክፍል 1⃣

በአሁኑ ዘመን እዉነተኛ ፍቅር ከፊልም ከቃናtv..እና ከአማረኛ ፊልም እያዩ የሚመኙ አሉ ፡፡ ግን እዉነተኛ ፍቅር ገና ማህበሪዊ ሚዲያ ሳይመጣና እንደ አሁኑ ሞደርን ስልጣኔ ሳይመጣ በፊት የተጀመረ ነዉ ..በፊት እዉነተኛ ፍቅር ምን ይመስል ነበር፡፡ እንደ ዘመኑ ፊልም ተጣልቶ መታረቅ ይሆን ?? እስከ ተከታታይ ታሪክ ጀምረናል እስከምንጨርስ አብረዉ ይከተሉን

#በቅድመ ኢስላም በጃህሊያ ዘመን ወደ ኢስላም ጥሪ ከመጀመሩ በፊት አስራአምስት አመት ገደማ አንድ ውብና ተክለ ሰውነቱ ያማረ ወጣት ካዕባ አጠገብ ከሚገኘው በኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረዐ) ቤት አጠገብ አለፈ፡፡
#ወጣቱ ሲያዩት ፊቱ እንደ በድር ጨረቃ የፈካ ፤ መልከመልካም ፣ የዐይኖቹ ጥቁረት የበረታ ፣ የሽፋሽፍቶቹ ፀጉር ረዥም ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ፣ አንገቱ መለሎ፣ አይኖቹ በተፈጥሮ የተኳሉ ፣ ቅንድቡ ቀጭን እና ረዥም ከሩቅ ሲያዩት እጅግ ሲበዛ ቆንጆ ሲቀርቡት ተወዳጅ #ጥርሱ #ነጭ አፍንጫው ቀጥ ያለ ነበር፡፡
#በወቅቱ የከድጃ ቤትና የዳረል አሰድ ቢን አብድልዑዛ ፣ ቤት ከካዕባው ጥቂት እርምጃ ነበር የሚርቀው፡፡ አንድ የአይሁድ መነኩሴ በከድጃ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ሳለ መልከመልካሙን ወጣት አየው ፣ ከድጃንም ወጣቱ ተጠርቶ እንዲመጣ አዘዛት ፣ ወጣቱም በከድጃ አገልጋይ ተጠርቶ መጣ፡፡
#አይሁዳዊው #መነኩሴ ወጣቱን በትህትና ልብሱን ከትከሻው አካባቢ ገልጦ እንዲያሳየው ጠየቀው ፣ ወጣቱም እንደተጠየቀው አደረገ ፣ አይሁዳዊው ትከሻው አካባቢ ባየው አስደናቂ ነገር ተደሰተ አቅፎም ሳመው፡፡
#ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ከድጃ ለአይሁዱ "ይህንን ድርጊትህን ቁረይሾች ቢያዩህ አንተን ከመቅጣት ትዕግስት የላቸውም " አለች፡፡
#በርግጥ #የአይሁዱ #ድርጊት ለምን እንደሆነ ከድጃን (ረዐ) የገባት ነገር የለም ፣ ወጣቱን ስታየው ፊቱ የፈካና የሚያምር አንደበተ ርቱዕ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ አይሁዱ ለከድጃ እንዲህ አላት፡፡
"በተውራትና በኢንጂል ኪታቦች ላይ ሰፍሮ እንዳየሁት የአንድ ብርቱ ሰው መምጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እዚሁ በመካ ነው ፣ እናትና #አባቱ #በልጅነቱ #ይሞታሉ ፣ አጎቱ ያሳድጉታል ወደ መዲናም ይሰደዳል ፣ የሻምን ስልጣን በእጁ ያደርጋል ፣ በመካ ያሉትን ጣኦታት በሙሉ ሰባብሮ በማስወገድ ካዕባን ንፁህ ያደርገዋል፡፡"
#ከድጃ አይሁዱ የተረከላትን በጥሞና አዳመጠች ፣ በንግግሩም ተማረከች ልቧ ጓጓ ወጣቱንም ለማወቅ ፈለገች፡፡
#በሌላ #ጊዜ አጎቷ ወረቃን ስለዚው ጉዳይ ጠየቀችው ፤ ወረቃም ወደ ሻምና ሶሪያ በመሄድ የኢንጅልን መፅሀፍ ስላጠናና ስለመረመረ ይመጣል ተብሎ የተተነበየው ታላቅ ሰው ከቁረይሾች እንደሚያገባ በገንዘብ እንደምትረዳውና ከጎኑ እንደምትሆን አረጋገጠላት፡፡

ይ.....ቀ......ጥ......ላ.......ል✍✍
منقول

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa