ፍቅር
ፍቅር =ፍቅር ከልብ (ልቦና) ውስጥ የሚወጣ ጠንካራ የመውደድ ስ?
🌀🌀ሰው እኮ!🌀🌀
✅ ካላገባህ ለምን አታገባም ?
✅ ካገባህ ምነው እስካሁን ሳትወልዱ ?
✅ ሁለት ልጆች ካሉህ ለምን ሶስተኛ አትጨምሩም ?
✅ ከሚስትህ ጋር ከተጋጫቹ ፍቺ እያለ ምን አሰቃየህ ?
✅ ተጫዋች ስትሆን ወረኛ ያደርጉሃል
✅ ዝምተኛ ስትሆን ውስጥህ ነገር እንደያዘ ነገር ያስቡሃል
✅ አንዳንዴ ተጫዋች አንዳንዴ ዝምተኛ ስትሆን እሱ እኮ እንዲህ ነው
አይጨበጥም ይሉሃል!
✴ኮስታራ ከሆንክ እሱኮ ፊቱ አይፈታም
✴ባጋጣሚ ሰላም ሳትል ካለፍክ ኩራተኛ ነው ብለው ያስወሩብሃል
በቃ ማውራት ነው !!
💠 ስትወፍር ያወራሉ
💠 ስትከሳ ያወራሉ
💠 ጎበዝ ከሆንክ ያወራሉ
💠 ደደብ ከሆንክ ያወራሉ
💠 ፀሀይ ሲሆን ሙቀቱ!
💠 ዝናብ ሲሆን ውይ ብርዱ!
💠 ስትናገር ተናጋሮ አናጋሪ ያደርጉሃል
💠 ግልፅ ስትሆን ይጠሉሃል
💠 ስትቀርባቸው ለጥቅም እንደሆነ ያስባሉ
💠 ስትርቃቸው ይፈልጉሃል
💠 ቀለል ብለህ ስትቀርባቸው ያረክሱሃል
💠 ስራ ከፈታህ ይንቁሃል
💠 ስራ ስተሰራ ያሙሃል
💠 ገንዘብ ካለህ ይንሰፈሰፉልሃል
💠 ካማረበህ ይቀናሉ
💠 ካስጠላብህ ያሽሟጣሉ
💠 ፀዳ ስትል ያፈጡብሃል
💠 ስትቆሽሽ ሊያዩህም አይፈልጉም
🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿
ይገርማል…!!
✴ ሰው ሲሞት ከንፈር መምጠጥ
✴ በሰው ውድቀት ማላገጥ
✴ ሰው ሲያልፍለት መቅናት
✴ ሰው ሲሰራ ማማት
✴ ካለህ ሰዎች ያውቁሃል
✴ ከሌለህ ሰዎችን ታውቃለህ
✴ ካለህ ሰዎች ያውቁሃል
✴ ከሌለህ ሰዎች ይንቁሃል
🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿
አሁንም እንገረም...!!
✳ ጥቅም እንጂ ፍቅር የለም!
✳ እኔ እንጂ እኛ የለም
✳ የላይ እንጂ የውስጥ የለም
✳ ከአፍ እንጂ ከልብ የለም
✳ ምላስ እንጂ ተግባር የለም
✳ ትምህርት እንጂ ዕውቀት የለም
✳ ስደት እንጂ ገንዘብ የለም
🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿🧿
ድንቅ ነው...!!
✅ ነጋዴው ይዋሻል
✅ ተማሪው ያላግጣል
✅ ዶክተሩ በእውቀቱ ይነግዳል
✅ ሃብታም ለድሃው አያዝንም
✅ በሽታና ሞት ቢበዛም የሚመከር ጥቂት እንጂ ብዙ የለም
✅ ብዙዎች በአለማዊ ጉዳይ ቢዚህ ሆነው
✅ መንፈሳዊውን ህይወታቸውን ረስተው
✅ ዓለማችን በጥፋት ተበከለች
✅ ክቡር ህይወት ርካሽ ሆነች
Source
ምርጥ መጣጥፍ ሆኖ ካገኙት ላይክ፣ሼር ያድርጉ
ምርጥ መጣጥፎች
FB adis press
ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም።
ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡
እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡
በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው?
ማንም ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡
ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡
በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡
አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን ይህም አስተማማኝ አይደለም።
ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡
ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡
ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡
እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡
ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡
Hiruy
10ሩ ልታውቃቸው ወይም ልታስታውሳቸው የማትፈልጋቸው መሪር እውነታዎች:-
1. አዎ አንድ ቀን ትሞታለህ ግን ያ ቀን መቼ እንደሆነ አታውቅም። ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ ለሞት ቀርበሃል።
2. አዎ ተፈጥሮ ካንተ ቁጥጥር ውጪ ነች። የምትወዳቸው ሰዎች አንድ ቀን ይሞታሉ ግን መቼ እንደሆነ አታውቅም።
3. ሁሉንም ሰው ማስደሰት አይቻልም። ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ይህን ለማድረግ የምትጋጋጥ ከሆነ ወዮልህ።
4. የለየለት ሀቀኝነት የለየለት ውሸት ነው። ለማስመሰል አታጎብድድ።
5. ገንዘብ የረዥም ጊዜ ደስታን ይሰጥሃል። ፍቅር ያለገንዘብ ግን ፊልም ላይ ብቻ ነው። ይህ ካለ እንኳን እንደ ማለዳ ጤዛ ብን ብሎ ይጠፋል።
6. በዚህ ምድር ምንም ነገር ቋሚ አይደለም ከለውጥ በስተቀር። አሁን ያለህ ምቾትም ይሁን ጉስቁልና አላፊ ነው። ብትፈልገውም ባትፈልገውም።
7. ወደድክም ጠላህም ዓለም እየከፋች እንጂ ምርጥ እየሆነች አትቀጥልም። ይህ የምታየው እውነት ነው።
8. አንዳንዶች እንድትለማመጣቸው ይፈልጋሉ። አንተን በሚያዩበት መነፅር እነሱን መመልከት ጀምር አትርመጥመጥ።
9. ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን ደንቆሮ አለቃህ እንደፈለገ ያንከባልልሃል። ይህ ህይወት ነው አምነህ ተቀበል።
10. ህይወት ሁሌም ፍትሃዊ ልትሆን አትችልም። አልነበረችምም። ድርሻህን አጊኝተሃል።
Israel Teshome
27/11/2022
⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷
ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ
Source
↪️➖
━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━
26/09/2022
ማዙካ ምን እያደረገች ነዉ ???
17/07/2022
25 ሕይወት ቀያሪ አባባሎች
ለእርስዎ ከ25ቱ የቱን 1ኛ ያደርጋሉ ?
1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
-ፍራንክ ኦሽን
2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
-ቶማስ ጄፈርሰን
3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
-ዶናልድ
4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ
5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
-ዋልተር ባግሆት
6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
-ጂም ዋትኪንስ
7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
-አርል ኒተንጋል
8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ
9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር
10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
-አልበርት አንስታይን
11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
-ካርል ጉስታቭ
12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት
13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ
14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ
15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
-ሱዚ ካስም
16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
-ብሩስ ሊ
17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ
18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን
19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
-ሮቢን ሻርማ
20. አለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
-ፖል ኮኢልሆ
21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
-ኤሪክ ቶማስ
22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
-የማዎሪ አባባል
23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
-ስኮት ቤልስካይ
24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
-ያልታወቀ ሰው
25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡
12/04/2022
💔💔💔....
በልብህ አስበህ የኔን ልብ ለመስበር💔
እግርህ ከኔ ርቆ ወደ ሌላ ሲበር፤
እመነኝ ፍቅሬ ሆይ😍
ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር፤
የሚል ግጥም ሰጥቼህ እቤት እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጁ አንገቴን ቀርቅሬ ቁጭ ብዬ አነባው፤
አየህ መለያየት ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው 🥺
ምን ላድርግ ሴት ልጅ ነኝ
ባደባባይ ስቄ ቤቴ ነው ማለቅሰው።
source telegram
❤የፍቅር ሳቅ😁
13/03/2022
#ፍቅር ግን ደስ ሲል.❤ ከሚወድት ጋር በደስታ መኖር .
ፍጣሪ ጥሩ የፍቅር ጓደኛ ይስጣችሁ
ከምትወድት ጋር መልካም ጊዜ ተመኝሁላችሁ ።
20/02/2022
#ፍቅር ጥላ ሲጥል
በገና ቢቀኙ
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ…..
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ምነው ቢናፍቁ
አገር ቢያቋርጡ
ቢሄዱ ቢርቁ
አመት ቢጠብቁ
ለሚወዱት ምነው............?
[ ገ/ክርስቶስ ደስታ ]
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
POSTCODE