Naod Ayelel

Naod Ayelel

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Naod Ayelel, Health/Beauty, Shew hola, Addis Ababa.

11/05/2026

የብልፅግና ጉዟችን፡ ከጠንካራ እሳቤ ወደ ተጨባጭ ስኬት!

ብልፅግና ፓርቲ ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሀገራችንን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማሻገር በተለያዩ ዘርፎች ሰፋፊ የለውጥ ጉዞዎችን አድርጓል። በዚህም በዲሞክራሲ ግንባታ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በመሰረተ ልማት እና በዲፕሎማሲ መስኮች ጉልህ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

ፓርቲያችን "በመደመር" እሳቤ ላይ ተመስርቶ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ተጨባጭ ውጤቶችን ማምጣት ችሏል፤

በዲሞክራሲ ግንባታ፡ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት፣ የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ገለልተኝነት በማረጋገጥ እንዲሁም የዜጎችን የሀሳብ እና የመደራጀት ነፃነት በማክበር አዲስ እና አካታች የፖለቲካ ባህል እንዲዳብር መሰረት ተጥሏል። በምክክር እና በውይይት የሚያምን ማህበረሰብ ለመገንባት ትልቅ እርምጃ ተጉዘናል።

በኢኮኖሚው መስክ፡ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በተግባር በመተርጎም፣ በግብርናው ዘርፍ (በተለይም በስንዴ ልማት እና በበጋ መስኖ) የታዩት ስኬቶች የኢኮኖሚያችን ዋልታ ሆነዋል። ከዚህም ባሻገር ከተሞቻችንን ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ የሚያደርጉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በማፋጠን፣ የስፖርት ቱሪዝምን እና የከተማ ገጽታን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ አዳዲስ የኢኮኖሚ አቅሞችን መፍጠር ተችሏል።

በማህበራዊ ዘርፍ፡ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትምህርት፣ የጤና እና የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ስራዎች በስፋት ተሰርተዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንደ ጠንካራ ባህል በማስረፅ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አቅመ ደካማ ዜጎችን መደገፍ እና ማህበራዊ ትስስራችንን የጠነከረ ማድረግ ችለናል።

በዲፕሎማሲው መስክ፡- የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ክብር እና ሉዓላዊነት በማዕከል ያደረገ ዲፕሎማሲን ተግብረናል። ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትስስርን ስናጠናክር፣ ታሪካዊው የ'ብሪክስ' (BRICS) አባልነታችን የዚሁ ስኬታማ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተሰሚነታችንን ያረጋገጠ የዲፕሎማሲ ጉዟችን ማሳያ ነው።

በባለፉት የለውጥ ዓመታት ያገኘናቸው ስኬቶች የሁላችንም የጋራ ጥረት ውጤቶች ናቸው።
ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር፣ በአብሮነት እና በወንድማማችነት መንፈስ የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
መንገዳችን መደመር ፣ ምርጫችን ብልፅግና ፣ መዳረሻችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ነው፤

መልካም የስራ ሳምንት!!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Photos from Prosperity party yeka woreda five branch's post 11/02/2026
06/02/2026
Photos from የካ ወረዳ 05 ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን's post 30/01/2026
Photos from የየካ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን እና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን's post 18/11/2025
07/11/2025

"ነዋሪዎቻችንን በማስተባበር ውብ፣ ጽዱ፣ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች የካን ዕውን ለማድረግ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን"!!

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Shew Hola
Addis Ababa