ኮኮብ ፔጅ
ጤናዎ የሁሉም ነገር መሰረት ነው!
እባኮዎን በወቅቱ አስፈላጊ ምርመራ በማድረግ ጤንነቶን ይጠብቁ መልካም ጤንነት ተመኘውላችሁ የእናተው ዶክተር ሰብለ አለሙ ነኝ ሚዲያን በአግባቡ እንጠቀም
14/06/2026
13/06/2026
12/06/2026
Visit TikTok to discover videos! Watch, follow, and discover more trending content.
11/06/2026
ጠዋት በባዶ ሆድ ለብ ያለ ውሃ መጠጣት የሚያስገኘው አስገራሚ ጥቅም!💧
ሙቅ ውሀ መጠጣት በጨጓራ ዙሪያ ያሉ የደም ስሮች እንዲፍታቱ በማድረግ እና የጨጓራ ጡንቻዎችን በማላላት ቶሎ እንዲነቃና ለቁርስ ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል
ምን ምን ጥቅሞች አሉት❔
✔ የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል
ለብ ያለ ውሃ የጨጓራና የአንጀት ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ፤ የምግብ መፈጨት ስርአታችን ስራውን እንዲጀምር እንደ ማስነሻ ያገለግላል እንዲሁም ድርቀትን ይከላከላል
✔ የጨጓራ አሲድን ያረጋጋል
ለብ ያለ ውሃ ስንጠጣ የጨጓራ አሲድን በማቅጠን/በመበረዝ በጨጓራ ግድግዳ ላይ የሚፈጥረውን የማቃጠል ስሜት ወዲያውኑ ይቀንሰዋል እንዲሁም የአሲድ ፍሰትን ወደ ታች በመግፋት በጨጓራና በጉሮሮ መገናኛ አከባቢ የተጠራቀመ አሲድ ካለ፣ ውሃው ጠርጎ ወደ አንጀት እንዲወርድ ያደርገዋል። ይህም የቃር ስሜትን ለማጥፋት ይረዳል
✔ የደም ዝውውርን ያሻሽላል
የውሃው ሙቀት የደም ስሮቻችን እንዲሰፉ ስለሚያደርግ፣ ወደ ጨጓራና አንጀት የሚሄደው የደም ፍሰት እንዲጨምር ያደርጋል። ይህም የጨጓራ ውስጠኛው ሽፋን በፍጥነት እንዲያገግም ይረዳል
✔ የጨጓራ ጡንቻዎችን ያዝናናል
በሙቀቱ አማካኝነት በጠዋት የሚሰማንን የጨጓራ መኮማተር፣ መነፋት እና ቁርጠትን ይቀንሳል (ለወር አበባ ህመምም ሊያግዝ ይችላል)
✔ በሆድ ውስጥ ያሉ ቅባቶችን ያስወግዳል
ከእራት የተረፉ እና በጨጓራችን ውስጥ ተጣብቀው የቀሩ ቅባቶች እና የምግብ ትርፍራፊዎች በቀላሉ እንዲሟሙና እንዲወገዱ ይረዳል እንዲሁም በለሊት በጨጓራችን ውስጥ የሚከማቹ ትርፍ ንፍጥ መሰል ፈሳሾችን ጠርጎ በማውጣት፣ የምንበላው ቁርስ ንጥረ-ነገር በደንብ እንዲመጠጥ ያደርጋል
❗ታዲያ ስንጠጣ በጣም ትኩስ መሆን የለበትም፤ ለብ ያለ ከሆነ በቂ ነው እንዲሁም አንድ ከበዛ ሁለት ብርጭቆ ቀስ ብሎ መጠጣት እና ከ30 ደቂቃ በኋላ ቁርስ መብላት ይመከራል
እርሶስ ጠዋት የትኛውን ያስቀድማሉ? ☕ ቡና ወይስ 💧 ለብ ያለ ውሃ?
Click here to claim your Sponsored Listing.