Dr.Tenagne Clinic
Is Private Health care Institution Which is Owned & governed by highly experianced Doctors.
ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን በዛሬው ርዕሳችን
ደም ካንስር ምንድን ነው? ምልክቶቹስ? የሚለውን ስናይ
የደም ካንሰር ማለት እንደ መቅኒ ያሉ ደም በተሰራባቸው ቦታዎች የሚጀምሩ የበሽታዎች ቡድን ማለት ነው። እነዚህ በሽታዎች በጣም ብዙ ያልተለመዱ የደም ሴሎች እንዲፈጠሩ ያደርጉታል, ይህም የደም ሴሎቻችንን መደበኛ ተግባራት ያበላሻሉ በተለምዶ የደም ሴሎቻችን ሶስት ትልልቅ ስራዎች አሉዋቸው፡ ጀርሞችን መዋጋት፣ ብዙ ደም እንዳንፈስ ማድረግ እና በመላ ሰውነታችን ኦክስጅንን መሸከም ናቸው።
👉ሁሉም አይነት የደም ካንሰር የየራሳቸው የሆነ ምልክቶች ቢኖራቸውም የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ግን የሁሉም ዓይነት የደም ካንሰር ምልክቶች ይሆናሉ፡-
- ትኩሳት /ብርድ ብርድ ማለት
- ድካም ድካም ማለት/ አቅም ማጣት
- እራስ ምታት
- ለተለያዩ ኢነፌክሽኖች መጋለጥ
- የምግብ ፍላጎት መቀነስ/ከባድ የሆነ የክብደት መቀነስ
- ከብብት ውስጥና በአንገት አካባቢ የሚገኙ እጢዎች ማበጥ
- በእንቅልፍ ወቅት የሚከሰት ማላብ
- በተደጋጋሚ የሚከሰት ነስር
- አጥንት/መገጣጠምያ ላይ የሚሰማ ህመም
ምክንያቶች ፦ የደም ካንሰር መከሰቻ ምክንያቶች በግልጽ ማወቅ ባይቻልም የሚከተሉትን ምክንያቶች እንደ መላ ምት ማስቀመጥ ተችሏል፡-
- ለሌላ የካንሰር ህመሞች የሚሰጡ የጨረርም ሆነ ሌሎች ህክምናዎች
- ሲጋራ ማጨስ
- በቤተሰብ ውስጥ የዚህ ህመም ታሪክ ካለ ሊወራረስ መቻል
የዚህ ህመም ምልክቶች ከሌሎች ህመም ምልክቶች ጋር በአብዛኛው ተመሳሳይነት አለው በመሆኑም ማንኛውም አይነት ህመም እንደተሰማ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ነገሮች ሳይባባሱ መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡
11/09/2024
እንኳን ለ2017 ዓ/ም በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፤ አዲሱ አመት የጤናና የስኬት እንዲሆንላችሁ እየተመኘን ክሊኒካችን ተጨማሪ Advanced የlaboratory ምርመራወችን በመጨመር የረጅም አመት የሕክምና ልምድ ባላቸው ባለሞያወቻችን የ24 ሰዓት የተማላ አገልግሎት እንሰጥወታለን ፤ ይምጡ ለጤናዎ ዘወትር እንተጋለን!
30/11/2022
A mother presented with PPH to the health center following home delivery. Due to unavailability of ambulance, this BSc Midwife tried his best to manage her and carried her himself to a hospital after referral. The mother is currently alive, thanks to this hero.This is a humble dear
Respect❤❤❤
Via Hakim
👉የደም ግፊት ቀውስ(Hypertensive Crisis)
የደም ግፊት ቀውስ ድንገተኛ፣ ከባድ የደም ግፊት መጨመር ነው። የደም ግፊት ንባብ 180/120 ሚሊሜትር ሜርኩሪ (ሚሜ ኤችጂ) ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን ነው። የደም ግፊት ቀውስ የሕክምና ድንገተኛ አደጋ ሲሆን ወደ ልብ ድካም፣ ስትሮክ ወይም ሌሎች ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።
የደም ግፊት ቀውስ ባለባቸው ሰዎች ላይ በጣም የተለመዱት ምልክቶች ራስ ምታት (74.11%)፣ የደረት ሕመም እና የትንፋሽ ማጠር (62.35%)፣ አከርካሪ (49.41%) እና ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ (41.17%) ናቸው።
👉በመሆኑም እነኚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከተሰማወት በፍጥነት በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም ሄደው ይመርመሩ።
ሰሚት ከሞሐ በስተ ምዕራብ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት እንገኛለን።
15/10/2022
ክሊኒካችን ይምጡ መፍትሄ ያገኛሉ ::
አድራሻችን፦ሰሚት ከሞሐ ፋብሪካ በስተ ምዕራብ 200ሜ ገባ ብሎ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት እንገኛለን!
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ደግሞ ስለ ኩላሊት ጠጠር የተወሰነ እናካፍላችሁ
👉የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው?
የኩላሊት ጠጠር ጠንካራ የሆነ በኩላሊት ወይም በሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር ጠጠር ነው። በሽንት ውስጥ የጠጣር ነገሮች ወይም እንደ ካልሲያም ኦክሳሌት፣ ዩሬት ወይም ፎስፌት ያሉ ቅንጣቶች መብዛት ምክኒያት እንደሆነ ይታመናል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቅንጣቶች በሽንት ውስጥ ተከማችተው ቀስ በቀስ በመጠን ከጨመሩ በኋላ
በረጅም ጊዜ ጠጠር ይፈጥራሉ።
ምንም አይነት እክልበማይኖርበት ጊዜ ሽንት ውስጥ ቅንጣቶች እንዳይሠባሠቡ የሚያደርጉ ንጥረ ነገሮች አሉ። የነዚህ ንጥረ ነገሮች መዛባት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር አስተዋፅዖ ያደርጋል። የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር የጠጠር ህመም የሀሞት ከረጢት ውስጥ ከሚከስተው የሀሞት ጠጠር የሚባለው ህመም የተለየ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።
የሽንት ማስተላለፊያ ጠጠሮች ምን አይነት መጠን ፣ ቅርፅና ቦታ ይኖራቸዋል?
ጠጠሮች በመጠንና ቅርፅ ይለያያሉ።ቅርጻቸውም ለስላሳ ገጽ ያላቸው ድቡልቡልና ሞላላ ሊሆን እንደሚችሉ ሁሉ በጣም ሻካራና በወል የማይታወቅ ቅርፅ ያላቸው ሊሆን ይችላል። ለስላሳ ገፅ ያላቸው ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ቀነስ ያለና ለመወገድ ብዙ የማያስቸግሩ ናቸው። በአንፃሩ ሻካራ ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ከፍተኛ ሲሆን በቀላሉ መወገድ የማይችሉ ናቸዉ። ጠጠር በየትኛውም የሽንት ማስተላለፊያ አካል ውስጥ ሊከሰት ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ በኩላሊት ተፈጥሮ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ (ዩሬተር) አልፎ ጠባቡ ቦታ ላይ ይቀረቀራል።
ኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
1.በቀን የሚወስደው የፈሳሽ መጠን ማነስ
2.በቤተሰብ ውስጥ የጠጠር ህመም መኖር
3.አመጋገብ: የእንስሳት ተዋፅዖ ፣ ጨው አብዝቶ መመገብ ፣ በዝቅተኛ መጠን አትክልት መወሰድ
4.ሞቃታማ በሆነ አካባቢ መኖር
5.ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዲሁም፤ የሽንት ፍሰት መዛባት
6.ለመሽናት የሚያግዙ መድሀኒቶች እና የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሀኒቶች
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
እንደ ጠጠሩ ቦታ መጠንና ቅርፅ የሚለያዩ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡-
በሆድ አካባቢ የሚሰማ ህመም
ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት እና አጠዳፊ የሽንት ፍላጐት መኖር የሽንት ፊኛ ዉስጥ ጠጠር መኖሩን አመላካቾች ናቸዉ።
ጠጠር በሽንት ማስወገድ
ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
ደም የቀላቀለ ሽንት
በሚሸኑ ጊዜ ማመም ወይም ማቃጠል
የታቸኛው የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ የተቀረቀረ ጠጠር ካለ ሽንት መፍሰስ ከጀመረ በኋላ በድንገት ማቋረጥ ሊኖር ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የሽንት ቧንቧ መዘጋት ሊያጋጥምና ቋሚ ወይም ጊዜያዊ የኩላሊት ስራ መዛባት ሊያጋጥም ይችላል።
እነኚህ ምልክቶች ሲኖሩ የኩላሊት ጠጠር ሊኖር ስለሚችል አስፈላጊውን ምርመራ ያድርጉ!
👉ይምጡ ሰሚት ከለስላሳ ፋብሪካው በስተ ምዕራብ 200 ሜ ገባ ብሎ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት እንገኛለን ፤ ክሊኒካችን የተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲሁም የአልትራሳውንድ ምርመራ የረጅም አመት ልምድን ባካበቱ ሀኪሞቻችን እና ሌሎች ባለሞያወቻችን ቀልጣፋ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠቱን እንደቀጠለ ነው።
23/09/2022
Dr.Tenagne Clinic:
September 23, 2022
https://youtube.com/shorts/hVvwbetUtUU?feature=share
September 23, 2022
https://youtube.com/watch?v=38hBhDKlEzs&feature=share
30/08/2022
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ ቤተሰቦቻችን
Hyperhidrosis(excessive sweating)
ከመጠን ያለፈ የእጅ ላብ ካለብዎት ወደ
ክሊኒካችን ይምጡ መፍትሄ ያገኛሉ ::
አድራሻችን፦ሰሚት ከሞሐ ፋብሪካ በስተ ምዕራብ 200ሜ ገባ ብሎ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት እንገኛለን!
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ ቤተሰቦቻችን
የጨው እና የስኳር መጠን መቀነስ እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብ ሕመም እና ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ቀላል መንገዶች ናቸው። አንድ ሰው የጨው አወሳሰዳቸውን በቀን እስከ 5 ግራም ወይም 1 የሻይ ማንኪያ መገደብ እና በምትኩ ትኩስ ወይም የደረቁ እፅዋትን እና ቅመሞችን መጠቀም ተገቢ ሲሆን ወደ ስኳር ሲመጣ ደግሞ በቀን ከ50 ግራም ወይም 12 የሻይ ማንኪያ ስኳር መብለጥ የለበትም። እንዲሁም ከ 2 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በተሰጡ ተጨማሪ ምግቦች ውስጥ ጨው እና ስኳር እንዳይጨምሩ ያስታውሱ ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም በተጨማሪም እንደ አኩሪ አተር እና አሳ መረቅ ያሉ ጨዋማ ሾርባዎችን እና ቅመሞችን ከመጠቀም መቀነስ ይገባል።
አድራሻችን፦ሰሚት ከሞሐ ፋብሪካ በስተ ምዕራብ 200ሜ ገባ ብሎ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት እንገኛለን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa