Abdi boru
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abdi boru, Health/Beauty, Addis Ababa.
20/05/2023
1. ‹‹ደስተኛ ለመሆን መርሁ፡- የምትሠራው ሥራ፣ የምታፈቅረው ሠው፤ ተስፋ የምታደርገው ነገር ሲኖርህና እነዚህን መመሪያዎች ስትተገብር ነው፡፡››
2. ‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡››
3. ‹‹ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡ ምክንያቱም ትክክል ስለሆነ፡፡››
4. ‹‹ሳይንስ ዕውቀትን፤ ጥበብ ደግሞ ሕይወትን ያደረጃል፡፡››
5. ‹‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡››
6. ‹‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡››
7. ‹‹የሠው ልጅ በሠውነቱ ያገኘውን ክብርና ማዕረግ በውሸት ድምጥማጡን ያጠፋዋል፡፡››
8. ‹‹ሁሉም ዕውቀቶቻችን ከስሜቶቻችን ጀምረው በመረዳት ቀጥለው በምክንያት ያበቃሉ፡፡ ከምክንያት በላይ ምንም የለምና፡፡››
9. ‹‹ዘላቂ ሠላም የሚገኘው መካነ መቃብር ውስጥ ብቻ ነው፡፡››
10. ‹‹ለማሠብ ድፈር! የራስህን አዕምሮ ለመጠቀም ብርታት ይኑርህ፡፡››
11. ‹‹ነፃነት ማለት የሠው ልጅ በመወለድ ያገኘው ተፈጥሯዊ መብቱና በሰብዓዊ ሃይሉ የሚጎናፀፈው የግል ሐብቱ ነው፡፡››
12. ‹‹ብልሕነት ልትማረውም ሆነ ልታስተምረው የማትችለው ተሠጥኦ ነው፡፡››
13. ‹‹የፍርድ ጉድለት ሌላ ስሙ ድድብና ነው፡፡ በዚህ ፍርድ ጉድለት ምክንያት የሚመጣ ውድቀት ምንም መፍትሄ እንደሌለው እናውቃለን፡፡››
20/05/2023
Click here to claim your Sponsored Listing.