Tsehayneh Aderaw
🎓 Economics graduate from Arbaminch University & living in Bahirdar!! now
29/05/2026
ውጤቱን ይገምቱ - ይሸለሙ!
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ግንቦት 22፣
ቅዳሜ 1:00 | በሀንጋሪ ቡዳፔስት፣ ፑሽካሽ አሬና ስታድየም ፒኤስጂ ከ አርሰናል፣
የዚህን ጨዋታ ውጤት በትክክል ቀድመው የገመቱ 3 ተከታዮች የሞባይል ካርድ ይሸለማሉ።
ታዲያ ሽልማቱን ለማግኘት ፦
➊ የገፃችን ተከታይ ይሁኑ ፣
➋ ዉጤቱን ኮመንት ላይ ያስፍሩ ፣
➌ ፖስቱን ላይክና ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ ፣
ማሳሰቢያ ፦ ውጤቱን በትክክል ቢገምቱም የገፁ ተከታይ ካልሆኑ፣ ላይክና ሼር ካላደረጉ ከዉድድሩ ዉጭ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም የገፁ ተከታይ መሆን፣ ላይክና ሼር ማድረግን አይርሱ፡፡
ውጤቱን በትክክል ማግኘትና ህጉን ማክበር ያሸልማል።
መልካም ዕድል !!
With ጉርሻ page – I just got recognized as one of their top fans!
12/05/2026
ብልጽግና አማራ ክልል አሁን ያለው ይህ ነው
09/05/2026
''ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ስንዴ ምርት የሰጡት ማብራሪያ የውሸት ሪፖርት ነው ተባለ'' ኢትዮጵያ ቼክ''
ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሰሉልታ አካባቢ የሚገኝ የስንዴ ማሳን በጎበኙበት ወቅት ኢትዮጵያ በዘንድሮው የምርት ዘመን ያስመዘገበችውን ውጤት በተመለከተ የሰጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል።
በመግለጫቸውም ሀገሪቱ በዚህ በጀት ዓመት ከ330 ሚሊዮን ኩንታል (33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) በላይ ስንዴ ማምረት መቻሏንና ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር እንደሚያደርጋት ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ይህ በመንግስት በኩል የቀረበው አሀዝ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የግብርና እና የኢኮኖሚ መረጃ ተንታኝ ተቋማት ሪፖርቶች ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ይታይበታል።
የአሜሪካ የእርሻ ዲፓርትመንት (USDA) የውጭ እርሻ አገልግሎት (FAS) እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2024 እና በሜይ 2025 ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች መሰረት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አካባቢ እንደሚገኝ ተገምቷል።
ምንም እንኳን ተቋሙ በኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማት እና የክላስተር ግብርና ምርታማነትን እየጨመረ መሆኑን ቢገልጽም የተመዘገበው ጭማሪ በመንግስት ከተጠቀሰው 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ገደማ ያነሰ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የሳተላይት ምስሎችን እና የመሬት ላይ መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ የUSDA ትንታኔዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ ለእርሻ የዋለው መሬት ስፋት እና የተገኘው ምርት መጠን መንግስት እንደሚለው "በአራት እጥፍ" አድጓል የሚለውን መረጃ አያረጋግጡም።
በተመሳሳይ እንደ FAO (የዓለም የምግብ እና ግብርና ድርጅት) ያሉ ተቋማት መረጃዎችም የኢትዮጵያን ምርት ከ7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ አያደርሱትም።
ኢትዮጵያ "ግብፅን በሶስት እጥፍ በመብለጥ ከአፍሪካ አንደኛ ሆናለች" የሚለውን መግለጫ በተመለከተ ዓለም አቀፍ የንግድ እና የግብርና መረጃዎች የተለየ ምስል ያሳያሉ።
የUSDA እና የኢንዴክስ ቦክስ (IndexBox) የ2024/25 ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግብፅ በ9.2 እስከ 9.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዓመታዊ ምርት አሁንም ከአፍሪካ ቀዳሚነቱን እንደያዘች ነው። ኢትዮጵያ በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ከግብፅ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
መንግስት ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ጀምራለች ቢልም የዓለም አቀፍ የንግድ መረጃዎች (እንደ OEC ያሉ) ግን ኢትዮጵያ አሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴ ከውጭ እንደምታስገባ ያሳያሉ።
ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ከኬንያ፣ ሮማኒያ እና ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ስንዴ ገዝታለች። በተቃራኒው ወደ ውጭ የተላከው የምርት መጠን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተመዝግቧል።
እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በዓለም ባንክ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፤ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የታየው የስንዴ ዋጋ ንረት (በአንድ ዓመት ውስጥ የ28% ጭማሪ) እና በምግብ እርዳታ ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር አለመቀነስ፣ ሀገሪቱ "ትርፍ ምርት አምርታለች" ከሚለው መግለጫ ጋር የሚጋጩ ተጨባጭ እውነታዎች ናቸው።
በአጠቃላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው የ33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የምርት ሪፖርት ከገለልተኛ ዓለም አቀፍ ተቋማት ግምቶች (ከ5.5 - 7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) ጋር እጅግ ሰፊ ልዩነት ያለው ሲሆን የሀገሪቱ የገቢ ንግድ መረጃ እና የገበያ ዋጋም የቀረበውን "ትርፍ ምርት" አያረጋግጡም።
Via:- ኢትዮጵያ ቼክ
09/05/2026
''ፍትሕ በሌለበት ፍትሕ መጠየቅ መንግስትን መደገፍ ነው! የአዲስ አበባ ተወላጆች ሕብረት መልዕክት''
"የግፍ ማሳያው እና የሽሮሜዳው ሰማእት- ኦሮሮ"
መቼም እንዲህ ያለው አሳዛኝ ታሪክ መንግስት አላት ከምትባለው ኢትዮጵያ፣ ወይም ደሞ ከኦሽቪትዝ የስቃይ ካምፖች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ከየትም ሊሰማ አይችልም።
ተገኝ ባልቻ ይባላል፣ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቹ ኦሮሮ እያሉ ይጠሩታል። ኦሮሮ በሽሮሜዳ የታወቀ የሽመና ባለሙያ ነበር፣ የመሸጫ ሱቅም ነበረው። ኦሮሮ ተግባቢ፣ ደግ፣ ለሰው አዛኝ፣ ህፃን አዋቂውን አክባሪ፣ በትንሽ ትልቁ ተፈቃሪ ነበር የሽሮሜዳ ምልክት ነው።
"የኮሪደር ልማት" ከመጣ ወዲህ ግን የኦሮሮ ሁለመና ተቀየረ መጀመሪያ ለልማት ብለው የስራ ቦታውን አፈረሱበት። ምትክ መስራያ ቦታ ሲጠይቅ አባረሩት፣ ኦሮሮ ባቀናው መንደር ባዶ ኪሱን፣ ባዶ እጁን ቀረ። ያን የመሰለ ጨዋና ለሁሉ ወጣት አርአያ የነበረ ልጅ ሰካራም ሆነ፣ ይባስ ብሎ የአእምሮ መቃወስ ደረሰበት።
ኦሮሮ ከሳምንት በፊት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአንድ ፖሊስ ጋ በመጋጨቱ ለቀናት ታስሮ ተፈታ። በሀዘን ላይ ሀዘን ሆነና በዚህ መሀል ወላጅ አባቱ አረፉ። አባቱን ቀብሮ፣ ከዘመድ ጎረቤቶች ጋር በድንኳን ውስጥ ተቀምጦ ሀዘኑን እየተወጣ እያለ ፖሊሶች መጥተው ትፈለጋለህ ብለው ይዘውት ሄዱ።
ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ ሲደርስ ግን የጠበቀው ነገር ያልተጠበቀ ነበር፣ በቀደም የተጣላው ፖሊስ መሳሪያውን ደግኖ ቆሟል። ኦሮሮ በፖሊሶች ተይዞ፣ ራሱን መከላከል ወይም ሮጦ ማምለጥ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ፣ ፖሊሱ ያለርህራሄ በያዘው መሳሪያ በርካታ ጥይቶችን አርከፍክፎ ገደለው።
የሽሮሜዳው አንበሳ ኦሮሮ፣ መሀል አስፋልት ላይ የውሻ ሞት ሞተ፣ ደመ-ከልብ ሆነ በዚህ የተነሳ ዳሜሮሽ (ሽሮሜዳ) ከባድ ሀዘን ላይ ወድቃለች።
የአዲስ አበባ ወጣት በግዜ ግፈኛ አገዛዝን ካልተቃወምክ በየቦታው የምትሰማው የግፍ ግድያ በየደጃፍህ እየመጣ እንደ ''ኦሮሮ!'' ቆርጥሞ እየበላህ የግፍ አገዳደልን ትሞታለህ።
''ኦሮሮ ነፍስ በሰላም ትረፍ!''
Via:- የአዲስ አበባ ተወላጆች ሕብረት
ፍትሕ በሌለበት ፍትሕ መጠየቅ መንግስትን መደገፍ ነው!
Category
Website
Address
Bahir Dar