Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ, Health/Beauty, Addis ababa, Addis Ababa.
24/09/2026
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ10 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከወረዳው ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን በጋራ በፓርቲ አሰራርና የአደረጃጀት መመሪያ ዙሪያ ለህብረት እና ለቤተሰብ አመራሮች ስልጠና ተሰጥቷል ።
አቶ በለጠ ይፍሩ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ10 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አባሉ ህጎችን እና የዲሲፕሊን መመሪያዎችን ግልፅ በመሆን የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግባችንን ለማሳካት ስልጠናዉ ያግዛል ብለዋል።
የአዲስ ከተማ ወረዳ10 ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አይሻ አህመድ የዲሲፕሊን መመሪያውን ማዕከል ባደረገ ማንኛውም የፓርቲ አመራርና
አባላት ህጎችና አሰራሮች የማክበር ግዴታ፤የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን የማጠናከር ግዴታ፤የፓርቲውን እና የመንግስት ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ፤ሙስና፣ ብልሹና አድሏዊ አሰራሮችን የመታገል ግዴታ እና የፓርቲውን ውስጣዊ አንድነት፣ጥራትና ጥንካሬ የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት አብራርተዋል። ኃላፊው አክለውም ሰልጣኞች እዚህ ያገኙትን እውቀት ለሌሎች በየደረጃው በማሳወቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
አክለውም የፓርቲው አባላት መልካም የፓርቲ ስነ-ምግባር መላበስ እንደሚገባ በመግለጽ እነዚህ መመሪያዎች ሳይሸራረፉ በሁሉም የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተግባራዊ ሊደረጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
24/09/2026
የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ እቅድ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱን የወረዳው ጥምር የጸጥታ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ10 አስተዳደር ከተለያዩ የጸጥታ አደረጃጀት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። በቀጣይ የሚከበሩ በዩኔስኮ የተመዘገቡና በድምቀት የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ላይ ለጸጥታ ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ በተባሉ ጉዳዮች ላይ እቅድ በማውጣት ጥናትን መሰረት ያደረገ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸው፤ በበዓላቱ ወቅትም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የራሳቸውን ጥቅም እና ፍላጎት በማስቀደም የሀገርን ገጽታ የሚያበላሹ ስለሚኖሩ የተጀመረው የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራው ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ይኖርበታል በማለት ተገልጿል ።
በውይይቱ የተገኙ ጥምር የጸጥታ አካላትም በበዓላት ወቅት በሚከናወኑ የጸጥታ ስራዎች የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸው፤ ሠላም ወዳዱ ማህበረሰብ ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አሳስበዋል።
adkw10_prosperity
23/09/2026
ቅጠል ተራን ወደ ንፁህ አረንጓዴ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገን
በቅጠል ተራ 960 ቤቶችን በአራት ወር ዉስጥ ገንብተን ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች መልሰን አስተላልፈናል።
ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ የነበረና የሰው ህይወትም ጭምር በአስከፊ ሁኔታ በእሳት አደጋ ያጣንበት አካባቢም ነበር።
ዛሬ ግን እጅግ ያማሩ ፣ ዘመናዊና ሁሉንም ነገር የተሟሉላቸው ባለ 9 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎች ላይ 960 ቤቶች ተገንብተው ወደ ምቹ መኖሪያ አካባቢ ተቀይሯል።
"የመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር" በ11, 000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች በአጠቃላይ 960 ቤቶች ያሉት ሲሆኑ፣ ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች በውስጡም የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ፥ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች በዘመናዊ መልክ ተሟልተው ተገንብተዋል።
ይህ በመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር የሰው ህይወትን የሚቀይር ፥ መርካቶ አካባቢን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸው ( ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ) ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።
ቃል በተግባር ማለት ይህ ነው፥ እንደዚህ ዓይነት የተወሳሰበ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለሰው ልጆች የሚመጥኑ፥ ነዋሪዎች የክብር ኑሮ እንዲኖሩ፥ ህይወታቸውን የሚቀይሩ ተግባራትን ያለ እረፍት 24/7 በመፈፀም ነዋሪዎች አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ማድረግ ነው ።
የስራዎቻችንን ማዕከል ሁሉ ሰው ተኮር አድርገን፥ ከተማችን ውብ ፅዱ፥ ለነዋሪዎቻችን የተመቸች ከተማ እንድትሆን ያለ እረፍት የመስራት ተግባራችን ይበልጥ አጠናክረን
እንቀጥላለን።
ካላችሁ አካፍላችሁ ከከተማ አስተዳደራችን ጎን በመሆን የበጎ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ፥ ዛሬም በቅጠል ተራ የበጎነት መንደር እንድንቀይር ያገዛችሁን በተለይ ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ፥ በግንባታው የተሳተፋችሁ ሁሉ በነዋሪዎች ስም ከልብ እናመሰግናለን ።
ቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ ተቀይፘል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
23/09/2026
"ኢትዮጵያ፦ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ" ስንል የምታድገዋንና ገናና የምትሆነዋን የወደፊቷን ኢትዮጵያ በምናባችን አስቀምጠን ነው።
የመደመር መንገድ ገፅ 360
22/09/2026
በተያዘው ሳምንት መጨረሻ መከበር የሚጀመሩ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የሰላም ሰራዊት አባላት ዝግጁነት ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ::
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር የሰላም ዘብ ለሆኑ የሰላም ሰራዊት አባላት የእራት ግብዣ በማድረግ ስምሪት ሰጥቷል::
በስምሪት ፕሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አማካሪ አቶ መኮነን ያኢ
የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው በመስራታቸው በከተማችን ታላላቅ የአደባባይ በዓላት ያለአንዳች የፀጥታ ችግር እየተከበሩ መሆናቸውን ጠቅሰው ከፊታችን ባሉ ቀናት የምናከብራቸው በዓላት የተሳኩ ሆነው እንዲጠናቀቂ የሰላም ሰራዊቱ እየሰራ ያለው የሰላም ማስከበር ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደመቀ ዋኘው በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት አካባቢያቸውን በተጠንቀቅ እየጠበቁ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ገልፀው ይህም በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ብለዋል።
የወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ ግርማ በበኩላቸው መላው የፀጥታ መዋቅራችን በዓላቱ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ስምሪት ወስደው እየተጉ በመሆናቸው ክብር ይገባቸዋል ብለዋል::
21/09/2026
ለአደባባይ በዓላት ድምቀት ዝግጅቷን ያጠናቀቀችው ውብ አዲስ አበባ!!
አዲስ አበባ በባህሎቿ ውበት ፈክታ፣ በመስከረም ወር ለሚከበሩት የመስቀልና የአባይ/የኢሬቻ አደባባይ በዓላት ድምቀት ልዩ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥራለች። ከተማዋ በዓላቱን በድምቀትና በደማቅ ሁኔታ ለማስተናገድ ሁለንተናዊ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አጠናቃለች።
በመዲናዋ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች እና ውብ የኮሪደር ልማቶች ለበዓሉ ድባብ ልዩ ድምቀትና ማራኪ ገጽታን አላብሰዋታል፡፡ እነዚህ አዲስ መልክ የያዙ የህዝብ መዝናኛዎችና አደባባዮች በዓሉን ለሚታደሙ እንግዶች ምቹና ንጹህ ከባቢን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
ሕዝባዊ እሴቶቻችንን በሚያንጸባርቁት በዚህ ታላቅ የበዓል ወቅት፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶች በአንድነት በመሆን የህብረተሰባችንን ፍቅርና አብሮነት ሊያጠናክሩ ይገባል።
21/09/2026
ከመስከረም እስከ መስከረም፤ የብዝሃነት ውበት፣ የአብሮነት ድምቀት
የብዝሃነታችን ድምቀት፣ የአብሮነታችን ማሰሪያ፣ የወል እውነቶቻችን ማጎልበቻ የሆኑት የመስከረም ወር በዓላት፣ የሚያስተሳስሩንን የጋራ እሴቶች በማጉላት የአንድነታችንን ጥንካሬ የምናሳይባቸው እናቶች ናቸው። *ኢትዮጵያዊነት በተለያዩ ማንነቶች ውስጥ የሚገለጥ፣ በመከባበርና በመተሳሰብ የሚጠነክር የጋራ ማንነት ነው።*
እኛ ኢትዮጵያውያን ከአባቶቻችን በክብር የተረከብነውን ሀገር ክብሯና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ የጋራ አደራ ያለብን ህዝቦች ነን። ብዝሃነታችንም የሚያራርቀን ግድግዳ ሳይሆን፣ በመከባበር፣ በመቻቻልና በጋራ እሴቶች ላይ ተመሥርቶ የሚያስተሳስረን ገመድ እንዲሆን መሥራት የዘመኑ ትውልድ ኃላፊነት ነው።
መስከረም ይህንን የጋራ መንፈስ በተግባር የምናይበት ወር ነው። አዲሱን ዓመት በእንቁጣጣሽ ዜማ አጅበን፣ በደስታ ተደስተን፣ በአንድ ማዕድ ተቋርሰን፣ ትናንትን በይቅርታና በፍቅር ሸኝተን ነገን በብሩህ ተስፋ የምንቀበልበት ወቅት ነው። የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላትም የየራሳቸውን ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴት ጠብቀው፣ በብዝሃነታችን ውስጥ ያለውን ውበት፣ በልዩነታችን ውስጥ ያለውን የጋራ እውነት የምናሳይባቸው ተምሳሌታዊ የአብሮነት መድረኮች ናቸው።
እነዚህ በዓላት በሰላምና በአብሮነት ሲከበሩ የሀገራችንን ማህበራዊ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ሀብትና ባህል ለዓለም ማስተዋወቅ የሚያስችል የቱሪዝም አቅምም ናቸው። ስለዚህ የበዓላቱን እሴት መጠበቅ፣ በሰላም እንዲከበሩ መትጋትና ከበዓላቱ የሚመነጩ አስተሳሰሪ ሁነቶችን ማጎልበት የአብሮነታችንን መሠረት ከማጠናከር ባሻገር ለጋራ ብልፅግና የሚያደርሰን የጋራ ጉዞ ነው።
በዚህ መንፈስ አብሮነትንና አንድነትን ማጠናከር፣ የጋራ እሴቶችን ማስረጽና ማህበረሰቡን በጋራ ሥራ ባለቤት ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በተለያዩ ደረጃዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ይህም የበዓላትን ድምቀት ከአከባበር ባሻገር ወደ ዘላቂ አብሮነት፣ ወደ የጋራ ኃላፊነትና ወደ የጋራ ብልፅግና የሚሸጋገር እንዲሆን ያደርጋል።
20/09/2026
ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የብልፅግናችን መሰረት ነው!
መስከረም በሀገራችን ኢትዮጵያ የጨለማው ዝናብ አልፎ፣ ብርሃን የሚፈካበት፣ ተፈጥሮ በለመለመው አረንጓዴ እና በቢጫው አደይ አበባ የሚሸለልበት ልዩ የምስራች ወቅት ነው። ይህ ወር የአዲስ ዘመን መባቻ ብቻ ሳይሆን፣ የተለያየ ባህል፣ እምነት እና ወግ ያላቸው የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላቶቻቸውን በጋራ እና በድምቀት የሚያከብሩበት የህብረ ብሔራዊነታችን ማሰሪያ ነው።
የኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊነት ዋና ውበቱና ጥንካሬው ልዩነቶቻችን የምስጢርና የመዋበያ አበቦች መሆናቸው ነው። በዚሁ በመስከረም ወር የሚከበሩት እንደ እንቁጣጣሽ (አዲስ ዓመት)፣ መስቀል (ደመራ)፣ እሬቻ፣ እና ሌሎችም አካባቢታዊ ባህላዊ በዓላት የአንድነታችን፣ የሰላማችን እና የእርስ በእርስ ትስስራችን ህያው ማሳያዎች ናቸው።
የመስከረም በዓላት የሃይማኖትና የባህል ድንበሮችን ተሻግረው፣ የማህበረሰባችንን ፍቅር፣ ይቅር ባይነት እና የእንግዳ ተቀባይነት እሴቶች የሚያጎሉ ናቸው። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሚከበሩት የበዓላት ስነ-ስርዓቶች የየራሳቸው የሆነ ባህላዊ ቀለምና ድምቀት ያላቸው ሲሆኑ፣ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያዊነትን የባህል ሀብት ያበለፅገዋል።
መስከረም የቅያሬና የፅናት ምልክት እንደመሆኑ መጠን፣ የክረምቱን ስራ አጠናቆ ወደ አዲስ የስራና የምርት ዘመን የመሸጋገሪያ ወቅት ነው።
ስለሆነም፣ እነዚህን ውብና ታሪካዊ በዓላት ስናከብር፣ የነበረንን በጎ የአብሮነት ባህል በማጠናከር፣ ይቅር መባባልንና አንድነትን በማስቀደም፣ ሀገራችንን ወደ ተሻለ ብልፅግና እና ከፍታ ለማሸጋገር በጋራ ልንቆም ይገባል።
ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የብልፅግናችን መሰረት ነው!
20/09/2026
በትጉህ ልጆቿ የቱሪስት መዳረሻዎቿን ያበራከተች ህብረ ብሄራዊት ከተማ! አዲስ አበባ!
በስም ብቻ አብባ የቆየችው አዲስ አበባ ከጥቂት ዓመታት በፊት የቱሪስት መሸጋገሪያ እንጂ መዳረሻ እንዳልነበረች ይታወሳል፡፡
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ለቱሪስት መስህብነት ጎላ ብለው የሚጠቀሱ መዳረሻዎች ብዙም አልነበሯትም፤ የነበሩት ዕድሜ ጠገብ ቅርሶቿም ቢሆኑ አስታዋሽ ስላልነበራቸው የህልውና አደጋ ተጋርጦባቸው ቆይተዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) የገበታ ለሸገር ኢኒሸቲቭ አንፀባራቂ ጉዞውን የጀመረው የከተማችን ለውጥ ነባር ቅርሶችን በማደስ ዘመን ተሻጋሪ ገፅታን እንዲላበሱ አስችሏል፤ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማበራከትም መዲናችን የስዕበት ማዕከል አድርጓታል፡፡
ከፍተኛ የሆነ የፅዳት ጉድለት የነበረበትንና የተለያዩ የውንብድና ወንጀሎች ጭምር ሲፈፀሙበት የነበረውን ‹‹እሪ በከንቱ›› ይባል የነበረውን አካባቢ የወዳጅነት አደባባይ እና የወዳጅነት ፓርክ በመገንባት ለህፃናት መጫዎቻ፣ ለሰርግ እና መሰል ሁነቶች ድምቀት እንዲሁም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎች የስዕበት ማዕከል ማድረግ ተችሏል፡፡ በአቅራቢያውም ግዙፉ የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት በመገንባቱ የተማሪዎች፣ የተመራማሪዎች እና የሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የዕውቀት ማዕድ ሆኗል፡፡
መሀል ከተማ ላይ ቢሆንም ከነዋሪዎች እርቆ የቆየው ቤተ መንግስትም ከተደረገለት ዘመን ተሻጋሪ እድሳት ባሻገር በግቢው ውስጥ ግዙፉ የአንድነት ፓርክ በመገንባቱ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ዜጎች የቱሪስት መስህብ መሆን ችሏል፡፡
በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ጭምር በስም እንጅ በአካል የማያውቁት እንጦጦ እና አካባቢውም ዋነኛ የስዕበት ማዕከል መሆኑ መጀመሩ በየቀኑ የሚታይ እውነታ ነው፡፡ በአካባቢው ‹‹እንጨት በመሸከም›› ይተዳደሩ የነበሩ እናቶችም፣ ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር በተገነባላቸው የእንጀራ ፋብሪካ፣ የኑሮ ደረጃቸው ከፍ ማለት ጀምሯል፡፡
በእንጦጦ ፓርክ አዲስ ገፅታን መላበስ የቻለው እንጦጦ ተራራ እና አካባቢው የሁለት ግዙፍ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች መነሻ በመሆኑም የስዕበት ማዕከልነቱ በእጅጉ ጨምሯል፡፡ ንፁህ አየር የሚቀበሉ አረጋውያን፣ የሚቦርቁ ህፃናት፣ ልምምዳቸውን የሚሰሩ አትሌቶች፣ የተለያዩ ቀረፃወችን የሚያደርጉ አርቲስቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶችና ታዳጊዎች እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች ከእንጦጦ እስከ መሀል ከተማ በተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ላይ ሲዝናኑ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡
መነሻቸውን ከእንጦጦ ተራራ በማድረግ እስከ ፒኮክ መናፈሻ እንዲሁም እስከ ቀበና ወንዝ የተገነቡት የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ከተማችን ለቱርስት መዳረሻነት ያላትን ዕምቅ አቅም ከፍ አድርገው አሳይተዋል፡፡
የሁሉም ጥቁር ህዝቦች የድል ምልክት ተደርጎ የሚወሰደውን፣ በአባት እናቶቻችን የህይወት መስዋዕትነት የተመዘገበውን፣ የአድዋ ድልን ለመዘከር የተገነባው የዚህ ትውልድ አሻራ፣ ግዙፉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ጎብኝዎች የሚጨናነቅ የከተማችን እንዲሁም የሀገራችን ምልክት ሆኗል፡፡
የአፍሪካ፣ የእሲያ፣ የአውሮፓ እና በሌሎችም አህጉራት የሚገኙ ሀገራት መሪዎች ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ሲመጡ የአበባ ጉንጉን በክብር የሚያስቀምጡበት፣ ዓለም አቀፍ የስዕበት ማዕከል በመሆኑ የአድዋ ድል መታሰቢያ የሁላችንንም ልብ የሚያሞቅ አኩሪ ታሪክ ነው፡፡
ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚመች መልኩ የተገነባው ለሩጫም፣ ለመዝናኛም ፣ ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ውድድሮች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ግዙፉ የአድዋ ፓር
19/09/2026
"ከንፁህ ሳህኖች ወደ ንፁህ ከተሞች!" በሚል መሪ-ቃል የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የዓለም የፅዳት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።
በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ10 አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር አስተባባሪነት ይህንኑ የዓለም የፅዳት ቀንን ምክንያት በማድረግ "ንፁህ ሳህኖች ወደ ንፁህ ከተሞች!" በሚል መሪ-ቃል የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የጽዳት ንቅናቄ ዋና ዓላማም በወረዳው ህብረተሰቡንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የፅዳት ስራን ባህል ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡
adkw10_prosperity
Category
Website
Address
Addis Ababa
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda 10 Prosperity ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.