Ethiopian health today
Ethiopian Health Today is for awareness creation: health, education,foreign relation,Aid organizations,and professional development.
05/09/2026
War is brutal !!!!
More than a stethoscope.
When Dr. Addis fled Ethiopia, he feared he had lost the profession he loved.
Requalifying in a new country was not easy, but he persevered.
Today in Rwanda, he is practicing medicine again, serving patients in Rwanda and proving that refugees bring their talent to the places they found safety.
05/09/2026
አንዳንዶች ሲያሾፉ አየን🤔 Mocking 📌
ቆይ እናንተ የጤና አክቲቪስቶች ግን ችግር አለባችሁ እንዴ? የሐገሪቱ ታላላቅ የጤና ሴክተሩን በቅርበት ማየታቸውኮ ጥሩ ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፤ እና የሃገሪቷ እርዕሰ ብሔር ከጎበኙትና ምን እናሻሻል ካሉ ክፍተቶችን ማሳየት ከእናንተ ይጠበቃል እንጅ 12 ኛ ክፍል እንዳላለፈ ካድሬ ተራና ርካሽ ወሬ አታውሩ።
ለጤናው ትኩረት ልትሰጡ እና እየሰጣችሁ ስለሆነ Abiy Ahmed Ali and et als እናመሰግናለን።
05/09/2026
Big news 👌 Yes bravo.
Seminar Serious 😒 🤔
EHT: Recommends Ethiopian Public Health Institute to revise it the wording error.
05/09/2026
ኮንሳልታንት ምንድነው? ኢትዮጵያ ኮንሰልታንት አላት ወይ?
05/09/2026
The new face of Africa
African Union
04/09/2026
በደቡብ ምዕራብ ክልል ጤና ቢሮ ዉስጥ እየተደረገ ያለዉ ስር ነቀል የአመራሮችና የሠራተኞች ግምገማ በሚበረታታ ሁኔታ እየተካሄደ ነዉ
የክልሉ መንግስት ይህንን ስር ነቀል ግምገማ በማካሄድ ችግሮችን ለመፍታት እየሄደ ላለዉ እርምጃ ልመሠገን ይገባል።በክልሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የፓርቲና መንግስት አስተባባሪዎች የተመራ ግምገማ በቢሮ ደረጃ ስካሄድ በማየቴ ደስተኛ ነኝ። ይህ ደግሞ የክልሉ መንግስት ችግሮችን ለመፍታት ፣ሌብነትንና ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ቁርጠኛ መሆኑን ያሳያል።ትናንት በተደረገዉ የቢሮ ሠራተኞች ግምገማ ችግር ፈጣሪዎች ተበጥረዉ የተለዩበት እንደነበር ለማረጋገጥ ችያለሁ።ዛሬም ተሰናባቾችም ሆኑ የሚቀጥሉ የቢሮ አመራሮች ዘንድ ግልጽ መስመር ለማስቀመጥ በተከበሩ አቶ ፋጂዮ ሳፒና በተከበሩ አቶ ነጋ አበራ የሚመራ ጥልቅ ግምገማ እየተካሄደ ነዉ።
የህዝብን እሮሮና ጩሄት በመስማት የክልሉ መንግስትና አጠቃላይ አመራሮች ያለልዩነት እርምጃ እንዲወሰድ ስላደረጉ በክልሉ ህዝብ ስምና በግሌ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
✍️DrAsrate Wolde
04/09/2026
በኢትዮጵያና በኔዘርላንድ መካከል በጤና ዘርፍ ስላለው የቆየና ውጤታማ ትብብር እንዲሁም ወደፊት ሊጠናከሩ ስለሚችሉ የትብብር አቅጣጫዎች በኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ፓስካል ግሮተንሁይስ የተመራ ልዑካን ቡድን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችን የጤና ሥርዓታችንን በዘላቂነት ማጠናከር፣ የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነትና ጥራት ማሻሻል እንዲሁም በጋራ ቅድሚያዎቻችን ላይ በመመሥረት ትብብራችንን ይበልጥ ማጠናከር በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሃሳብ ተለዋውጠናል።
ኢትዮጵያ ከኔዘርላንድ ጋር ያላትን የጤና ትብብር በማጠናከርና የሚኖሩ አዳዲስ ዕድሎችን በመጠቀም፣ በጤና ዘርፍ የሚገኘውን ዘላቂ ውጤት ይበልጥ ለማስፋት በቀጣይም በቅርበት እንሰራለን።
Dr Mekdes Daba, Minister of Health
04/09/2026
Ethiopian Public Health Institute
04/09/2026
የሕብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አምራች ሕብረተሰብ መገንባት ነው።
ኢትዮጵያን ላለፉት 100 ዓመታት ያገለገለውን፣ ታሪካዊ ወረት እና ዘመናዊ አቅምን ያጣመረውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ ተመልክተናል።
የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው። ተቋሙም በወረርሽኝ ልየታ፣ በበሽታ ክትትልና ምላሽ፣ በላብራቶሪ፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን እና በጤና ስጋት ዝግጁነት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በጥንካሬ እየደገፈ ይገኛል።
በክልሎች የድንገተኛ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋሙና የሪፈራል ላብራቶሪዎችን ማስፋፋቱ የሀገሪቱን የጤና ዝግጁነት አቅም እያጠናከረ ያለ ወሳኝ ተግባር ነው።
በቀጣይም የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም የጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል በመሆን ዓለም አቀፍ ሚናውን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት እያደረገ ነው።
የትላንትን ታሪክ ጠብቆ፣ ዛሬን በዘመናዊነት ዋጅቶ፣ ወደ ነገ የሚገሰግስ እንደዚህ ያለ ተቋምን መደገፍና ማጠናከር ለነገ የማንለው ተግባር ነው። ኢንስቲትዩቱ የሀገርን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ አቅም በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።
HE Temesgen Tiruneh
04/09/2026
ቀን 27/12/2018ዓም
ሰበር የነፃ ህክም ዜና !!!
ጳጉሜና ነፃ ህክሞና
በአገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል!!!
ሆስፒታላችን አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል የአዲሱን ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን የተለያዩ የህክምና አገልግሎት ፓኬጆችን በማዘጋጀት ከፍሎ የመታከም አቅም የሌላቸዉን የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለያዩ የህክምና ክፍሎችለማገዝ ወሰኖል ።በዚህ መሠረት
1ኛ,ጳጉሜ 1እና2 ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ
ቀዶ ህከምና በነፃ
(ስክሪኒንግ ወይም ለይታ ነሃሴ 28,29እና 30 በሆስፒታላችን ይካሄዳል
2ኛ,ጳጉሜ 3 እና 4 ነፃ የስኳርና የደም ግፊት ምርመራ(በሆስፒታላችን)
3ኛ,ጳጉ ሜ5 ነፃ የኢንዶስኮፒእና ኮሎኖስኮፒ ምርመራ በጨጓራ፤በጉበት፤በአንጀትና ቆሽት ህክምና ሰብስፔሻሊስት
4ኛ,ጳጉሜ 5 የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ሲቲ ስካንን ጨምሮሙሉ ነፃ ምርመራ(ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር)
ማሳሰቢያ:-
1ኛ,በፊት ስራ ላይ ያሉ የህክምና ፓኬጆች እንደተጠበቁ ናቸዉ።
2ኛ, መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ከሚሰሩበት ተቋም ደብዳቤና የመስሪያ ቤት መታወቂያ መያዝ አላባቸዉ።
አገዉ ምድረ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል!!!
መልካም አዲስ ዓመት!!!
✍️EHT
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa