ለባድ Ethiopia

ለባድ Ethiopia

Share

አልሃምዱሊላህ

28/09/2026

🔴 ሰበር ዜና! 🔴

የኦሮሚያ ክልል አዲስ የዞን አስተዳደር መዋቅር ይፋ አደረገ!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማፋጠን እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ይበልጥ ለማቀላጠፍ በሚል ቀደም ሲል የነበሩትን 21 ዞኖች በ6 ዓበይት (ዋና ዋና) የክልል ክፍሎች ሥር የሚያደራጅ አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ዘርግቷል።

በዚህ አዲስ አወቃቀር መሠረት ክልሉ በስድስት ዋና ዋና መዋቅሮች የተከፈለ ሲሆን እነሱም፦

1️⃣ ማዕከላዊ ኦሮሚያ

2️⃣ ምሥራቅ ኦሮሚያ

3️⃣ ደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ

4️⃣ ደቡብ ኦሮሚያ

5️⃣ ምዕራብ ኦሮሚያ

6️⃣ ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ

📌 የመዋቅር ለውጡ ዋና ዓላማዎች፦

የአስተዳደርና የልማት ሥራዎችን በብቃት ለመምራት

የሕዝብን ጥያቄዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ በፍጥነት ለመመለስ

ሀብትና የሰው ኃይልን ባልተማከለ መልኩ በተሻለ ሁኔታ ለማስተባበር

ይህ አዲስ አወቃቀር ቀደም ሲል የነበሩትን ዞኖች እንደየቅርበታቸው በእነዚህ ስድስት አበይት መዋቅሮች ሥር በማቀናጀት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተገልጻል።

👇 የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ!

ስለዚህ አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ለውጥ ምን ያስባሉ? ሃሳብዎን በኮመንት ያስፍሩልን፤ ለሌሎችም እንዲደርስ Like እና Share ማድረጎን አይርሱ!

#ሰበርዜና #ኦሮሚያ

28/09/2026

ብዙዎቻችን ማሰብንና መጨነቅን አንድ አድርገን እንመለከታቸዋለን። "እየተጨነቅኩ ሳይሆን እያሰብኩ ነው" ብለን ራሳችንን እንሸውዳለን። ነገር ግን እውነታው ይኸው ነው፦ ችግሮች ሀዘን የሚሆኑብን ስለምናስብ ሳይሆን… ስለምንጨነቅ ነው! በመካከላቸው ያለው ልዩነት ደግሞ የሰማይና የምድር ያህል የራቀ ነው።

1ማሰብ ምንድን ነው?

ማሰብ ማለት አላህ የሰጠንን ታላቅ የአእምሮ ጸጋ ተጠቅሞ ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ መውጫ መንገድን ማፈላለግ ማለት ነው። ችግር ሲገጥመን በሰከነ መንፈስ ራስን ጠይቆ ወደ መፍትሄ መጓዝ ንቁነት ነው። ማሰብ የሚያተኩረው በመንስኤዎች ላይ መወያየት፣ ከስህተት መማር እና አላህ በሰጠን አቅም ልንቀይረው የምንችለውን ነገር ለማስተካከል ሰበብ ማድረስ ላይ ነው።

በእስልምናችን ማሰብና ማስተንተን (ተፈኩር) የኢባዳ (የአምልኮ) ያህል ትልቅ ቦታ አለው። አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ ውስጥ በብዙ ቦታዎች ላይ "አታስቡምንም? አታስተነትኑምንም?" እያለ ይጠይቀናል። ማሰብ ብርሃን ነው፤ ካለንበት የችግር ጨለማ የምንወጣበትን መውጫ ቀዳዳ ያሳየናል።

2 መጨነቅምንድን ነው?

በሌላ በኩል መጨነቅ ማለት ወደኋላ አልፎ ለሄደው ነገር እየቆጩ ራስን መውቀስ፣ ወይም መጪው ዘመን ምን ይዞ እንደሚመጣ በማያውቀው ደካማ አእምሮ ነገን አስቀድሞ መፍራት ነው። መጨነቅ በአላህ ውሳኔ (ቀድር) ላይ ሙሉ በሙሉ አለመተማመንን (ተወኩል ማጣትን) ይወልደዋል። የሰው ልጅ ሁሉንም ነገር በእጁ ሊቆጣጠር ሲሞክር ይጨነቃል።

📌 በሁለቱ መካከል ያለው ዋና ልዩነት በአጭር ቃላት፦

ማሰብ፦ መፍትሄ ላይ ያተኩራል፤ መጨነቅ፦ ችግሩ ላይ ብቻ ይሽከረከራል።

ማሰብ፦ ወደ ተግባርና ተስፋ ይመራል፤ መጨነቅ፦ ወደ ፍርሃትና መበሳጨት ይወስዳል።

ባጭሩ ማሰብ መውጫ መንገድን ይፈልጋል፤ መጨነቅ ግን የነበረውን መንገድ ይዘጋል።

ታላቁ ነብይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ካስተማሩን ዱዓዎች መካከል፦ «አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ሀሚ ወል ሁዝን...» (አላህ ሆይ! እኔ ካለፈ ነገር ሀዘንና ከምንመጣው ዘመን ጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ) የሚለው ይገኝበታል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከጭንቀት በአላህ የተጠበቁት፣ መጨነቅ ሰውን ከተግባር እንደሚያስወጣው ስሚያውቁ ነው።

3. ወደ ልብ እረፍት የመመለሻ መንገዶች

አንድ ሙስሊም ሊኖረው የሚገባው ትልቁ መሳሪያ "ተወኩል" (በአላህ ላይ ሙሉ በሙሉ መደገፍ) ነው። ሰበቡን ማድረስ (ማሰብና መስራት) ከእኛ ሲሆን፣ ውጤቱን ለአላህ መስጠት ደግሞ የእውነተኛ አማኝ መገለጫ ነው።

"ነገ ምን እሆናለሁ? ነገሮች ቢበላሹስ?" ብሎ መጨነቅ ዛሬ የተሰጠንን ወርቃማ ጊዜ በባዶ ማጥፋት ነው። አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣኑ እንዲህ ይለናል፦
«لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا»
"አላህ ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።" (አል-በቀራህ፡ 286)።

ይህ ማለት የገጠመህ ችግር ምንም ያህል ትልቅ ቢመስልም፣ አንተ ውስጥ እሱን የማለፍ አቅም ስላለህ ብቻ ነው አላህ የመረጠህ። ስለዚህ የገጠመህን ችግር ለመፍታት አስብበት እንጂ አትጨነቅበት። ያንተን ድክመትና አቅም የሚያውቀው ፈጣሪህ መውጫውን መንገድ ያዘጋጅልሃል።

ማጠቃለያ፦
ሀሳብ ሲመጣባችሁ ወደ መፍትሄ ቀይሩት። መስራት የምትችሉትን ስሩ፣ መለወጥ የማትችሉትን ግን ለአላህ (ሱ.ወ) ውሳኔ ስጡና ልባችሁን እረፍት ስጡት። ልባችንን ከጭንቀት አፅድተን፣ በሰከነ አእምሮ ከሚያስቡት፣ ሰበብ አድርሰው በአላህ ላይ ሙሉ ተወኩል ከሚያደርጉት ምርጥ ባሮቹ ያድርገን።

28/09/2026

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት (ጨፌ) ባካሄደው የ7ኛው የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ፣ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰይሟል።

በጉባኤው ወቅት የክልሉን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አዲስ መዋቅር እና አመራር የቀረበ ሲሆን፣ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክልሉን በኃላፊነት እንዲመሩ በይፋ ተሰይመዋል።

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

28/09/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቅርቡ የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አደረጃጀት ላይ ጉልህ ለውጥ እንደሚኖር ተሰማ። እንደ መንግስት አዲስ ፖሊሲና የትኩረት አቅጣጫ፤ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኮሚሽኖች፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች እና ኤጀንሲዎች ሊዋሃዱ፣ ስማቸው እና የስራ ድርሻቸው ሊቀየር፣ አሊያም ፈጽሞ አዳዲስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

ይህ አዲስ እቅድ ይፋ የሆነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል አስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።

በምክር ቤቱ የውሳኔ ሰነድ ላይ እንደተብራራው፤ በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 56 እና በምርጫ ህጉ መሰረት፣ በየአምስት ዓመቱ የሚደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ አዲስ የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት ማዋቀር ስለሚጠበቅ ይህ ርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በዚህም መሰረት በ2018 ዓ.ም የተካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የፌደራል መንግስቱን በአዲስ መልክ ለማደራጀት የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ በምክር ቤቱ ተጨማሪ ግብዓቶች ታክለውበት ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ተወስኗል።

በዚህም መሰረት አንዳንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሊዋሃዱ፣ ስማቸው እና የስራ ድርሻቸው ሊቀየር፣ አሊያም ፈጽሞ አዳዲስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።ኮሚሽኖች፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች እና ኤጀንሲዎችም እንዲሁ።

ይህ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) የደረሰው ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ሲያጸድቀው፣ መንግስት በአዲሱ መዋቅር ህግ መሰረት ሰፋ ያለ የሚኒስትሮች የካቢኔ ሹም ሽር ያካሂዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል።

27/09/2026

✨ ሰላም በኢስላም አስተምህሮ ✨
ኢስላም ለሰላም የሚሰጠው ቦታ ማዕከላዊና መሠረታዊ ነው፤ በነጥብ ሲጠቃለል፡
🔹 የቃሉ ትርጉም: "ኢስላም" እና "ሰላም" ከአንድ ስረ-ቃል የተገኙ ናቸው። "አስ-ሰላም" (የሰላም ባለቤት) ደግሞ ከ99ኙ የአላህ ስሞች አንዱ ነው።
🔹 የዕለት ተዕለት ሰላምታ: ሙስሊሞች ሲገናኙ የሚያቀርቡት "አስ-ሰላሙ አለይኩም" (ሰላም በእንተ ላይ ይሁን) የሚለው ጥሪ የሰላም አምባሳደርነታቸው መገለጫ ነው።
🔹 የሙስሊም ብያኔ: ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) "ሙስሊም ማለት ሰዎች ከምላሱና ከእጁ ሰላም የሆኑለት ሰው ነው" ብለዋል።
🔹 የውስጥ ሰላም: እውነተኛ የመንፈስ ዕረፍት የሚገኘው አምላክን በማስታወስ ነው ("አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ" — 13:28)።
🔹 ማህበራዊ ሰላም: በሰዎች መካከል ሰላምን ማውረድና ማስታረቅ በኢስላም ትልቅ ምንዳ ያለው አምልኮ ነው።
💡 በአጭሩ: ሰላም በኢስላም የጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪ፣ ከራስና ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በፍትህና በመልካምነት የመኖር ህያው መንገድ ነው!

Mohammed Umer Dilkamo

27/09/2026

(ዘ-ሐበሻ መረጃ) ብሌን ማሞ ለጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ይህን ጥያቄ አቀረበች፡ - "ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ላይ እያሳዩ ያለውን አቋም አጥብቀው ሲተቹ ቆይተዋል። ኤርትራ አሁን እየተጓዘችበት ያለውን መንገድ እንዴት ይገመግሙታል?"

የአምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ ምላሽ ይህን ይመስላል፡ የኤርትራ አመራር የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት አቅም ጠንቅቆ ያውቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያን ትዕግስት ሆን ብሎ መፈታተን የሚያስከትለውን አስከፊ መዘዝ በሚገባ ይረዳል።

"በኤርትራ አቋም ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ቅራኔ አለ። ለኤርትራ ሉዓላዊነትን እንደ ትልቅ መርህ እያነሱ፣ ያንንኑ መርህ በጎረቤት ሀገር ላይ መጣስ አይቻልም። ዓለም አቀፍ ድንበር ጥሳችኋል፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በወታደራዊ ኃይል ጣልቃ ገብታችኋል፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሉዓላዊነትም ደፍራችኋል። ሉዓላዊነት እንደየፍላጎቱ የሚመረጥ እና የሚለጠጥ መርህ አይደለም።

"ኢትዮጵያ የችግሩን ስር መሰረት፣ የተሳተፉትን ተዋንያን እና በስተጀርባ የሚራመደውን ስውር ፍላጎት ቁልጭ አድርጋ ታውቃለች። ግጭቱን ማን እንደጠነሰሰውና የማን ስትራቴጂካዊ ጥቅም እየተስተናገደበት እንደሆነ አልተምታታብንም። አሁን እነዚህን አላማዎች በውክልና (በተላላኪዎች) ለማሳካት የሚደረገው ጥረት ይህንን ሃቅ አይቀይረውም። የሚቀይረው የግጭቱን መልክ ብቻ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ የማያወላዳ እውነት ላስምርበት እወዳለሁ፤ ትግራይ፣ አማራ ወይም አፋር የኤርትራ የጦርነት አውድማ ይሆናሉ ተብሎ ሊታሰብ አይገባም። አሁን ያለው አካሄድ ገፍቶ ወደ ለየለት ግጭት የሚያመራ ከሆነ፣ መዘዙ በመጨረሻ የኤርትራን ምድር ማንኳኳቱ አይቀርም። ይህ የወታደራዊ ሳይንስ ህግ እንጂ የቃላት ፉከራ አይደለም። የሌላን ሀገር ትዕግስት ደጋግሞ የሚፈታተን መንግስት፣ ትዕግስትም ልክ እንዳለው ሊገነዘብ ይገባል።

"ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የጦር ሰው እንደመሆናቸው ይህንን መርህ በሚገባ ይረዱታል። ጦርነት አንዴ ከተለኮሰ በኋላ፣ አቅጣጫው ሁልጊዜ በጀማሪዎቹ ቁጥጥር ስር እንደማይውል ያውቃሉ። ኢትዮጵያ ትዕግስትን የመረጠችው፣ ትዕግስት የራሷን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ስለሚያገለግል ነው። ይህ ግን የአቅም ማጣት ወይም የቁርጠኝነት ጉድለት ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም።

"ኤርትራ ነገሮችን ወደ ለየለት ግጭት ለማስፋት ከመረጠች፣ ለውሳኔዋ መዘዝ ራሷንም አሳልፋ ለመስጠት መዘጋጀት ግድ ይላታል።"

የእናንተን አስተያየት ደግሞ በኮመንት እንጠብቃለን።

27/09/2026

ታሪካዊ ድል በታሪካዊቷ የዋግ ሹሞች ሀገር — ሰቆጣ!

​በዋግ-ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችው ታሪካዊቷ ሰቆጣ ከተማ፣ በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ትልቅ ታሪካዊ ድል ተመዝግቧል።

​ሀገር አፍራሽ እና የውጭ ጠላቶች ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት ቡድን፣ ጽንፈኛው የፋኖ አካል እና ሌሎች አጥፊ ኃይሎችን አደብ ማስገዛት መቻሉን ተከትሎ፤ በከተማዋ ሰላም ሰፍኗል።

​ይህን ታላቅ የድል ምዕራፍ ተከትሎ የሰቆጣ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የተሰማቸውን ወሰን የሌለው ደስታና አክብሮት አደባባይ በመውጣት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

​ድል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት
ፕረዚደንት ጥላሁን ከበደ አድናቂዎች ጉሩፕ-President Tilahun kebede Fan Group
የማንሰራራት ዘመን በኢትዮጵያ
Digital Ethiopia 2030

27/09/2026

የናይልና የቀይ ባሕር ስትራቴጂክ ፎረም በተያዘው ወር ወደ ተግባር ይገባል
++++++++++++++

- የኢትዮጵያን ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ መብቶች ለማስከበር የተቋቋመው የቀይ ባሕርና የናይል
ስትራቴጂክ ፎረም ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ እንደሚገባ የፎረሙ ሰብሳቢ አበበ ገመቹ (ዶ/ር) ገለፁ።

የፎረሙ ሰብሳቢ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የፎረሙ ምሥረታ መነሻና መሠረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታና ታሪካዊ አጋጣሚዎች ያገናዘበ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ እጅግ የሚያሳዝንና ኢ-ፍትሐዊ መሆኑን ለዓለም ለማስገንዘብ ፎረሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ምሁራን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሙግት ማቅረብና የፖሊሲ ግብአቶችን ማመንጨት እንዳለባቸው በመታመኑ ፎረሙ ሊቋቋም ችሏል። ይህንን መሠረታዊ ሐሳብ በመያዝ ሰባት አባላት ያሉት የመሥራች አባላት ኮሚቴ ተመርጦ የፎረሙን አወቃቀር ወደ ተግባር የመቀየር ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ የባሕር በር እንድታጣ በመደረጉ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ መጣሉን ያነሱት አበበ (ዶ/ር)፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት ለመቀልበስና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት ምሁራን ሊደግፉ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሀገር ሆና ሳለ ከሩቅ የመጡ ሀገራት ወታደራዊ ቤዝ እና የንግድ ቀጠና አድርገው ሲጠቀሙበት፣ ኢትዮጵያ ግን እንደ «ሬድ ሲ ካውንስል» ባሉ ስብስቦች አባል እንዳትሆን ተደርጋ መገለሏ የሚያስቆጭ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዓባይ ወንዝ 86 በመቶ የውኃ አስተዋጽኦ እያደረገች መጠቀም ያልቻለች ቢሆንም የዓባይን ግድብ በመገደቧ ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር ችላለች ያሉት ዶክተሩ፤ በዚህም ዓባይን ለዘፈንና ለግጥም ብቻ ሳይሆን ለልማት በማዋል ለትውልድ የሚተላለፍ ዘላቂ ሀገራዊ ሀብት መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

ፎረሙ አስፈላጊ ሰነዶቹን አዘጋጅቶ ለኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ማመልከቻ ማስገባቱን ጠቅሰው፤ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓም ድረስ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ወደ 11 የሚጠጉ ዓላማዎች ያሉት ይህ ፎረም፤ ተደራራቢ ጫናዎችን፣ ታሪካዊና ቴክኖሎጂካዊ ዳራዎችን በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ለመሞገትና በናይል ወንዝ ዙሪያ የቀደሙ የቀኝ ገዢ ውሎችን ለመቀልበስ ይሰራል። የናይልና የቀይ ባሕር ጉዳይ ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ መንግሥት ወይም ቡድን የሚተው ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል፡፡

የፎረሙ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ሁለት ወራት ገደማ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ የመጀመሪያው ውይይት መካሄዱን ገልፀዋል። የፎረሙን ጥናታዊ ውይይቶችና የፓናል ውይይቶች አዲስ አበባ አመራር አካዳሚና የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በርካታ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ እየደገፉት ይገኛሉ ብለዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን

#አባይ #ኢትዮጵያ #ዲፕሎማሲ

27/09/2026

የጦርነት ሜዳው ኤርትራ ይሆናል-ጄኔራል ባጫ‼️
የኤርትራ አቋም በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ትግራይ፣ አማራ ወይም አፋር የኤርትራ የጦር ሜዳ አይሆኑም-ጄኔራል ባጫ ደበሌ‼️
የአሁኑ አካሄድ ወደ ሙሉ ጦርነት ከሄደ ጦርነቱ ወደ ኤርትራ ግዛት መግባቱ አይቀርም ሲሉ ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከሆርን ሪቪው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።
ይህ ተራ ንግግር ሳይሆን የወታደራዊ አመክንዮ ጉዳይ ነው ያሉት ጄኔራሉ የሌላ ሀገርን ሉዓላዊነት በተደጋጋሚ የሚፈትን መንግስት ትዕግስትም ልክ እንዳለው መረዳት አለበት ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወታደራዊ ሰው ናቸው እና ይህንን መርህ ይረዳሉ። ጦርነቱ አንዴ ከተጀመረ፣ ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ እንደሚችል፣የኤርትራ ግዛት ሊቀየር እንደሚችል ያውቃል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ትዕግስትን ተግባራዊ አድርጋለች ምክንያቱም ትዕግሥት ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት ስለሚጠቅማት በማሰብ ነው። ይህ የአቅም ማጣት ወይም የውሳኔ እጥረት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም።
በእኔ እሳቤ የፅምዶ መነሻ መቀሌ ወይም አስመራ ሳይሆን ካይሮ ነው ብለዋል።

Category

Website

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ለባድ Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.