Fuuldurri keenya ifa

Fuuldurri keenya ifa

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fuuldurri keenya ifa, Health/Beauty, Addis Ababa.

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 05/12/2025
03/12/2025
24/07/2025

አረንጓዴ አሻራ ለዘላቂ ሀገራዊ እድገት!

አረንጓዴ አሻራ ለመጭው ትውልድ ተሻጋሪ ምንዳ ፣ ህብረ - ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከረያ ፣ በጋራ የመቆምና በጋራ የማደግ ባህልን የሚያፀና የዘመኑ አርበኝነት ማሳያ የብሔራዊነት ኩራት ነው!

ኢትዮጵያ ውበቷም ህልውናዋም የሚረጋገጠው ፣ ታሪኳም የሚታደሰው ፣ የዕድገቷም ሚስጥር የሚጀምረው የአረንጓዴነት ተፈጥሯዊ ስሪቷን መመለስ ሲቻል መሆኑን በመረዳት ፓርቲያችን ሊገነባ ላቀደው የማይበገር ኢኮኖሚ ሁሉም ዜጋ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ አቅጣጫ አመላክቷል።

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለመቋቋምና የአገራችንን ዕድገትና ብልፅግና በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል በችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች በመሳተፍ አገራችን እየተገበረችው ያለውን የዛሬው አረንጓዴ አሻራችን ለነገዋ ኢትዮጵያ የብልጽግና መሠረት ነው።


በትብብር መቆምና በጋራ የመልማት ትሩፋት የችግራችን ሁሉ መውጫ መንገድ ነው። አረንጓዴ አሻራ አንዱ ብሔራዊነትን በማጽናት ሀገራዊ ልዕልናን የምንገነባበት የአርበኝነት መገለጫ መንገድ ነው። አረንጓዴ አሻራ ለመጭው ትውልድ ተሻጋሪ ምንዳ ፣ ህብረ- ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከረያ ፣ በጋራ የመቆምና በጋራ የማደግ ባህልን የሚያፀና የዘመኑ አርበኝነት ማሳያ የብሔራዊነት ኩራት ነው።


አረንጓዴ አሻራ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ያጠናከረ ፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስር የፈጠረ ፣ ሁሉንም ማህበረሰብ ተሳትፎ ያረጋገጠ የጋራ የወል እውነታችን ነው።

24/07/2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ !!

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገራችንን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በማሻሻል፣ ኢኮኖሚውን በማሳደግ፣ እንዲሁም ለአካባቢው ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በራሷ ሀብት ላይ ያላትን እምነት የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው።

ግድቡ ትልቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ በመሆኑ ለጎረቤት አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር ዕድል ይኖራል። ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል የጎረቤት አገሮችን ኢንዱስትሪዎች በማሳደግ የዜጎችን የኑሮ ደረጃም ከፍ ያደርጋል።

በተጨማሪም ግድቡ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተም ጠቀሜታዎች አሉት። ለምሳሌ የደን መጨፍጨፍን በመቀነስ ለአረንጓዴ ልማት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa