Ethiopian for African
INTERNATIONAL MINDS
🇪🇹🇪🇹🇪🇹❗
#
10/06/2026
United Horn of Africa requires Strong Ethiopia leading through
10/06/2026
🇪🇹የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጀግና ነው የሚል ብቻ ላይክ ያድርግ 🇪🇹ሀገርን ማገልገል ክብር ነዉ🇪🇹
09/06/2026
አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የስህበት ማዕከልነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች!
ዛሬ ከጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል Africa CDC ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዦን ካሴያ ጋር በቀጣይ ኖቬምበር ወር ላይ ከተማችን አዲስ አበባ 5ኛውን አለምአቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማካሄድ መመረጥዋንና ኮንፈረንሱን በጋራ ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬአማ ውይይት አድርገናል።
አዲስ አበባ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመሰረተ ልማት በሰራናቸው ስራዎች ፣ በነዋሪዎቻችን እንግዳ ተቀባይነት፣ሰላሟ የተረጋገጠ ከተማ በመሆኗ እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ ምቹ ከተማ መሆን በመቻሏ “የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት እና ደህንነትን ማላቅ/...to advance Africa’s health soverignity and security agenda./ በሚል 5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ዝግጅቶች በስፋት በጋራ በመከናወን ላይ ነው፡፡
5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ የሃገራት መሪዎች ፣ሚኒስትሮች ፣የህብረተሰብ ጤና መሪዎች፣ፖሊሲ አውጭዎች ፣ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላትን የሚሳተፉበት ትልቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ነው ።
ፊጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
Today, I held a highly productive discussion with Minister of Health Dr. Mekdes Daba and the Director General of the Africa CDC, Dr. Jean Kaseya, regarding the selection of our city, Addis Ababa, to host the 5th International Conference on Public Health in Africa (CPHIA), which will take place next November. We also discussed key areas of collaboration to jointly organize the conference.
In recent years, Addis Ababa has become an increasingly attractive destination for major international gatherings, thanks to the significant infrastructure developments undertaken across the city ,the hospitality of our residents, being secured city and its growing capacity to successfully host global events. In this context, extensive preparations are being carried out in collaboration with partners to organize the 5th International Conference on Public Health, under the theme:
“Advancing Africa’s Health Sovereignty and Security Agenda.”
The conference will bring together Heads of State, ministers, public health leaders, policymakers, researchers, and other stakeholders and partners.
May God bless Ethiopia and its people.
09/06/2026
የቀጣናው ግርማ ሞገስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር የጀርባ አጥንት፣ የሰላሟ ዋስትና እና የሕልውናዋ የመጨረሻው ምሽግ ጠንካራ፣ ዘመናዊ እና ለሕዝቧ ታማኝ የሆነ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይል ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በረጅም ዘመናት ታሪኩ በርካታ የጀግንነት ውጣ ውረዶችን ያሳለፈ እና አኩሪ ገድሎችን አስመዝግቧል፤ በቅርብ ዓመታት የተደረገው ጥልቅ እና ሁለንተናዊ የሪፎርም ሥራ ደግሞ ተቋሙን ወደ አዲስ የልዕልና እና የክብር ምዕራፍ አሸጋግሮታል።
የዚህ ታሪካዊ ሪፎርም ዋነኛ እና አንኳር ስኬት፣ ሠራዊቱን ከርዕዮተ ዓለም ጠባቂነት አላቅቆ የኢትዮጵያ እና የዜጎቿ የጋራ ክብር እና ደኅንነት ዘብ እንዲሆን ማድረግ መቻሉ ነው።
ባለፉት ዘመናት የፀጥታ እና መከላከያ ተቋማት የፖለቲካ ሥርዓቶች እና የገዢ ፓርቲዎች አገልጋይ ሆነው መቆየታቸው በተቋማቱ እና በሕዝቡ መካከል መተማመንን ሲሸረሽር ቆይቷል።
ይሁን እንጂ፣ በአዲሱ የለውጥ ጉዞ እነዚህ ተቋማት ሕገ መንግሥቱን ብቻ መሠረት አድርገው ሀገራዊ ተልዕኳቸውን እንዲያከናውኑ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ እንዲሆኑ ተደርገዋል።
የሕግ፣ የአሠራር እና የአደረጃጀት ሪፎርም በማድረግ ኢትዮጵያን የሚመጥኑ ተቋማት እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን፣ ይህ ስብራት መጠገኑ ሠራዊቱ የፖለቲካ ሥርዓት ሲቀየር አብሮ የሚፈርስ ሳይሆን፣ በገለልተኝነት እና በሙያዊነት እንዲሁም ራስን እና ሀገርን የሚያስቀጥል ጠንካራ ተቋም እንዲሆን አስችሎታል።
ከሥነ ልቦናዊ እና መዋቅራዊ ነፃነት ባሻገር፣ ሠራዊቱ ከኋላ ቀር አደረጃጀት እና የትጥቅ ሥርዓት ወጥቶ እጅግ ዘመናዊ ወደሆነ የውጊያ አቅም መሸጋገሩ ነው።
የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማትን ለማዘመን በተሠራው ሰፊ እና የተቀናጀ ሥራ፣ ሰብዓዊ፣ መዋቅራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ብቃት ያላቸው ጠንካራ ተቋማት ተፈጥረዋል። ዛሬ ላይ ተቋማቱ ዘመናዊ እና ዘመን ተሻጋሪ ሆነው በአዲስ መልክ በመደራጀታቸው፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስከበር የሚያስችል የላቀ ቁመና ተላብሰዋል።
በተጨማሪም፣ ዘመናዊ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ እና በራስ አቅም በመፍጠር ረገድ የሀገርን አቅም በከፍተኛ ደረጃ እየገነቡ ይገኛሉ። ሠራዊቱ ለግዳጅ አፈጻጸም የሚያስፈልጉትን ትጥቆች እና ስንቆች በራስ አቅም ለማሟላት ዳር የደረሰ ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያን ከባንዳ እና ከባዕዳን ሴራ በአስተማማኝ ሁኔታ መከላከል ወደሚችልበት የማይበገር ደረጃ ላይ ደርሷል።
የመከላከያ ሠራዊቱ ልዕልና እና ሞገስ የሚለካው በዘመናዊ ትጥቁ እና በቴክኖሎጂው ምጥቀት ብቻ ሳይሆን፣ ለሕዝቡ ባለው ጥልቅ ፍቅር፣ የአደራ ጠባቂነት እና ሥነ ምግባር ጭምር ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊት ዜጎችን ከማንኛውም እንግልት፣ ከመብት ጥሰት፣ ከሞት እና ከመፈናቀል አደጋ ለመታደግ ከፍተኛ የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈል ሌት ተቀን በግንባር ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
ዘመናዊ እና ዘመን ተሻጋሪ አድርጎ ከማደራጀት ባለፈ፣ ይህ ሪፎርም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማሻሻል ረገድም አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ይህን መሰል ሀገር ወዳድነት እና ለሕዝብ ደኅንነት የሚከፈል መሥዋዕትነት፣ ሠራዊቱ በመልካም ስሙ፣ በሕዝብ አክባሪነቱ እና በጀግንነቱ በሕዝቡ ዘንድ እጅግ የተወደደ እና የኩራት ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ሀገራችንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ከሚቃጡባት አደጋዎች ለመጠበቅ እና የሕዝባችንን ዘላቂ ደኅንነት ለማረጋገጥ ሠራዊቱን ይበልጥ ማጎልበት እና ማጠናከር ተችሏል።
ይህ ጽኑ ሥነ ምግባር ያለው እና በሙያዊ ብቃቱ የላቀው የኢትዮጵያ መከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊ
09/06/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
"የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባችንን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎብኝተናል። በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ህትመት(3D printing)፣ የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው። እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው።
ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው። ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ስራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን እድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል!"
09/06/2026
❤🇪🇹🇪🇹
06/06/2026
አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ ለአዲስ
ለአዲስ አበባ አዲስ የሆነ እና በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የጤና አገልግሎት ተጀምሯል፡፡አግልገሎቱ የከተማችንን ህዝብ የጤና አገልግሎት በአዲስ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ ነው፡፡ ይህ ብዙ የተባለለት የጤና አገልግሎት የዲ.ኤን፣ኤ (DNA) የፎረንሲንክ እና የስነ-ምረዛ ምርመራ ልህቀት ማዕከል ሲሆን ማዕከሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል፡፡
የማዕከሉ አገልግሎት ስራ ሲጀመር አገራችን ከፍተኛ ወጪ የምታወጣባቸው የጤና ምርመራ አግልገሎቶች በአገር ውስጥ እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ በዚህም ውጪ አገር በመላክ ረጅም ጊዜ ይወስድ የነበረው ምርመራ በአገር ውስጥ ፈጣን በሆነ መንገድ ማግኘትን ያስችላል፡፡ በዚህም በከፍተኛ ደረጃ ጊዜንም ወጪንም ይቆጥባል ተብሎለታል፡፡
ማዕከሉ ለአዲስ አዲስ የሚያሰኘው ሌላው ጉዳይ ዘመናዊ ምርመራ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን የጤና መረጃ ማዕክል የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም ማዕከሉ የDNA መረጃ ማካመቻና ማነፃፀሪያ ሲስተም (CODIS)፣ በወንጀል የተጠረጠሩ ፣ ወላጅነትን ለማረጋገጥ የሚቀርቡ የማስረጃ ጥያቄዎችን እና ተመሳሳይ የዘር መለያ ፣ የቤተሰብ ግንኙነት የዘር ሀረግ መለይትንና ማረጋገጥን የመሳሰሉ ዘመናዊ አግልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ ማእክል ነው፡፡
ማዕከሉ ከጤና ባሻገር የአገራችንን የፍትህ ስርዓት በማገዝም እጥፍ ድርብ ጠቀሜታ እንዳለው ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የፍትህ ስርዓቱ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በዚህ ማዕክል የሚሰጡ የDNAን አይነትና ተዛማጅ የጤና ምርመራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ በዚህም እነዚህ አግልግሎቶች ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ማግኘት ከተቻለ ቀልጣፋ ፍትህም ማግኘት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የህብረተሰቡ የመብት ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ ማዕከሉ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ በእነዚህና በመሳሰሉት የማእከሉ አዳዲስ አግልግሎቶች የተነሳ አዲስ የጤና ቴክኖሎጂ በአዲስ ተጀመረ ተብሎሎታል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
GOOD