Zeheabsha

Zeheabsha

Share

beauty and health

Photos from Zeheabsha's post 07/12/2023
07/12/2023

ይህንን ነው መፍራት..........

26/05/2023

70 ዓመት ዳቦ ያበሉን የ'ሸዋ ዳቦ' መሥራች አቶ ዘሙይ ተክሉ አርፉ ።
*******************************************************
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች " ሸዋ ዳቦ መጋገሪያ " የሚል መጠሪያ ያለው ዳቦ ቤት መሥራች አቶ ዘሙይ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ነፍስ ይማር ።

23/05/2023

ማታ ማታ ባል ያምረኛል ።

ከአበባ ብርሃኑ

አበባ ይዞ ከስራ የሚመለስ፣ ሲገባ ደግሞ ብሔሬን እስክረሳ ድረስ የሚስመኝ ፣ አንገቴን ስሞ ትንፋሼን የሚያዳምጥ፣ የልብ ምቴን አስተካክሎ ሲጨርስ አዋዋሌን የሚጠይቀኝ ፣ ራት ሳቀራርብ የሚያግዘኝ ፣ የመጀመሪያውን ጉርሻ ለኔ የሚያጎርሰኝ፣ አንዴ ጎርሶ ሙያየን የሚያደንቅልኝ ፣ ከራት በሁዋላ ዋይን ቀድቶ የሚያቀብለኝ፣ አጠገቤ ሆኖ እየዳበሰ ውሎውን የሚተርክልኝ -- የሚያማክረኝ ምናምን ----

ይህን ሁሉ ፍለጋ ፍቅር የሚያውቅ ሰው አገባሁ ።

ባገባሁት በነጋታው ፍቅረኛ መሆኑ ቀርቶ አባዎራ ሆነ ።

ውሎ ሲያድር ማታ ማታ
'የት ነህ?' እያልኩ ሶስት ጊዜ መደወል ጀመርኩ፣ ስልኩ ስለማይነሳ
'ደንበኛችን ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው-- ' ከምትለው ሴት ጋር ዝምድና ፈጠርን ። -'ደህና ነሽ ?' 'አስቸገርኩሽ እንግዲህ ' ምናምን እላት ጀመር።

እሷም ተጨንቃ
' ምን ታረጊዋለሽ አብዛኛው ባሎች እንዲህ ናቸው ' ብላኝ ታውቃለች።

አመሻሽቶ ሲገባ የአበባ ሽታ ሳይሆን ቢራ ቢራ እያለ መግባት ጀመረ በእጁም ኮቱን አንጠልጥሎ ስለሚገባ በእጅም ሳንነካካ እንቀራለን።

ሲገባ አያየኝም ፣ ሻሽ ልሰር ወይ አናቴ ላይ ድመታችንን ልሸከም አያይም ።

እራት ሳቀርብ ቲቪ ይከፍታል :---
ሳቀርብ ሳያየኝ ይጎርሳል ' ባለሙያ' በሚል ሙገሳ ፋንታ 'እስኪ ወጥ ነገሩን ጨምሪበት ' ይለኛል።

በልቶ ሲነሳ ማፅዳት እቀጥላለሁ እሱ ቲቪ ማየት ይቀጥላል ፣ ኳስ ከፍቶ ይመሰጣል 'ዋው ' እያለ ግብ ያደንቃል። አንዲት ድብልብል ጉድ ከኔ መብለጥዋ ያናድደኛል ---

ቢቸግረኝ የባልን አትኩሮት መሳቢያ ስድስት ሺህ መንገዶች የሚለውን መፅሃፍ ገዝቼ አንብቤ

ራሴን አሳምሬ ፣ ስስ ፒጃማ ለብሼ: እንዲያየኝ ፊት ለፊቱ መወዝወዝ ጀመርኩ። አትኩሮት ለመሳብ ነበር -- እሱ እቴ

'እስኪ ቲቪውን አትከልይኝ ' ብሎኝ ቁጭ።

አትኩሮት ለመሳብ የማደርገው ሁሉ አተካሮ ያስነሳብን ጀመር።

ልንተኛ ስንል ትራሱን ያቅፋል ፣ ስነካው ያንኮራፋል ፣ ያ ነገር ላይማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት ይመስላል
--- አለ አይደል ወዲያው ተሳፍሮ ቅርብ ይወርዳል ፣

በቃ:- አልጠራሁም እንጂ ወያላ በሉኝ :-
በር ከፍቶ ማስገባት እና ማውረድ ነገር።

ሁለት ሜትር አልጋችን ምንም ካልተጠቀምንበት የቤት ዕቃችን መሃል አንዱ ሆነ።

አብረን ከወጣን አለባበሴን የሚያደንቀው ሰውየ አሁን እራቁን ልውጣ ልልበስ ፣ ቦርሳ ልያዝ የቤታችንን ቡችላ ልዘል አያይም።

ወር ሲደርስ እንደ ኦዲተር አብረን ወጪ እና ገቢ መደመር ሆነ ስራችን ።

ሲመስለኝ ባለቤቴ ድሮ ሳንጋባ የነበረውን ፍቅሩን ሰርጋችን ላይ 'ሎጋሽቦ ' ሲጨፍር እና ሲዘልል ሳይጥለው አይቀርምና ሲወድቅበት ያየ ወይም የወደቀበትን የሚያውቅ ቢያሳውቀኝ ወሮታ ከፋይ ነኝ።》

24/03/2023

የስራው አይነት - ብብት ማሽተት

ደሞዝ - ከ74,000 እስከ 110,000 ዶላር በአመት

አለም ላይ አሉ ከሚባሉ አስገራሚ/weird ስራዎች አንዱ ነው - ብብት የማሽተት ስራ ! ደሞዙ ደግሞ ከከፍተኛ ተከፋይ ስራዎች ተርታ የሚመደብ ነው

ይህንን ስራ የሚቀጥሩት የዶዶራንት እና የብብት ሽታ ማጥፊያ ሽቶዎችን/ስፕሬይ በሚቀምሙ ድርጅቶች ነው:: ድርጅቶቹ የቀመሙትን ዶዶራንት ወይም ሽቶ ሰው ብብት ላይ ነፍተው ሰውዬው ለተወሰኑ ቀናቶች ገላውን ሳይታጠብ ይከርማል - ከዚያው የጠረኑን ለውጥ እያሸተቱ ለባለሞያው መንገር ነው🤗

አልያም ደግሞ ሰውዬው መጀመርያ ሳይታጠብ ይቆያል ከዚያም ብብት አሽታቹ አሽትቶ የሽታውን መጠን በደረጃ ያስቀምጣል:: ከዚያም ደግሞ ሰውዬው ዶዶራንቱን ወይም ሽቶውን ይቀባል -ብብት አሽታቹ በድጋሚ ያሸታል - ከዚያም ሰውዬው ከነሽታው ይቆይና በድጋሚ ይሸተታል🤗🙄

ይህ ብብት ማሽተት በእድሜ: በጾታ :በቆዳ ቀለም: ደንበኞች በሚመገቡት የምግብ አይነት እና በተለያዩ መመዘኛዎች ተከፋፍሎ የሚደረግ ሲሆን ብብት አሽታች ለመሆን ምንም አይነት የትምህርት ደረጃ አልያም የስራ ልምድ አይጠየቅበትም ይባላል

ለማንኛውም
የምትቀቡት ዶዶራንት እና የብብት ስፕሬይ/ሽቶ ይህንን ሁሉ ሂደት አልፎ ነው🤗
በዘመላክ እንድሪያስ

Photos from Zeheabsha's post 09/03/2023

ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ

| በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባለ ሦስት እና አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከቢሮው ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያው ተጠናቆ እና የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ÷ ከነገ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡

20/02/2023

እውነትም ስታገባ ይገባሀል

19/02/2023

ድምፃዊት ሀሊማ አብዱራህማን በጠና ታማለች‼️

ሁላችሁም በእየ-እምነታችሁ ፀልዩልኝ ብላችኋለች❗

ድምፃዊት ሀሊማ አብዱራህማን በነርቭ ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብታለች፡፡

ሀሊማ ከ-2 ሳምንታት ገደማ በፊት የጀማመራት ህመም በርትቶባት አልጋ እንድትይዝ አድርጓታል፡፡

ድምፃዊቷ ህክምናዋን እየተከታተለችበት ከምትገኝበት ሀሌሉያ ሆስፒታል ሆና በስልክ ከታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ጋር ባደረገችው ቆይታ አድናቂዎቿ እንደእየ እምነታቸው እንዲፀልዩላት እና በገንዘብም ድጋፍ እንዲያደርጉላት ተማፅናለች፡፡

👉ግሌሎባል ኒውስ ሃውስ

Photos from Zeheabsha's post 16/02/2023

ሰላም ለሁላችሁ:- እግዚአብሔር ጸሎትን በመልካም ይመልሳል። ሰላም ስለመጣ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። አባቶቻችንንና መሪዎቻችንንም እንዲሁ እናመሰግናለን። የታሰሩ ተፈትተው፣ ያዘኑ ተጽናንተው የምናይበት ጊዜ እንዲመጣ ጸሎታችን ነው። እግዚአብሔር ሃገርንም ምድርን የሚባርከው፣ የመንግስትን ሥራ የሚያቀናው ፍቅር ስንለብስ ነው። ተቃራኒው መንገድ ሰፊ፣ ብዙዎች የሚገቡበት ፍጻሜው ጥፋት ነው። እባካችሁ የደም ዘመን ይብቃን። የሞቱ ነፍሳቸው ሰላም ትረፍ። ለሃገር ለቤተክርስቲያን ሰላም ይሁን።
እባካችሁ አካፍሉት

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
KARULOVE123