To Daye Wollo Press

To Daye Wollo Press

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from To Daye Wollo Press, Health/Beauty, Adis Abeba, Addis Ababa.

25/03/2026

የኤርትራ ወታደራዊ ልዑካን መቐለ መግባታቸው ተነገረ‼

የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በየካቲት ወር መጨረሻ ቀናት መቐለ መግባታቸውን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገበ።

በብሪጋዴር ጄኔራል እዮብ ፋሰሃዬ የተመራው ይህ ልዑክ፣ ከመቐለ መግባቱም ባለፈ ከትግራይ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ (ማንጁስ) ጋር መወያየቱ ተመልክቷል።

ይህ ስብሰባ መካሄዱ የተነገረው፣ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የፌዴራል መንግሥቱን የኮሪደር ልማት የሚተች መግለጫ ባወጣበት ወቅት መሆኑ ዘገባውን አነጋጋሪ አድርጎታል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኤርትራ መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል።
Mereja = Wasu Mohammed

Photos from To Daye Wollo Press's post 03/03/2026

ሰበር 🔥🔥🔥🔥​🇮🇷

በኢራን የአባት ስልጣን ወደ ልጅ ተላለፈ!
በኢራን ለረጅም አመታት በስልጣን ላይ የነበሩትን አያቶላ አሊ ካሜኒን በመተካት ልጃቸው ሞጅታባ ካሜኒ አዲሱ የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪ (Supreme Leader) ሆነው መመረጣቸው ተዘገበ።

የኢራን የሊቃውንት ምክር ቤት ሞጅታባ ካሜኒን በአባታቸው ቦታ እንዲተኩ በምስጢር መርጧቸዋል።

ይህ ውሳኔ እንዲጸድቅ የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) ከፍተኛ ግፊት ማድረጉ ተገልጿል።

ኢራን ከ1979 አብዮት በኋላ የዘር ውርስ ስልጣንን (Monarchy) አውግዛ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ስልጣኑ ከአባት ወደ ልጅ መተላለፉ በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ውዝግብ ሊያስነሳ እንደሚችል ተገምቷል።

* የሞጅታባ ማንነት አዲሱ መሪ ሞጅታባ ካሜኒ እስካሁን በይፋዊ ስልጣን ባይታወቁም፣ ከበስተጀርባ ሆነው የአብዮታዊ ዘበኛውን እና የሀገሪቱን የደህንነት መዋቅር ሲዘውሩ እንደነበር ይነገራል።
ይህ ለውጥ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ውጥረት ያለው ተፅእኖ ከባድ መሆኑን ተንታኞች ይገልፃሉ።
Stay connected with Ethio info

03/03/2026

ቀጣይ የኢትዮጵያ ጠ/ ሚ የመሆን ከፍተኛ እድል ያላት ሴት ኢትዮጵያዊት ፓለቲከኛ/ ባትሆንም እንኳ
አንድ እርምጃ ወደፊት አሰተሳስብ ያለት ።እንዳቺ ያለ ኢትዮጵያ ታብዛልን ውጤትሸም ለሀገርሸ ይመር

Photos from ESAN TV ኢሳን ቲቪ's post 03/03/2026
03/03/2026

"ሻዕቢያ በድጋሚ ከዚህ በውሃላ ከሞከረን መጨረሻው ይሆናል!"

ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር)

01/03/2026

ሰበር ዜና‼️ የሆርሙዝ የባህር በር ተዘጋ!

ኢራን የሆርሙዝ የባህር መስመርን (Strait of Hormuz) አሁን ዘጋች።

ይህ ድርጊት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል ተብሎ እየተሰጋ ነው።

👉 የአውሮፓ ህብረት የባህር ኃይል ኦፊሰር ባረጋገጠው መሰረት፣ የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ የንግድ መርከቦች የባህር በሩን ማለፍ "አልተፈቀደም" ሲል አግዷል።

በአሁኑ ሰዓት በባህረ ሰላጤው የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንቅስቃሴያቸውን አቁመዋል።

👉 ይህ መስመር የዓለም የነዳጅ አቅርቦት ዋነኛ መንገድ ነው። 20% የሚሆነው የዓለም የነዳጅ አቅርቦት በዚህ መስመር ያልፋል።

መዘጋቱ የነዳጅ ዋጋ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል።

👉 ውጥረቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሲሰጡ ነበር፤ አሁን ግን ያ ስጋት ወደ እውነት ተቀይሯል።

21/02/2026

ደቡብ ወሎ ዞን ወረዳወች አቀማመጥ

Photos from To Daye Wollo Press's post 27/01/2026

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ስምምነት
ጠላትን የሚያንቀጠቅጥ ወዳጅን ደግሞ በኩራት የሚያስፈነድቅ ታላቅ የምስራች!

ኢትዮጵያዊነት ማለት ታሪክን ሰርቶ ማሳየትና ሁልጊዜም በአሸናፊነት ከፍታ ላይ መገኘት መሆኑን ዓለም ዳግም አረጋግጣለች። በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጸመው ያ ታሪካዊ ወታደራዊ ስምምነት ዛሬ ወደ መሬት ወርዶ በተግባር መታየት ጀምሯል።

ይህ ጥምረት ለቀጣናው ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚሰጠው መልዕክት አንድና ግልጽ ነው! "ኢትዮጵያን መንካት እሳትን መጫወት ነው!" በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታነጸውና በሰለጠነ የሰው ኃይል የፈረጠመው ጦራችን፣ አሁን ደግሞ ከዓለማችን ግዙፍ ኃይል ጋር በመጣመር የማይደፈር፣ የማይበገርና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያስከብር የጥንካሬ ማማ ሆኗል።

🌟ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በፈጠረችው በዚህ ታላቅ ወታደራዊና ቴክኖሎጂያዊ ትብብር አማካኝነት፣ ለዘመናት የነበራትን ቀጣናዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በይበልጥ መልሳ አጠናክራለች። ይህ ስኬት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልህና ቆራጥ አመራር የተገኘ ሲሆን ሀገራችን ለደህንነቷና ለሉዓላዊነቷ የሚያሰጋትን ማንኛውንም ኃይል በዘመናዊ መንገድ ለመመከትና ለመደምሰስ ሙሉ ዝግጁ መሆኗን ለዓለም ያበሰረችበት የኃይል መግለጫ ነው።
በቢሾፍቱ ግቢ የታየው የቴክኖሎጂ ልዕልና ኢትዮጵያ ለቀጣናው ስጋት ለሆኑት የሽንፈት አዋጅ ለወዳጆቿ ደግሞ የድል ብስራት መሆኗን አረጋግጧል። በአዲሱ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ክብሯን ጠብቃና ጠላቶቿን አሳፍራ የታላቅነት ማማ ላይ መውጣቷን ዓለም ዛሬ በትህትና አይታለች!

Photos from To Daye Wollo Press's post 23/01/2026

ሱ 35 ጀት ለኢትዮጵያ አድስ ሉአላዊነት ..❗️

ኢትዮጵያ አለም ላይ የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ስሪት የሆነውን ሱ 35 ጀት ከሩስያ መግዛቷ ተሰማ………

ይህን እጅግ አስደማሚ ጀት ኢትዮጵያ መግዛቷ እጅግ ይደንቃል!! ወደ 6 የሚሆኑ ሱ-35 ጀቶችን ጀግናው የኢትዮጵያ አየር ሀይል በቅርቡ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም አየር ሀይሉን ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚያሰልፈው ታሪካዊ ግዢ ነው። በኢትዮጵያ ሰማይ ላይም እነዚህን በራሪ አናብስት ሲወነጨፉ በቅርቡ እናያለን።

ኢትዮጵያ ካሁን በፊት ከራሺያ የገዛቻቸውን Su-27 ጀቶች በ su-35 ለመተካት በማቀድና ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በማሰብ ግዢው መፈፀሙ ተገልጿል።

Photos from To Daye Wollo Press's post 23/01/2026

በምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት በምስጢራዊነቱ እና በታማኝነቱ የሚታወቀው የኤርትራ የስለላ መዋቅር ፣ ከውስጥ እየተሸረሸረ እና አባላቱ ወደ ኢትዮጵያ የደህንነት መዋቅር እየገቡ መሆኑን አንድ አዲስ የትንታኔ ሪፖርት አጋለጠ። "ሆርን ሪቪው" ዛሬ ባወጣው እና ጥልቅ የደህንነት ምንጮችን በጠቀሰው ዘገባው፣ ይህ ክስተት "ድንገተኛ ሽሽት" ሳይሆን ስልታዊ እና የተዋቀረ የደህንነት መረጃ ፍሰት (Intelligence realignment) መሆኑን አመላክቷል።

ሪፖርቱ እንደሚያብራራው፣ የኤርትራ መንግስት ፓርቲ (ህግደፍ) ለዓመታት የገነባው እና በጥርጣሬ እንዲሁም በፍጹም ታማኝነት ላይ የተመሰረተው የደህንነት ግንብ ስንጥቅ እያሳየ ነው። ቀደም ሲል በሽግግር ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተሰግስገው የነበሩ፣ እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት እና በኤርትራ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ የስለላ ወኪሎች፤ አሁን ላይ ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት (NISS) እያዞሩ ነው።

ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን የደህንነት መዋቅር "ከውስጥ ሆኖ የማየት" እና የመቆጣጠር እድል ፈጥሮለታል። ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቅርብ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ክበብ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሳይቀሩ፣ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት በምስጢር መልዕክት በመላክ "ስርዓቱን ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውንም አስተማማኝ ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን" እየገለጹ ነው። እነዚህ ባለስልጣናት የፕሬዝዳንቱን ከስልጣን መውረድ "ሀገሪቱን ለማዳን የቀረ ብቸኛ አማራጭ" አድርገው እንደሚመለከቱት ተጠቁሟል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ይህንን የመረጃ የበላይነት እና የውስጥ ዘልቆ መግባት አቅም ብትይዝም፣ እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ከስልጣን ለማወረድ ያነጣጠረ ቀጥተኛ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥባለች። ሪፖርቱ እንደሚያትተው፣ ኢትዮጵያ ይህንን እርምጃ ያልወሰደችው በአካባቢው ሊፈጠር የሚችለውን ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ቀውስ በመስጋት እና የቀጥታ ጣልቃ ገብነት የሚያስከፍለውን ጂኦ-ፖለቲካዊ ዋጋ በመፍራት ነው።

ለኢትዮጵያ፣ የኤርትራ የደህንነት መኮንኖችን መቀበል ማለት የሰው ኃይል ማግኘት ብቻ አይደለም የሚለው ዘገባው፣ ይህ ማለት የአስመራን "የስለላ ጥበብ"፣ ኢላማ የመለየት ስልት፣ የክትትል መረብ እና የውስጥ ደህንነት ዶክትሪን ሙሉ በሙሉ በእጅ እንደማስገባት ይቆጠራል። የኤርትራ ትልቁ መሳሪያ የነበረው "ምስጢራዊነት" አሁን ወደ ጉዳትነት ተቀይሯል።

ዘ-ሐበሻ የተመለከተው ሪፖርቱ እንዳመለከተው፣ ይህ ጉዳይ በምስጢር በተያዘ ቁጥር፣ በኤርትራ መንግስት ላይ የሚፈጥረው የሥነ-ልቦና ጫና የከፋ ይሆናል። እያንዳንዱ ታማኝ ተብሎ የሚታሰብ ባለስልጣን "ድርብ ወኪል" (Double agent) ተደርጎ እንዲጠረጠር ያደርጋል። ታማኝነት ሲሸረሸር እና የውስጥ መተማመን ሲጠፋ፣ የመንግስቱ ጥንካሬ ወደ "ቲያትር" ይቀየራል።

ሪፖርቱ ሲደመድም፣ የአፍሪካ ቀንድ አሁን የገባበት ምዕራፍ በንግግር እና በአዋጅ የሚካሄድ ጦርነት ሳይሆን፤ በምስጢር ኮሪደሮች ውስጥ ታማኝነት ሲፈርስ፣ መረጃዎች ሲሾልኩ እና መንግስታት በይፋ ከመናገራቸው በፊት ቁጥጥር ሲያጡ የሚታይበት "የስለላ ጦርነት" ምዕራፍ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ ይህንን "የመረጃ የበላይነት" እንደ ጦር ሜዳ ትጠቀምበታለች ወይስ እንደ መደራደሪያ መሳሪያ? የሚለው የጊዜ ጉዳይ ይሆናል።
ምንጭ:-ዘ-ሐበሻ ዜና

Photos from To Daye Wollo Press's post 12/01/2026

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ ወደ ሠላም መግባታቸው ተነግሯል‼

በአማራ ክልል ትጥቅ አንስተው ከመንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ከገቡት የፋኖ መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ ወደ ሠላም መምጣታቸው ተሰምቷል።

ኮሎኔሉ በወሎ አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ክፍል ይመሩ እንደነበር ተነግሯል።

ኮሎኔል ፋንታሁን ከወር በፊት አፋሕድን በመወከል ከመንግስት ጋር የሠላም ስምምነት የተፈራረመው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ የመጣበትን መንገድ ተከትለው ወደ ሠላም እንደመጡ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

ሰላም ለሀገራችን ሰለም ለኢትዮጵያ ።

Photos from To Daye Wollo Press's post 08/01/2026

📍ከካራካስ ወደ ቴህራን ? አደገኛው የዴልታ ፎርስ አዲሱ ተልዕኮ

በቬንዙዌላ ምድር የኒኮላስ ማዱሮን እጅ ወደ ኋላ ጠምዝዘው በቁጥጥር ስር ያዋሉት እነዚያው የልዩ ኃይል ኮማንዶዎች፣ ገና የካራካስ አቧራ ከጫማቸው ሳይራገፍ ፊታቸውን ወደ ሌላ የጦር ቀጠና አዙረዋል። አሁን የነፋሱ አቅጣጫ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየነፈሰ ነው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ "ዴልታ ፎርስ" (Delta Force) የተሰኘው የአሜሪካ ቁንጮ የጦር ክፍል በፍጥነት ራሱን እያሸጋገረ ነው።

ባለፉት ቀናት የአሜሪካ ግዙፍ ስትራቴጂካዊ የጭነት አውሮፕላኖች አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው በእንግሊዝ በኩል ወደ ምስራቅ ሲገሰግሱ ታይተዋል። በሆዳቸው የያዙት ተራ መሣሪያ አይደለም፤ ማዱሮን ለመያዝ በተደረገው ኦፕሬሽን ቁልፍ ሚና የነበራቸው እና "Night Stalkers" (የሌሊት አዳኞች) በመባል የሚታወቁትን ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ጭምር ነው። ነገሩን ይበልጥ ምስጢራዊ ያደረገው ደግሞ ሰኞ ዕለት የተፈጠረው ክስተት ነው። በግሪክ እና በቆጵሮስ የአየር ክልል ላይ ድንገተኛ እና ያልተብራራ "የመገናኛ ጨለማ" (Blackout) ተከስቶ ነበር። ይህ በአጋጣሚ የሆነ ሳይሆን፣ አሜሪካ እነዚህን ገዳይ ኃይሎች እና የጦር መሳሪያዎች ከዓለም አይን እና ከራዳር ዕይታ ውጭ አድርጋ ወደ ቀጠናው ለማስገባት የተጠቀመችበት ስልት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

አሁን ላይ የዴልታ ፎርስ አባላት፣ ከአሜሪካ ሬንጀርስ (Army Rangers) እና ከአውሮፓ ከተንቀሳቀሱ የአየር ወለድ ኃይሎች ጋር በመሆን በኢራቅ፣ በሶሪያ እና በዮርዳኖስ ድንበሮች ላይ አዲስ ምሽግ እየያዙ ነው። ዋና ኢላማቸውም መሳሪያ አንፈታም ብለው ያመጹት እና በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎች እንደሆኑ እየተነገረ ነው።

ሁኔታው የከፋ ጦርነት ምልክት ያሳያል። የአሜሪካ የነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች ቀጠናውን እያካለሉ ሲሆን፣ የስለላ አውሮፕላኖችም የኢራንን ጠረፍ እየዞሩ መረጃ ይለቅማሉ። የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) ዋና አዛዥም ረጅሙን ጉዞ አድርገው ባህሬን ገብተዋል።
ውጥረቱ ያለው እዚህ ላይ ነው፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት "ኢራን ሰላማዊ ሰልፈኞችን ከገደለች አሜሪካ መሳሪያዋን ወልውላ ዝግጁ ናት (Locked and loaded)" ሲሉ ዝተው ነበር። ያኔ የሟቾች ቁጥር ነጠላ ነበር፤ አሁን ግን ወደ 35 አምርቷል። ጥያቄው... የካራካሱ ኦፕሬሽን በቴህራን ደጃፍ ይደገም ይሆን? የሚለው ነው።
NBC

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address

Adis Abeba
Addis Ababa