Hiwot Addis ketema

Hiwot Addis ketema

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hiwot Addis ketema, Health/Beauty, Addis Ababa.

Photos from Addis ketema woreda 10 Communication's post 08/05/2026
22/05/2025
16/05/2025

የጤና ሚኒስቴር ከጤና ሙያ ማህበራት አመራር እና ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና በባለሙያ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ዉይይት አድርገዋል።
__________

በዛሬው እለት የጤና ሚኒስቴር እና የጤና ሙያ ማህበራት አመራር እና ተወካዮች በተገኙበት በተደረገዉ ዉይይት የማህበረሰባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለህብረተሰቡ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት እንዲኖረዉ ለህብረተሰባችን ያልተቋረጠ አገሎግሎት እየሰጡ ያሉትን ከልብ አመስግነው ፥የሙያ ማህበራትም ለጤናው ዘርፍ የተቀረጹ ስትራቴጂዎች ዉጤታማ እንዲሆኑ ካላቸው ጉልህ ድርሻ አንጻር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።

የጤና ባለሙያ ጥያቄዎች በተገቢና እና በህጋዊ መንገድ በሚቀርቡበት ሁኔታም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለህብረተሰቡ ሙያዊ ስነምግባሩን በጠበቀ መልኩ የጤና አገልግሎቶች ሳይቋረጡ መቀጠል እንደሚያስፈልግ እና መንግስት በተዋረድ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር እያደረጋቸው ያሉ ውይይቶች ዘላቂነትን በማረጋገጥ ለጋራ ተግዳሮቶች የጋራ መፍትሄ በመፈለግ በቀጣይም እንደ ሴክተር የታቀዱ እቅዶች ተፈጻሚነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ ለዚህም የሚያግዙ ተጓዳኝ ስራዎችን በጋራ በበለጠ ቅርበት እና ትብብር ለመስራት በመስማማት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: https://t.me/M0H_EThiopia

05/05/2025

የስንዴ አብዮተኛዉ ድንቁ መሪ

Photos from Addis Ketema Woreda 10 Prosperity   ፓርቲ's post 25/03/2025
13/03/2025

ሰላም ለሀገር ብልጽግና

ሰላም ለአገር ብልጽግና አስፈላጊ ነው። ሰላም ሲኖር መንግስትና ዜጎች በልማት ላይ ማተኮር ይችላሉ። ይህም የኢኮኖሚ እድገትን ያፋጥናል፣ የስራ እድል ይፈጥራል፣ የኑሮ ደረጃን ያሻሽላል እንዲሁም ሀገራችንን በሁሉም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያደርጋታል።

ሰላም ለማህበረሰብ እድገት ወሳኝ ነው። ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች እርስ በርስ በመተባበርና በመደጋገፍ ወንድማማችነታቸው እና እህትማማችነታቸው እንዲሁም ህብረ ብሔራዊነታቸውን ያጠናክራሉ። ሰላም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እርስ በርስ እንዲተሳሰቡና እንዲከባበሩ በማድረግ ማህበራዊ እና ብሄራዊ አንድነታቸውን ይጠናክራል።

ሰላም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ልማት መሰረት ነው። ሀብቶች ለጦርነት ወይም ለግጭት ከመባከን ይልቅ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለመሠረተ ልማትና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ይውላሉ። ለዚህም ማሳያ ባለፉት 3 እና 4 አመታት ሀገራችንን ባጋጠማት የጦርነት ታሪክ በሰዉ ህይወትና በንብረት ብዙ ዉድመት ተከሰቷል።

ሰላም የፖለቲካ ስርዓታችን እንዲረጋጋና እንዲዳብር፣ እንዲሁም ዜጎች በነፃነት ሃሳባቸውን እንዲገልጹና እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።

በቅርቡ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት ይፋ ያደረገው የሰላም ጥሪ በአካባቢው ግጭት እንዲቆም እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለመ ነው። ይህ ጥሪ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ታጣቂ ሃይሎች የቀረበ ሲሆን መንግስት ለሰላማዊ ውይይት እና ግጭቶችን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ያሳያል።

የሰላም ጥሪው በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን በተለይም የአካባቢው ነዋሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪውን በመደገፍ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ እያቀረቡ ነው። ፓርቲ ያችን ብልፅግና ለሰላም ያለውን ቦታ ሰፊ ነው ሰላም የሰፍነባት እና የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

የሰላም ጥሪዉን ተቀብለዉ ወደ ማህበረሰብ የተቀላቀሉት ትክለኛዉን መንገድ መርጠዋል፡፡ ከዚህ የሰላም መንገድ ዉጭ ያለዉ የሀይል አማራጭ አዉዳሚና ለሀገር ብልጽግና የማይበጅ መሆኑን በማመን በተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ ሃይሎች የሰላም ጥሪዉን እንዲቀበሉ ፓርቲያችን ያሳስባል፡፡

ሰላም ዉድ ሀብት ነዉ፡፡ ለሀገር ብልጽግናም የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ሰላምን ለማስፈን በጋራ ቆመን የሀገራችንን ብልጽግና እዉን ማድረግ ይጠበቅብናል፡

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 01/03/2025
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa