GateHealthinfo
Getahun Zerefa
11/02/2026
"ሞሮኮ የአውሮፓ ሀገራት ስጋት ትሆናለች" — አርሴን ቬንገር
| ታዋቂው ፈረንሳዊ አሰልጣኝ እና የፊፋ የእግር ኳስ ልማት ሃላፊ አርሴን ቬንገር፣ የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን በአለም መድረክ ላይ ስላለው ጥንካሬ እጅግ ከፍተኛ ግምት ሰጥተዋል።
ቬንገር በሰጡት አስተያየት፣ ሞሮኮ በቀጣዩ የአለም ዋንጫ ለአውሮፓ ሀገራት ዋነኛ እና አስፈሪ ተፎካካሪ እንደምትሆን ተንብየዋል።
አሰልጣኙ አክለውም፣ "አሁን ላይ ሞሮኮን ከአፍሪካ ሀገራት ተርታ ብቻ መመደብ አይቻልም፤ ቡድኑ ከምርጥ የአውሮፓ ሀገራት ጋር እኩል መሰለፍ የሚችል ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።
የቬንገር ትንቢት፡
* የአለም ዋንጫ ባለቤትነት፡ ቬንገር ሞሮኮ በቀጣዮቹ አምስት የአለም ዋንጫ ውድድሮች ውስጥ ዋንጫውን የማንሳት አቅም እንዳላት ገልጸዋል።
* ደረጃው፡ የቡድኑ ወቅታዊ አቋም እና ጥንካሬ ከአፍሪካ አልፎ ከአውሮፓ ሀያላን ጋር የሚመጣጠን መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሞሮኮ በኳታሩ የአለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በመድረስ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር መሆኗ የሚታወስ ሲሆን፣ የቬንገር አስተያየትም ይህንን ተከታታይ ስኬቷን መነሻ ያደረገ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ጌጡ
11/02/2026
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
****************
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገት ስኬት የማይተካ ሚና የተጫወቱት አቶ አማን፤ የታላቅ ራዕይ ባለቤትና ብርቱ ሰው እንደነበሩም ኢቢኤስ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።
የጌት ኸልዝ ገፅ በአቶ አማን ፍስሃጽዮን ህልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
19/09/2025
ሚስቱን ሱፐር ማርኬት አድርሷት እሷ እቃዎችን ገዝታ እስክትወጣ ውጪ ሆኖ እየጠበቃት ነበር።
(ባይመከርም)እሷን እየጠበቀ እያለ በአጠገቡ ገራሚ ሰውነት ያላት ሴት ስታልፍ በመስታወቱ ያያል።ከዚያም ለተፈጥሮ እና ለፈጣሪ የእጅ ስራ ትልቅ ክብር ስላለው አላስቻለውም - ከመኪናው ወርዶ እያደነቀ ይከተላታል።
በዚህ ጊዜ ነበር ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ከባድ መኪና የሰውዬውን መኪና ጨፍልቆ ከመሬት የደባለቃት…
አንዳንዴ ማምለጫ መንገድህ አይታወቅም
•••••••••••••••••••••
-Wasu M
18/09/2025
🇪🇹 ኢትዮጵያዊው ደራሲ አበረ አዳሙ ለብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ታጩ
| የእጩዎች ዝርዝሩ በብራዚሊያ በተካሄደው ሁለተኛው የብሪክስ የባሕላዊ እሴቶች ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል።
📚 በዝርዝሩ ከብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢራንና ኢንዶኔዥያ ጨምሮ ከሌሎችም ሀገራት የተወጣጡ 27 ደራሲያን ተካተውበታል፡፡
በብሪክስ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ዙሪያ በተካሄደው ውይይት ወቅት፤ የሥነ ጽሑፍ ምሁራንና አሳታሚዎችን የሚያካትት የብሪክስ ሀገራት የጸሐፊዎች ማኅበር ምሥረታም እውን ሆኗል፡፡
የማኅበሩ ዋነኛ ዓላማ ቀጣይነት ያለው የባሕል ልውውጥን ማሳደግ እና በሥነ ጽሑፍ መስክ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስተባበር እንዲሁም የሽልማቱን አዘጋጅ ኮሚቴ መደገፍ ነው።
“የብሪክስ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት ስለ ሀገራቸው ባሕልና ወጎች ለሚጽፉና ዕውቀትን ለሚያሰራጩ ደራሲያን ልዩ ዕድል ነው።
የዚህ ሽልማት ሀሳብ ተሳታፊ ሀገራት በባሕላቸውና በወጋቸው መነፅር አማካኝነት እርስ በእርሳቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲተዋወቁ ነው፤ ምክንያቱም ሥነ ጽሑፍ የሀገራትን ታሪክና ወግ ለማቆየት ወሳኝ መሣሪያ ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የሽልማቱ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል ዘለዓለም መልዐክ ተናግረዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።
18/09/2025
ያማል!
ገና ወጣት ነው እጅግ በጣም። አደጋ በአጭር አስቀርቶታል። ሌላኛው ከባዱ መታመም ወላጆች የልጃቸውን ድንገተኛ ሞት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መስማታቸው ነው። ከሰአታት በፊት በቲክቶክ ገፁ ላይ ደስተኛ እና ሳቂታ የነበረ ልጅ በሚዘገንን የመኪና አደጋ ሞተ ሲባል ለማመን ይከብዳል።******
ወዳጆቼ ህይወት እንዲህ ነች! እኛ ማለት እያንዳንዳችን እንደዚህ ነን። ዘላለም አንኖርም ከደቂቃ በኋላ ምን እንደምንሆን አናውቅም።ለዝች ህይወት ነው እንግዲህ ስንሰዳደብ ፤ ስንባላ ፤ ስንጣላ ስንነቃቀፍ የምንውለው።*****
ለሹፌሮች ደግሞ!
እባካችሁ እያስተዋላችሁ አሽከርክሩ ፤ ለራሳችሁም ፤ ለሌላውም ሰው ህይወት ተጠንቀቁ! ውድ ነፍሳችሁን ድንገት አታስነጥቁ ፤ የሌላውንም አትንጠቁ! ስለቸኮላችሁ ቶሎ አትደርሱም መድረስ የፈለጋችሁት ቦታ ቀድማችሁ ብትደርሱም ፤ ብታረፍዱም ምንም ነገር ከልኩ አያልፍም። *****
እግረኞች ደግሞ!
ሁሌም በትክክለኛው መንገድ ላይ ሂዱ ፤ተራ ነገር ቢመስልም የትራፊክ ህጎችን ለመከተል ሞክሩ አካባቢያችሁን በንቃት ተከታተሉ። መኪና ሰው ሰራሽ ነው ፤ እናንተ ደግሞ እግዚያብሄር ሰራሽ ናችሁ። እናንተ ከመኪና በላይ ዋጋችሁ ውድ ነው። ለራሳችሁ ክብር ስጡ ዋጋችሁን እወቁ።
R.I.P ኢብሳ ጉተማ
18/09/2025
ማስታወቂያ
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ለእነዋሪ ቴክኒክና ሙያ ነባር የቀንና የማታ ሰልጣኞች በሙሉ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በእነዋሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰጠኛ ኮሌጅ ውስጥ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4
በ - Data base management
በ - Animal science
በ - Garmenit production
በ - Constraction ሙያ ዘርፎች እየሰለጠናችሁ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ስለሆነም ተቋርጦ የነበረውን ስልጠና ለመጀመር አሰፈላጊ ቅድመ ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ
ከ 08/1/2018 ዓ.ም እስከ 16/1/2018 ዓ.ም ድረስ በኮሌጁ ሬጅስትራል ቢሮ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ እየገለጽን ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
ለቀን ሰልጣኞች
1 የ 5ወር ወጭ መጋራት ብር 750
2 የመመዝገቢያ ብር 100
ለማታ ሰልጣኞች
1 ወርሀዊ ክፍያ 450 ብር እና የመመዝገቢያ 100 ብር
መሆኑን አውቃችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከተቀመጠው ጊዜና ቀን ውጭ ዘግይቶ የሚመጣ ሰልጣኝ በቅጣት የምናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920660746/0920631464 መደወል ትችላላችሁ።
18/09/2025
ከባህር ወለል በታች 292 ሜትር ዝቅ ተደርጎ የተገነባ መተላለፊያ ዋሻ
| ይህ በባህር ውስጥ የተሠራው የመንገድ ዋሻ The Ryfylke Tunnel ተብሎ የሚጠራ ሲሆን መገኛውም በኖርዌይ ውስጥ ነው። ርዝመቱም 14.4 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ ከባህር ወለል በታች 292 ሜትር ዝቅ ተደርጎ የተገነባ ነው።
ይህ ስምጥ ዋሻ ኖርዌይ ውስጥ Stavanger የተባለ ቦታን Ryfylke ጋር የሚያገናኝ ከመሆኑም በላይ ጉዞን የሚያሳጥ እንዲሁም፣ የመርከብ ላይ ትራንስፖርትን ጨርሶ የሚያስቀር ነው ተብሎለታል። የዋሻው ግንባታ እ.ኤ.አ 2013 ተጀምሮ በ2019 ሊጠናቀቅ ችሏል።
18/09/2025
“150 ሰዎችን አውጥተን ቤቶቹን አሽገናል ” - ኢ/ር ወንድሙ ሴታ
| በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መጠሪያው ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም በተባለ አካባቢ የመሬት መንሸራት አደጋ ማጋጠሙ፣ ድልድይ በመደርመሱ ነዋሪዎችም ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጓል።
ስለአደጋው ለኤኤምኤን ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጂ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ፣ “ አደጋው ሚኪሊላንድ ኮንደቀሚኒየም ብሎክ 13 ጋ ብቻ አይደለም። ከሚኪሊላንድ የመጀመሪያ ደረጃና መካከለኛ ት/ቤት አጥርም በተመሳሳይ መልኩ ጉዳት የደረሰበት ሁኔታ አለ ” ብለዋል።
በሌላ ቦታ ወረዳ 14 አንድ ቤተ እምነት ግቢ ውስጥ ያለ የዋዕለ ህፃናትና መጸዳጃ ቤት ላይ የደረሰ ተመሳሳይ ጉዳት መኖሩንም አክለዋል።
“ ይሄ ጉዳት ምልክት ማሳየት የጀመረው ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ/ም አካባቢ ነው። በኮንዶሚኒየሙ ባለው ጀርባ መንገድ ላይ ስንጥቅ መታየት ነበር የጀመረው ” ሲሉም የሁነቱን መነሻ አስረድተዋል።
“ ሲጀምር የመሬት መሰንጠቅ ነው የነበረው በኋላ ላይ ግን በተለይ ከነሐሴ አጋማሽ ወዲህ ባለው ከፍተኛ የሆነ ዝናብ አፈሩ በጣም ከፍተኛ የውሃ መጠን በሚይዝበት ጊዜ ልል በመሆኑ ወደ መስመጥ፣ የታችኛው የወንዙ ክፍል ደግሞ የመሸርሸር አደጋ እንደደረሰ አይተናል ” ነው ያሉት።
ኢ/ር ወንድሙ መንስኤው በተመለከተ ምን አሉ ?
“ እዛ አካባቢ ያለው ወንዝ ከፍተኛ ተዳፋት የነበረ ቦታ ነው፤ የሚነሳበትንም ቦታ ከጉለሌ ቦታኒካል ጋርደን ጀምሮ ካሽመንት እየሰበሰበ የሚመጣ ነው። የሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም በሚሰራበት ጊዜ ወደ 123 ፍሎር የሚጠጋ ነው።
አብዛኛው ከዛ ይወጣ የነበረው የተቆፈረ አፈር ምልስ የነበረበት፣ መንገዱም ሲሰራ ያንን ታሳቢ ያላደረገ፣ ከአካባቢው የሚመጣው ውሃ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት ያ የመሬት መሰንጠቅ ወደ መሬት መስመጥ፣ በታችኛው የወንዝ ተፋሰስ ክፍልም መንሸራተት አምጥቷል።
ሳይቱ ወደ 123 ብሎኮች አሉት፤ ወደ 4272 የሚጠጉ አባውራዎች የሚኖሩበት አካባቢ ነው። ከዚህ ሁሉ ቦታ ከህንፃ ላይ የሚወርደው የዝናብ ውሃ ወደ ወንዝ መሄድ መቻል አለበት።
በኮንዶሚኒየሞቹ ዙሪያ ያሉ የጎርፍ ማፋሰሻ ቱቦዎች በተለያዬ ቆሻሻ የተደፈኑ በመሆናቸው ውሃው ወደ ወንዙ አይሄድም፤ እዛው ነው የሚሰርገው። እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ከ8 እስከ 12 ሜትር የሚሆን አዲስ ምልስ አፈር በዛ አካባቢ እንዳለ ነው ያሳየን ” ብለዋል፡፡
ለነዋሪዎቹ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ ስለመስራት ተጠይቀው ምን መለሱ ?
በነዋሪዎቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ምን የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ሲጠየቁ፣ “ ምልክት ከታዮበት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች፣ ባጠገቡ ካለው ት/ቤት ጋር ውይይት አድርገን በተለይም ብሎክ 13 ስሰነበረ የበለጠ ተጋላጭ የነበረው በጊዜያዊነት ከቤት እንዲወጡና እንደዲታሸግ ተደርጓል ” ብለዋል።
በቦታው የሰዎችና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳይኖር የመከልከል ሥራ መሰራቱንም፣ ምሁራን አቀረቡት ባሉት ሪፓርት መሰረት የማቅለያ ሥራ ለመስራት መታቀዱንም ጠቁመዋል።
ኢ/ር ወንድሙ፣ “ አጠገቡ ያሉ መንገዶች በመደርመሳቸው ለአደጋ ተጋላጫነታቸው ስለሚጨምር በአንድ ብሎክ ውስጥ የሚኖሩ ወደ 150 ሰዎችን አውጥተናል። ቤቶቹንም አሽገናል” ሲሉምተናግረዋል፡፡
ዘላቂ መፈትሄ የሚሆነው ወንዙን ከላይኛው ተፋሰስ ጀምሮ በእርከን የማስተካከልና ከሰው እንቅስቃሴ የጸዳ ማድረግ መሆኑን፣ ይህ ካልተሰራ የአደጋ ስጋቱ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚሄድ ምክረ ሀሳብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን መገኘነቱን አስረድተዋል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።
18/09/2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቪስታራ አውሮፕላኖች አደጋ ሊደርስባቸው ተቃርቦ እንደነበር ተዘገበ
| በህንድ የኢንዲራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (IGIA) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ላይ ባለው ከባድ የሥራ ጫና ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቪስታራ አየር መንገድ አውሮፕላኖች በኅዳር 10 ቀን 2023 አደጋ ሊደርስባቸው ተቃርቦ እንደነበር የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ ባወጣው የመጨረሻ ዘገባ ላይ አስታወቀ።
አንድ የ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን ሊነሳ ሲዘጋጅ፣ ከጎኑ የ ቪስታራ አየር መንገድ አውሮፕላን ለማረፍ እየተቃረበ ነበር።
በከፍተኛ ነፋስ ምክንያት የቪስታራ አውሮፕላን የማረፍ ሙከራውን ሲያቋርጥ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር ሊጋጭ ተቃርቦ እንደነበር ተገልጿል።
የሁለቱም አውሮፕላኖች የትራፊክ ግጭት መከላከያ ስርዓት (TCAS) “እርስ በእርስ ይራቁ” የሚል ማስጠንቀቂያ በመስጠት ግጭቱን ማስቀረት ችሏል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በሁለቱም አውሮፕላኖች ውስጥ በድምሩ 227 ሰዎች ነበሩ።
የአደጋው ዋና መንስኤ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪው ከፍተኛ የሥራ ጫና በመኖሩ “አእምሯዊ የመጫን አቅም በላይ” መድረሱ እንደሆነ የምርመራ ሪፖርቱ ገልጿል። ይህም ቅድሚያ መስጠት የሚገባቸውን የደህንነት ተግባራት በአግባቡ እንዳይከታተል አድርጎታል።
ተቆጣጣሪው የኢትዮጵያ አውሮፕላንን የመነሻ ፈቃድ በጊዜው ቢሰርዝ ኖሮ፣ አደጋው ሙሉ በሙሉ ሊወገድ ይችል እንደነበር ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የህንድ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለስልጣን ደህንነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን እንዲተገብር ተጠይቋል ሲል ካፒታል በገጹ አስነብቧል።
18/09/2025
ተዘርፌያለሁ
| የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጀማል አህመድ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት በአቶ አብነት ገብረመስቀል ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተዘርፌያለሁ ሲሉ ከባድ የሙስና ውንጀላ አቀረቡ።
ይህ አስደንጋጭ ክስ የመጣው፣ አቶ አብነት ገብረመስቀል ‘ክለቡን ለመጥለፍ ሴራ እየተካሄደ ነው’ ሲሉ መግለጫ ከሰጡ በኋላ ነው።
🔴 "የቦርድ አባል አልነበርኩም፤ የገነባሁትን አካዳሚ አፈረሱብኝ"
አቶ ጀማል ለዘ-ሐበሻ በሰጡት ምላሽ፣ የክለቡ የቦርድ አባል ተደርገው መቅረባቸው ስህተት መሆኑን ገልጸዋል። "የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አባል ሆኜ አላውቅም፤ የቡድኑ እጅግ ታማኝ ደጋፊ ነበርኩ። ቡድኑን ለመርዳት የራሴን በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ አውጥቻለሁ" ብለዋል።
የውጭ ተጫዋቾችን እና አሰልጣኞችን ገንዘባቸውን አውጥተው በመክፈል ወደ ክለቡ እንዲመጡ ይደግፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጀማል፣ አሁንም ቡድኑ የሚጠቀምባቸው ሁለቱ አውቶቡሶች በግል ገንዘባቸው የተገዙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ከክለቡ ጋር ግንኙነታቸው የተቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ከባድ ውንጀላዎችን አቅርበዋል። “የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከመሆናቸውና፣ አኔና አብነት ከመካሰሳችን ከሁለት ዓመት በፊት ነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቀቄ የወጣሁት (ድጋፌን ያነሳሁት)” ብለዋል። ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያው የገንዘብ ምዝበራ እንደሆነ ገልጸዋል። “በ2010ን ጨምሮ ለዓመታት ለክለቡ ያሰባሰብኩት ገንዘብ በሙሉ በአብነት እና በዳዊት አማካኝነት ወደ ሌላ አካውንት ገብቶ ተዘርፏል። ለዓመታት በሚሊኒየም ይካሄድ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችም በተመሳሳይ በእነሱ መዘረፉን በማወቄ የተፈጠረ ቅሬታ ነው” ሲሉ ከሰዋል።
ሁለተኛው እና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በቢሾፍቱ የገነቡት ዘመናዊ የእግር ኳስ አካዳሚ መፍረስ እንደሆነ ተናግረዋል። "ይህ አካዳሚ የዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲኖረው፣ ከራሴ ገንዘብ በተጨማሪ፣ ሚድሮክ የሚመራቸው ድርጅቶችን ድጋፍ ጨምሮ፣ ሼህ መሐመድን አሳምኜ እና ከቢጂአይ ጋር ተነጋግሬ የጀመርኩት ነበር። ነገር ግን ውሳኔው፣ ከጀርባዬ ጀማል እንዳይሰማ ተብሎ በሶስት የወንጀል ተባባሪዎች ብቻ ተወስኖ ወደ ዋናው ቡድን ማሰልጠኛነት ተቀየረ፤ ዳዊት እና አብነት ይገኙበታል። በዚህ ቅሬታ ነው የወጣሁት።” ሲሉ ገልጸዋል።
🔴 "ወደ ክለቡ አልመለስም" - የአቶ ጀማል የመጨረሻ ውሳኔ
"አቶ ጀማል ክለቡ ይመለስ" የሚሉ ቅስቀሳዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ወደ ክለቡ አመራር የመምጣት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ አስረድተዋል። "የአሁኑ አመራሮች እና አንዳንድ የደጋፊ ቡድኖች በተደጋጋሚ ስሜን በሀሰት ሲያጠፉ እና በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያካሂዱብኝ ቆይተዋል። አብነት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ደጋፊዎችን አደራጅተው ሲያስፈራሩ ነበር። የአብነት ከእስር መፈታትም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አድርገው አክብረዋል። የሱን ክስ መቋረጥ ተከትሎ ወደ ክለቡ ላለመለስ ወስኛለሁ” በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል።
"የእኔ ተልዕኮ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ በሙሉ ተለውጧል" ያሉት አቶ ጀማል፣ አሁን ትኩረታቸው ትልቅ ድርጅት እንደመምራታቸው “ሰው መር የሆነ፣ በህዝቡ እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር፣ ማህበራዊ ኃላፊነታቸው መወጣት” ላይ መሆኑን ገልጸው፣ እግር ኳስ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንዳልሆነ አክለዋል።
የሊቨርፑል ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ጀማል፣ ለታሪካዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ታሪክ ልዩ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል። “ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያው አርበኛ ክለብ ነው፣ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን ብሎ በእውነተኛ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ፣ ለብዙ ዓመታት እውነተኛ የኢትዮጵያ ወዳጆች የደገፉት፣ እኔም ብዙ ጊዜ የደገፍኩት፣ ብዙ ሰው ያስተዋወቀኝ ክለብ ነው። ለክለቡ ትልቅነት ሁሌም እመኛለሁ፣ ለክለቡ ያለኝ ፍቅር ዕድሜ ልኬን በልቤ ይኖራል፣ ግን ክለቡን ለመቀላቀል አልፈልህም” ሲሉ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል።
ይህ የአቶ ጀማል ጠንካራ ምላሽ የመጣው፣ በአሜሪካ የሚገኙት አቶ አብነት ገብረመስቀል ክለቡን "ለመጥለፍ የሚደረግ የድብቅ ሴራ" አለ ሲሉ የክለቡን ጠቅላላ ጉባኤ ለመስከረም ወር መጨረሻ ከጠሩ በኋላ ነው።
የአቶ ጀማል አህመድ ክስ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ያለውን የአመራር እና የፋይናንስ ቀውስ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩት ሲሆን፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ ውጥረት እንደሚኖር አመላካች ነው። የክለቡ አባላት እና ደጋፊዎች በቀረቡት ከባድ ክሶች ላይ ተመስርተው የክለባቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ መወሰን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። #ዘሐበሻ
Category
Website
Address
Addis Ababa
GET