Our Dam

Our Dam

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Our Dam, Health/Beauty, Addis Ababa.

15/08/2025

ታላቋን ኢትዮጵያ እውን እያደረገ ያለ ፓርቲ ፡- ብልጽግና!!

ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ ትርክቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራረቡና የሚያስተሳስሩንን እውነታዎች በማጉላት፣ ከትናንት ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር ወንድማዊና እህታዊ ህብረትን በብሔሮች መካከል ማጠናከርን ይመርጣል።

ብልፅግና ፓርቲ ሃገራዊ አንድነትን መትከል አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መዘርጋት ትልቅ ራዕይ አንግቦ የተነሳና ራዕዩም እውን እያደረገ የለውጥ ጉዞውን በውጤት እያረጋገጠ የመጣ ፓርቲ ነው።

የለውጡ ትልቁ ግብ ከሆነው አንደኛው የዲሞክራሲ ማበብ ባህሉን በማስፋት ረገድ የማህበረሰቡ ንቃተ ህሊና ጋ አስፍቶና አልሞ በመስራት ከፓለቲካ እስረኝነት በመውጣት ለሀገር አንድነትና ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥና ብልጽግና ማረጋገጥ ያስችል ዘንድ አስፍቶ በማሰብ እምርታ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል ሁኔታ ለዘመናት እስር ቤት የታሰሩትን መፍታትና የሀገር የለውጡ አካል እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ፣ በተለያዩ ጊዜያት በሽብርተኝነት ተፈርጅ ወደ ውጪ አገር የወጡና ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው የነበሩ ነፃ በማድረግ ለሀገራቸው ለውጥ በአንድነት ቆመው የለውጡ ተዋናይ እንዲሆኑ እድል የሠጠ ስርዓት ያበጀ ሂደት ፓርቲ ነው።

የዲሞክራሲ ምህዳሩና ባህሉ የበለጠ እንዲያብብና በተግባር እንዲተገበር ሁሉም ኢትዬጵያዊ ዜጋ አንድ ላለችን ሀገር በመምከር የተፎካካሪ የጋራ ምክር ቤት ተቋም መፍጠር በተያዙ እሳቤዎችንና አላማዎች ላይ ግልጽ የሆነ ውይይት ነፃ ሀሳቦችን በማቅረብ ለውጡን ለማበብ ፈርቀደጃ ስራዎች ለመስራተ ተችሏል።

አቃፊነትን በተግባር ያሳየና ከማሳየትም ባለፈ ቀግልጽ በተጨባጭ ሆኖ በመገኘት የሚታይ እምርታዊ ውጤት የተመዘገበበት እሳ ነው። ለዚህም ከአጋርነት በመውጣት ስለ ሀገር ጉዳይ በእኩል በመሳተፍ እኩል ሀሳብ በመስጠት እኩል በመስራት በእኔነት ስሜት በመስራት ለለውጥ ማረጋገጥ ትልቅ ስራ መስራት ተችሏል።

ለዚህም በህብረ ብሄራዊ አንድነት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መርህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በማሳተፍ ሁሉም ብሄረሰብ ያሳተፈ ሁሉም ዜጋ ባሳተፈ መልኩ ዲሞክራሲን በመትከል ስራዎችን በውጤት በመቀየር ትልቅ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት ተችሏል።

ሌላኛው የፍትህ እና የሚዲያ ተቋማት ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ ገለልተኛና በማድረግ የተቋማቸውን ህልው በማስጠበቅ ህግና ስርዓቱን በሚጠብቅና በሚያከብር መልኩ ተልዕኮዋቸው በነፃት እንዲመሩ የተደረገበት አግባብ በዲሞክራሲ ምህዳሩ ከማስፋት አንፃር ትልቅ እምርታዊ ለውጥ የመጣበት ሂደት እጅግ የሚበረታታ ነው።

15/08/2025

ብልፅግና ፓርቲ በስራ ትጋት እና ፅናት በሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳና!!

ብልፅግና ፓርቲ የስራ ትጋትን እና ፅናትን የሚያንፀባርቀው በሀገራዊ ልማት እና ብልፅግና በመገንባት ረገድ ነው። ብልፅግና ፓርቲ አጀንዳው "ልማት እና ብልፅግና" መሆኑን አፅንኦት በማድረግ፣ ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልዶች የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ዘላቂ ስራ እንደሚያስፈልግ ያምናል።

ብልፅግና ፓርቲ በቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ወይም የግል ጥቅም ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብን በመግራት ፣ የሀገርን አንድነት እና የህብረተሰብ ግንኙነትን እንደ መሠረታዊ የለውጥ እሴት ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ህዝቦች በጋራ ዓላማ ለመስራት ፅናት ለማሳየት የሚያበቁበት መንገዶች ናቸው።

የሀገርን ለውጥ ለማምጣት በመስዋዕትነት እና በቀጣይነት የሚደረግ ጥረት ያስፈልጋል ፤ ይህም በተለይ በአስተዳደራዊ፣ በማህበራዊ፣ እና በልማታዊ ሂደቶች ውስጥ የፅናት እና የጊዜ ቆይታ ያለው አቀራረብ ይጠይቃል። ፓርቲው የሚያተኩረው በስኬታማ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው ፤ በዚህም ተግባራዊ ለውጥ ማሳየት ተችሏል።

ብልፅግና ፓርቲ በስራ ፅናት ከአጭር ጊዜ ውጤቶች ይልቅ ዘላቂ ለውጦችን በማምጣት ረገድ አተኩሮ ይሰራል ። በተለይም፣ በሀገራዊ ሪፎርም እና በልማት ሂደቶች ውስጥ የተከናወኑት ለውጦች ለቀጣዩ የእድገት ጉዞ መሰረት እንደሚሆኑ ያሳየ ነው ። ይህም የስራ ፅናትን እና ትጋትን ያሳያል።

15/08/2025

Category

Website

Address

Addis Ababa