Ethiopian Cancer Society
Sharing ideas
23/03/2025
ኦንኮ የፓቶሎጂ ምርመራ ማዕከል በአለርት ሆስፒታል አካባቢ አጠቃላይ የፓቶሎጂ እና የላቀ የላብራቶሪ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነዉ። 🎉
ማዕከላችን የእርስዎን የጤና እንክብካቤ ፍላጎቶች ለማሟላት ሳምንቱን ሙሉ ለ 24 ሰዓት እየሰራ ይገኛል።
የአገልግሎት ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት ይቀላቀሉን።የእርስዎ ጤና ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው!
Onco Advanced Diagnostic Center is providing comprehensive pathology and advanced laboratory services, conveniently located near Alert Hospital! 🎉
Our state-of-the-art facility is equipped with cutting-edge technology, ensuring you receive top-notch care whenever you need it. We are working all week, 24 hours a day, to meet your healthcare needs.
Join us in enhancing healthcare accessibility and quality within our community. Your health is our top priority!
📞0949048888 | 0949065555| 0949045555
ዛሬ ዓለም አቀፍ የካንሰር ቀን ነው፣ ይህን ምክንያት በማድረግ ስለ ካንሰር መከላከል፣ መለየት እና ማከም የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ጥቂት ግንዛቤ ማስጨበጫ መልእክት እናጋራችሁ።
1. ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ
ጤናማ ምግብ መመገብ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ እንዲሁም ከትምባሆ እና ከአልኮል መቆጠብ የካንሰር ህመምን ሊከላከሉ የሚችል መንገዶች ናቸው። ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶችን ማዘውተርም እንዲሁ።
2. መደበኛ የጤና ምርመራ ማድረግ
መደበኛ የጤና ተከታታይ ምርመራ ማድረግ የካንሰርን ምልክቶች በጊዜ ለመለየት ይረዳል። በተለይም የቆዳ፣ የጡት፣ የማህፀን የመሳሰሉ የካንሰር አይነቶችን በጊዜ ማወቅ ህክምናውን ቀላል እና ውጤታማ ያደርገዋል።
3. ስለ ካንሰር ምልክቶች መገንዘብ
ያልተለመዱ የሰውነት ለውጦች፣ እንደ ያልተለመደ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የረጅም ጊዜ የሆነ ድካም፣ የቆዳ ለውጦች፣ ወይም ያልተለመዱ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታዩ እብጠቶች የካንሰር ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እንደነዚህ አይነት ምልክቶች ካጋጠሙ ወዲያውኑ ወደ ሃኪም መሄድ ያስፈልጋል ።
4. የካንሰር ህክምና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ
የካንሰር ህክምና ረጅም እና ትግስት የሚያስፈልገው ሊሆን ይችላል። ስለዚህ፣ የስነ-ልቦና እና የቤተሰብ ድጋፍ ለህክምናው ውጤታማነት እጅግ አስፈላጊ ነው። የካንሰር ታካሚዎች እና ቤተሰቦች በሂደቱ ውስጥ መደገፍ እና መረዳት ይገባቸዋል።
የካንሰር በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የጤና ተግዳሮት ቢሆንም፣ በጥናት፣ በግንዛቤ እና በህክምና ውስጥ የተደረጉ ማሻሻያዎች ብዙ ሰዎችን ህይወት እንዲያድኑ አድርጓል።
-በአለም አቀፍ የካንሰር ቀን ስለ ካንሰር መከላከል እና ህክምና ግንዛቤ በመለዋወጥ እንዲሁም በዚህ በሽታ ላይ የሚዋጉ ሰዎችን በመደገፍ እንተባበር መልዕክታችን ነው።
24/10/2024
💡ካንሰር ምንድን ነው?
✅ካንሰር በሰውነት ውስጥ ያሉ ሴሎች (ህዋሳት) ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ እድገትና ስርጭት ሲያካሂዱ የሚከሰት በሽታ ነው ።
እነዚህ ሴሎች (ህዋሳት) ዕጢዎችን ሊፈጥሩ፣ በአቅራቢያቸው ያሉ ሕብረ ሕዋሳትን ሲወርሩ በደም ዝውውርና በሊምፋቲክ ሥርዓት አማካኝነትም ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊዛመቱ ይችላሉ።
💡የካንሰር መንስኤዎች
✅ማንኛውም ሰው ካንሰር ሊይዘው ቢችልም በርካታ ምክንያቶች ግን ይህን አጋጣሚ ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ካንሰር የሚነሳው በሴሎች ዲ ኤን ኤ ውስጥ በሚከሰቱ ለውጦች (ሚውቴሽን) ምክንያት ነው ።
እነዚህ ሚውቴሽንዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀሰቀሱ ይችላሉ፤ ከእነዚህም መካከል ፦
🔻ጀነቲካዊ ምክንያቶች- አንዳንድ ግለሰቦች ለአንዳንድ ካንሰሮች (ለምሳሌ BRCA1 እና BRCA2) የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ በዘር የሚተላለፉ ሚውቴሽንዎችን ይወርሳሉ።
🔻አካባቢያዊ ተጽእኖ- ለአንዳንድ ኬሚካሎች እና ጨረሮች መጋለጥ
🔻የአኗኗር ዘይቤዎች- ማጨስ፣ የአልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ መጠጣት፣ የአመጋገብ ችግርና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
🔻ኢንፌክሽን- አንዳንድ ቫይረሶችና ባክቴሪያዎች (ለምሳሌ፣ ኤች ፒ ቪ(HPV)፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ እንዲሁም ኤች ፓይሎሪ) ከተወሰኑ የካንሰር ዓይነቶች ጋር የተያያዙ ናቸው።
💡አለማችን ላይ በብዛት የሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች
✅ካንሰር በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል። በአለማችን ላይ በብዛት የሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
1. የጡት ካንሰር
2. ሳንባ ካንሰር
3. የፕሮስቴት ካንሰር
4. የአንጀትና ፊንጢጣ ካንሰር
5. የቆዳ ካንሰር
📍በኦንኮ የናሙና ምርመራ ማእከል ኢሙኖሂስቶኬሚስትሪን ጨምሮ የተለያዩ የካንሰር አመላካች ምርመራዎችን ያገኛሉ።
ለብልት ፍሬ ካንሰር አጋላጭ ሁኔታዎች
🔻ያልወረደ የብልት ፍሬ: አንደኛው ወይም ሁለቱም የብልት ፍሬዎች ከሆድ ወደ የብልት ፍሬ አቃፊ መግባት ሲኖርባቸው ሳይገቡ ይቀራሉ ማለት ነው።
🔻 የቤተሰብ ታሪክ : በብልት ፍሬ ካንሰር የተጠቃ አባት ወይም ወንድም መኖር የመያዝ አጋጣሚውን ከፍ ሊያረገው ይችላል። ይሁን እንጂ በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱት የብልት ፍሬ ካንሰሮች በጣም ጥቂት ናቸው ፤ የብልት ፍሬ ካንሰር የያዛቸው አብዛኞቹ ወንዶችም የበሽታው የቤተሰብ ታሪክ የላቸውም ።
🔻 የኤች አይ ቪ ኢንፌክሽን: አንዳንድ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት በኤች አይ ቪ ኤድስ የተያዙ ሰዎች በበሽታው የመያዝ አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ ነው።
🔻 ዕድሜ : በብልት ፍሬ ካንሰር ከሚጠቁት ግማሽ የሚያህሉት ከ20 እስከ 34 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶች ናቸው ። ይሁን እንጂ ይህ ካንሰር ሕፃናትንና አረጋውያንን ጨምሮ በማንኛውም ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወንዶችን ሊያጠቃ ይችላል ።
ምልክቶቹስ❓
በብልት ፍሬ ካንሰር የተያዙ አንዳንድ ወንዶች ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ላያሳዩ፤ ካንሰሩም ሌሎች የጤና እክሎች፣ የመውለድ ችግር መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ በሚደረጉ ምርመራዎች ሊገኝ ይችላል።
🚩እብጠት
አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያው በብልት ፍሬ ካንሰር ምልክት በብልት ፍሬ ላይ ያለ እባጭ፤ አሊያም ደግሞ የተለየ የመጠን መተለቅ ነው። ( በተለምዶ አንደኛው የብልት ፍሬ ከሌላው ትንሽ በልጦ ወይም ከሌላኛው ዝቅ ብሎ ሊገኝ ይችላል።) አንዳንድ የብልት ፍሬ እብጠቶች ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ።
🚩ያለእድሜ ጉርምስና
አንድሮጂን የሚያመነጩ እብጠቶች በወጣት ወንዶች ላይ ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ላያመጡ ይችላሉ። ይሁን እንጂ በወንዶች ልጆች ላይ የፊትና የሰውነት ፀጉር ማደግ የመሳሰሉ ከተለመደው ገና በልጅነታቸው የጉርምስና ምልክት ሊያሳይ ይችላል።
📍ኦንኮ የፓቶሎጂ ምርመራ ማዕከል
የባዮፕሲ (ናሙና) ምርመራ እና ኢሚዩኖሂስቶኬሚስትሪ አገልግሎት ይሰጣል።
ልክ እንደ ሌሎች በሽታዎች የእያንዳንዱን ቤት በር እያንኳኳ ያለ በሽታ ነው።
ካንሰር በጊዜ ከታወቀ በአግባቡ ከታከመ ይድናል። ሁሉም ሰው ስለ በሽታው ግንዛቤ ይኑረው።
05/03/2024
04/03/2024
01/03/2024
የካቲትን ለኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን!
በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር የካቲትን ለኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን እንለግሳለን!
እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/ethio_telecom
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/ethiotelecom
ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/ethiotelecom/
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom
ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH
ቲክቶክ፡ http://www.tiktok.com/?lang=en
ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!
22/02/2024
THE SITUATION OF CANCER IN ETHIOPIA: In Ethiopia, cancer accounts for about 5.8% of total national mortality. Although population-based data do not exist in the country except for Addis Ababa, it is estimated that the annual incidence of cancer is around 60,960 cases and the annual mortality is over 44,000
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
SUPPORTINGVICTIMS