MozoCare Et

MozoCare Et

Share

Mozocare - Find Healthcare Abroad

08/03/2024

🎉እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ March 8 አደረሳችሁ💥
👩‍🦰የሴቶች ቀን በብዙ አገሮች ብሔራዊ በዓል ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ በደማቁ ታስቦ ይውላል።✨

👀የሴቶች ቀን ለምን ይከበራል❓
👉መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ3 ሴቶች አንድዋ ፆታዊ ጥቃት ይደርስባታል።
👉በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 129 ሚሊየን የሚጠጉ ሴቶች የትምህርት እድል አያገኙም ።
👉በየሁለት ደቂቃው በወሊድ ምክኒያት የምትሞት እናት አለች፡፡
👉ከ200 ሚሊዮን በላይ ሴቶች የግርዛት ሰለባ ሆነዋል፡፡

👩‍🦱በሴቶች ላይ የሚደርሱ ችግሮች ማህበረሰቡን የሚጎዱ ስለሆኑ ሁላችንም ችግሮቹን ለመቅረፍ ልንተባበር ይገባል:: የሴቶች ቀን እነዚህን እና የመሳሰሉ ችግሮች ያጋጠማቸውን ሴቶች ከጎናቸው እንዳለን የምናሳይበት፤ በተለያየ ዘርፍ ውጤታማ የሆኑ ሴቶችን የምናበረታታበት ነው::✨

🧐እናንተስ የሴቶች ቀንን እንዴት ለማክበር አስባችኋል?
🧍‍♀️በህይወታችሁ ውስጥ ያሉ ሴቶችን በመንከባከብ ምን ያህል ዋጋ እንዳለቸው አሳዩዋቸው፡፡ ራሳቸውን ከተለያዩ በሽታዎች እንዲከላከሉ እና ጊዜውን የጠበቀ ሙሉ ምርመራ እንዲያደርጉ አስታውሷቸው፡፡ሴቶችዬም ራሳችሁን ተንከባከቡ፡፡ ✨
👩‍⚕️ስንቶቻችን ነን ራሳችንን በመፈተሽ ካንሰርን መከላከል እንደምንችል የምናውቀው?
1.የጡት ካንሰር፡
➡️ማንኛዋም ከ20 ዓመት በላይ የሆነች ሴት በየወሩ የራሷን ጡት መመርመር አለባት፤የወር አበባ የምታይ ሴት ከሆነች በየወሩ የወር አበባዋ መጥቶ ከሄደ ከ5 እስከ 7 ቀናት በኋላ ብታደርገው ይመከራል፡፡
🤰የእርግዝና ጊዜ ላይ አልያም 👵 የማረጥ (menopause) ጊዜ ላይ ያለች ሴትም ብትሆን በየወሩ የምታስታውሰውን የተለየ ቀን ( ልደት፣ ወርሃዊ በዓል የሚከበርበትን ቀን ) በመጠቀም ይሄን የራሷን ጡት የመፈተሽ ሂደት ብታደርገው ይመከራል፡፡
➡️ማንኛዋም 40 ዓመት የሞላት ሴት በጤና ባለሙያ የሚደረግ የጡት ምርመራ ስለማድረግ ከሀኪም ጋር መመካከር አለባት፡፡
የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ በጡት ካንሰር የመያዝ አደጋን ባይቀንስ እንኳን በሽታው ቶሎ ታውቆ ተገቢውን ሕክምና ለማግኘት ይረዳል።
2. የማህፀን በር ካንሰር
➡️ማንኛዋም ሴት የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ ከጀመረች ከ 3 ዓመት በኋላ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ መጀመር አለባት፡፡
3.የ HIV ምርመራ
➡️በ አመት 1 ጊዜ ወይም ሁሌ ለጠቅላላ ምርመራ በሚሄዱበት ጊዜ የኤችአይቪ ምርመራ ማድረግ ይመከራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
ለHIV አጋላጭ የሚያረጉ ሁኔታዎች ለመቀነስ የመከላከል መንገዶችን ማለትም መታቀብ ፣መወሰን እና መጠቀምን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
4.የስነ ተዋልዶ ጤና፡
➡️የወሊድ መከላከያን በተመለከተ፣ ስለ የወር አበባ ዑደት መዛባት፣ የወሲብ ጤና እና ከማረጥ ጋር የተያያዙ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ጨምሮ ስለ አጠቃላይ የስነ ተዋልዶ ጤና ከሃኪምዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ውይይት ማድረግ::
5. አጠቃላይ የጤና ምርመራ፡
🩺እንደ የደም ግፊት፣ የልብ ምት ፣የሙቀት መጠን፣ የደም ግሉኮስ ያሉ ምርመራዎችን በተለይም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው አመታዊ ምርመራዎችን ማድረግ፡፡
6. Body Mass Index (BMI)፡-
➡️ይህ ከቁመትዎ አንፃር ሊኖርዎት የሚገባውን ክብደት ይነግረዎታል፡፡ ከመጠን ያለፈ ወይም ከመጠን ያነሰ ክብደት የጤና ችግሮችን ሊያመለክት ይችላል። ጤናማ ክብደትን መጠበቅ ለተለያዩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል። ለዚህም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ🥗 እና ፣ስብ ከበዛባቸው ምግቦች መቆጠብ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ🏃‍♀️ በእጅጉ ይረዳል፡፡
💁‍♀️ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ምርመራዎች እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል የራስሽን እና በዙሪያሽ ያሉትን ጤና ጠብቂ፡፡ 👫
🙋🏻ይህንን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት ፍቅራችሁን አሳዩ፡፡💌
👩‍⚕️መልካም የሴቶች ቀን ይሁንላችሁ🧑‍⚕️
ከ Mozocare🌟

✈️በውጭ ሀገር ጥራት ያለው ህክምናን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት MozoCare አብሯችሁ ነው! 🌎

04/03/2024

ስለ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምን ያውቃሉ?
🌟 ካንሰር የሚለው ቃል የህዋሶችን ጤናማ ባልሆነ መልኩ ማደግ እና መባዛትን ያመለክታል፡፡
👩‍⚕️የማህፀን በር ጫፍ ላይ የሚገኙ ህዋሶች በተፈጥሮ ባሉ ሆርሞኖች ምክኒያት የተለያዩ ለውጦችን በየጊዜው ያስተናግዳሉ፡፡ በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለፉት ህዋሶች ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ በሚባል በግብረ ስጋ ግኑኝነት በሚተላለፍ ቫይረስ ሲጠቁ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እንዲፈጠር ምክኒያት ሆናሉ፡፡ ✨
ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
🩺 ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ከ100 በላይ አይነቶች ስላሉት ማንኛውንም ሴት ለዚህ ቫይረስ የመጋለጥ እድል አላት፡፡
ስለዚህም ማንኛዋም የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽማ የምታውቅ ሴት ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ እድል አላት፡፡
ይሁን እንጂ፡
➡️ በለጋነት ዕድሜ (ከ20 ዓመት እድሜ በታች) የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች
➡️ ከተለያዩ ወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች
➡️ በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ያጋጠማቸው ሴቶች (ለምሳሌ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ)
➡️ በአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡

🥼 በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች የማህፀን በር ካንሰር ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል፤ በሽታው ከተባባሰ በኋላ ግን ምልክቶች እየታዩ ይመጣሉ ።
👉 ከወር አበባ ወቅት ውጭ ከማህፀን ደም መፍሰስ
👉 የዳሌ ህመም
👉 በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ህመም
👉የወር አበባ ጊዜ የተራዘመና ከባድ መሆን
👉የመውለጃ ጊዜ ወይም ዕድሜ ካለፈ በኋላም ከማህፀን ደም መፍሰስ ማጋጠም
👉 ያልተለመደ ወይም ለየት ያለ ጠረን ያለው የብልት ፈሳሽ
👉ድካም፣ የወገብ ህመም፣ መክሳት፣ የሆድ ህመም ናቸው ።

💁‍♂️የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚያስከትላቸው ጉዳቶችስ ምንድናቸው?
❎የደም መርጋት
❎የደም መፍሰስ
❎ፊስቱላ
❎የሆድ ድርቀት
❎የመሽናት ችግር
❎መካንነት
❎ውስጣዊ የሰውነት አካል ከጥቅም ውጪ መሆንና የመሳሰሉትን ጉዳቶች በማምጣት የማህፀን በር ካንሰር እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ህመም ነው፡፡

27/02/2024

የጡት ካንሰር ህክምና በMozoCare

👩‍⚕️ የጡት ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን 👩‍🦰 ለሞት ከሚዳርጉ የካንሰር አይነቶች ውሰጥ በአንደኝነት ይቀመጣል፡፡
💡የጡት ካንሰርን የመከላከል ስልቶች ብዙ ጊዜ የሚያተኩሩት ጤናማ የአኗኗር ሁኔታዎችን🥗🏃🏻 በመከተል እና ህመሙ ከተከሰተ በኋላ ደግሞ በቶሎ ህክምናን በማግኘት የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ ላይ ነው። ✨

✈️ በህንድ፣ ቱርክ፣ወይም አውሮፓ እውቅና ባላቸው ከ300 በላይ ሆስፒታሎች ውስጥ ጥራት ያለው የጡት ካንሰር ህክምናን በተመጣጣኝ ዋጋ 🌎በMozoCare ያግኙ፡፡

👨‍⚕️የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፡

📲 ስለሚያስፈልጎት የጡት ካንሰር ህክምና አይነት ማማከር፡፡ የሚያስፈልጐት ህክምና ምንድን ነው? ቀዶ ጥገና፣ የጨረር ህክምና፣ ኬሞቴራፒ ወይስ የሆርሞን ህክምና?🧑‍⚕️
🗒የተሟላ የህክምና እና የጉዞ ዕቅድ ማዘጋጀት፤
📁 የሚያስፈልጉ ሙሉ መረጃዎቸን ማዘጋጀት፤ ከዚህ በፊት የት እንደታከሙ ፣ ምን አይነት ህክምና እንዳረጉ የሚያሳይ ሙሉ መረጃዎች መሰብሰብ ።
🏥በሚፈልጉት ሀገር ጥራት ያለው የጡት ካንሰር ህክምና የሚሰጡ የሆስፒታል አማራጮችን ማሳወቅ
💵የሚያስፈልጉ የጉዞ ቀድመ ሁኔታዎችን እና አጠቃላይ ወጪዎችን ማሳወቅ ፣
🛫 የአየር ትኬት መቁረጥ እና ማረፊያ ቦታን ማመቻቸት 🛋
👨‍⚕️ህክምናውን ጨርሰው ሲመለሱ በሀኪም የተደገፈ ክትትል ማድረግ

💁‍♂️በአጠቃላይ ለጥቄዎቻችሁ አፋጣኝ መልስ📞 በመስጠት እና በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ከጎናችሁ በመሆን ህክምናችሁን በሰላም አጠናቃችሁ ወደ ሙሉ ጤንነታችሁ እስክትመለሱ ድረስ አብረናችሁ ነን🤝::

🙌Looking for high-quality Breast cancer treatment at affordable prices? Look no further!

🌟 Mozocare offers a wide range of medical services, including mastectomy, lumpectomy, quadrantectomy, radiation therapy, Hormonal therapy and chemotherapy treatments around the world✨

🌎More than 300 Hospitals📍 at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

22/02/2024

ካንሰር ምንድን ነው?
ካንሰር በሰው አካል ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ እና ባልተለመደ የሕዋሳት መባዛት ምክንያት የሚከሰት በሽታ ሲሆን በመጨረሻም የካንሰር እጢ ይፈጥራል ፡፡ ካንሰር ከተጠቃው የአካል ክፍል በመነሳት በአቅራቢያው ወዳሉ የአካል ክፍሎች ወይም ወደሌሎች የአካል ክፍሎች ካንሰሩ እንደ ጀመረበት ቦታና እንደ ካንሰር አይነቱ የሚወሰን ቢሆንም በደም ዝውውር ውስጥ ሊሰራጭ ይችላል፡፡

❓የካንሰር ዓይነቶች እነማን ናቸው

👉የጡት ካንሰር፦ይህ የጡት ህዋስ የሚያጠቃ የ ካንሰር አይነት ነው።
👉የማህጸን ካንሰር ፦ይህ የማህጸን ህዋስ የሚያጠቃ የ ካንሰር አይነት ነው።
👉ካርሲኖማ፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከሰውነታችን አካላት ላይ ነው፡፡
👉ሳርኮማ፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከሕብረ ሕዋሶች (tissues) ነው፡፡
👉የደም ካንሰር (ሉኬሚያ)፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው በአጥንት መቅኒ ውስጥ ካሉ የደም ህዋሳት ነው፡፡
👉ሊምፎማ እና ማይሎማ፦ ይህ የካንሰር አይነት ከሊምፍ ኖድ እና የበሽታ መከላከያ ስርዓት (immune system) የሚመነጭ ነው፡፡
👉የማዕከላዊ ሥርዓተ ነርቭ ካንሰር፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከአንጎል እና ከአከርካሪ አጥንት መቅኒ ነው።

❓ለካንሰርየሚያጋልጡምክንያቶች ምንድን ናቸዉ

➡️👨‍🦳እርጅና
➡️🚬ሲጋራ ማጨስ
➡️☀️ለፀሐይ ብርሃን ወይም አልትራቫዮሌት ጨረር መጋለጥ– ለረጅም ሰአታት በቀን፤ ለረጅም አመታት፤ እንዲሁም የቆደ ቀለማቸው ስስ በሆኑ ሰዎች ላይ የቆዳ ካንሰር ያስከትላል
➡️🥂አልኮሆል መጠጥ
➡️ለኬሚካል መጋለጥ
➡️ቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች
➡️የኢስትሮጅን ሆርሞን መዛባት
➡️ለችግሩ አጋላጭ ባህሪያት (ለምሳሌ ጤናማ ያልሆነ አበጋገብ፣ በቂ ያልሆነ እንቅልፍ፣ 🏃‍♂🏃‍♂የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እጥረት፣ ጭንቀት🤦‍♂
➡️ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ – 🥩ስብ፤ጨው፤ስኳር፤ሳቹሬትድ እና ትራንስ ፋት የበዛበት እንዲሁም በተቀራኒው አትክልትና ፍራፍሬን 🥗አዘውትሮ አለመጠቀም ነው፡፡

የካንሰር ሕክምና ዘዴዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ
1⃣ራዲዮ ቴራፒ (Radio Therapy )

2⃣ታርጌትድ ቴራፒ (Targeted Therapy)

3⃣ቀዶ ጥግና (Surgery)

4⃣ኢሚውኖ ቴራፒ (Immunotherapy)

5⃣ሆርሞናል ቴራፒ (Hormonal Therapy)

6⃣ኪሞቴራፒ (Chemotherapy)

7⃣ሴል ቴራፒ (Cell therapy)

8⃣የካንሰር ክትባት (Cancer Vaccine)

MozoCare በሕክምናው ላይ እንዴት መርዳት ይችላል ?
የት ሄጄ ልተታከም ብለው በፍለጋ ላይ ከሆኑ ✈️በህንድ፣ ቱርክ፣ወይም ስፔን ሀገሮች ላይ ህክምናውን እንዲያገኙ አመቻችተናል።

🙌Looking for high-quality cancer treatment at affordable prices? Look no further!

🌟 Mozocare offers a wide range of medical services, including what the stage the cancer is which therapy you need Radio Therapy ,Immunotherapy,Hormonal Therapy ,Chemotherapy Other such as check if the cancer has spread there.✨

🌎More than 600 Hospitals📍 at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ

21/02/2024

🧐 የራስን ጡት በመዳሰስ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው ?
💡የራስን ጡት መመርመር እጅግ በጣም ቀላል የቅድመ ካንሰር ምርመራ አይነት ሲሆን፤ የጡት ካንሰር ካለም በጊዜ ታውቆ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሳይዛመት ለማዳን ያስችላል።✨

💁‍♀️ ይሄን ማን ማድረግ አለበት ?
💡ማንኛዋም ከ20 ዓመት በላይ የሆነች ሴት በየወሩ የራሷን ጡት መመርመር አለባት፡፡
👱‍♀️የወር አበባ የምታይ ሴት ከሆነች በየወሩ የወር አበባዋ መጥቶ ከሄደ ከ5 እስከ 7 ቀናት በኋላ ብታደርገው ይመከራል፡፡
🤰የእርግዝና ጊዜ ላይ አልያም 👵 የማረጥ (menopause) ጊዜ ላይ ያለች ሴትም ብትሆን በየወሩ የምታስታውን የተለየ ቀን ( ልደት፣ ወርሃዊ በዓል የሚከበርበትን ቀን ወ.ዘ.ተ..) በመጠቀም ይሄን የራሷን ጡት የመፈተሽ ሂደት ብታደርገው ይመከራል፡፡✨
🫃በእርግዝና ጊዜ የሚደረግ የምርመራ ውጤት በእርግዝና ጊዜ በተፈጥሮ ጡት ላይ የሚያጋጥሙ ለውጦችን ከግምት ውሰጥ ያስገባ መሆን አለበት🧑‍⚕️

❓ለራስ ጡት እንዴት የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ ይቻላል ?
🌟የራስን ጡት በመዳሰስ የቅድመ ካንሰር ምርመራን የመተግበር ሂደት ሲከናወን በቂ ብርሀን ያለበትን ክፍል እና ንፁህ መስታወትን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡✨
💡የሚከተሉት ቀጣይ መደረግ ያለባቸውን ተግባራትን ይገልፃሉ፡-
🙎‍♀️ራስን ዘና ማረግ እና ከ ወገብ በላይ ልብስን አውልቆ ከመስታወት ፊት ለፊት ቀጥ ብሎ መቆም🧍‍♀️::
👯‍♀️ ክንድን በማጠፍ በመዳፍ ወገብን ይዞ በመስታወት እያዩ እራስን መቃኘት👯‍♀️::
👀 ይህም በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት ካለ ፣ የጡት ጫፍ ወደ ዉስጥ መሰርጓድ፣ የጡት ቆዳ ቀለም መቀየር ፣የሁለቱ ጡት መጠን እኩል ያለመሆን ምልክቶች ካሉ ለማወቅ ይጠቅማል።✨
🙆‍♀️እጅን ከፍ በማድረግ የራስን ቅል በእጅ በመደገፍ ብብት አከባቢ እብጠት መኖሩን እና አለመኖሩን በመስታውት ማየት🙆::
🛏 ጠንከር ያለ አልጋ ላይ ወይም ደረቅ ቦታ ላይ በጀርባ በመተኛት 🙋🏻የግራ እጅን ከጭንቅላት በላይ ማኖር። በብታችን ትይዩ ትራስ በመጨመር በቀኝ እጅ የመሐል ሦስት ጣቶች (ጠቋሚ ፣የመሀል እና የቀለበት ጣት )በመጠቀም የግራ ጡትን ከብብት ጀምሮ ከላይ ወደታች ክብ በሆነ አኳኋን መዳሰስ። የእጃችንን ኃይል እየቀያየርን ጡታችንን ሦስት ጊዜ በደንብ መዳሰስ ያስፈልጋል። ከዚያም የጡት ጫፍን በመደሳስ ለውጥ መኖሩ እና አለመኖሩን መለየት። በተመሳሳይ ለተቃራኒው ጡት መስራት👩‍⚕️ ።
💡ከጡት ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ መኖሩን እና አለመኖሩን መለየት፡፡ ደም የቀላቀለ አልያም ፣ መግል የያዘ ፈሳሽ ከጡት ጫፍ ሚወጣ ከሆነ ትኩረት ሰጥቶ መመልከት ያስፈልጋል።🩺
🏥በአጠቃላይም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከታዩ በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማረግ አስፈላጊ ነው 🧑‍⚕️::

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

18/02/2024

👩‍⚕️ስለ ጡት ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?

🗣 የጡት ካንሰር ስሙ እንደሚያመለክተው ከጡት ህዋሶች የሚነሳ የካንሰር አይነት ነው። ይህ የሚከሰተው በጡት ውስጥ ያሉ ህዋሶች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ሲያድጉ እና ሲባዙ ለአደገኛ ዕጢ መፈጠር ምክንያት ስለሚሆኑ ነው። የጡት ካንሰር በሴቶች እና በወንዶች ላይ ሊከሰት ይችላል:: ነገር ግን በ👩‍🦰 ላይ በጣም የተለመደ ነው።✨

የጡት ካንሰር ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

👉 በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት
👉 ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መዉጣት
👉 የጡት ቆዳ ወደ ዉስጥ መሰርጎድ
👉 የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም
👉 የጡት ጫፍ ከጊዜ በኋላ ወደ ዉስጥ መግባት
👉 የጡት ቆዳ ቀለም መቀየር
👉በሁለቱ ጡት ከፍተኛ የመጠን ልዩነት መኖር እና የታመመዉ ማበጥ ይገኙበታል።

❓የጡት ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
🧑‍⚕️የጡት ካንሰርን የመከላከል ስልቶች ብዙ ጊዜ የሚያተኩሩት ጤናማ የአኗኗር ሁኔታዎችን በመከተል እና ጉዳትን በመቀነስ ላይ ነው።

1️⃣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል፡
🏃🏻 መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ🤽‍♀️
⏲ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ
🥗 በአትክልትና ፍራፍሬ የበለፀገ የተመጣጠነ አመጋገብ መከተል።🥙
❌ አልኮል መጠጣትን እና ሲጋራ ማጨስን ማስወገድ🚭
🤱 ጡት ማጥባትን ማበረታታት

2️⃣ቅድመ ምርመራን ማድረግ
💡 የቅድመ ምርመራ ዋና ዓላማ የጡት ካንሰር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንዳለ ሳይስፋፋ በፊት በማወቅ አስፈላጊውን የሕክምና መፍትሔ ማግኘት እንዲቻል ማድረግ ነው።🥼
👀 የሚከተሉት ከጡት ካንሰር የቅድመ ምርመራ አይነቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው :
➡️የእራስን ጡት በመዳበስ መፈተሽ፡
ራስን መፈተሽ በራስ ጡቶች ላይ ለውጦችን የማግኘት መንገድ ሲሆን ማንኛዋም ከ20 ዓመት በላይ የሆነች ሴት በየወሩ እንድታደርገው ይመከራል፡፡✨
💡የወር አበባ የምታይ ሴት ከሆነች በየወሩ የወር አበባዋ መጥቶ ከሄደ ከ5 እስከ 7 ቀናት በኋላ ብታደርገው ይመከራል፡፡ የወር አበባ የማታይ ሴት ከሆነች በየወሩ የምታስታውን የተለየ ቀን ( ልደት፣ ወርሃዊ በዓል የሚከበርበትን ቀን ወ.ዘ.ተ..) በመጠቀም ይሄን የራሷን ጡት የመፈተሽ ሂደት ብታደርገው ይመከራል፡፡👍
➡️ በጤና ተቋም የሚደረግ የጡት ምርመራ
💡ይህ በጤና ባለሙያ ማለትም በሐኪም ወይም በነርስ ጡትን በመዳሰስ የሚደረግ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ዓይነት ሲሆን በአጠቃላይ ዕድሜአቸው 50 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሴቶች ቢያንስ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ይህን ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል፡🧍‍♂️
➡️ ዘመናዊ የምርመራ መሳሪያዎችን መጠቀም፡
💡 ይሄ የጡት ጤንነት ያለበትን ትክክለኛ ደረጃ ለማወቅ በተሻለ የሚረዳ ሲሆን እንደ Mamography (የጡት ራጅ)፣ የጡት አልትራሳውንድ እና የጡት ኤም አር አይን ያጠቃልላል፡፡

3️⃣ የጡት ካንሰር ሕክምና
💡የጡት ካንሰር ሕክምና ውጤታማነት በዋነኝነት የሚወሰነው ህመሙ በተደረሰበት ደረጃ ላይ ነው፡፡
🩺 ስለዚህ ከላይ ለተጠቀሱት የቅድመ ምርመራ አማራጮች ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡
👨‍⚕️ የጡት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ እንደ ቀዶ ጥገና፣ የጨረር ሕክምና፣የሆርሞን ህክምና እና ኬሞ ቴራፒ የመሳሰሉ የህክምና አማራጮች አሉ፡፡ እንደየአስፈላጊነታቸው በተናጠል ወይም በጋራ ሊሰጡም ይችላሉ፡፡ ✨
🌟 በየጊዜው የሚሰሩ ጥናቶች በጡት ካንሰር ለተጠቁ ሰዎች የተሻሻሉ💊 የሕክምና ዘዴዎችን እና ሁለገብ አቀራረቦችን በመፍጠር ሕይወታቸውን ለማቅለል የሚሞክሩ ናቸው፡፡✨

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

16/02/2024

የኩላሊት ህክምናን በMozocare

✈️ በህንድ፣ ቱርክ፣ወይም አውሮፓ ከ300 በላይ ሆስፒታሎች ውስጥ ጥራት ያለው የ ኩላሊት ህክምናን በተመጣጣኝ ዋጋ🌎 በ Mozocare ያግኙ፡፡

🏥 ሆስፒታሎቻችን በአለም አቀፍ ደረጃ የ JCI እውቅና አላቸው፡፡
💊 የኩላሊት ጤና ምክር፣ የኩላሊት እጥበት ፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ ፣ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ህክምናን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት የኩላሊት ህክምና እና የኩላሊት ጤና ምክርን በሆስፒታሎቻችን ያገኛሉ፡፡

🙎‍♂️የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፡

📲 ስለ ኩላሊት ህክምና ማማከር
🗒የተሟላ የህክምና እና የጉዞ ዕቅድ ማዘጋጀት
💡በኩላሊት ንቅለ ተከላ ጊዜ የኩላሊት ሰጪ፣ የኩላሊት ተቀባይ እንዲሁም አጋዥ (አስታማሚን ) ጨምሮ የሚያስፈልጉ ሙሉ መረጃዎቸን ማዘጋጀት👨‍👩‍👦
🌎ጥራት ያለው የኩላሊት ህክምና የሚሰጡ የሆስፒታል አማራጮችን ማሳወቅ
📁የሚያስፈልጉ የጉዞ ቀድመ ሁኔታዎችን እና አጠቃላይ ወጪዎችን ማሳወቅ ፣
🛫 የአየር ትኬት መቁረጥ እና ማረፊያ ቦታን ማመቻቸት፣
👨‍⚕️ህክምናውን ጨርሰው ሲመለሱ በሀኪም የተደገፈ ክትትል ማድረግ

💁‍♂️በአጠቃላይ በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ከጎናችሁ በመሆን ህክምናችሁን በሰላም አጠናቃችሁ ወደ ሙሉ ጤንነታችሁ እስክትመለሱ ድረስ አብረናችሁ ነን🤝::

🙌Looking for high-quality renal treatment at affordable prices? Look no further!

🌎Mozocare offers a wide range of medical services, including nephrology consultation, Kidney dialysis, Kidney transplant, Hydronephrosis and chronic kidney disease treatments in more than 300 Hospitals at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

12/02/2024

🌟 የኩላሊት ጤናማነት ለሰው ልጅ አጠቃላይ ጤና ወሳኝ ነው። ኩላሊት ቆሻሻን ከደም ውስጥ በማጣራት፣ የደም ግፊትን በመቆጣጠር እና ለተለያዩ የሰውነት ተግባራት አስፈላጊ የሆኑ ሆርሞኖችን በማመንጨት ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡✨

💡የኩላሊት ጤናን ለመጠበቅ አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች እነሆ፡-

👨‍⚕️ሀኪምዎን አማክረው አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመስራት ንቁና ቀልጣፋ መሆን እንዲሁም ራስን ከተለያዩ በሽቻዎች መጠበቅ🏃‍♂️፡፡

🥗 ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ፕሮቲንን ጨምሮ በሁሉም አይነት ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ምግብን በመመገብ፤ ስብ የያዙ እና ከመጠን በላይ ጨው(ሶዲየም) ወይም ስኴር ያላቸውን ምግቦችን በመቀነስ ከደም ግፊት ፣ከደም ስኳር መጠን መጨመር እንዲሁም ሌሎች ተዛማች በሽታዎች ራስን መከላከል ይቻላል🍲፡፡

⏲ የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር፤ ብዙ የሚሟሟ ፋይበር ያለባቸውን ምግቦች ለመመገብ ጥረት ያድርጉ፡፡🥑 አቮካዶ፣ የተልባ ዘሮች እና ጥራጥሬዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይመገቡ፡፡ ይህም ሰውነትዎ ከምግብ የሚወስደውን ካሎሪ ብዛት ይቀንሳል 🥙 ።

🫗 በቂ የውሃ መጠን መውሰድ የሰውነት ፈሳሾችን ሚዛን በመጠበቅ ኩላሊት በአግባቡ ስራውን እንዲሰራ ያደርጋል በአጠቃላይ በቀን ከ8-10 ኩባያ ውሃን መጠጣት ይመከራል🫙።

🙅 ትንባሆ ማጨስን እና አልኮል መጠጣትን ያቁሙ፡፡እነዚህ ጎጂ ልማዶች ወደ ኩላሊትዎ የሚሄደውን የደም መጠን በመቀነስ ለከፋ የጤና ችግር ይዳርጋሉ፡፡

💊ብዙ ጊዜ (በተደጋጋሚ) የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ከመውሰድ ይታቀቡ። በተለይ ያለ ሀኪም ትእዛዝ መድሀኒቶችን በፍፁም አይውሰዱ፡፡

👩‍⚕️ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ ይህም ሢባል የደም ግፊት ምርመራ ፣የአልቡሚን እና ክሪያቲኒን ምርመራ፣ የጂ.ኤፍ. አር. ምርመራ ያድርጉ።✨

🙌 Looking for high-quality renal treatments at affordable prices? Look no further!

🌎Mozocare offers a wide range of medical services, including nephrology consultation, Kidney dialysis, Kidney transplant, Hydronephrosis and chronic kidney disease treatments in more than 300 Hospitals at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

10/02/2024

👀 ስለ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ምን ያህል ያውቃሉ ? ✨

🏥 የኩላሊት ንቅለ ተከላ የኩላሊት ህመም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ የምንመርጠው የህክምና አይነት ነው። ከኩላሊት እጥበት ይልቅ ንቅለ ተከላ ማከናወኑ ታካሚዉ ረጅም እድሜ እንዲኖረው እና ህይወቱም የተሟላ እንዲሆን ይረዳል። ጥራት ያለው ንቅለ ተከላ ከተካሄደ ታማሚዉ ህይወቱ ሙሉ በሙሉ ከበሽታው በፊት እንደነበረው ይመለሳል ማለት ይቻላል🧑‍⚕️።

🥼 የኩላሊት ንቅለ ተከላ መቼ ያስፈልጋል?
የኩላሊት ንቅለ ተከላ አስፈላጊ የሚሆነው ታማሚው የኩላሊት በሽታው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ የኩላሊት እጥበት እየወሰደ ከሆነ ወይንም የኩላሊት በሽታው ወደ የመጨረሻ ደረጃ እየተቃረበ ሆኖ፤ ነገር ግን የኩላሊት እጥበት ያልጀመረ ከሆነ ብቻ ነው።✨

❓የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና በዋናነት ምን ጠቀሜታዎች አሉት?

1. የተሻለ የጤነኛ ኩላሊትን ስራ የመተካት ችሎታ ስላለው ህመምተኛው ህይወቱን በበቂ ሀይል እና ምርታማነት እንዲኖር ያግዛል።
2. በየጊዜው የኩላሊት እጥበት ከማካሄድ ነፃ ስለሚሆን ከገንዘብ ወጪ ፣ ከጊዜ ብክነት ፣ ከመንገላታትና፤ ከኩላሊት እጥበት ጋር ተያይዘው ከሚመጡ ችግሮች ይድናል።
3. የኩላሊት እጥበት ከሚደረግላቸው ይልቅ የተሻለ እድሜ የመኖር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
4. የምግብ እና የመጠጥ ገደቡን ይቀንሳል::

🗣 ተተኪ ኩላሊት ከየት ምንጮች ሊገኝ ይችላል?
1. በህይወት ካለ የደም ዝምድና ካለው ሰው፤ እስከ 4ተኛ የትውልድ ሀረግ ድረስ::
2. የደም ዝምድና ከሌላቸው ለጋሾች ፤ ለምሳሌ ጓደኛ ፣ የትዳር ጓድኛ ወይንም የነሱ ቤተሰቦች::
3. የአእምሮ እንቅስቃሴ ከሌለው የሞተ ለጋሽ።

👨‍⚕️ከኩላሊት ተከላ በኋላ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች✨
💊መድሃኒት መውሰድዎን አያቁሙ ወይም መጠኑን አይለውጡ። ሁሌም የመድኃኒቶችን ዝርዝር እና በቂ የመድሀኒት ክምችት መያዝ ያስፈልጋል👆
👩‍⚕️ በሐኪም ቤት ያልታዘዙ መድኃኒቶችን ወይም የዕፅዋት ሕክምናዎችን አይውሰዱ።
🧭 የደም ግፊት ፣ የሽንት መጠን ፣ ክብደት እና የደም ስኳር (በሀኪሙ የሚመ ከር ከሆነ) በየዕለቱ መመርመር ሊጠበቅባቸው ይችላል::
🩺 ድንገተኛ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ስለ ህመሞዎ መረጃ የሌለዉን ሐኪም ማማከር ከፈለጉ/ካለብዎት ስለ ቀዶ ጥገና ታሪክዎ
ማሳወቅ እና ስለ መድ ሃኒቶም አጭር መረጃ መስጠትን አይዘንጉ።🧑‍⚕️
🥗 ጤናማ አመጋገብ መከተል 🍽እና ከሀኪምዎ ጋር ተማክረው የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግም ይገባል🤽‍♀️፡፡
🫙በቂ ውሃ መጠጣትም አስፈላጊ ነው🧂
🏥መደበኛ የህክምና ክትትል ማድረግም የግድ ይሆናል::

✈️ በህንድ፣ ቱርክ፣ወይም አውሮፓ ከ300 በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ሆስፒታሎች ውስጥ ጥራት ያለው የ ኩላሊት ህክምናን በተመጣጣኝ ዋጋበ Mozocare ያግኙ✨፡፡

🙌 Looking for high-quality medical treatments at affordable prices? Look no further!
🌎 Mozocare offers a wide range of medical services, in more than 300 Hospitals at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

08/02/2024

✈️ በህንድ፣ ቱርክ፣ወይም አውሮፓ ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው ህክምና ማገኘት ይፈልጋሉ? ✨

🌟 MozoCare ታካሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማገዝ:
🌎ከ32 በላይ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ
🏥 ከ300 በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ካላቸው ሆሰፒታሎች እና
🥼ከ10,000 በላይ የጤና ባለሙያዎች ጋር አብሮ ይሰራል
💊 የካንሰር፣ የመካንነት፣ የልብ፣ የአይን፣ የአጥንት ህክምና፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ፣ የጉበት ንቅለ ተከላ፣ እና የመሳሰሉት በሆስፒታሎቻችን ከሚሰጡ ህክምናዎች ጥቂቶቹ ናቸው::✨

🙍‍♂️የምንሰጣቸውም አገልግሎቶች፡
📲ስለ ሚያስፈልግዎት የህክምና አይነት ማማከር
🗒የህክምና እና የጉዞ ዕቅድ ማዘጋጀት
🌎በምትፈልጉበት ሀገር የሆስፒታል አማራጮችን ማሳወቅ፣
📁 የጉዞ ቀድመ ሁኔታዎችን እና አጠቃላይ ወጪዎችን ማሳወቅ
🛫የአየር ትኬት መቁረጥ እና ማረፊያ ቦታን ማመቻቸት
👩‍⚕️ህክምናውን ጨርሰው ሲመለሱ በሀኪም የተደገፈ ክትትል ማድረግ

🙋‍♂️በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ከጎናችሁ በመሆን ህክምናችሁን በሰላም አጠናቃችሁ ወደ ሙሉ ጤንነታችሁ እስክትመለሱ ድረስ አብረናችሁ ነን፡፡

🙌 Looking for high-quality medical treatments at affordable prices? Look no further!

🌎Mozocare offers a wide range of medical services, including nephrology consultation, Kidney dialysis, Kidney transplant, Hydronephrosis and chronic kidney disease treatments in more than 300 Hospitals at more than 32 countries and growing! Take advantage of our expertise and personalized care👌.

🏢 መገናኛ ሲቲ ሞል አራተኛ ፎቅ
📞 / Whats app 📲 +251979013000
🪩 www.mozocare.com/am
✉️[email protected]

19/01/2024

በህንድ፣ ቱርክ ወይም አውሮፓ ውስጥ ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የህክምና አማራጮችን ይፈልጋሉ? ከ 32 በላይ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ከ 600 በላይ ምርጥ ሆስፒታሎች ጋር የሚሰራውን Mozocareን ይሞክሩ። እንኳን አደረሳችሁ!
WhatsApp: +251979013000
📞 : +251116594050
www.mozocare.com/am
[email protected]

18/01/2024

Happy Holidays from MozoCare Et

Looking for high-quality medical treatments at affordable prices? Look no further! Mozocare offers a wide range of medical services, including cosmetic surgery, dental procedures, and wellness treatments in more than 300 Hospitals located at more than 32 countries; and growing!

Wishing you and your loved ones a happy and healthy holiday season! 🎁🌟

Take advantage of our expertise and personalized care. Call us @:
WhatsApp: +251979013000
📞 : +251979016000
www.mozocare.com/am

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Citi Mall, 4th Floor, Megenaga
Addis Ababa
1000