Kolfe Woreda 02 Prosperity Party Inspection And Ethics Commission
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kolfe Woreda 02 Prosperity Party Inspection And Ethics Commission, Health/Beauty, Addis Ababa.
23/05/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የብልፅግና ኢ/ስ/ኮ ቅ/ጽ/ቤት አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት የቡና ጠጡ መርሃ-ግብር የማካሄድ መርሃ ግብሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የቡና ጠጡ ፕሮግራም ባህላዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም በህዝብና በፓርቲው መካከል ያለውን መቀራረብ ለማጠናከር ያለመ ሲሆን የተጀመሩ የልማትና የሰላም ስራዎችን ለማስቀጠል ብልፅግናን መምረጥ እንደሚገባ ተመላክቷል።
13/05/2026
#ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፖርቲ!!
ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የግንዛቤ ፈጠራ መድረኮ ተካሄደ!!
ቀን 05/09/2018 ዓ/ም የኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወ2/የብ/ኢ/ስነ/ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 2 ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግና ማንፌስቶ:ምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ እና ለህብረት :ለቤተሰብ እና ለአባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሆን የጥያቄና መልስ ውድድር ፕሮግራም በዛሬው እለት ተካሄዷል!!
11/05/2026
#ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፖርቲ !!
የመልካም ልምድ ልውውጥ ስኬታማ አፈፃፀሞችን ለማስቀጠል እና ወሳኝና ቁልፍ ተግባር ነው ።
ግንቦት 03/2018 ዓ ም ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የኢ/ስ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ወደ ኮልፌ ክ/ከተማ የብልጽግና ኢ/ስ/ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ተካሔደ።
ለልምድ ልውውጡ የተዘጋጁ ሰነዶች የተሞክሮ ቅመራ ሰነድ በክፍለከተማው የዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በወይዘሮ ሉባባ አደም እ የቀረበ ሲሆን ቴክኖሎጂ የማበልጸግና ቴክኖሎጂው አጠቃላይ የመረጃ ማዘመን ተግባር በአቶ ደረጀ ፍቃዱ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት።
በቁርጠኛ የአመራር ሰጪነት የተጠኑ ውጤትን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣው የልምድ ልውውጥ በክፍለከተማችን ኮሚሽን መደረጉ በስኬት ያከናወናቸውን ውጤታማ ተግባራትን በዝርዝር ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ውጤትን ተቋማዊ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ በመሄዱ ባለፊው የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም በታላቅ ስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን በተቋሙ አቶ በያን ገመዱ ተገልጿል ።
በመድረኩ የተገኙት የወረዳው ብልፅግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን አመራሮች የተደረገው የልምድ ልውውጥ ለእያንዳንዱ ተቋማት የተሞክሮ ማዕከል ሊሆኑ እንደሚችሉ 24/7 በመትጋት የተገኘውን ወሳኝ ውጤትን ለሌሎች በማካፈል እንደ የተሞክሮ ማዕከል ለመሆን እንሰራለን ሲሉ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የብ/ኢ/ስ/ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ከባሺ ገልፀዋል ።
ለልምድ ልውውጡ የተገኙት የኮሚሽኑ የወረዳ አመራሮች በበኩላቸው ሁሌም የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማትን ልምድና አሰራርን እንደ መነሻ በመጠቀም በቀጣይ ለእያንዳንዱ ተግባር ተደማሪ አቅም ይሆናል በማለት ገልፀዋል። ውጤታማ የተቋም መረጃ አያያዝና የሰራተኞች ቁርጠኝነት እንዲሁም የአመራር ሰጪነት በኮሚሽኑ አጠቃላይ ስራዎችበቂ ልምድ መቅሰማቸውን ጠቅሰዋል ።
27/03/2026
!!
በወረዳ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የተዋቀረ ቡድን የ3ተኛ ሩብ አመት የኢንስፔክሽን ምልከታ ጀመረ።
መጋቢት18/2018 ዓ/ም ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 2 የብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 2 የብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ3ተኛ ሩብ አመት የኢንስፔክሽን ተግባር በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል::
ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር የኢንስፔክሽን ተግባራት ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን በማንኛውም ተግባር ጠንካራ ፓርቲ ሲኖር ጠንካራ አባል፣የጠራ ተግባር አፈጻጸምና ጠንካራ ግንዛቤ በመያዝ ፓርቲን በማጠናከር እና በመገንባት የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልፅዋል::
21/02/2026
የወረዳ 2 የብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ_ምግባር ኮሚሽን ቅ/ፅ ቤት የኮሚሽን ኮሚቴ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ ፕሮግራም!!
30/01/2026
በተሰሩ ስራዎች ላይ ልምድ ማካፈልና ልምድ መውሰድ ለቀጣይ ቀሪ ተግባራት አቅም ይሆናል !!!
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ 05 ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ- ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት በመገኝት የልምድ ልውውጥ አካሄደዋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ብልፅግና ኢንስፔክን እና ስነ ምግባር ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ሀ/ገብረኤል በኮሚሽኑ ተቋም ግንባታ ፣በኮሚሽኑ አሰራርና አደረጃጀት፣ መደበኛ የኮሚሽኑ ተግባራትን ስራ ላይ በማዋል የተከናወኑ ተግባራት፣ የተጠያቂነት ስርዓትን በመዘርጋት የመጣ ለውጥ፣ ምቹ የስራ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ የተከናወኑ ተግባራትን የልምድ ልውውጥ ለመውሰድ መገኘታቸውን ገልጸዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አስማማው ቻረው መርጠው ለመጡ እንግዶች ከፍ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን እንደ ወረዳ ጠንካራ የኢንስፔክሽን ስራ በመስራት ብልፅግና እግር እንዲተክል ለማድረግ ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት፣የኮሚሽን አመራር ኮሚቴ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በትጋት እየሰራ በመሆኑ ውጤታማ ነን ብለዋል።
22/01/2026
!!
በወረዳ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የተዋቀረ ቡድን የወረደውን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት 2018 ዓ.ም የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም የኢንስፔክሽን ምልከታ ጀመረ።
ቡድኑ ባለፉት 6 ወራት በክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በእቅድ መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን እና የተገኘ ውጤቶችን በሰነድና በአካል የሚታይ መሆኑ ተገልፆዋል።
ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር የኢንስፔክሽን ተግባራት ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን በማንኛውም ተግባር ጠንካራ ፓርቲ ሲኖር ጠንካራ አባል፣የጠራ ተግባር አፈጻጸምና ጠንካራ ግንዛቤ በመያዝ ፓርቲን በማጠናከር እና በመገንባት የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልፅዋል::
Click here to claim your Sponsored Listing.