Eva Gizepa
This page evangelical purpose
15/09/2023
" አታፍሪምና አትፍሪ፤ አተዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4)
13/10/2022
እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፥ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፥ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላስታወቀን ነበር ።
(መጽሐፈ መሳፍንት 13:23)
09/10/2022
ውድ ተማሪዎች መልካም ፈተና!!!!
02/10/2022
28/09/2022
"At a time of rampant misinformation, climate denial & attacks on human rights, we need education systems that distinguish fact from conspiracy, instill respect for science & celebrate humanity in all its diversity."
-- UN Secretary-General António Guterres at the Summit.
27/09/2022
📚📚📚 📚📚📚
🙏🙏🙏 🙏🙏🙏
📚 ግዕዝ ፡ በአፍሪካ ቀንድ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በኤርትራ ፡ በጥንት ፡ የተመሠረተና ፡ ሲያገለግል ፡ የቆየ ፡ ቋንቋ ነው። የግዕዝ ፡ አመጣጥ ፡ በግምት ፡ የዛሬ ፡ ፫ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ከየመን ፡ እና ፡ ደቡብ ፡ አረቢያ ፡ በመነሣትና ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ በመሻገር ፡ በኤርትራ ፡ እና፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከሰፈሩ ፡ የተለያዩ ፡ የሳባውያን ፡ ነገዶች ፡ ቋንቋና ፡ በጊዜው ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይነገሩ ፡ በነበሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ ዘገምተኛ ፡ ውኅደት ፡ ነው።[1] በአክሱም ፡ መንግሥትና ፡ በኢትዮጵያ ፡ መንግሥት ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነበር።
📚 ኦሪት ፡ ዘፍጥረት ፡ ፳፱ ፡ በግዕዝ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ
ግዕዝ ፡ ከአማርኛና ፡ ሌሎች ፡ ኢትዮ-ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ጋር ፡ ሲወዳደር ፡ «ንጹሕ» ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው።[1] ግዕዝ ፡ እስከ ፡ ፲ኛው ፡ ክፍለ-ዘመን ፡ መጀመሪያ ፡ ድረስ ፡ ዋነኛ ፡ የመግባቢያ ፡ ቋንቋና ፡ ልሳነ ፡ ንጉሥ ፡ ነበር።[1] ከ ፲፫ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ ግን ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ መነገር ፡ አቁሞ ፡ በሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በትግርኛ ፡ እንዲሁም ፡ በማዕከላዊው ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፡ በአማርኛ ፡ ተተካ።[1] ዛሬ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሥነ-ስርዓት ፡ እንዲሁም ፡ በኤርትራ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያ ፡ ካቶሊክ ፡ ቤተክርስቲያን እና ፡ በቤተ-እስራኤል ፡ ሥነ-ስርዓቶች ፡ ይሰማል። በሰሜን፡ ኤርትራ ፡ የሚገኘ ፡ ትግረ ፡ የሚባል ፡ ቋንቋ ፡ ከሁላቸዉ፡ የሰሜን ፡ኢትዮጵያ ፡ቋንቋዎች፡ ለግእዝ ፡ በቅርብ ፡ ይዛመዳል ፡ እና። ትግረ ፡ ፸ በመቶ ፡ ግእዝ ፡ ነዉ ፡ እና ፡ በመቀጠል ፡ ትግርኛ ፡ እና ኣማርኛ።
📚 ቋንቋው ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ አባል ፡ እየሆነ ፡ በደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ውስጥ ፡ ይካተታል። ደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ በመባሉ ፡ ግዕዝ ፡ የሣባ ፡ ቋንቋ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ የተጻፈው ፡ በግዕዝ ፡ ፊደል ፡ አቡጊዳ ፡ ነው። ይህም ፡ ፊደል ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ለአማርኛ ፣ ለትግርኛ ፡ እና ፡ ለሌሎችም ፡ ቋንቋዎች ፡ ይጠቀማል። በመላውም ፡ የአፍሪቃ ፡ አህጉር ፡ ውስጥ ፡ የመጀመሪያውና ፡ ብቸኛ ፡ አፍሪቃዊ ፡ የራሱን ፡ ፊደላት ፡ የያዘ ፡ ቋንቋ ፡ ሲሆን ፣ በዓለምም ፡ ላይ ፡ ዋናና ፡ የስልጣኔ ፡ አራማጅ ፡ ከሚባሉት ፡ ቋንቋዎች ፡ አንዱ ፡ ነው። በግዕዝ ፡ ጽሕፈት ፡ ፳፮ ፡ ፊደላት ፡ ብቻ ፡ ይጠቀሙ ፡ ነበር ፤ እነርሱም፦
👉 ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ መ ፣ ሠ ፣ ረ ፣ ሰ ፣ ቀ ፣ በ ፣ ተ ፣ ኀ ፣ ነ ፣ አ ፣ ከ ፣ ወ ፣ ዐ ፣ ዘ ፣ የ ፣ ደ ፣ ገ ፣ ጠ ፣ ጰ ፣ ጸ ፣ ፀ ፣ ፈ ፣ ፐ
ናቸው።
📚 ሊቁ ፡ ሪቻርድ ፓንኩርስት ፡ እንደሚጽፍ ፣ አንድ ፡ ተማሪ ፡ በመጀመርያው ፡ አመት ፡ ፊደሉን ፡ ከተማረ ፡ በኋለ ፣ በሚከተለው ፡ አመት ፡ መጀመሪያይቱ ፡ የሐዋርያው ፡ የዮሐንስ ፡ መልእክትን ፡ ከአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግዕዝ ፡ ከትዝታ ፡ ለመጻፍ ፡ መማር ፡ ነበረበት። በሦስተኛው ፡ ደረጃ ፡ የሐዋርያት ፡ ሥራ ፡ በአራተኛውም ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ በግዕዝ ፡ ማስታወስ ፡ ነበረበት። ይህንን ፡ ከጨረሰ ፡ ታላቅ ፡ ግብዣ ፡ ይደረግና ፡ ልጁ ፡ ጸሐፊ ፡ ይሆን ፡ ነበር።
📚 በብሪቲሽ ፡ ቤተ-መጻሕፍት ፡ (የእንግሊዝ ፡ አገር ፡ ብሔራዊ ፡ ቤተ-መጻሕፍት) ፡ ውስጥ ፡ ፰፻ ፡ የሚያሕሉ ፡ የድሮ ፡ ግዕዝ ፡ ብራናዎች ፡ አሉ።
📚 በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ፡ ትምህርቶች ፡ ዘንድ ፣ ግዕዝ ፡ የአዳምና ፡ የሕይዋን ፡ ቋንቋ ፡ ነበር። ፊደሉን ፡ የፈጠረው ፡ ከማየ አይኅ ፡ አስቀድሞ ፡ የሴት ፡ ልጅ ፡ ሄኖስ ፡ ነበረ። ከባቢሎን ፡ ግንብ ፡ ውድቀት ፡ በኳላ ፣ ከአርፋክስድ ፡ ወገን ፡ የዮቅጣን ፡ ልጆች ፡ ቋንቋውን ፡ እንደ ፡ ጠበቁት ፡ ይባላል። የዮቅጣን ፡ ልጅ ፡ ሣባ ፡ ነገዶች ፡ ከዚያ ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ አሻግረው ፡ ወደ ፡ ዛሬው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ያስገቡት ፡ ይታመናል። እንዲሁም ፡ ካዕብ ፡ እስከ ፡ ሳብዕ ፡ (አናባቢዎችን ፡ ለመለየት) ፡ ወደ ፡ ፊደል ፡ የተጨመረበት ፡ ወቅት ፡ በንጉሥ ፡ ኤዛና ፡ ዘመን ፡ እንደ ፡ ነበር ፡ ይባላል።
✍️ የግዕዝ ምንጭ
21/09/2022
አሜን
03/07/2022
በመተሐራ ጌታ መልካም ጊዜ ሠጠን....ከሰማይ ድምፅ መጣ።
02/07/2022
ዛሬ መልካም ይሆናል
Click here to claim your Sponsored Listing.