Million Bifato Hidano

Million Bifato Hidano

Share

Songs

01/06/2026

ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው፤
ተመራጩ ይህን ታላቅ ህዝብ እንዴት አገልግለው ህይወቱን ይቀይራሉ የሚለው ጉዳይ ይበልጥ ያሳስበኛል።

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል

Photos from Million Bifato Hidano's post 29/05/2026

✔የጨቤ ጋምቤልቱ ወረዳ ሥራ አስፈፃሚዎች በእውነቱ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል🙌 በርካታ ምሁራን ወጣቶች ዛሬ ግን ለ 100 በላይ ሥራ አጦች ቅጥር እየተፈፀመላቸው በመሆኑ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን🙌 መሪዎቻችንን ክፉ አይንካቸው🙌 ዘመናቸው ይባረክ🙌ለተቀጣሪ ወንድሞችና እህቶች ደግሞ እንኳን ደስ አላችሁ🙌 የለቅሶአችሁ ወራት አልፎ የሳቅ ዘመን ስለመጣላችሁ ደስ ብሎኛል እያልኩኝ ሕዝባችሁን በቅንነትና በታማኝነት ከሙስና በፀዳ አእምሮ እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ።
# ለወረዳችን ሥራ አስፈጻሚዎች አደራ ማለት የምፈልገው🙏 ድንገት መረጃ ሳይደርሳቸው የቀሩ ተመራቂዎች ሊኖሩም ስለሚችሉ ይህ መልካምነታችሁ ይቀጥላል የሚል እምነት አለኝ።
daga raare macciisha yaa togooti. sirchi'ne buddeena hooge hudiroonke yesuusi su'minni🙌❤❤❤❤❤

Photos from Million Bifato Hidano's post 22/05/2026

በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልሎች አቅራቢያ ባሉ የድንበር አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው ሁከት፣ የሰዎች ሞት እና የንብረት ውድመት እጅግ አሳሳቢ እና ልብ ሰባሪ ነው። እንዲህ ያሉ የሃይል ድርጊቶች በአስቸኳይ መቆም አለባቸው። ንጹሃን አርሶ አደሮች እና ሲቪሎች በአስተዳደር ክፍተቶች ወይም ባልተፈቱ የአካባቢ ውዝግቦች ምክንያት መቼም ቢሆን ዋጋ ሊከፍሉ አይገባም። ሁለቱም የክልል መንግስታት እና የፌደራል ባለስልጣናት የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ለመጠበቅ፣ እንዲሁም ደህንነትን ለማረጋገጥና ግጭቱ ይበልጥ እንዳይባባስ ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃዎችን የመውሰድ ህገ-መንግስታዊ እና የሞራል ሃላፊነት አለባቸው።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዘላቂ ሰላምን በሃይል ብቻ ማምጣት አይቻልም። ከሁለቱም ወገን ያሉ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና የተከበሩ ግለሰቦች በአንድነት በመቀመጥ የገጭቱን መንስኤዎች መወያየት እና ለትውልዶች አብረው በኖሩት ጎረቤት ማህበረሰቦች መካከል ያለውን እምነት እንደገና መገንባት ይኖርባቸዋል። በሁከቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በአስቸኳይ ያስፈልጋቸዋል። ከሁሉም በላይ፣ የሰው ልጅ ህይወትን መጠበቅ እና ሰላማዊ አብሮነትን መልሶ ማምጣት ከማንኛውም ሌላ ጉዳይ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

05/05/2026

መዝሙር 121 (Psalms)
7፤ # እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።

Barra Hachumo'ne!!

02/05/2026

የክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሺፈራው ሹጉጤ ቤተሰብ ዛሬ ደማቅ ታሪክ ሰርቷል!🎉 ለሀገራቸው በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው መስክ ትልቅ አሻራ ያሳረፉት አምባሳደሩ፣ ዛሬ ደግሞ በምሳሌነት የሚጠቀሱ ልጆችን ለታላቅ ማዕረግ በማብቃት የእጥፍ ድል ባለቤት ሆነዋል። ልጆቻቸው ዶ/ር አማኑኤል እና ኢንጅነር ምንቴ ከፍተኛ ትምህርታቸውን በስኬት አጠናቀው ለምርቃት መብቃታቸው ተሰምቷል። ይህ ስኬት ለቤተሰባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ጠንካራና ባለራዕይ ትውልድ ለሚመኝ ወገን ሁሉ ታላቅ ኩራትና አርአያ ሆኖ ተመዝግቧል። ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሺፈራው ሹጉጤ፣ ለሀገር የሚተርፉ ቁምነገረኛ ልጆችን ለዚህ ማዕረግ ስላበቁ እንኳን ደስ አለዎት እንላለን፤ ተመራቂዎቹም በሙያቸው ለሀገራቸው ብርሃን እንዲሆኑ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን።

Photos from Million Bifato Hidano's post 01/05/2026

Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስተዳደር


​መሠረተ-ልማቶችን ፊትሃዊ በሆነ መልኩ መጠቀም የማንኛውም ሀገር ዜጋ ሊገሰስ የማይችል መሠረታዊ መብት ነው። ይሁን እንጂ በዳዬ ከተማ አስተዳደር የሚስተዋለው ተደጋጋሚና ረጅም ሰዓት የሚወስድ የኃይል መቆራረጥ የህዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከባድ እያደረገው ይገኛል።

#​ዋና ዋና ተጽዕኖዎች፦

​የንግድ እንቅስቃሴዎች፦ መብራት በዋናነት ለስራቸው የሚጠቀሙ አነስተኛና ከፍተኛ ተቋማት ስራቸውን ማከናወን ተስኗቸዋል።

​ማህበራዊ አገልግሎቶች፦ የጤና ተቋማትና የውሃ አቅርቦትና ባንክ በማብራት መቆራረጥ ምክንያት ከፍተኛ መስተጓጎል እየገጠማቸው ነው።

​የተማሪዎች ትምህርት፦ ተማሪዎች በምሽት ለማጥናትና ስራዎቻቸውን ለመስራት ተቸግረዋል።

​"የዜጎችን ጩኸት መስማትና ለአገልግሎት መቆራረጥ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል"

​የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ሆነ የየደረጃው የሚገኙ የክልላች ኤሌክትሪክ አግልግሎት ቢሮ ነውና ዳዬ ኤሌክትሪክ ማዕከል ፣ የዳዬ_በንሳ ከተማ ህዝብ እያሰማ ያለውን ቅሬታ ሰምታችሁ ዘላቂ መፍትሄ እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Photos from Million Bifato Hidano's post 15/04/2026

ከምሁራን መንደር አንዱን ምሁር ወጣት ላሰተዋዉቃችሁ።❤
ምሁር ወጣት ተመስገን ቢፋቶ ይባላል፣ትልቅ ለዉጥ ማምጣት የሚችል ብርቱ ወጣት ስለሆነ፣ ፓርትያችን የሚገባዉን ቦታ ብሰጡትና ብጠቀሙት መልካም ነዉ ባይ ነኝ።

12/04/2026

የብዙ ሰዎች አባትና ተሱፍዎች
እንወዳቿለን ሺህ ዓመት ኑሩልን ❤❤❤

የቡና ኢኮኖሚ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ፣ የሥራ አርበኛና ተምሳሌት የብዙሀን እንጀራ አባት ክቡር እና ሙሉጌታ ዱካሞ 🥰💯👏🥰
እናንተን መድረስ ያልቻሉ ክፉዎች የተለያዩ ክፉ ምኞታቸውን ብገልጹም ፈጣርህን ስለምታስቀድሙ ሁሌም በከፍታው ናቸው ።

የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዲስ አመራሮችን መረጠ ፤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የተከናወነ ሲሆን፣ የሲዳማ ክልል ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በመወከል የቀረቡት ታዋቂው ባለሀብት የተከበሩ አቶ አሰፋ ዱካሞ የቦርድ አመራር ሆነው ተመርጠዋል።

እና ሙሉጌታ ዱካሞ 🥰💯🥰👏
የሲዳማ ክልል ብሎም በመላው አለም ላይ ጥራት ያለውን ቡና በማቅረብ የሚታወቁት በተለያዩ የንግድ የእርሻና የፋብሪካዎች ባለቤት ትሁት የዋህና የብዙ ሺህዎች ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረው መልካም ሰው ነው።

👉 ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የቀረቡት መሥፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1)= በንግድ ፈቃድ ላይ የተመዘገበ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል።
2)= ቢያንስ የአንድ ፋብሪካ ባለቤትነት የሚጠይቅ ስሆን አቶ አሰፋ ዱካሞ ከዚህ በላይ ፋብሪካዎችና የተለያዩ ኢንዱስትሪ ያሉት ታማኝ ባለሀብት ነው ።

ይህ አዲስ አደረጃጀት በኢትዮጵያ የግል ዘርፍ እና በኢንዱስትሪው ልማት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንሎት እመኛለሁ የተከበሩ አሰፋ ዱካሞ( Daye Bensa Coffee CEO) 🥰❤💯❤🥰

08/04/2026

Dancha Loosu yanna ikkittohe ❤️❤️❤️❤️

09/02/2026

Yesira Baldereboche Gar Des yemil gize nebrn(staff)❤️❤️❤️

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Awassa