seid Yimam gojamew

seid Yimam gojamew

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from seid Yimam gojamew, Health/Beauty, Ethiopian, Addis Ababa.

Photos from seid Yimam gojamew's post 31/12/2024

እኔ እምለው የቻግኒ አመራሮች ደሞ ምን እያሉ ነው
ሚኒሻውን እየሰበሰቡ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ እያለ የሚቀደዱት በምነኛ ነው
እረ ሳክስ አቁሙ የማናው መሰላቹህ የማያዋጣ መቀላመድ ያስበላቹሀል
እረፉ እውነት ለናተ ጥሩ አይመጣም ልምከራቹህ
እውነት እንደ አብሮ አደግ እንደመሆናችን ምክር ልለግሳቹህ ነገር ግን የማታርፉ ከሆነ እያንዳንዳቹህን የማጋለጥ ስራየን እቀጥላለሁ ከነ ፎቶዋቹህ ከነቅስቃሲያቹህ የለለ ያልተፈጠረ ነገር አትስሩ አታውሩ
አዳጋው ለናተ ነው
ፋኖ በናተ አፍ የሚጠራ አይደለም
የአማራን ህዝብ ትግልም ልታስቆሙት አትችሉም
በግፍ የሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ላይ ከጨፍጫፊው ለይተን አናያቹህም ለፍርድ እንደምትቀርቡ አትጠራጠሩ እኛ አሁን እየተናገርን ነው ቡኋላ ተገድጀ ነው ጫና ኖሮብኝ ነው መለማመጥ አያዋጣም እያሰባቹህ ስሩ እያሰባቹህ ተናገሩ
ጉዳቱ ለኛ ሳይሆን ለራሳቹህ ነው
ልብ ያለው ልብ ይበል
እንግዲህ ፍርዱን ለተመልካች
እንዚህን ነው እንግዲህ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ የሚሉት

23/11/2024

ሴራቸው ተጋለጠ!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የውጊያ ሜዳውን በማጥራት ላይ ነው።

ሁላችሁም አዕምሯችሁን ጠብቁ።

ጎንደር ውስጥ ለአገዛዙ እጅ ሰጡ እየተባሉ ድራማ የሚሰራባቸው ግለሰቦች በሙሉ በሚባል ደረጃ:-
☝ሰርገው የገቡ የብአዴን ሰላዮች
☝የዝናሽ ታያቸው ቡድን ሰርጎ ገቦች
☝የፋፍህዴን ሰርጎ ገቦች
☝የዲቃላ ስኳድ ሰርጎ ገቦች
☝የኦሮሙማና ትግሬ ተላላኪ ዲቃላዎች
መሆናቸው ተረጋግጧል።

የአማራ ፋኖ በጎንደር በየቀጠናው ባደረገው ክትትል በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለው መረጃ የሰጡ የፀረ አማራ ቡድኖች ተላላኪዎች በርካታ ሲሆኑ፤ በዚህ ምርመራ መሰረት ተቋማዊ ክትትሉ እረፍት የነሳቸው ሰርጎ ገቦች በቡድንም በተናጠልም ወደላካቸው አካል ብአዴን እየሄዱ መስጠታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ፋኖዎች እጅ ሰጡ በሚል ድራማ መንግስት የሚደልቀው የራሱን ሰዎች ወስዶ ነው።
ቆጋ ሚዲያ

Photos from seid Yimam gojamew's post 23/11/2024

የመከላከያ ሰነድ ተገኝቷል!
መንግስት አልቻልኩም ብሏል፤ ወረዳዎች ከቁጥጥሩ ውጭ መሆናቸውን አምኖ ፅንፈኛውን ሀይል ከክልሉ መድና እና ከዞን ከተሞች ብቻ መግፋት ችያለሁ ብሏል። የፋኖን ክፍፍል ተጠቅሜ ስራ እሰራለሁ፣ የስልክና መብራት አገልግሎት አቋርጨ ህዝብን በማማረር ጦርነት በቃኝ እንድል አደርጋለሁ፣ ስለ ፋኖ መጥፎ መጥፎ ድስኩር በመልቀቅ ዘራፊ እና ደፋሪ ነው እላለሁም ብሏል።

ፋኖን ከክርስትና ሀይማኖት ጋር ብቻ በማያያዝ ህዝበ ሙስሊሙን የመነጠል ተልዕኮም ውጤታማ ሆኖ አግንቸዋለሁ ማለቱ አስገርሞኛል። በተለይ ወሎ ውስጥ ይህ ስልት ውጤት አምጥቷል። በግልፅ መንግስት ሴራውን ስለነገረን ነው የገረመኝ። የወሎ ህዝብ ታዲያ ምነው ዝም አልክ? ዘውዱ ሰጥአርጌ ሲሸውድህ ዝም ማለትህ ገርሞኛል።
ሼር ሼር ሼር🙏🙏🙏

23/11/2024

የበላይ ትንፋሾች
የአማራው የነፃነት መብራቶች
ድል ለአማራ ፋኖ

23/11/2024

Ethiopia on the way to state collapse!
Does ethiopia on the way from state failure to state collapse?/ኢትዮጵያ ከሀገረ መንግስት #ውድቀት ወደ ሀገረ መንግስት መፍረስ እየተሸጋገረች ይሆን?። ኢትዮጵያዊያን ከምንጊዜውም በላይ ልንነጋገርበት የሚገባ ቁልፍ ጥያቄ ነው። ውሃው ከፈሰሰ በኋላ ለማፈስ ብንጣጣር ማግኘት የምንችለው በጣም ትንሹን ነው። የቀረው ይሰረጋል። እጃችን ከዘገነው ውስጥም ጥቅም የሚሰጥ ነገር ስለመቅረቱ ያጠራጥራል። ወይም የቀደመ የውሃነቱን ይዘት ሙሉ በሙሉ ያጣል። ወደ ቀደመው የውሃነት ይዘት ለመመለስ አድካሚ ስራ ይፈልጋል። ወይም ላይመለስ ይችላል።
የሀገረ መንግስት ጉስቁልናዎች ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም፥
👉State Frajaile_የመጀመሪያ ደረጃ ሲሆን በአንድ ሀገረ መንግስት ውስጥ ስንጥቅ መከሰቱን ያሳያል። ለምሳሌ በ1993 ዓ.ም ህወሓት ለሁለት ሲከፈ፣ ከ1997 ምርጨ ማግስት የተነሳው ውዝግብ፣ በ2010 ዓ.ም የኢህአደግ የውስጥ ሽኩቻ የሀገረ መንግስቱ የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሞት የነበረባቸው የፖለቲካ አውዶች ናቸው።
👉State Failure_በመጀመሪያው ደረጃ የታየው ስንጥቅ በአግባቡ ባለመሰፋቱ ምክንያት በመንግስትነት የተሰየመው ሀይል ሲበዛ ደካማ ሆኖ ሲገኝ ነው። ከቅቡልነት ማጣት ተገዳዳሪ ሀይሎች እስከመከሰት የሚደረስ ነው። ተገዳዳሪ ሀይሎች ስንጥቁን የመጠገን አሊያም ሀገረ መንግስቱን የመበተን ሚና ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ የኢህአዴግን የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ የብልጽግና እና የህወሓት ፍትጊያ የወለደው የሰሜኑ ጦርነት ኢትዮጵያን ከሐገረ መንግስት ስንጥቅ ወደ ሐገረ መንግስት ውድቀት አሸጋግሯታል።
👉State Collapse_የሐገረ መንግስት መፈጥፈጥ ነው። በመጀመሪያው የጉስቁልና ደረጃ ተጠግኖ አልድን ያለው ስንጥቅ ወደ መበተን ደረጃ ሲደርስ ነው። የብልጽግና ስርአት ለሚመራት ሀገሩ በሰሜኑ ጦርነት የሸለማትን የሐገረ መንግስት ውድቀት ሳይፈታ ከአማራ ጋር የጀመረው ጦርነት ኢትዮጵያን ከሐገረ መንግስት ውድቀት ወደ ሐገረ መንግስት መበተን እንድትሸጋገር እያንደረደራት ነው።
በሶስቱ የሐገረ መንግስት ጉስቁልናዎች ውስጥ ያለው የደረጃ ልዩነት ብቻ ነው። የጉስቁልናው መጠን ከፍና ዝቅ ማለት። የሀገረ መንግስት ጤናማነት ትልቁ መለኪያ ሀገረ መንግስቱ የተመሰረተበትን ዓላማ የማሟላት ጉዳይ ነው። state on purpose ማለት ነው።
አንድ ሀገር ከሀገረ መንግስት ጉስቁልና አንጻር የሚገኝበትን ደረጃ ለመለካት የሚያገለግሉ መመዘኛዎች አሉ።
®️የግዛት አንድነት
®️የዜጎች ደኅንነት
®️የዳኝነት ገለልተኝነት
®️የሀገር መከላከያ ሰራዊት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት
®️ለዜጎች አገልግሎት ማቅረብ... እና ሌሎችም ናቸው።
ከእነዚህ መመዘኛዎች አንጻር ሲታይ፥
👉የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ከምንጊዜውም በላይ ጥያቄ ምልክት ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው። #ሱዳን እስከ 50 ኪሜ የሚደርስ ወረራ ፈጽማለች። ብሄራዊ አጀንዳ መሆን ያልቻለ ጉዳይ ነው። የፌደራል መንግስቱ እንደ እጅ ስራ ውጤቱ አበባ የመንቀልና የመትከል ያህል ከዚያም በቀለለ መንገድ ሲያፈርስ ሲሰራት ከሚውላት አዲስ አባባ ውጭ በአራቱም የኢትዮጵያ ግዛት መቀሌም ሆነ ባሕርዳር፣ አምቦም ሆነ ጂጂጋ #መላወስ አይችልም። የትግራይ ክልል ወደ ራስ ገዝነት ከተሻገራ ሁለት አመት አልፏል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የብልጽግና ስርአትን አፍርሰው የራሳቸውን መዋቅር የዘረጉ ሀይሎች ተፈጥረዋል። በተለይም የአማራ ፋኖ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባቂ ሀይል ሆኖ መጥቷል።
👉የብልጽግና ስርአት የዜጎችን ደኅንነት ከመጠበቅ ይልቅ መንግስታዊ ቀውስና ግጭት እየጠመቀ ንጹሐን ዜጎችን በብሔራቸው፣ በሚናገሩት ቋንቋ፣ በሚከተሉት እምነት፣ በተወለዱበት አካባቢ በጅምላ ማዋከብ፣ ማፈን፣ ማሰር፣ መረሸን፣ ገንዘብ መቀበል መሠል የተራ ሽፍታ ተግባር እየፈጸመ ነው። አማራነት በተለይም በወንጀለኛነት የሚያስገምት ማንነት ሆኗል። ከዚህም ባስ ሲል ህዝቦችን ከህዝቦች ለማዘጋጀት መንግስታዊ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ነው። ከሰሞኑ በሰላሌ የአማራና የኦሮሞ ህዝብን ለዘር ፍጅት የጠራበት የከሰረ ፕሮጀክት ማሳያ ነው።
👉የብልጽግና ስርአት ወንበሩን ህዝቦችን በማጋጨትና በጦርነት ላይ የተመሠረተ ነው። ጦርነት ሳይኖር መንግስት ሆኖ ለመቆም የማይችል መሆኑን ያረጋገጠ ነው። የሐገር መከላከያ ሰራዊት በመሠረታዊነት የቆመለትን የሐገር ዳር ድንበር የመጠበቅ ጉዳይ ወደ ጎን በመተው በውስጥ ጉዳይ ሲያቦካ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊት በፖለቲካ ጣልቃ መግባት ትልቁ የሐገረ መንግስት መውደቅ ምልክት ነው።
የዳኝነት ገለልተኝነትና ለዜጎች የተሟላ አገልግሎት የመስጠት ጉዳይ በግልጽ የሚታይ ነው። ስለሆነም በመመዘኛዎች መነጸርነት ሲታይ ኢትዮጵያ ለመበተን ቋፍ ላይ ያለች ሀገር መሆኗ ይታያል።

©️የአማራ ፋኖ በጎጃም ሚዲያ ክፍል

23/11/2024

የኦሮሞ ብልጽግና ከብቶች (እንድገመው - የጋማና የዳልጋ ከብቶች) እራሳቸው ገድለው፣ እራሳቸው እያለቀሱና እያፏለሉ ይገኛሉ። መፏለሏን ተያት ጫልቱ!

የወረሙማው ስርዓት በህዝባችን ላይ ያላደረሰው የግፉ አይነት የለም። ኢመደበኛ ኃይል አሰማርተው ህዝባችን ከማፈናቀል እስከ መጨፍጨፍ የደረሰ የግፍ አይነቶችን አድርሰውብናል። ይባስ ብሎም ላለፉት ሁለት ዓመት ሰራዊት አሰማርተው ይፋዊ ጦርነት ከፍተውብናል።

ዋናው ጥያቄ የወረሙማው ድንፋታና መፏለል "ውጤቱ ምን እየሆነ ነው?" የሚለው ነው።

1) በእነ ብርሃኑ ጁላ "እዚህም ና እዛም ና" የተባለለበት አራዊት ሰራዊት፣ እዚህም እዛም እየተማረከ፣ እዚህም እዛም እየተንጠባጠበ ነው። በተለይ ሰሞኑን በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ምርኮው ለጉድ ነው።

2) ትናንት በሰላማዊ ሰልፍ "አትግደሉን" ብለን የለመናቸው ሰዎች፣ ዛሬ በሰልፍ "ዳውን ዳውን ፋኖ" ይሉን ጀምሯል። "ዳውን ዳውን" የምትለው፣ አንድም ከአቅምህ በላይ የሆነን፣ ሁለትም አንጋጠህ የምታየውን ነውና እንረዳችኋለን 😉

ለማንኛውም ድሮንም ልከህ፣ ታንክም አንጋግተህ፣ ሰራዊትም አግተልትለህ ያቃተህን… በአንድ ተራ የወረሙማ አመራር ዲስኩርና የመግለጫ ጋጋታ ወይም በመንጋዎች የአደባባይ "የዳውን ዳውን" ድለቃ ለአፍታ የሚቆም ትግል የለም። ጩከትህ የቁራ ነው።

የአማራ አክቲቪስቶችም አገዛዙ እራሱ ገድሎ ሲያንቃርር ቢውል፣ መልስ አትስጡት። የአማራ ፋኖ እንኳን አንድን ምስኪን ንፁህ ወጣት ይቅርና ሊወጋው ቀየው ድረስ የመጣን የሰራዊት አባል ማርኮም አስታሞ፣ አብልቶና አጠጥቶ የሚሸኝ እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ነው።

ስናጠቃልል የወረሙማዋ እርግማንና ጩኸት… እኛ ጋር ሲደርስ መረዋ ሲቃ ሆኖ ነው። እና እንጣጥ እንጣጥ እያሉ እንቧ ማለትም ይቻላል - ወረሙማ 🙂
seid Yimam gojamew

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Ethiopian
Addis Ababa
1000