sisay yetrza

sisay yetrza

Share

wehemeya

13/04/2025
06/04/2025

ቡርኪና ፋሶ ከአሜሪካ ታስገባ የነበረው ልባሽ ጨርቅ ከዚህ ወዲያ እንዳይቀጥል በይፋ አገደች።

የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራዎሬ በጉዳዩ ላይ “አፍሪካ አህጉር እንጅ የቆሻሻ ገንዳ አይደለችም!” ብለዋል።

Photos from sisay yetrza's post 04/04/2025

ሸመት‼️
በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ የቡድኑ አመራር የነበረው ጃል ጉሬ (ሚልኬሳ ለታ) የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የፀጥታና አስተዳደር ምክትል ሆኖ መሾሙ ተዘግቧል።
ይህ እንዳለ ሆኖ የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ግንቦት 06/2016 ዓ.ም አውጥቶት በነበረው ዘገባ ላይ ጃል ጉሬ ከስድስት ግበረአበሮቹ ጋር እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልፆ መረጃው ተሰራጭቶ ነበር

04/04/2025

' ' መምህራን በኢኮኖሚ እንዲጠናከሩ የሚያስችል ነው - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

'የመምህራን ባንክ' በማቋቋም የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል በኢኮኖሚ እንዲጠናከሩ ለማድረግ እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመሆን 'የመምህራን ባንክ' ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በዚህም መምህራን መሰረታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ለአብነትም በአነስተኛ ወለድ የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ እና ሌሎችም መሰል ኢኮኖሚያዊ ድጋፎችን ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ነው የገለፁት።

“ለትምህርት ጥራት መጠበቅ የመምህራን የኢኮኖሚ ጥያቄ መመለስ አለበት” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደሞዝ ጭማሪ ማድረግ ስለማይቻል በመሰል አማራጮች መምህራንን ለማገዝ እንደሚሰራ ነው ያመላከቱት።

ሚኒስትሩ በዘርፉ በቂ የሆነ የሰው ኃይል በእውቀት ብሎም በቁጥር እንደሌለ በመግለፅ፣ ሞያው አማራጭ ስላጡ የሚገባበት መሆኑን ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አያይዘውም “የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ” በሚል በ2019 ዓ.ም ላይ ለመተግበር የታቀደው አሰራር በዘርፉ ያለውን የመምህራን እጥረት ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ በተገኙበት ውይይት ባደረገበት መድረክ ላይ ነው።

03/04/2025

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው ተባለ

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቋል።

''የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑንም የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ አሰራር ተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው።

03/04/2025

የሊቢያው ኮለኔል መሀመድ ጋዳፊ በሥልጣን ዘመናቸው ለዜጎች ያደርጉ የነበረውን በጥቂቱ ...

ለሊቢያ በኮለኔል ሞሀመድ ጋዳፊ የስልጣን ዘመን 17 አሥገራሚ የዜግነት ጥቅሞች

1. የኤሌክትሪክ ኃይል ለሊቢያ ዜጎች ያለምንም ክፍያ ለመላው የአገሪቷ ዜጋ በነፃ ይዳረሳል፣

2. በሊቢያ ሕግ፣ ባንኮች ለዜጎቻቸው የሚያበድሩት ብድር ምንም አይነት ወለድ አይከፈልበትም

3. በአገረ ሊቢያ ዜጎች የቤት ባለቤት መሆን እንደሰብአዊ መብት ይቆጠራል፤ ጋዳፊ የሊቢያ እያንዳንዱ ዜጋ የመኖሪያ ቤት የማግኘት የመንግሥት ግዴታ እንዲሆን አድርጓል

4. የሊቢያ ዜጎች ትዳር ሲውጡ ለሙሽሮች መቋቋሚያ 50,000 የአሜሪካን ዶላር ይሰጣቸዋል፣

5. በአገረ ሊቢያ ትምህርትና ሕክምና ነፃ ነው፤ ጋዳፊ ፊደል የቆጠሩ ዜጎችን ቁጥር ከ25 በመቶ ወደ 83 በመቶ አሳድገዋል፣

6. ወደግብርና የሚገቡ ሊቢያውያን የግብርና መሳሪያና ቦታ በነፃ ይሰጣቸዋል፣

7. ለሊቢያውያን ዟጎች በአገሩቷ ሊቢያ ውስጥ ባሉ የህክምና መሥጫ ሆሥፒታሎች የማይቻል ሕክምና በሙሉ በመንግስት ወጪ ህክምናውን የሚያገኙበት በሌላ አገር እንዲያገኙ ይደረጋል፤

8. እያንዳንዱ ሊቢያዊ ዜጋ በወር 2,300 የአሜሪካን ዶላር የዜግነት ይከፈለዋል፣

9. ማንኛውም የሊቢያ ዜጎች መኪና መግዛት ሲፈልጉ መንግስት 50 በመቶ የወጪ እገዛ ያደርግላቸዋል፣

10. በጋዳፊ የሥልጣን ዘመን ሊቢያ ውሥጥ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 14 ሳንቲም ነበር የሚሸጠው

11.በጋዳፊ የሥልጣን ዘመን ሊቢያ ከየትኛውም አገር ሆነ አበዳሪ ተቋማት ሠባራ ሳንቲም ብድር የለባትም፣

12. አንድ የተመረቀ ሊቢያዊ ሥራ እስኪያገኝ ድረስ በተመረቀበት ሙያ ሊያገኝ የሚችለውን ደሞዝ መጠን ከመንግስት በየወሩ ይሰጠዋል፣

13. የሊቢያ ከምታወጣው ነዳጅ እና ከነዳጅ ንግድ ትርፍ በጥቂቱ ተቀነጣጥቦ ለመላው የአገሪቷ ዜጎች የባንክ አካውንት
ውስጥ ከነዳጅ ከሚገኘው ትርፍ ይገባላቸዋል።

14. በአገረ ሊቢያ በሞሀመድ ጋዳፊ የስልጣን ዘመን አንድ ሊቢያዊት እናት ልጅ ሥትወልድ መንግስት 5,000 የአሜሪካ
ዶላር ይሰጣታል፣

15. በጋዳፊ የስልጣን ዘመን 40 ዳቦ በሊቢያ 15 ሳንቲም ይሸጥ ነበር ( የአርባ ህጸናት ቁርሥ 15 ሳንቲም)

16. ብጋዳፊ የሥልጣን ዘመን 25 በመቶ የሚሆኑት ሊቢያውያን የዩንቨርስቲ ዲግሪ አላቸው፣

17. በበረሃማዋ አገር ‹‹ታላቁ ሰው ሠራሽ ወንዝ›› የተሰኘውን የዓለማችንን የእርከን ፕሮጀክት ለሊቢያ ያሰሩት ሞሀመድ ጋዳፊ ናቸው፡፡
Source -Steemit.com

01/04/2025

ህይወትን የምትሰጥ እናት ለሆስፒታል ለምን ትከፍላለች? ትራወሬ‼️
በቡርኪኒፋሶ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታል ሴቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ ልጅ እንዲወልዱ ተወስኗል።
እኔ የተወለድኩት ከሴት ልጅ ነው ሴት ልጅ ህይወትን ወደ እዚች ምድር ለማምጣት ብዙ ክፍያ ስትጠየቅ ማየት አልፈልግም ።
ድሃ እናቴ እኔን ለመውለድ በሚከፈል ክፍያ ምክንያት እኔን ልታጣ ነበር። ፈጣሪ ባይፈቅድ ኖሮ እኔም በህይወት የለሁም ነበር:: ዛሬ የዚህች አገር ፕሬዚዳንትም አልሆንም ነበር። ስለዚህ ህይወትን የምትሰጥ እናት ለሆስፒታል መክፈል የለባትም።
የብርኪናፋሶ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ትራኦሬ

Photos from sisay yetrza's post 18/03/2025

በሶማሊያው ፕሬዝዳንት ላይ የመግደል ሙከራ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ዛሬ ማለዳ ላይ ከግድያ ሙከራ ተርፈዋል፣ ጥቃቱ በአልሸባብ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ተሰምቷል።

ፕሬዝደንቱን ያጀቡ መኪኖች ከቪላ ሶማሊያ ቤተመንግስት እንደወጡ ብዙም ሳይቆይ ኃይለኛ ፈንጅ በቅርብ ርቀት ከፈነዳ በኋላ፣ ከፕሬደንቱ አጃቢ ብረትማ SUV መኪኖች አንደኛው በጣም የተጎዳ ሲሆን በርካታ የፕሬዚዳንቱ አጃቢዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ ላይ የደረሰ ምምም ጉዳት እንደሌለ ነው የተሰማው።

17/03/2025

የቤልጂየም ዲፕሎማቶች ከሩዋንዳ ለቀው እንዲወጡ 48 ሰዓታት ተሰጣቸው

ፖል ካጋሜ "ቤልጂየም፣ እናንተ ማን ስለሆናችሁ ነው? የኛ ኃላፊ ያደረጋችሁ ማን ነው? ሩዋንዳውያን በፈጣሪ እናምናለን ፈጣሪ ቤልጄምን የሩዋንዳ መሪ አድርጓል?" ሲሉ ተናግረዋል።

በኮንጎ ግጭት ምክንያት ሩዋንዳ ከቤልጂየም ጋር ያላትን ግንኙነት አቋረጠች

ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት ጋር በተያያዘ ቤልጂየም ሩዋንዳን "በተደጋጋሚ አናንቃለች" በሚል ነው ሩዋንዳ ግንኙነቷን ለማቋረጥ የወሰነችው።

ሩዋንዳ ለአማጺ ቡድኑ ኤም23 በምታደርገው ድጋፍ ምክንያት የአውሮፓ አገራት ማዕቀብ እንዲጥሉባት ቤልጄም ጥሪ ስታደርግ ቆይታለች።

የቤልጂየም ዲፕሎማቶች ኪጋሊን ለቀው እንዲወጡ 48 ሰዓታት ተሰጥቷቸዋል።

የቀድሞዋ ቅኝ ገዢ ቤልጄም የሩዋንዳ እርምጃ "ያልተመጣጠነ" ነው ስትል ወቅሳ የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥም አስታውቃለች።

አሜሪካ እና የተባበሩት መንግሥታት ሩዋንዳ ለኤም23 ድጋፍ እየሰጠች ነው ቢሉም ሩዋንዳ ሐሰት ነው ብላለች።
ሩዋንዳ ቤልጂየምን "የቅኝ ግዛት ቅዠቷን ማስቀጠል ትፈልጋለች" ስትል ከስሳለች።

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ "ቤልጂየም፣ እናንተ ማን ስለሆናችሁ ነው? የኛ ኃላፊ ያደረጋችሁ ማን ነው? ሩዋንዳውያን በፈጣሪ እናምናለን
ፈጣሪ ቤልጄምን የሩዋንዳ መሪ አድርጓል?" ሲሉ ተናግረዋል።

የቤልጂየም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሲን ፕሪቮት በማኅበራዊ ሚዲያ "ያልተገባ እርምጃ ነው። ከሩዋንዳ ጋር መግባባት ሲያቅተን ለንግግር ዝግጁ እንዳልሆኑ ያሳያል። በቤልጄም ያሉ የሩዋንዳ ዲፕሎማቶች ተቀባይነታቸው ተሽሯል" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

በኤም23 እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎች ግጭት ምክንያት ወደ 7,000 ሰዎች ተገድለዋል።

BBC

Photos from sisay yetrza's post 15/03/2025

ባለስልጣኑ በማህበራዊ ሚዲያ በፃፉት ፅሁፍ ምክኒያት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ያነሱት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ቅዳሜ፣ መጋቢት 6/ 2017 ዓ.ም ተነሳ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ተሰማ ግጭትን የሚቀሰቅሱ፣የክልሉን እና የምክር ቤቱን ክብር የሚነኩ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው ያለ መከሰስ መብታቸው መነሳቱ ተገልጿል።

የቤንሻንጉል ክልል በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አቶ ዮሐንስ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያነሳሳ ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሠራጨታቸውና፣ መንግሥትን በኃይል ለመጣል ከሚጥሩ አካላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አመላካች መረጃዎች መኖራቸውም ተገልጿል።
የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው በዚሁ አስቸኳይ ስብሰባ ያለመከሰስ

መብታቸውን ሲያነሳ ለምክር ቤቱ ማብራርያ የሰጡት የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ሐሚድ፣ ግለሰቡ 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው ውሳኔዎችን ካሳለፈ በኋላ በዚህ ድርጊት መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል።

የምክር ቤቱ አባል በተጠረጠሩበት ጉዳይ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የቀረበውን ማብራሪያ ተከትሎ የአቶ ዮሐንስ ተሰማ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ማጽደቃቸው ተገልጿል።
አቶ ዮሐንስ ተሰማ የተቃዋሚው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) አባል ሲሆኑ በቁጥጥር ስር የዋሉት እሁድ የካቲት 30/2017 ዓ.ም. ነበር።

ፖለቲከኛው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከሌሎች ሁለት ፓርቲውን የወከሉ የምክር ቤት አባሎች ጋር በመሆን የተሻሻለው የክልሉ ሕገ መንግሥት እና የተወካዮች ብዛት ያሻሻሉት አዋጆች "ተፈጻሚ እንዳይሆኑ" ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ አቤቱታ ባቀረቡበት ሳምንት ነው።

የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር እና የምክር ቤት አባል አቶ ዮሃንስ እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም

አቶ ዮሃንስ ወደ ፍርድ ቤት ያልቀረቡት የምክር ቤት አባል በመሆናቸው ያገኙት ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መያዛቸውን በመጥቀስ "ለመርማሪ ፖሊሶች ቃል ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሆን እንደሚችልም" ተናግረው ነበር።
ሦስት የምክር ቤት አባላት የካቲት 25 ለሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ ባቀረቡት የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ፤ ከ100 ወደ 165 ያደገው የምክር ቤት መቀመጫ ብዛት ለምርጫ ክልሎች የተከፋፈለበት መንገድ "የሕዝብ ብዛትን ሳይሆን የወረዳ ቁጥርን" መሰረት ያደረገ እንደሆነ በመጥቀስ ተቃውመው ነበር።

Via BBC

Photos from Yeneta tube የኔታ  ቲዩብ's post 12/03/2025
12/03/2025

የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ደህንነት የሚረጋገጠው የከተማው ማስተር ፕላን ተግባራዊ በማድረግ እንጂ ወልቂጤ ለሁለት በመክፈል የሚረጋገጥ ሰላም በፍፁም አይታሰብም።

ወልቂጤ፣ March 12/ 2024 (GNN) የጉራጌ ህዝብ የከተማ ምስረታ መነሻ፤ ታታሪነትና ስራ ወዳድነት መገለጫ ወልቂጤ እንደሆነ ይነገራል።
ጉራጌ ጫካ መንጥሮ፤ ገደል አቃንቶ የሰራው ከተማ ነው ወልቂጤ።

ወልቂጤ ለጉራጌ ከተማ ብቻ አይደለም ልጅም ነው፤ ለዚያው የበኩር ልጅ ነው። በሁሉም ጉራጌ ዘንድ ወልቂጤ ልዩ ስፉራ ይይዛል። ጉራጌ ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ዞሮ ተዟዙሮ ከተማ ይገነባል ሀብት ያፈራል መነሻው ወልቂጤ ነው። ለድሀው ለሀብታሙ በእኩል ያሳደገ የለወጠ ልዩ ስፉራ ያለው ከተማ ነው።

የጉራጌ ህዝብ ታሪክ ባህልና ቅርስ በጥቂቱ ቢሆንም ወልቂጤ ከተማ ላይ ነው የሚገኘው። አቃፊው ሰው አክባሪው ጉራጌ ወደ ከተማው የመጡት ሁሉ በእኩል ተቀብሎ እንዲለወጡ እንዲከብሩ አድርጓል። በወልቂጤ ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ዜጎች በነፃነት የሚኖሩበት የሚሰሩበት የሚከብሩበት ቦታ ነው።

ይህ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ ዛሬም ያለው የጉራጌ ህዝብ ባህል፤ እንግዳ ተቀብሎ ማክበር ማገዝ አሁን አሁን የጎዳው እንጂ የጠቀም አልሆነም።

ወደ ጉራጌ እርስት ከሌላ ቦታ ፈልሰው ከመጡት የህብረተሰብ ክፍሎች አንዱ ቀቤና ነው። ከሀድያ ወገን እንደሆነ የሚነገረው ቀቤና በሂደት የመገፋት ታሪክ ገጥሞት ወደ ጉራጌ እርስት መሰደዱ ወገንም ጠላትም የሚያውቀው ሀቅ ነው። ባጎረስኩ ተነከስኩ ሆነና፤ እውነት ተሽሮ ቀቤና ዛሬ የጉራጌ መሬት ላይ ባለእርስት እንዲሆን ተፍቅዶለታል።

ለጉራጌ ያልበጀው እንዲያውም የህለውና አደጋ እንዲደቀንበት ያደረገው ህገ መንግስቱ ጉራጌ እርስት ላይ ባለ መሬት ባለታሪክ እንዲሆኑ ያደረገ ይመስላል። ይህ አልበቃ ብሎ ጉራጌ ዋጋ ከፍሎ የገነባው ያቆመው ከተማ ላይ ስጋት ደቅኗል።

ሞሽን በሚል የፌደራል መንግስት አጀንዳ የህግ መሰረት የሌለው አሰራር ሸፍጥ ጉራጌ እርስት ላይ ተጫነ። ጉራጌ ለአራት ቦታ እንዲከፈል አደረገው። ይህም በታሪክ ወደ ጉራጌ ምደር ለመጡት ዜጎች ባለእርስት አድርጓቸዋል።

ከጀርባው የመንግስት የተደበቀ አጀንዳ ያነገበ፤ ጉራጌ የህልውና አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ብሎም እንዲበተን ዋጋ ከፍሎ ያቆማት ከተማም እንዲነጠቅ የተሰር ሴራ ነው። ጠንካራ የኋላ ደጀን ያለው የቀቤና ወረዳ ካድሬና አክቲቪስት ገፋ በል የሚል ሀይል ከኋላው አንግቦ ወልቂጤ የእኔ ነው የሚል ድፍረት አላብሶታል።

ለቀቤና ሀይል የፌደራል መንግስት ስውር እጅ ብቻ አይደለም። ሌላ ደጋፊ ሀይልም አለው። ዝርዝሩን ለወደፊቱ በስፋት ዳሰሳ የምናደርግበት ይሆናል።

ባለፉት 6 አመታት የቀቤና ወረዳ ካድሬና አክቲቪስት የወልቂጤ የሰላም ስጋት ሲሆን እነዚህ አካላት ከኋላ አንግቦ ነው። ከተማው በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሰዎች ይዘረፋሉ፤ ይገደላሉ። በወልቂጤ ከተማ ማታ የክላሽ ድምፅ የብሬን ጩኸት መስማት የየቀኑ ተግባር ነው። በከተማው ዙርያ ወታደራዊ ስልጠና ልምምድ ተጧጥፏል።

ሌላኛው የጉራጌ ህዝብ አደጋ ውስጥ እንዲቆይ ያደረገው፤ ከአብራኩ የወጣው ባንዳው አመራር ነው። ያቆመው ዋና ከተማው የገነባው መዲናው ተደራጅቶ ማስከበር እዳይችል ከመንግስት ሸፍጥ ጋር በማበር ጉራጌን ማሳደድ ማሰር መርጦ ለቀቤና ካድሬና አክቲቪስት መንገድ መጥረግ መርጧል፣ ከጀርባ ሆነው ለሚዘውሩት መላላክ መርጧል። እወክለዋለሁ የሚለውን የጉራጌ ሕዝብ ረስቷል።

ሁሉንም አካላት ያመነበት የከተማው ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን በዋናነት እንቅፋት የሆነው መንግስት ነኝ የሚለው አሻጥረኛ ነው። ከተማው ስላሙን ሲናጋ የተጠቀመው ከጉራጌ ውጪ የሆነው ነው።

አሁን አሁን ያመጡት አዲስ እቅድም አለ። አስቂኝ ቀልድ። ወልቂጤን ለሁለት መክፈል። በብዙ ቀቤናውና ሌላው ህዝብ በደስታ የታየ ቀልድ ነገር ግን ሳያፍሩ ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ይገኛሉ።

የወልቂጤ ሰላምና ደህንነት ከተማዋ ለሁለት በመክፈል፤ ቀቤናን በማስታጠቅ የሚረጋገጥ ሳይሆን። ወልቂጤ የጉራጌ እርስት መሆኑን በመቀበል ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ በማድረግና ህገወጥ መሳርያ ሻጭ አደብ በማስያዝ ነው።

የጉራጌ የመደራጀት ጉዳይ ግን ላፍታም መዘግየት የለበት።ጉራጌ ካልተደራጀ በገዛ እጁ እርስቱ አይደለም እራሱ(ማንነቱ) አሳልፎ እንደመስጠት የሚቆጠር ነውና። ጉራጌ ተደራጅ።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa