Abba Seenaaf

Abba Seenaaf

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abba Seenaaf, Health/Beauty, Addis Ababa.

29/09/2025

የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ማጥበቂያ፣ የሰላም እሴት መገንቢያ፡ ኢሬቻ!

የጥንታዊው የገዳ ስርዓት አንዱ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ ኢትዮጵያውያን በአብሮነት ደምቀው የሚያከብሩት ፍቅር፣ መተሳሰብ የሚዳብርበትና ፈጣሪ የሚመሰገንበት የሰላም የደስታ በዓል ነው፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በመሰባሰብ፣ በመተሳሰብ፣ በህብር ደምቀው የሚያከብሩት ኢሬቻ የሀገራችንን መልካም ገፅታ አጉልቶ የሚያሳይ የወል ሀብታችን ነው፡፡

የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነትና የአብሮነት መገለጫ የሆነው ኢሬቻ ማህበረሰባዊ መቀራረብን ያሳድጋል፣ በህብረተሰቡ መካከል መግባባትን እና መተማመንንም ያጠናክራል፡፡ የሰላም እሴት በመገንባት የእርስ በርስ መከባበርን እንዲሁም ትስስርንም ያጠብቃል።

መደመር፣ አብሮነት እና ትብብር ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ በሆነበት በምንገኝበት ቀጠናዊና ዓለም ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ ኢሬቻን የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላት ብሩህ እና ከዛሬም የተሻለ ነገአችንን በጋራ ለመገንባት ፋይዳቸው የጎላ ነው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa