Salem Magazine

Salem Magazine

Share

Celebrating 10 Years.

Salem Media (ሳሌም) is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.

03/10/2026
30/09/2026

የአሜሪካ የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት (ICE) እስር ቤት ያለችውን ወጣት ኢትዮጵያዊት ኤግላ ጥላሁንን በዋስ ለማስፈታት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ተጀመረ።

👉 FOLLOW US
https://youtu.be/XaONQtu8O84?is=yOswNfPNOZWOzIWK

በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ነዋሪ የሆነችውን ወጣት ኤግላ ጥላሁንን፣ በሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ ከሚገኘው የኢሚግሬሽንና ጉምሩክ አስፈጻሚ (ICE) እስር ቤት በዋስ ለማስለቀቅ የታለመ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በጎ ፈንድ ሚ ድረ-ገጽ ላይ ተጀምሯል።

ከታውሰን ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ ጤና ሳይንስ ዘርፍ ባሳለፍነው ግንቦት ወር የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው ወጣት ኤግላ ጥላሁን፣ ለዕረፍትና ለጉብኝት ወደ ካሊፎርኒያ ግዛት ባቀናችበት ወቅት በሳን ዲዬጎ ከተማ ዉስጥ በፌዴራል የኢሚግሬሽን የደህንነት አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሏ ይታወቃል።

የኤግላ ጓደኛ የሆነችውና በኮሎምቢያ ሜሪላንድ ግዛት ነዋሪ በሆነችው ማህሌት ኃይሉ የተከፈተው ይኸው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጽ እንደሚያሳየው፣ ወጣቷን ከእስር ለማስፈታት መንግሥት የሚጠይቀውን የዋስትና ማስያዣ ቦንድ ለመክፈልና ወደ ሜሪላንድ እንድትመለስ ለማድረግ የ30 ሺህ ዶላር የማሰባሰብ ግብ ተቀምጧል።

ዘመቻው በተጀመረ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ530 በላይ ለጋሾች ከ30 ሺህ ዶላር በላይ ሙሉ ለሙሉ ለማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን፣ አሁንም ገንዘብ የማሰባሰብ ሂደቱ ከ30 ሺህ ዶላር በላይ ቢያልፍም ህዝቡ ገንዘብ ማዋጣቱን አሁንም ቀጥሏል።

የማኅበረሰቡ አባላት ወጣቷን ወደ ቤተሰቦቿ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ የዘመቻው አዘጋጆች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ወጣት ኤግላ ጥላሁን በቁጥጥር ሥር የዋለችበት ዝርዝር የኢሚግሬሽን ምክንያት እስካሁን በይፋ አልተገለጸም።

በICE ማቆያ እስር ቤት የሚገኙ ታሳሪዎች ፣ ለጠበቃ የሚከፍሉት ገንዘብ ስለሌላቸው እና በዋስ እንዲፈቱ የሚያስችል አቅም ስለሌላቸው፣ በዚህም ምክንያት በርካታ ስደተኞችና ቤተሰቦቻቸው ለሕግ ባለሙያ ክፍያና ለዋስትና ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በዲጂታል አማራጮች ለማሰባሰብ እንደሚገደዱ የዘርፉ ገምጋሚዎች ይገልጻሉ።

የGoFundMe ሊንክ እና ዝርዝር መረጃው፦
https://gofund.me/0a2af59e7

የዜናውን ዝርዝር ሊንኩን በመጫን ያገኛሉ
👉https://youtu.be/XaONQtu8O84?is=5eeZyA3wF7Src4Mn

29/09/2026

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዛሃራ የብራድ ፒትን ስም ከስሟ በህግ ሰረዘች!

Follow us
https://youtu.be/XaONQtu8O84?is=yOswNfPNOZWOzIWK

በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዛሃራ ጆሊ እና በሆሊውዱ ዝነኛ ተዋናይ ብራድ ፒት መካከል ያለው የቤተሰብ ትስስር በህግ መቋረጡ ተረጋገጠ። የዓለምን ትኩረት የሳበውና ለዓመታት የዘለቀው የአንጀሊና ጆሊ እና የብራድ ፒት የፍቺ ውዝግብ፣ አሁን ላይ በልጆቻቸው ህጋዊ ውሳኔ አዲስ ምዕራፍ ይዟል።

የሆሊውድ ዝነኛ ጥንዶች አንጀሊና ጆሊ እና ብራድ ፒት ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ያሳደጓት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዛሃራ ማርሊ ጆሊ፣ የአባቷን መጠሪያ “ፒት” የሚለውን የቤተሰብ ስም ከማንነቷ ላይ በህግ እንዲሰረዝላት ያቀረበችው አቤቱታ በሎስ አንጀለስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙሉ ዕውቅና አግኝቷል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ፣ ቀደም ሲል “ዛሃራ ማርሊ ጆሊ-ፒት” ተብላ ትጠራ የነበረችው ወጣት፣ ከአሁን በኋላ ህጋዊ ስሟ “ዛሃራ ማርሊ ጆሊ” ብቻ ሆኖ እንዲመዘገብ ወስኗል።
የ21 ዓመቷ ወጣት ዛሃራ፣ ከዚህ ቀደም በምትማርበት ኮሌጅ ውስጥ በተካሄደ ይፋዊ ስነ-ስርዓት ላይ ራሷን “ዛሃራ ማርሊ ጆሊ” በማለት በማስተዋወቅ ከአባቷ መራቋን በተግባር አሳይታ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ጉዳዩን ፍጹም ህጋዊ መልክ አስይዛዋለች።

ይህ በአባታቸው ላይ የተወሰደው ጠንካራ እርምጃ በዛሃራ ብቻ የተገደበ አይደለም። ከእሷ በተጨማሪ ሺሎህ፣ ማዶክስ እና ቪቪየን የተባሉት ወንድም እና እህቶቿም በተመሳሳይ መልኩ “ፒት” የሚለውን የአባታቸውን ስም ከማንነታቸው ላይ ህጋዊ በሆነ መንገድ አስወግደዋል።

የብራድ ፒት እና የአንጀሊና ጆሊ የፍቺ እና የልጆች አስተዳደግ ውዝግብ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ ልጆቹ ከአባታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ የእናታቸውን ወገን መምረጣቸውን ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በግልጽ ያሳያል።

👉https://youtu.be/kCgRJSYzqjU?is=hifMB6oeP4P3mspZ

29/09/2026

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የአሜሪካ ወታደር ዶ/ር ሜሪ አምባቸው

👉 PLEASE FOLLOW US
https://youtu.be/nyomuofRre8?is=SqrKcjPvCMdNEjD6

ዶ/ር ማርያማዊት (ሜሪ ) አምባቸው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ ሲሆን፣ በመቀጠልም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በዌስት ቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ህክምና ትምህርት ቤት በ2009 በስኬት አጠናቀው የጥርስ ቀዶ ጥገና ዶክተር ሆነዋል።

ከትምህርት ገበታቸው እንደተመረቁ ለአሜሪካ ጦር ሰራዊት በመቀላቀል ለ7 ዓመታት ያህል በንቁ ወታደራዊ የጥርስ ህክምና መኮንንነት አገልግለዋል። በቆይታቸውም ላሳዩት ከፍተኛ የሙያ ብቃትና የላቀ የህክምና አፈጻጸም በርካታ የወታደራዊ ምስጋና ሜዳሊያዎችን ተሸልመዋል።

ዶ/ር ማርያም በአሁኑ ወቅት በሰሜን ካሮላይና ግዛት ፋየቴቪል ከተማ ውስጥ ዴንታል ላቭ የተሰኘ የራሳቸውን ዘመናዊ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ባለቤት ናቸው። በሙያቸው እጅግ የተመሰከረላቸው፣ ከተራ የጥርስ እጥበት ጀምሮ እስከ ውስብስብ የጥርስ ተከላ እና የጥርስ ውበት ህክምናዎችን በደግነትና በሩህሩህነት ያከናውናሉ።

በተጨማሪም በአሜሪካ የጥርስ ህክምና ማህበር (ADA) እና የሰሜን ካሮላይና የጥርስ ህክምና ማህበር አባል ከመሆናቸውም በላይ፣ ከጥቂት የጥርስ ሐኪሞች የሚሰጠውን የክብር ፌሎሺፕ ማዕረግ አግኝተዋል።

ዶ/ር ማርያም አምባቸው ከቀን ተቀን የህክምና ስራቸው ውጭ በትርፍ ጊዜያቸው ህብረተሰባቸውን በበጎ አድራጎት ያገለግላሉ። በየወሩ በተለያዩ ክሊኒኮች ነፃ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፣ ህጻናትን ስለ ጥርስ ጤና አጠባበቅ እና ስለ መሪነት ብቃት (Leadership skills) በበጎ ፈቃደኝነት ያስተምራሉ።

በህይወታቸውም “የሚያበረታታኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵስዩስ 4:13) የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል መመሪያቸው እንደሚያደርጉት ይገልጻሉ።

https://youtu.be/7Kh7x9dYGfo?is=3W1sd8U577UKnfO-

28/09/2026

✨ 🇪🇹 THE ETHIOPIAN FALL FESTIVAL IN ALEXANDRIA!
🇪🇹 ✨የኢትዮጵያ ፎል ፌስቲቫል በአሌክሳንደሪያ 🇪🇹 ✨

Mark your calendars! We would love for you to join us as we celebrate community, culture, and connection at this year’s Ethiopian Fall Festival! 💛💚❤️ Bring your family and friends to experience rich traditions, amazing entertainment, and great networking opportunities. There is truly something for everyone!

📅 Sunday, October 11, 2026
⏰ 1:00 PM – 7:00 PM
🎪 Chinquapin Park
📍 3210 King St, Alexandria, VA 22302

✨ WHAT TO EXPECT:
🎶 Live Ethiopian cultural music & entertainment
🛍️ Cultural vendors & artisan markets
☕ Traditional Ethiopian coffee ceremony
🎉 Family-friendly activities & networking
🤝 Community resource tables & exhibits
📚 Local community service
🎭 Fashion Show
⚽️ Soccer Tournament

Admission: $10 - Ages 13 & Up
Age 12 & Under FREE and memories are guaranteed. Come celebrate with us! 🎉

👇 TAG a friend in the comments who needs to come with you!...

𝐄𝐂𝐒𝐀𝐂 | community Empowerment + Advocacy 𝐄𝐂𝐒𝐀𝐂 | community Empowerment + Advocacy 𝐄𝐂𝐒𝐀𝐂 | community Empowerment + Advocacy

28/09/2026

ከ7 የተለያዩ ሴቶች፣ 11 ልጆችን የወለደው ሮቤርቶ ካርሎስ ሀብቱን በሙሉ ማጣቱን ገለፀ።

ታዋቂው የዓለም ዋንጫ አሸናፊው፣ የሪያል ማድረድ የእግር ኳስ ክለብ እና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር ተከላካይ ሮቤርቶ ካርሎስ በእግር ኳስ ዘመኑ ያፈራውን ከፍተኛ ሀብት በግል ችግሮች ምክንያት በአንድ ጀምበር ማጣቱን በቁጭት ገለጸ።

ተጫዋቹ በስፖርታዊ ህይወቱ 133 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመት እጅግ ግዙፍ ሀብት አፍርቶ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም የጨዋታ ችሎታው ጣራ በነካበት ወቅት በሳምንት 85,000 ፓውንድ ይከፈለው እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም ካርሎስ አሁን ላይ ካፈራው አጠቃላይ ሀብት ውስጥ 99 በመቶ ያህሉን ማጣቱን ይፋ አድርጓል። “ባንክ አካውንቴን ባዶ ካደረጉብኝ ሰዎች ጋር ችግር ነበረብኝ። በወኪሎች እና በቤተሰብ ጉዳዮች ምክንያት በእግር ኳስ ያገኘሁትን 99 በመቶ አጥቻለሁ። ስህተቶችን ሠርቻለሁ፣ ለዚህም ነው ወጣት ተጫዋቾች እኔ የሠራሁትን ተመሳሳይ ስህተት እንዳይሠሩ የምጠይቀው።

ካርሎስ ይህ ሁሉ ንብረቱ የጠፋበትን አስደንጋጭ ምሽት ሲያስታውስ፣ “በአንድ ሐሙስ ዕለት እኩለ ሌሊት ላይ ተኛሁ፣ አርብ ዕለት ደግሞ መኖራቸውን እንኳን የማላውቃቸውን በርካታ ሰነዶች ተቀበልኩ። አጠቃላይ ታሪኬን ያጣሁት ያኔ ነበር” ብሏል።

ለዚህ ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ዋነኛ መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የቤተሰብ ምስቅልቅል አንዱ መሆኑ ተነግሯል። የ53 ዓመቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ የ15 ዓመታት ትዳሩ በ2025 የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህ የፍቺ ክስ ከፍተኛ ሀብቱን ለከባድ የንብረት ክፍፍል ውጊያ ዳርጎታል።

የግል ህይወቱ ውብስብ የነበረው ካርሎስ፣ ከሰባት የተለያዩ ሴቶች 11 ልጆችን መውለዱን የገለጸ ሲሆን፣ በቅርቡ በ2026 መጀመሪያ ላይ ደግሞ ሶሄይላ ታሂሪ ከተባለችው ሦስተኛ ሚስቱ ጋር በድጋሚ ጋብቻ መመስረቱ ታውቋል።

ከማስታወቂያ፣ ከደሞዝ ፣ ወደ ክለቦች ከሚያደርጋቸው ዝውውሮች ያገኘውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ፣ ዘላለም የሚያልቅ አይመስለኝም ነበር ያለዉ ሮቤርቶ ካርሎስ ፣ ለዚህ ሁሉ የደረገው የተሳሳተያኗኗር ዘይቤው እንደነበረ በቁጭት ይናገራል።

የቀድሞው ኮከብ አሁን ላይ የደረሰበትን የሀብት መክሰር ለወጣት ተጫዋቾች እንደ ትልቅ ማስጠንቀቂያና መማሪያ ሊሆን እንደሚገባ እየመከረ ይገኛል።

https://youtu.be/kCgRJSYzqjU?is=hifMB6oeP4P3mspZ

28/09/2026

እባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ሁልጊዜም ቢሆን ፖለቲካዊ መፍትሔ አለ ፤ ሰላም ደግሞ ምርጡ መድኃኒት ነው ።” ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ በእሁድ የእረፍት ጊዜያቸው ከልጅ ልጃቸው ጋር ያሳለፉትን ሰላማዊ የከሰዓት በኋላ ጊዜ አስመልክቶ፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በጦርነትና በግጭት ውስጥ ላሉ ቤተሰቦችና ሕፃናት ያላቸውን አጋርነትና አሳሳቢ ስሜት ገልጸዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደገለጹት፣ ከልጅ ልጃቸው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲጫወቱና ሲስቁ የነበረው ተራ የሚመስል ቅጽበት ትልቅ ስጦታ መሆኑን አስታውሷቸዋል። ይሁን እንጂ ይህ በቤት ውስጥ የሚሰማቸው ደስታና ምስጋና፣ በዓለም ዙሪያ በጦርነት ጥላ ስር ለሚገኙ፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ለሚታገሉ ወላጆች፣ ጥለዋቸው ለተሰደዱ ቤቶችና ያለ ዕድሜያቸው ለተቀጠፉ የሕፃናት የልጅነት ጊዜያት ካላቸው ጥልቅ ሃዘን ጋር አብሮ እንደሚጓዝ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በግጭት ውስጥ ለሚገኙ የዓለም መሪዎች ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ፦ “እባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ሁልጊዜም ቢሆን ፖለቲካዊ መፍትሔ አለ። ሰላም ምርጡ መድኃኒት ነው” ብለዋል። በየትኛውም ቦታ የሚገኝ እያንዳንዱ ሕፃን ከፍርሃት ነፃ የሆነ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኝታ ቦታ፣ የሚጨብጠው እጅ እንዲሁም የልጅነት ነፃነቱን የሚያገኝበት ሰላማዊ ዓለም እንዲኖረው ምኞታቸውን ገልጸዋል።

https://youtu.be/7Kh7x9dYGfo?is=qpeU6DzVVt7POmK8

28/09/2026

ትልቅነት የሚለካው ሌላውን በትከሻህ ገፍተህ ስትጥል ሳይሆን፣ ዝቅ ብለህ የወደቀውን ስታነሳ ነው።

ሰብዕናህን ከፍ የሚያደርገው የአምባህ ስፋት ወይም የኑሮህ ቅንጦት ሳይሆን፣ የሐሳብህ ልዕልናና የልብህ ታላቅነት ነው። ከፍታ ማማ ላይ ቆመህ ዓለምን ቁልቁል የምትንቅ ከሆነ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ዓለምም መልሳ በትዝብት ትንቅሃለች።

በታላቅ ቤትህ ጥላ ስር ሆነህ ትንሿን ጎጆ በታናሽነት ካየሃት፣ ዘመን ተገልብጦ በአንተ ላይ የሚፈርድበት ዕለት ሩቅ እንዳልሆነ አትዘንጋ። በማዕረግህና በስፍራህ የምትጸናው፣ በቦታው ልክ በሚመጥን ትህትና እና በጥልቅ ዕውቀት ስትታገዝ ብቻ ነውና አስተውል!

ይህን ዘላለማዊ ሰብዓዊ እውነት በተግባር መስከረው ካለፉ የዓለማችን ብርቅዬ ዕንቁዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ የቁም ነገር፣ የክብር እና የትህትና ተምሳሌት የሆነው የሩጫው ንጉሥ ኃይሌ ገብረሥላሴ ግንባር ቀደሙ ህያው ምስክር ነው።

ኃይሌ ገብረሥላሴ በበርሊን ማራቶን ላይ መሮጥ ብቻ ሳይሆን፣ በደማቅ ቀለም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው የጻፈው። ከ2006 እስከ 2009 ዓ.ም በተከታታይ አራት ዓመታት ሙሉ የድሉን ዘውድ በመድፋት የዓለምን ቀልብ መግዛት ችሏል። በተለይም በ2008 ዓ.ም የገዛ ራሱን የዓለም ሪከርድ በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በማሻሻል፣ በበርሊን አደባባዮች ላይ የሰው ልጅ የጽናት ጥግ ምን ያህል ከፍታ እንዳለው አሳይቷል።

ይሁን እንጂ የኃይሌ የበርሊን ታላቁ ድል ያገኘው የወርቅ ሜዳሊያ ወይም ያስመዘገበው አስገራሚ ሰዓት ብቻ አልነበረም፤ ከሁሉም በላይ የሰዎችን ልብ የገዛው የእሱ የማይደበዝዝ ሰብዓዊነት እና ወደር የለሽ ትህትናው ነበር።

የኃይሌ ማራኪ ፈገግታ፣ ቅንነትና አስተዋይነት ከተለያዩ የዓለም ማዕዘናት የመጡ ህዝቦችን በአንድ ፍቅር አስተሳስሯል። ኃይሌ የቱንም ያህል የዝና ማማ ላይ ቢወጣም፣ በዓለም ህዝብ ልብ ውስጥ ዘላቂ መቅደስ እንዲኖረው ያደረገው ንጹህ ማንነቱ፣ ዕውቀቱና ትህትናው መሆኑን አስመስክሯል። እርሱ ከፍታ ላይ ሆኖ ዓለምን በታናሽነት ቁልቁል አላየም፤ ይልቁንም ዓለም አብራው ወደ ድል ከፍታ እንድትወጣ የብርሃን መንገድ አሳይቷል እንጂ።

ትላንትም ያደረገው ይህንን ነው የሀገሩ ልጅ ትዕግስት ማራቶኑን አሸንፉ ስትወድቅ ፣ አንስቶ ፣ አይዞሽ ብሎ፣ እንባዋን አብሶ ፣ እስከጥግ ድረስ የስዕብናውን ከፍታ ለአለም አሳይቷል ።

https://youtu.be/kCgRJSYzqjU?is=hifMB6oeP4P3mspZ

25/09/2026

Ethiopiaian Excellence Award በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆችን፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በሳይንስ ስነ-ጥበብ እና ንግድ ዘርፎች ለወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ያበረከቱትን ጉልህና ፋና ወጊ አስተዋፅዖ ለመዘከር፣ ለማበረታታት፣ እውቅና ለመስጠትና ለቀጣዩ ትውልድ አርአያነታቸውን ለመዘከር በመጪው November 01, 2026 ዓ/ም በዋሽንግተን ዲሲ በተለያዩ ዘርፎች ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊሸለሙ ነው።

ይህን ሽልማት ያዘጋጀው መቀመጫውን አሜሪካን ሐገር ያደረገው Golden Nile Media and Event የተባለ በኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ከማንኛውም የዘር፣ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ወገንተኝነት ነጻ የሆነ ድርጅት ነው።

በዘንድሮው መርሃ-ግብር የክብር የሽልማት በተለያዩ ዘርፎች ከሚያገኙት መካከል አርቲስት ፀጋዬ እሸቱ፣ ወ/ሮ ጤናዳም ይልማ ፣ አቶ ሽዋ ኢታና፣ ወ/ሮ ቆንጂት አረጋ፣ አቶ ኤርሚያስ ብርሃነ እና ወ/ሪት ገነት ሲዳ ይገኙበታል ።

ስፕሪንግ ፊልድ በሚገኘው ወተር ፍሮንት ኤቨንት ሴንተር አዳራሽ ዉስጥ በደመቀ ሁኔታ በሚካሔደው ዝግጅት ላይ በርከት ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበረሰብ መሪዎችና የተለያዩ የክብር እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ይታደመብታል።

👉https://youtu.be/7uqfmDl9Wsw?is=b1VFBNkeeS4wEbMP

Telephone

Address


50 S Pickett Street
Addis Ababa
22304

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Salem Magazine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.