Debr Team
በጋራ መስራት በጋራ ማደግ በጋራ መድረስ
ከኛ ጋር በጋራ ሰርታችሁ ከኛ ጋር ማደግ ትችላላችሁ! "we are ambassadors!"
17/09/2025
የማንበብ ጊዜ ነው ✍️✍️✍️✍️
ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው።
ነገር ግን 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...
#የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...
#ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...
#ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።
1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
#የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።
#ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን የሚቀጥሉት አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።
፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።
፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።
ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡
#አንተም በተመሳሳይ መንገድ አልፈህ በአዲስ ህይወት ከፍ ብለህ መብረር ትችል ዘንድ ታላቅ ማንነትህን እንደገና ውለደው!!!
ህይወት ቀጣይነት ያለው የእድገት እና የለውጥ ጉዞ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣ እንደገና መጀመር፣ ያለፈውን ትተን አዲስ ጅምር መቀበል እንደሚያስፈልገን ሊሰማን ይችላል። ይህ የዳግም ልደት ሂደት እንደገና መጀመር ብቻ ሳይሆን እውነተኛውን ማንነታችንን ገልጦ ከሱ ጋር ተስማምቶ መኖር ነው። ይህን የለውጥ ጉዞ እንዴት መጀመር እና ታላቅ ማንነትን እንደገና መውለድ እንድትችል የሚከተሉትን አድርግ:-
1. ለውጥን ተቀበል
ለውጥ የማይቀር ነው፣ እናም ይህን እውነት በመቀበል፣ እራሳችንን ለአዳዲስ መልካም አጋጣሚዎች እና እድሎች እንከፍታለን። የተለመደውን እና ምቹ የሆነውን ነገር መተው ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የምር የምናድገው እና የምንለወጠው በእነዚያ የለውጥ ጊዜያት ነው። ለውጥን ስንቀበል ካለፈው ውሱንነት ተላቀን ማለቂያ ወደሌለው እምቅ አለም እንገባለን።
2. ውስጣዊ ጥንካሬህን ፈልገህ አግኝ
በዳግም መወለድ እና መለወጥ ጉዞ ውስጥ ውስጣዊ ጥንካሬን ማግኘት አስፈላጊ ነው። ውስጣዊ ጥንካሬ የሚመጣው ከውስጥ ነው እና በጣም ጨለማ በሆነው ጊዜ ውስጥ እንኳን ሊመራን የሚችል ኃይል ነው። ተስፋ መቁረጥ በሚሰማን ጊዜ እንድንቀጥል የሚነግረን ውስጣዊ ድምፅ እና ኋላ ስንቀር ወደ ፊት የሚገፋፋን ጉልበት።
3. ያለፈውን ተወው
ያለፈው ህይወትህ ምንም ይሁን ምን ዳግም መወለድ እና መታደስ ለውጥ ለማድረግ እንዳልዘገየን ያስታውሰናል። የማይጠቅመንን ትተን ለአዲስ ጅምሮች ቦታ ለመስጠት በውስጣችን ያለውን ታላቅ ኃይል ያስታውሰናል። በራሳችን ላይ ካስቀመጥናቸው ገደቦች የመላቀቅ እና የሚጠብቁንን ማለቂያ የሌላቸውን እድሎች የመቀበል እድል ነው።
4. እውነተኛ ማንነትህን ተቀበል
ዳግም መወለድ ዋናውን ማንነታችንን መግለጥ እና ከእሱ ጋር ተስማምቶ መኖር ነው። ገጣሚው ሩሚ በአንድ ወቅት እንደተናገረው፡ “ትናንት ጎበዝ ስለነበርኩ ዓለምን መለወጥ ፈልጌ ነበር። ዛሬ ጥበበኛ ስለሆንኩ ራሴን እየቀየርኩ ነው” በማለት ተናግሯል። ዳግም መወለድ ውጫዊ ሁኔታዎችን መለወጥ ሳይሆን የውስጣችንን ገጽታ መለወጥ ነው። ይህም የራሳችን ህይወት ጠቢብ መሆን፣ እንደ ግለሰብ ማደግ እና እራሳችንን ከእውነተኛ አላማችን ጋር ማጣጣም ነው።
5. ፈተናዎችን ማሸነፍ
እውነተኛ ለውጥ የድሮውን የአቅም ገደብ ጥለን የማናውቀውን እንድንቀበል ይጠይቀናል። ለውጡ የሚያም እና የማይመች ሊሆን ይችላል፣ ግን እውነተኛ አቅማችንን የምናገኘው በዚህ ሂደት ውስጥ ነው ። አስታውስ፣ እያንዳንዱ ፍጻሜ አዲስ ጅምር ነው፣ እናም በአንተ ውስጥ ህይወትህን የመወሰን እና ውብ የወደፊት ህይወትን መፍጠር የሚችል እምቅ ሀይል አለ።
#ማጠቃለያ
ዳግም መወለድ የለውጥ እና የመታደስ ጉዞ ነው። እንደገና ለመጀመር ፣ የማይጠቅምህን ነገር ለመተው እና የራስህ ምርጥ እትም ለመሆን አንተ የምትፈጥረው እድል ነው። ጉዞውን በድፍረት እና በጽናት ተቀበል። በአንተ ውስጥ ውብ እና አርኪ የሆነ የወደፊት ህይወትን የመፍጠር ሃይል እንዳለ አስታውስ።
አንድ ሰው ሊለውጥ ስለሚችል ሼር ያድርጉ 🙏
10/09/2025
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ለመላው የደብሪያንስ እና ኢቲኬሪያንስ እንኳን ለ2018 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ🥳 አመቱ የስኬት የደስታ የመተሳሰብ ይሁንላችሁ!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ አመት!
Happy New Year!
04/09/2025
የአመቱ መጨረሻ የሆነው እሁድን ከኛ ጋር አሳልፉ👌 ለየት ያለ ጊዜ ይኖረናል። አዲሱን አመት እንዴት እንስራበት? ምንስ እንስራ? እንዴት እንለወጥ? ኑ በደንብ ታተርፋላችሁ። እሁድ እንገናኝ 🧭🕰⏰
our products
27/02/2025
Habit Training.....
06/02/2025
call now 0930865051
ስለጸጉር እንክብካቤ ሲያስቡ የትኛው ምርታችንን ይመርጣሉ።
በባህርዛፍ ዘይት እና ካስተር ዘይት ውህድ የተዘጋጀውን ተፈጥሯዊ የመዋቢያ ምርታችንን እናስተዋውቅዎ
OG Castor Oil with Eucalyptus Oil
ዛሬውኑ ይሞክሩት
Etcare
14/01/2025
ዛሬ በደብር ቲም ለአዳዲስ ሰዎች የሚሆን የቢዝነስ ገለፃ ከምሽቱ 2 ስዓት ላይ።ሁላችንም አዳዲስ ሰዎችን እንዲሁም የጀመሩ ልጆቻችንን እንጋብዛለን።
ዝግጁ ናችሁ ???????
are you ready??????!
"We are most of etcare ambassadors"!
join by the link below👇
https://t.me/Debrteam
call 0930865051
10/01/2025
''ከታላቅ መዋል ታላቅ ያደርጋል ''
ኑ አብረን እንዋል ከታላላቆች መንደር!
የ7 ድርጅቶች ባለቤት ከሆነው ማቲዎስ መባ ጋር ልምድ እና ተሞክሮዎች በነፃ ያግኙ።
አይቀርም!
🎉 ልዩ የetcare+ ዝግጅት
💡 ልዩ ቆይታ ከታላቁ መሪ ማቴዎስ መባ ጋር💡
የግል እና ሙያዊ ክህሎትዎን ከፍ ለማድረግ ዝግጁ ነዎት?
እንግዲያውስ ነገ በሚደረገው ከባለራዕዩ መሪ የድርጅታችን መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ ጋር ልዩ የetcare + Event ላይ እንገናኝ
በዋጋ ሊተመን የማይችል ግንዛቤን ለማግኘት እና የሽያጭ ስልቶችን ከታላቁ መሪ ለመማር ይህ እድል የእርስዎ ነው።
📅 ቀን: 03/05/2017
🕒 ሰአት፡ከቀኑ 08፡00
📍 ቦታ፡ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
በሁሉም የህይወትዎ ዘርፍ የላቀ ለመሆን አስፈላጊ የህይወት ክህሎቶችን ይማሩ።
ቅዳሜ አይቀርም!
09/01/2025
ዛሬ ነው ይደውሉልን
06/01/2025
እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ደብር ቡድን ለሁላችሁም በዓሉ
የሰላም
የፍቅር
የመተሳሰብ እና
የድህነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
መልካም የገና በዓል!
Happy Christmas!
DebrTeam
"we are most of etcare ambassadors!"
Click here to claim your Sponsored Listing.
06/01/2025