Aloe cosmo distributor
ካሉበት ቦታ ሆነዉ በ0911895111 ከደወሉልን እኛ ከተፍ እንላለን የ?
በአለም ላይ በ ምርጥ ማርቶቻቸዉ የተውደዱትን የአለም ገበያን የተቆጣጠሩት ምርቶች እዚህ እኛ ጋር በቀላሉ ማግኝት ይቸላሉ…በ ኦሪጅናል እቃዎች ዉበትዎን ይጠብቁ..በተጨማሪ አዲስ ኮስሞቲክስ ቤት መክፈት ለምትፈልጉ ሙሉ የእቃ አቅርቦት ከጥሩ ማማከር ጋር እንሰጣለን…
24/06/2016
Description
Repair Rebuilding Thickening Treatment
DEEP TREATMENT rebuilds with aloe vera, protein & shea butter
Strengthens and helps repair breakage
Promotes thick, strong, growing hair *
Great for ALL types of hair!
Helps promote thick, strong, healthy hair. Enriched with aloe vera, shea butter and botanical thickeners to provide hair with the necessary nutrients needed for deep intense conditioning, rebuilding and thickening! Moisturizes and strengthens weak, damaged hair. Great for the whole family and can be used on all types of hair including color treated, bleached, weaved, braided and relaxed.
24/06/2016
Description
Strengthens & rebuilds
Won’t clog hair folicles
Stops hair breakage
Extra light formula
Helps promote strong, healthy growing hair. Its unique, non-oily formula helps repair damaged hair and helps mend split ends. It also adds luster, conditions, softens, and adds beautiful shine to hair.
24/06/2016
Hask Placenta Plus Olive Oil Leave In Conditioning Treatment is enriched with olive oil. This conditioning treatment moisturizes damaged hair.
24/06/2016
01/04/2016
ለደረቅ ቆዳ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
ደረቅ ቆዳ ያላቸዉ ሰዎች ቆዳቸዎ የሚያፈከፍክ ከመሆኑም በላይ ሲታይም ዉበት የጎደለዉ ሊመስል ይችላል፤ሲነኩትም ሻካራነት ይኖረዋል፡፡ቆዳችን ደረቅ የሚሆነዉ የቆዳዉ የላይኟዉ ክፍል ርጥበት መያዝ ሳይችልና የወዝ ማመንጨት ሀይሉ ዝቅተኟ ሲሆን ነዉ፡፡ጠንካራ ሳሙናዎች እና መታጠቢያዎች ሌሎች ኬሚካሎች ደጋግሞ መጠቀም ቆዳን ሊያደርቀዉ ይችላል፡፡
ታዲያ መፍትሄዉ በተቻለ መጠን የቆዳን የተፈጥሮ ቅባት መጠበቅ አስፈላጊ ነዉ፡፡ከታጠቡ በኋላ ወዲያዉ ቅባቶችን መጠቀም አስፈላጊ ነዉ፡፡ የምንጠቀማቸዉ ክሬሞች ቅባታማ መሆን አለባቸዉ፡፡ወዛማ ቅባቶችን የማንጠቀም ከሆነ የማሳከክ ችግር ከዚያም አልፎ አለርጂ ሊያስከትል ይችላል
01/04/2016
ለወዛማ ቆዳ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
ወዛማ ፊት ወዝ አመንጪ እጢዎች በርከት ያለ ዘይት ያመነጫሉ፡፡ይህ በተፈጥሮ የሚወሰን ስለሆነ ሁኔታዉን መለወጥ አይቻልም፡፡
መፍትሄዉ ከተቻለ ለወዛማ ፊት በተዘጋጀ ዘይትአልባ ሳሙና ወይም የፊትን ወዛማነት የሚቀንስ ፈሳሽ የፊት ማጽጃ በመጠቀም ፊትን ማጠብ ይህም ካልሆነ ለብ ባለ ዉሀና በሳሙና መታጠቡ ጠቃሚ ነዉ፡፡ብዙ ጊዜ በ እኟ ሀገር ብዙ ሰዎች ባለማወቅ ቫዝሊን ሆነ ሌላ ቅባት መቀባት ለቆዳ ጠቃሚ ስለሚመስላቸዉ አዘዉትረዉ ይቀባሉ፡፡ይህም ወዛም ፊት ያላቸዉ ሰዎች ለከፋ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ሊወገድ የሚገባ ልማድ ነዉ፡፡እንዲሁም ወዛም ቆዳ ያላቸዉ ቅባታማ የፊት ክሬም ሆነ ስክራብ ፈጽሞ መጠቀም የለባቸዉም፡፡
ኦሊቬራ 99% ውሃ ቢሆንም ቀሪው 1% እጅግ በጣም ኃይለኛ ነው, ይህም 100 ንጥረ ነገሮች አብረው በጣም ጥሩ ይሰራሉ ምክንያቱም ይህ ነው ኦሊቬራ ዕድገት ሂደት እና ሰውነት ሥርዓቶች ሁሉ ጤናማ ተግባር ወሳኝ በርካታ ማዕድናት ይዟል. ኦሊቬራ ውስጥ ያሉት ንጥረ ነገሮች በሚከተሉት ምድቦች ውስጥ ሊመደቡ ይችላሉ: ቫይታሚኖች, የማዕድን, የስኳርና ኢንዛይሞች, Lignins, አሚኖ አሲዶች, Anthraquinones, Saponins, በነህምያ አሲዶች Salicylic አሲድ.
26/03/2016
አራት ቀላል ተግባራትን በቅደም ተከተል በመተግበር የቆዳ ድርቀትን ይከላከሉ
የቆዳ ድርቀት የሚከሰተው አየር ከቆዳ በሚስበው ርጥበት አማካይነት የቆዳ ሴሎች ስለሚታፈኑና የቆዳዎን ደህንነት የሚጠብቅልዎ ግድግዳ ስለሚዳከም መሆኑን ያውቁ ኖሯል?
በደረቃማ ወቅት ቆዳዎ ልክ እንደወቅቱ የአየር ሁኔታ ሊደርቅብዎት እና ጥሩ ስሜት እንዳይኖርዎ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ አመቱን ሙሉ አምረውና ጥሩ ስሜት እየተሰማዎ እንዲከርሙ እንፈልጋለን፤ በመሆኑም በያዝነው በጋ አና በመጪው የበልግ ወቅቶች የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል የሚያስችሉዎትን በቅደም ተከተል የሚተገበሩ አራት ተግባራትን እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡
የፀሃይ መከላከያ ቅባት ይጠቀሙ
ፀሃይ ቆዳችን ላይ ያለዉን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ የፀሀይ መከላከያ ቅባቶች ከፍተኛ አስተዋጽዎ አላቸዉ ፡፡ ቆዳችን በፀሃይ የመጎዳት ዕድሉ በከፍተኛ ቦታዎች ወይም በደጋ አካባቢ ይጨምራል፡፡ ስለሆነም ከቤት የመዉጣት እቅድ ካለዎት የፀሃይ መከላከያ ቅባት መቀባትዎን ያረጋግጡ፡፡
ለእጅዎ ጥንቃቄ ያድርጉ
የእጅዎ ቆዳ በጣም ስስ፣ በቀላሉ የሚጎዳ እና ሁልጊዜም ማለት ይቻላል፣ ለጉዳት ተጋላጭ ነው፡፡ ለዚህም ነው የቆዳዎን የጉዳት መጠን ከሚያመለክቱ የሰውነት ክፍሎች አንዱ የሆነው፡፡ በእጅዎ የተለያየ የቤት ቁሳቁሶች እንዲሁም የልብስ ጽዳት ሲከዉኑ ጎንት ይጠቀሙ ፡፡ የእጆችዎን የቆዳ እርጥበትም ይጠብቁ፡፡
የሚለብሷቸው አልባሳት ከተሰሩባቸው ነገሮች ጋር በተያያዘ ተገቢውን ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
እንደ ሱፍ፣ ናይለን እና ፖሊስተር ያሉ ልብስ የሚሰራባቸው ነገሮች ሰውነታች|ንን ሊያሳክኩ እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል? በጥጥ (በኮተን) የተሰሩ ልብሶችን በአንጻሩ ይህን ችግር አያስከትሉም ይህም በማከክ አማካኝነት ከሚመጣ የቆዳ ችግር ይከላከላል፡፡
እርጥበት እንዲሰጡ በተሰሩ ምርቶች ብቃት ይተማመኑ
ቆዳዎ ከድርቀት ያመልጥ ዘንድ በሄዱበት ሁሉ ሎሽን እንዳይለይዎ እንመክርዎታለን፡፡
26/03/2016
በኦርጋኒክ የፓፓያ ክሬም ወይም ስክራብ የታከመ ገጽታ
ብዙውቻችን ጸጉራችንን ማሳገድ እጅግ ፈታኝ እና በዙ ጊዜ ሲወስድብን እናሰተውላለን።
እኛም ለዛሬው በቀላሉ እንቁላልን በመጠቀም እንዴት ጸጉርን ማሳደግ እና መንከባከብ ይቻላል የሚለውን ልናካፍላችሁ ወደድን።
እንቁላል ለጸጉር እድገት አስፈላጊ የሆነውን ፕሮቲን በውስጡ በመያዙ ጸጉራችንን በቀላሉ ሊያሳድግልን ይችላል ተብሏል።
b05470764b8a232808e357228e6a8827_L
አዘገጃጀት
• በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ሁልት እንቁላል ሰብረን በመጨመር አዛ ውስሁጥ ሁለት የሾርባ ምንኪያ የወይራ ዘይት ቀላቅለን በደንብ አንድ ላይ ማዋሃድ።
አጠቃቀም
• ጸጉራችንን በሻምፖ ወይም በሳሙና በማደረግ በደንብ መታጠብ።
• የታጠብነውን ጸጉር በፎጣ ተጠቅመን ማድረቅ።
• በመቀጠልም የደረቀው ጸጉራችን ላይ ያዘጋጀነውን የእንቁላል ውህድ ሙሉ በሙሉ መቀባት፥ አዚህ ጋር ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር የጸጉራችን ጫፎች ሳይቀር ሙሉ በሙሉ የእንቁላሉ ውህድ ተዳርሶ መቀባት አለበት።
• የተቀባነውን የእንቁላል ውህድ በሻወር ኮፍያ ወይም በፔስታል ጠቅልለን በማሰር ከ10 እስከ 20 ደቂቃ ማቆየት።
• የመታጠቢያ ሰዓታችን እንደደረሰም ጸጉራችን ሙሉ በሙሉ በኮንዲሺኘር በማደርግ መታጠብ ይኖርብናል።
ማሳሰቢያ፦
• የተቀባነውን እንቁላል ከ20 ደቂቃ በላይ በጸጉራችን ላይ ማቆየት የለብንም ምክንያቱም እንቁላሉ በቆየ መጠን ጸጉራችንን ከመጥቀም ይልቅ ጉዳት ስለሚያስከትል።
• ይህንን የእንቁላል ውህድ በወር አንድ ጊዜ ብቻ መጠቅም በቂ ነው።
በእንቁላልን በዚህ መልኩ በመጠቀምም ጸጉራችን በቃሉ እንዳይበጣጠስ፣ ወዙን የጠበቀ እና ቶሎ እንዲያድግ ማድረግ እንችላለን።
በተጨማሪም ጸጉራችንን በምንታጠብበት ጊዜ ኦርጋኒክ የሆኑ እንቁላል ትሪትመንቶችን መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡
የጸጉር መነቃቀል
ብዙ ሰዎች በቀን ከ50 እስከ 100 የሚደርስ ጸጉር በማንኛውም ምክንያት ይነቃቀልባቸዋል። በቀን በቀን ጸጉራቸውን ሲታጠቡ ወደ 250 የሚደርስ የጸጉራቸውን ክፍል ያጣሉ ወይም በመነቃቀል ይወገዳል። በተጨማሪም በጠዋት ተነስተው ጸጉራቸውን በማበጠሪያ በሚያበጥሩበት ጊዜ እንዲሁ የተወሰነው የጸጉር ክፍል ይበጣጠሳል። ብዙውን ጊዜ ደግሞ የወንዶች ጸጉር ከመሀል አናታቸው ወደኃላ ይሸሻል።
በጥቅሉ ግን የጸጉር መነቃቀል ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች ጥቂቶቹን እንይ:-
በዘር
በዘር የመጣ የጸጉር መመለጥ እጅግ የተለመደ ሲሆን ይህም የቀስ በቀስ ሂደት ያለው እና እድሜ በጨመረ ቁጥር እየባሰ የሚሄድ ይሆናል።
የራዲየሽን ህክምና ለካንሰር ህመም ተብሎ የሚደረገው የራዲየሽን ህክምና የጸጉር መነቃቀልን ያስከትላል።
አራስነት (ልጅ የወለደች ሴት)
አራስ የሆነች (የወለደች) ሴት ጸጉሯ በከፍተኛ ሁኔታ ሊነቃቀል ይችላል። በእርግዝና ወቅት ጤናማ የሚመስል ጸጉር ሊኖር ቢችልም የኤስትሮጂን ሆርሞን መጠን ሲቀንስ አብዛኛዎቹ ሴቶች የጸጉር መነቃቀል ይገጥማቸዋል። ይህ ጊዜያዊ ችግር ሲሆን የሆርሞን ሁኔታው ሲስተካከል ጸጉር ወደ ቀድሞ ይዘቱ ይመለሳል።
የታይሮይድ ህመም
የታይሮይድ ህመም የምንለው የታይሮይድ ሆርሞን በሰውነታችን ውስጥ መብዛትም ይሁን ማነስ ይህንን ችግር ያስከትላል። ይህም የጸጉራችንን ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል።
መድሀኒቶች ለተለያዩ በሽታዎች ተብለው የሚወሰዱ አንዳንድ መድሀኒቶች የጸጉር መነቃቀል እንደተጎዳኝ ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ምንጭ:- የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል
Aloe Cosmo
coming soon.............
just stay your home and call us we'll come....
Click here to claim your Sponsored Listing.