Star Men Beauty Salon እስታር የወንዶች የውበት ሳሎን

Star Men Beauty Salon እስታር የወንዶች  የውበት  ሳሎን

አላማችን ፅጉር ማስትካካል ብቻ ሳይሆን ውበትንም ማላብስ ነው።

[06/28/18]   ፀጉርህ ሸብቷል?

ሽበት ብዙውን ጊዜ የእርጅና እና የአረጋዊነት ምልክት ተደርጎ ይታያል። እርግጥ ነው፣
ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ፀጉር ይሸብታል። ይሁን እንጂ ሽበት የሚመጣው በእርጅና ምክንያት
ብቻ አይደለም። በቂ ምግብ እንዳለመመገብ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሸብቱ ታውቋል።
ሽበት ጠቆር ያለ ፀጉር ባላቸው ላይ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ ጾታም ሆነ የፀጉር ቀለም
አይመርጥም።
አንዳንዶች በመሸበታቸው ምክንያት ከዕድሜያቸው በላይ ያረጁ መስለው ሊታዩና ይህም
አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ባለመሸበታቸው ምክንያት ትክክለኛው
ዕድሜያቸውና መልካቸው አለመመሳሰሉ የሚያሳስባቸው ሰዎች አሉ።
ፀጉር ከሸበተ ሞተ ማለት አይደለም። እርግጥ ነው በዓይን የሚታየው ውጪያዊ የፀጉር
ክፍል በድን ነው። የእያንዳንዱ ፀጉር ሥር ከቆዳ በታች ጠልቆ ይገባል። ይህ ክፍል የፀጉር
ሥር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሕይወት ያለው የፀጉር ክፍል ይህ ብቻ ነው። የፀጉር ሥር እንደ
ፀጉር ፋብሪካ ሆኖ ያገለግላል። በሥሩ ውስጥ ያሉት ሴሎች በብዛት ተራብተው ፀጉር
ሲፈጠር የቀለም ሴሎች የሚሠሩትን ሜላኒን ይቀባል። በዚህም የተነሣ የቀለም ሴሎች
ሜላኒን መሥራት ካቆሙ ፀጉር ነጭ ይሆናል።
የቀለም ሴሎች በድንገት ሜላኒን መሥራታቸውን የሚያቆሙት ለምን እንደሆነ ማንም
የሚያውቅ የለም። በዚህም ምክንያት ለሽበት የሚሆን አስተማማኝ መድኃኒት ሊገኝ
አልተቻለም። በተጨማሪም ሥራቸውን አቁመው የነበሩ የቀለም ሴሎች እንደገና መሥራት
ሊጀምሩ እንደሚችሉ ሊታወቅ ተችሏል። ፀጉርን አስመልክተው የተነገሩ ብዙ አባባሎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። ኢየሱስ ከተናገራቸው ምሳሌዎች አንዱ ስለ ነጭ ፀጉር
ይናገራል። “አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልም” ብሏል። ( ማቴዎስ 5:​
36 ) እነዚህ ቃላት ሽበት ማስቀረትም ሆነ ማስወገድ ከሰው አቅም በላይ መሆኑ ከታወቀ
ብዙ ዘመን ያለፈው መሆኑን ያመለክታሉ።
አንዳንዶች ሜላኒን እንደመወጋት ያሉትን አዳዲስ ሕክምናዎች ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ
ፀጉራቸውን ቀለም ይቀባሉ። ይህም ቢሆን ዛሬ የመጣ ልማድ አይደለም። የጥንቶቹ
ግሪካውያንና ሮማውያን ፀጉራቸውን ቀለም ይቀቡ ነበር። የጥንት ግብጻውያን በበሬ ደም
ፀጉራቸውን ያቀልሙ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን ይኖር የነበረው ታላቁ ሄሮድስ
ዕድሜውን ለመሸሸግ ሽበቱን ቀለም ይቀባ እንደነበረ ተመዝግቧል።
ይሁን እንጂ በየጊዜው ቀለም መቀባት ጊዜና ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ
የአንዳንዶችን ቆዳ ሊያስቆጣ ወይም ሊያቆስል ይችላል። ሽበትህን በቀለም ለማጥቆር
ብትወስንም መቀባትህን ለማቆም የምትፈልግበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ
ከሥር የሚያድገውን ሽበት መሸሸግ አስቸጋሪ ይሆንብሃል። ሽበት በአዎንታዊ ጎኑ
የሚያምርና ከዚህ በፊት ያልነበረህን ግርማ ሞገስ የሚያስገኝልህ ሊሆን ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ “የሸበተ ፀጉር በጽድቅ መንገድ ሲገኝ የውበት ዘውድ ነው” ይላል።​—

[10/06/17]   ጥያቄ:- ብዙዎች ፀጉር ሲቆረጥ ቶሎ ያድጋል ብለው ያምናሉ። ይህ እውነት ነው?💇

መልስ:- በፍጹም። አንዳንድ ሰዎች የአንድ ዛፍ ቅርንጫፎች በግንዱ አማካኝነት
የሚያስፈልጋቸውን ንጥረ ነገሮች እንደሚያገኙ ሁሉ ፀጉርም ከሰውነት ምግብ እንደሚያገኝ
አድርገው ያስባሉ። ይሁን እንጂ ፀጉር አንዴ ከራስ ቆዳ አልፎ ከወጣ በኋላ ሙት ንጥረ ነገር
ይሆናል። በመሆኑም ፀጉርን መከርከም በእድገቱ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም።

[10/05/17]   የፀጉር እድገትና የፀጉር መርገፍ

ጥያቄ:- ፀጉር የተሠራው ከምንድን ነው?

መልስ:- ፀጉር እንደ ቃጫ ያለ ኬረቲን የተሰኘ ፕሮቲን አለው። እያንዳንዱ ፀጉር የሚወጣው
በራስ ቆዳ ላይ በሚገኝ ጉብር የተሰኘ ስንጥቅ በኩል ነው። ከእያንዳንዱ ጉብር በታች
ከፍተኛ የደም አቅርቦት ያለው ፓፒላ የሚባል ህብረህዋስ ይገኛል። ይህ ህብረህዋስ
በጉብሩ በኩል የሚያድጉና ወደ ፀጉርነት የሚለወጡ የፀጉር ሕዋሳት ያመነጫል።

[10/05/17]   ስለ ፀጉራችሁ ያላችሁን ግንዛቤ ማስፋት

“በየትኛውም ዘመን ሆነ ባሕል” ይላል አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ፣ “ፀጉር ስለ አንድ ሰው
ውስጣዊ ማንነት የሚያስተላልፈው መልእክት አለው።” እንግዲያው አብዛኞቹ ሰዎች
ፀጉራቸው የሚያምርና የሚማርክ ሆኖ እንዲታይ ለማድረግ ቢጥሩ ምንም አያስደንቅም።
ንቁ! መጽሔት የፀጉር ባሕርይንና አያያዝን በተመለከተ ከፍተኛ ልምድ ላካባቱ አራት ፀጉር
ሠሪዎች አንዳንድ የተለመዱ ጥያቄዎች አቅርቦላቸዋል። ይህ ቃለ መጠይቅ ፀጉራችሁ
ከምታስቡት በላይ ውስብስብ አሠራር ያለው መሆኑን እንድትገነዘቡ ያደርጋችኋል።

[07/02/17]   አንድ የእምነት ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ ቤት
ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።
ጸጉር አስተካካይ፦ታውቃለህ ፈጣሪ የለም
ተስተካካይ፦በመገረም እንዴት?
አስተካካይ፦አይታይህም?
ተስተካካይ፦ምኑ?
አስተካካይ፦እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ
ጦርነት፣ረሀብ፣ችግር፣ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ ፈጣሪ አንዴ
ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።
ተስተካካይ፦ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም
አስተካካይ፦ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?
ተስተካካይ፦ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ጺሙ የተንዠረገገ ሰው
አይኖርም ነበር።
አስተካካይ፦እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ አለመምጣታቸው ነው
እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ የተንዠረገገ እና የተንጨባረረ ጸጉር
አታይም ነበር።
ተስተካካይ፦ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው ነው ሰው
ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም።

[07/02/17]   Warning!!!
እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ማንባብ የተከለከለ!!
------------------------------------
ሰውየው ጸጉር ቤት ሄዶ በር ላይ አንገቱን ብቅ ያደርግና ጸጉር አስተካካዩን
"ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ወረፋ ይደርሰኛል?"
ይለዋል።
ጸጉር አስተካካዩም ወረፋ የያዙትን ደንበኞቹን ቃኘት ያደርግና
"ከሶስት ሰአት በኋላ" ይለዋል
ሰውየውም ትቶት ይሄዳል...
ከጥቂት ቀናት በኋላ ይሄው ሰውዬ አንገቱን ብቅ ያደርግና
"ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ወረፋ ይደርሰኛል?" ይለዋል።
ጸጉር አስተካካዩም ወረፋ የያዙትን ደንበኞቹን ቃኘት ያደርግና
"ከአንድ ሰአት በኋላ" ይለዋል።
ሰውዬው አሁንም ጥሎ ይሄዳል...
ከሳምንት በኋላ ይሄው ሰውዬ አንገቱን ብቅ ያደርግና
"ከምን ያህል ጊዜ በኋላ
ወረፋ ይደርሰኛል?" ይለዋል።
ጸጉር አስተካካዩም ወረፋ የያዙትን ደንበኞቹን ቃኘት ያደርግና
"ከሁለት ሰአት በኋላ" ይለዋል
ሰውዬው አሁንም ጥሎ ይሄዳል...
በዚህ ጊዜ ጸጉር አስተካካዩ ወደ ጓደኛው ዞር ይልና
"ታዴ ይሄ ሰውዬ በተደጋጋሚ እኔጋ
እየመጣ ከጠየቀ በኋላ ጥሎ ይሄዳል እስኪ ወዴት እንደሚሄድ ተከተለውና
ንገርኝ?" ይለዋል።
ታዴም ከአምስት ደቂቃ በኋላ ሰውዬውን ተከትሎ ይመለሳል።
ጸጉር አስተካካዩ:- "እሺ ታዴ: ሰውየው የት ነው የሚሄደው?"
ታዴ አይኖቹ እንባ እያቀረሩ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
"ቤት! ሚስትህ ጋር ነው የሚሄደው"

[03/26/17]   የሂና አጠቃቀም - የተፈጥሮ ቀለም ያለው ውብ ፀጉር እንዲኖረን | Natural Henna Hair Color in Amharic
ሂና በምንጠቀምበት ጊዜ ማስገባት ስላለብን ግብአቶች እና በአጠቃላይ ስለ አዘገጃጀቱ - ፀጉርን ወዛማና የሚያምር ተፈጥሮዓዊ ቀለም እንዲያገኝ ከማድረጉም በተጨማሪ ፎሮፎርን ፣ ማሳከክን ፣ የጸጉር መርገፍ ለመከላከልና የፀጉር እጅገት ፈጣን እንዲሆን ይረዳል፡፡
ለጸጉር መርገፍ በዘህ መለኩ መጠቀም እንችላለን
አንድ ኩባያ ሂና ከ 3 የሾርባ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ የተፈጨ በአንድ ኩባያ ለብ ያለ ውሃ ቀላቅሎ ለሁለት ሰዓታት ያህል ባለበት ሁኔታ መተው፤ ከዚያም ጸጉርን ተቀብቶ ከሶስት ሰአት በኋላ መታጠብ፡፡ ይህንን ለተከታታይ ሳምንታት መደጋገም።

[03/03/17]   ስለ ፀጉርህ ትጨነቃለህን?

[09/26/16]   ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!
- - - መልካም በዓል ይሁንላችሁ!! - - -

[08/25/16]   ሂናን ከእንቁላል እና ከሎሚ ጋር በመቀላቀል መጠቀም ለፀጉር እድገት ፣ ፎሮፎርን ለማጥፋት እና የተፈጥሮ ቀለም ያለው ውብ ፀጉር እንዲኖረን ይረዳናል

[08/24/16]   አሸናፊዎች ተስፋ አይቆርጡም ፤ ተስፋ የሚቆርጡም አያሸንፉም!!!

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!

[08/22/16]   ሁል ጊዜም መታጠብዎ ክፋት ባይኖረውም ፀጉራችን የምናሽበት መንገድ እና የምንጠቀማቸው ሳሙና፣ ሻምፑ እና ኮንዲሽነሮች ግን ጥንቃቄ ይሻሉ።
የጸጉራችን ውበት እና ጤና በአስተጣጠባችን ላይ የተመሰረተ ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፥ ባለማወቅ የምንከውናቸው የዘወትር ግድፈቶች የፀጉራችን እድገት ያቀጭጫሉ ብለው ያምናሉ።
ከዚህ በታችም በኒውዮርክ ከፍተኛ የፀጉር ባለሙያዎች የቀረቡ ፀጉራችን በአግባቡ ለማጠብ የሚረዱ ስልቶችን እንመለከታለን።
1. ፀጉርን በውሃ ማራስ
ሻምፑ ከመጠቀማችን በፊት ፀጉራችን በውሃ በደንብ ማራስ (በቀዝቃዛ ውሃ ቢሆን ይመረጣል)፤ ፀጉርን በሞቀ ውሃ መታጠብ ግን በጭንቅላታችን ላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ቅባትን በማሳጣት ሻምፑዎች ወይም ኮንዲሽነሮች በቀጥታ ወደ ሰውነታችን እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል።
2. ለረጅም ፀጉር ከሻምፑ በፊት ኮንዲሸነር ይጠቀሙ
ፀጉራችሁ ከወገባችሁ ከወረደ ከሻምፑ በፊት ኮንዲሽነር ቀብተው ይሹት፤ ይህም የፀጉራችን ጫፎችን ከመሰባበር እና ከድርቀት ይታደጋል።
ይህ ዘዴ የፀጉር ቀዳዳዎች በእርጥበት እንዲሞሉ በማድረግ ደማቅ እና ለስላሳ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።
3. የፀጉራችንን ስረኛ ክፍል ብቻ ሻምፑ መቀባት
ፀጉራችንን ስንታጠብ ሁሉንም የፀጉራችን ክፍል ሻምፑ መቀባት አይጠበቅብንም።
አዲስ ፀጉራችን ከጭንቅላታችን አጠገብ የሚገኝ በመሆኑ ቅባታማ ነው።
በአንፃሩ የፀጉር ጫፎች የሚሰባበሩ፣ የሚቆሽሹ እና እድሜያቸውም ዘለግ ያለ በመሆኑ በሻምፑ ስንታጠብ ከጭንቅላታችን ጀምረን የፀጉራችን ጫፎች እንዲዳረሱ በደንብ ማሸት ያስፈልጋል።
በዋናነት ግን አዳዲስ ፀጉር የሚበቅልባቸውን የፀጉር ስሮች በደንብ ማሸት የፀጉራችን እድገት እና ውበት ያሳድጋል።
4. በቀስታ እና በጥንቃቄ ማሸት
የፀጉር ስሮች መጎዳት ለፀጉር መሰባበር እና መጨማደድ ይዳርጋል።
ፀጉራችንን ስንታጠብ እነዚህን የፀጉር ስሮች የምንጎዳቸው ከሆነ ለዚህ ችግር ስለሚያጋልጡን ስንታጠብ በእርጋታ እና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሊሆን ይገባል።
ከፀጉራችን ስር ጀምረን ሻምፑ በመቀባት በቀስታ በሁለት እጃችን ክብ እየሰራን ሳይሆን ወደ ታች እስከ ጫፉ ድረስ እንደ ማበጠር እያደረግን ሻምፑውን ማዳረስ፤ ይህም የፀጉር እድገትን እና የደም ዝውውርን ያፋጥናል።
በክብ ቅርፅ ማሸት ፀጉራችን እንዲተሳሰር በማድረግ ለማበጠር አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ ፀጉርን ስለሚበጣጥስ ይህን እንቅስቃሴ ማቆም ተገቢ ነው።
5. ሁለት ጊዜ ከመታጠብ መቆጠብ
ፀጉርዎን ለወራት ሳይታጠቡ ከቆዩ አልያም በጣም ካልቆሸሸ በስተቀር ሁለት ጊዜ ሻምፑ ተጠቅመው መታጠብ አይኖርብዎትም።
ፀጉርን በተደጋጋሚ መታጠብ ለፀጉር መነቃቀል ስለሚዳርግ መጠንቀቅ ተገቢ ነው።
6. ፀጉራችንን ከመካከለኛው እስከ ጫፉ ድረስ ኮንዲሽነር በመቀባት በደንብ ማሸት
ፀጉራችን በሻምፑ በደንብ ካለቀለቅን በኋላ በጨርቅ አዳርቀን ኮንዲሽነሩን መቀባት፤ ለተወሰነ ደቂቃም በፀጉር ማስያዣ አስይዘን መቆየት፤ የፀጉራችን ስር ግን ኮንዲሽነር ማግኘት የለበትም።
ተጨማሪ ምክሮች
የምንጠቀማቸው ሳሙናዎች፣ ሻምፑ እና ኮንዲሽነሮች ከፀጉራችን አይነት ጋር ሊስማሙ ይገባል።
ለምሳሌ ደረቅ ፀጉር ላላችሁ የሚያረጥቡ ሻምፑዎችን እና ኮንዲሽነሮች መጠቀም ያስፈልጋል።
ፀጉርዎ ቅባታማ ከሆነ ደግሞ በየቀኑ ቢታጠቡት ይመከራል።
ደረቅ እና የተለመደ አይነት ፀጉር ካለዎ ደግሞ በሳምንት ለሶስት ቀናት ቢታጠቡት መልካም ነው።
ፀጉርዎን በሙቅ ውሃ ከመታጠብ ይቆጠቡ፤ ታጥበው እንደጨረሱም ማበጠር የከፋ ጉዳት ያስከትላል።
ሻምፑ እና ኮንዲሽነሮችን ተጠቅመን ስንታጠብ በደንብ አለማሸት ለፎረፎር እና ለፀጉር መበጣጠስ ይዳርጋል።

[08/22/16]   ፎረፎርን ለማጥፋት ሊረዳዎት የሚችሉ 5 ነጥቦች
ፎረፎርን ለማጥፋት ሊረዳዎት የሚችሉ 5 ነጥቦች
ፎረፎር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ይከሰታል። በተለይም በጸጉር ቆዳችን ላይ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳቶች ሲሞቱ ነው ፎረፎር የሚከሰተው።
ፎረፎር ፀጉር እንዲያልቅና እንዲበጣጠስ ከማድረጉም በላይ የጸጉር ውበትንና ቆዳን ይጎዳል።
ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶች ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።
1. በተለያዩ ሻምፖዎች እና ሳሙናዎች መታጠብ
2. እርጎ እና በርበሬ፦ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው እርሾ በአንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጉረብረብ እና መንተብተብ ይፈጥራል። ለዚህም እንደ እርጎ ያሉ ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን የሚይዙ የምግብ አይነቶችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ ነው።
ሁለት ማንኪያ የደቀቀ በርበሬ እና 1 ኩባያ እርጎ በመደባለቅ ፀጉራችን የሚበቅልበትን ቆዳ መቀባት እና ከአንድ ስአት በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይነገራል።
3. እሬት (ኦሊ ቬራ)
እሬት ፎረፎርን ለመከላከል በተለይም በኢትዮጵያ ለበረካታ ዘመናት ስንጠቀምበት ኖረናል።
በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።
4. አፕል
አፕል ለፀጉር እድገት የሚረዳው ፕሮሳይኒዲን ቢ – 2 የተባለ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን ተከትሎ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።
ሁለት ማንኪያ የአፕል ጭማቂ ከሁለት ማንኪያ ውሃ ጋር በመቀላቀል መቀባት፤ ከዚያም ከ15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ብሎም የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።
5. ዝንጅብል
ዝንጅብል ለሰውነት መጉረብረብ ወይም መመረዝ የሚያጋልጡ ነገሮችን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል።
ስለሆነም ዝንጅብልን በመላጥና በማድቀቅ ከሰሊጥ ዘይት ጋር በመደባለቅና የፀጉር ቆዳን በመቀባት ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

[08/22/16]   የሩዝ ውሃን ለማራኪ የፊት ገፅታ እና ፀጉር
የሩዝ ውሃ የፀጉር ድርቀትን በማስወግድ በአንፃሩ ፀጉር የተሻለ ልስላሴ እንዲኖረው እና መተጣጠፍ እንዲችል ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ድምጽ September 30, 2015
የሩዝ ውሃ ለፀጉራችን እና ቆዳችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የቅርብ ጊዜ የጥናት ውጤቶች ይፋ አድርገዋል።
የሩዝ ውሃ የፀጉር ድርቀትን በማስወግድ በአንፃሩ ፀጉር የተሻለ ልስላሴ እንዲኖረው እና መተጣጠፍ እንዲችል ያደርጋል።
በተጨማሪም የተጎዳ ፀጉር እንዲያገግም ከመርዳት ባለፈ ፀጉራችን የተሻለ ገፅታን እንዲላበስ፣ የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖረንም ያግዛል ነው የተባለው ።
ለቆዳችንም ልስላሴን የሚያጎናፅፍ ሲሆን፥ በቆዳ ላይ የሚደርስን የማቃጠል አደጋ ለማቀዝቀዝ እና ለማከም፣ በፀሃይ የሚደርስን የማቃጠል ስሜትም በተመሳሳይ ለማጥፋት ይጠቅማል።
በመሆኑም በሩዝ ውሃ ፀጉርን መታጠብ የተለያየ የጤና ጠቀሜታዎችን ያስገኝልናል።
የሩዝ ውሃ በውስጡ በርካታ አንቲኦክሲዳንትስ፣ ማዕድኖች፣ ቫይታሚን ቢ ፣ ኢ ከመያዙም በላይ “ፒተራ” የተሰኘውንና የሞቱ ሴሎች እንደገና እንዲያድጉ የሚያደርገውን
ንጥረ ነገር በመያዙ ከእርጅና ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እና ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው።
የሚያስፈልጉ ነገሮች፦
ግማሽ ኩባያ የሩዝ ውሃ፣ ነጭ፣ ቡኒ ወይም ሌላ አይነት ሩዝ ሊሆን ይችላል)
2(ሁለት) ኩባያ ውሃ
አዘገጃጀት፦
1.አላስፈላጊ ነገሮች ከሩዙ ላይ ለማስወገድ በመጀመሪያ ሩዙን በደንብ ይጠቡት፣
2.ከዚያም ሩዙን በጎድጓዳ ሳህን በማድረግ ሩዙ ሙሉ በሙሉ በውሃ እስኪሸፈን ውሃ ይጨምሩበት፣
3.ሩዙ ከውሃው ጋር እንዲብላላ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ይተውት፣
4.ውሃው በደንብ እስኪደፈርስ ድረስ ቀስ እያሉ ውሃውን ከሩዙ ጋር ያቀላቅሉት(ይህም በሩዙ ውስጥ ያሉ በርካታ ማዕድናት እና ቫይታሚኖች በውሃው ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል)፣
5.ከዚያም ውሃውን በሌላ ንፁህ ሳህን በመገልበጥ ለመጠቀም ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ፣
ይህን ውሃ ቢፈልጉ ለፊትዎን አልያም ለፀጉርዎ መጠቀም ይችላሉ።
በውሃው ፊትዎን ወይም ፀጉርዎን በማሸት ከተጠቀሙ ከአንድ ወይም ሁለት ሰዓት በኋላ ይለቃለቁት።
ምንጭ፦ www.hairbuddha.net

[08/22/16]   ፀጉርህ ሸብቷል?
ሽበት ብዙውን ጊዜ የእርጅና እና የአረጋዊነት ምልክት ተደርጎ ይታያል። እርግጥ ነው፣ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ፀጉር ይሸብታል። ይሁን እንጂ ሽበት የሚመጣው በእርጅና ምክንያት ብቻ አይደለም። በቂ ምግብ እንዳለመመገብ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሸብቱ ታውቋል። ሽበት ጠቆር ያለ ፀጉር ባላቸው ላይ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ ጾታም ሆነ የፀጉር ቀለም አይመርጥም።
አንዳንዶች በመሸበታቸው ምክንያት ከዕድሜያቸው በላይ ያረጁ መስለው ሊታዩና ይህም አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ባለመሸበታቸው ምክንያት ትክክለኛው ዕድሜያቸውና መልካቸው አለመመሳሰሉ የሚያሳስባቸው ሰዎች አሉ።
ፀጉር ከሸበተ ሞተ ማለት አይደለም። እርግጥ ነው በዓይን የሚታየው ውጪያዊ የፀጉር ክፍል በድን ነው። የእያንዳንዱ ፀጉር ሥር ከቆዳ በታች ጠልቆ ይገባል። ይህ ክፍል የፀጉር ሥር
ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሕይወት ያለው የፀጉር ክፍል ይህ ብቻ ነው። የፀጉር ሥር እንደ ፀጉር ፋብሪካ ሆኖ ያገለግላል። በሥሩ ውስጥ ያሉት ሴሎች በብዛት ተራብተው ፀጉር ሲፈጠር የቀለም ሴሎች የሚሠሩትን ሜላኒን ይቀባል። በዚህም የተነሣ የቀለም ሴሎች ሜላኒን መሥራት ካቆሙ ፀጉር ነጭ ይሆናል።
የቀለም ሴሎች በድንገት ሜላኒን መሥራታቸውን የሚያቆሙት ለምን እንደሆነ ማንም የሚያውቅ የለም። በዚህም ምክንያት ለሽበት የሚሆን አስተማማኝ መድኃኒት ሊገኝ አልተቻለም። በተጨማሪም ሥራቸውን አቁመው የነበሩ የቀለም ሴሎች እንደገና መሥራት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ሊታወቅ ተችሏል። ፀጉርን አስመልክተው የተነገሩ ብዙ አባባሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። ኢየሱስ ከተናገራቸው ምሳሌዎች አንዱ ስለ ነጭ ፀጉር ይናገራል። “አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልም” ብሏል። ( ) እነዚህ ቃላት ሽበት ማስቀረትም ሆነ ማስወገድ ከሰው አቅም በላይ መሆኑ ከታወቀ ብዙ ዘመን ያለፈው መሆኑን ያመለክታሉ።
አንዳንዶች ሜላኒን እንደመወጋት ያሉትን አዳዲስ ሕክምናዎች ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ፀጉራቸውን ቀለም ይቀባሉ። ይህም ቢሆን ዛሬ የመጣ ልማድ አይደለም። የጥንቶቹ ግሪካውያንና ሮማውያን ፀጉራቸውን ቀለም ይቀቡ ነበር። የጥንት ግብጻውያን በበሬ ደም ፀጉራቸውን ያቀልሙ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን ይኖር የነበረው ታላቁ ሄሮድስ ዕድሜውን ለመሸሸግ ሽበቱን ቀለም ይቀባ እንደነበረ ተመዝግቧል።
ይሁን እንጂ በየጊዜው ቀለም መቀባት ጊዜና ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ የአንዳንዶችን ቆዳ ሊያስቆጣ ወይም ሊያቆስል ይችላል። ሽበትህን በቀለም ለማጥቆር ብትወስንም መቀባትህን ለማቆም የምትፈልግበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ ከሥር የሚያድገውን ሽበት መሸሸግ አስቸጋሪ ይሆንብሃል። ሽበት በአዎንታዊ ጎኑ የሚያምርና ከዚህ በፊት ያልነበረህን ግርማ ሞገስ የሚያስገኝልህ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “የሸበተ ፀጉር በጽድቅ መንገድ ሲገኝ የውበት ዘውድ ነው” ይላል።

[08/22/16]   ስለ ፀጉርህ ትጨነቃለህን?
በርካታ ሰዎች የፀጉራቸውን ሁኔታ በመስተዋት እያዩ በየቀኑ ብዙ ሰዓት የሚያሳልፉ ሲሆን ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንተም ትገኝበት ይሆናል። ስለ ፀጉር ማሰብ ወንድ ሴት የማይል ከመሆኑም በላይ ትልቅ ጭንቀት የሚፈጥርበት ጊዜም አለ።
ስለ ፀጉርህ አንዳንድ ሁኔታዎችን እወቅ
በራስ ቅልህ ላይ ስንት ፀጉሮች እንዳሉ ታውቃለህ? በአማካይ 100, 000 ይደርሳሉ። አንድ ነጠላ ፀጉር የሚያድገው ዕድሜ ልክ ሳይሆን ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ይረግፍና ከጥቂት የሽግግር ጊዜ በኋላ ከዚያው ቀዳዳ አዲስ ፀጉር መብቀል ይጀምራል። አንድ ነጠላ ፀጉር የራሱ የሆነ የአስተዳደግ ኡደት አለው። (በገጽ 17 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።) በዚህ ኡደት ምክንያት ምንም ዓይነት የፀጉር ችግር ከሌለበት ሰው እንኳን በእያንዳንዱ ቀን ከ70 እስከ 100 የሚደርሱ ፀጉሮች ይረግፋሉ።
የፀጉር ቀለም የሚለያየው በምን ምክንያት ነው? ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒድያ እንዲህ በማለት ያብራራል:- “የፀጉር ቀለም በአብዛኛው የሚወሰነው ሜላኒን የተባለው ጥቁር ቡናማ ቀለም ባለው ሥርጭትና መጠን ነው።” ሜላኒን በፀጉር፣ በቆዳና በዐይን ውስጥ የሚገኝ የተፈጥሮ ቀለም ነው። የቀለሙ መጠን በጨመረ መጠን ፀጉርም ጠቆር እያለ ይሄዳል። የሜላኒን መጠን እያነሰ ሲሄድ ደግሞ የፀጉር ቀለም ከጥቁር ወደ ቡናማነት ወይም ወደ ቢጫነት ያደላ ይሆናል። ፀጉሩ ምንም ሜላኒን ከሌለው ግን ሙሉ በሙሉ ነጭ ይሆናል።
ከፎረፎር ሌላ ብዙዎችን የሚያሳስባቸው የፀጉር መርገፍ አለዚያም የፀጉር መሸበት ነው።

[07/18/16]   (NaturalNews) Ginger is historically considered one of
nature’s true wonders. Other than being a very
delectable spice, it is known to have a long list of
health benefits. It is used to treat conditions ranging
from nausea to heart problems. But not a lot of people
know that ginger can actually be used as a form of
health treatment. What are the different conditions
where ginger can be used as a hair treatment?
Here is a list of the benefits it can give to hair health:
Dandruff
Dandruff is one of the most difficult hair and scalp
problems to eradicate. Even with the presence of so
many specialized hair products for treating dandruff,
it continues to persist, causing frustration for men
and women worldwide. Ginger can actually prove to be
the answer to your dandruff problems. This is because
ginger has natural antiseptic properties that make it
an ideal fit for taking down dandruff.
You can make your own anti-dandruff mix at home
with the help of ginger. All you need to do is mix 2
tablespoons of freshly grated ginger with 3
tablespoons of sesame or olive oil and a dash of lemon
juice. Massage this mix into the scalp then leave it on
for 15-30 minutes before rinsing. You must use your
anti-dandruff mix at least three times a week until
you’re actually able to get rid of dandruff.
Hair Loss
People, especially men, have a higher tendency to lose
hair as they age. This can prove especially awkward,
as hair loss can dramatically change how a person
looks. Because of this, a lot of people worldwide are
investing in hair growing treatments with varying
results. But if you want your hair to grow back, you
must try using ginger. This is because ginger has the
natural ability to stimulate blood flow to the scalp.
Improved blood flow stimulates the hair follicles and
ultimately results in restored hair growth.
You can make your own hair growth mix at home with
the help of ginger. All you need is a tablespoon of
grated ginger. Mix it with 1 tablespoon of jojoba or
olive oil. Apply this mixture into your scalp, massaging
it in circular motions to improve blood flow even
further. After massaging this mixture, leave it on for
30 minutes. You shall experience a warm sensation in
your scalp, an indicator that the mix is actually
working. Rinse off the mixture. You can use shampoo
afterwards if desired.
Treating your head right with the help of ginger
A lot of people are investing a lot of money for
products and services designed to supposedly free
them from different hair and scalp ailments. Little do
these people know that they can actually save a ton
of money by going to ginger as their primary source
for hair and scalp treatment. Best of all, they can do
all these treatments in the comfort of their home and
even by themselves! Ginger is inexpensive, practical
and effective. What more can anyone want for hair
treatment, right?

[07/17/16]   Dear our customer we are Ready to give u sevice of Hair cutting, Bear cutting, Steam service, Leg washing, Brushing Hair in Black Hina and scarping and other services so please came to us and refresh ur self In our Beauty burbury

in case of if u want ask something thing we r in Around Ruzetera commercial Bank of Ethiopia 1st Floor
call us in :- +251 91 576 4179

[07/17/16]   አላማችን ፅጉር ማስትካካል ብቻ ሳይሆን ውበትንም ማላብስ ነው

[07/01/16]   አንድ የእምነት ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ ቤት
ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።
ጸጉር አስተካካይ፦ታውቃለህ ፈጣሪ የለም
ተስተካካይ፦በመገረም እንዴት?
አስተካካይ፦አይታይህም?
ተስተካካይ፦ምኑ?
አስተካካይ፦እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ
ጦርነት፣ረሀብ፣ችግር፣ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ ፈጣሪ አንዴ
ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።
ተስተካካይ፦ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም
አስተካካይ፦ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?
ተስተካካይ፦ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ጺሙ የተንዠረገገ ሰው
አይኖርም ነበር።
አስተካካይ፦እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ አለመምጣታቸው ነው
እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ የተንዠረገገ እና የተንጨባረረ ጸጉር
አታይም ነበር።
ተስተካካይ፦ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው ነው ሰው
ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም።

Want your business to be the top-listed Hair Salon in Dire Dawa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Ashewa Mina Mall
Dire Dawa
DD