ኤልያስ የወንዶች ቤተውበት L-YES Mens beauty salon

ኤልያስ የወንዶች ቤተውበት               L-YES Mens beauty salon

Comments

የእግዝሐብሔሪ ሰለም ከእናንተ ገሪ ይሁን

a style of cutting, arranging, or combing the hair; hairdo; coiffure

odaa style

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

[04/28/18]   😂😂
ኧረ ሙሉውን አንብቡት😂😂
...
ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ፀጉር ቤት አንድ ጀርመናዊ ቄስ ፀጉሩን ይስተካከል እና ሂሳብ ስንት እንደሆነ ፀጉር አስተካካዩን ይጠይቀዋል…

ፅጉር አስተካካዩም «ጌታዬ ለእርሶ አደረኩ ማለት ለጌታ አደረኩ ማለት ስለሆነ አላስከፍሎትም… በፍፁም አልቀበሎትም» ብሎ ይሸኛቸዋል…
:
በነገታው ጠዋት ፀጉር አስተካካዩ ወደ ሥራ ሲገባ ከበሩ ስር ከቄሱ የተላከ አጭር የምስጋና ፅሁፍ እና በርከት ያሉ የፀሎት መፀሃፎች እንደ ስጦታ ያገኛል……👼
:
በሌላ ቀን ደግሞ አንድ እንግሊዛዊ የፖሊስ መኮንን ፀጉሩን ይከረከም እና ሂሳብ ስንት እንደሆነ ይጠየቃል……
ፀጉር አስተካካዩም ‹አንተ ህብረተሰቡን የምታገለግል ፖሊስ ስለሆንክ
አላስከፍልህም ለህብረተሰቡ እንዳደርኩ ነው የምቆጥረው ስለዚህ ነፃ ነው» ብሎ ይሸኘዋል……
:
በነገታው ጠዋትም ፀጉር አስተካካዩ ወደ ሥራ ሲገባ ከበሩ ስር ከፖሊስ መኮንኑ የተላከ አጭር የምስጋና ፅሁፍ እና በርከት ያሉ የተለያዩ ስጦታዎችን ያገኛል……
:
በሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ሀበሻ ፀጉሩን ይስተካከል እና ሂሳብ ይጠይቃል ፀጉር አስተካካዩም… «ታላቁን የኦሎምፒክ ጀግና
አበበ ቢቂላን እና ኃይሌ ገብረስላሴን ካፈራች ሀገር የመጣ ሀበሻን ማስከፈል ይከብዳል…… ለነሱ ክብር እንዳደረኩት ስለምቆጥረው ነፃ ነው» ብሎ ይሸኘዋል……
:
በነገታው ጠዋትም ፀጉር አስተካካዩ ወደ ሥራ ሲመለስ


አስራ ሁለት ሀበሾች
ፀጉራቸውን ለመስተካከል ወረፋ ይዘው ነበር :
..
😂😂😂😂
አይ ሃበሻ
ሲኦል እራሱ በነፃ ከተባልን እኮ ሄደን እንሰለፋለን
:
መልካም ጊዜ

[04/25/18]   Come and get your hair done with exclusive
designs that will bring the best in you.

Timeline Photos

Timeline Photos

[07/02/17]   አንድ የእምነት ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ
ቤት
ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።
ጸጉር አስተካካይ፦ታውቃለህ ፈጣሪ የለም
ተስተካካይ፦በመገረም እንዴት?
አስተካካይ፦አይታይህም?
ተስተካካይ፦ምኑ?
አስተካካይ፦እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ
ጦርነት፣ረሀብ፣ችግር፣ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ
ፈጣሪ አንዴ
ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።
ተስተካካይ፦ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም
አስተካካይ፦ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?
ተስተካካይ፦ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ጺሙ
የተንዠረገገ ሰው
አይኖርም ነበር።
አስተካካይ፦እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ
አለመምጣታቸው ነው
እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ የተንዠረገገ እና የተንጨባረረ
ጸጉር
አታይም ነበር።
ተስተካካይ፦ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው
ነው ሰው
ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም።

Timeline Photos

Timeline Photos

Timeline Photos

amazing beard and mustache

£~¥€$

just now

Timeline Photos

Timeline Photos

[12/02/16]   ፀጉር የውበት አክሊል ነው ፡፡

[11/29/16]   Dear our customer we are Ready to give u sevice
of Hair cutting, Bear cutting, Steam service, Brushing Hair in Black Hina and
scarping and other services so please came to
us and refresh ur self In our Beauty barbery
in case of if u want ask something thing we r in
Around commercial Bank of Ethiopia melka branch new business center
call us in :- +251 931918434
L-YES Mens Beauty Salon

[11/29/16]   ስለ ፀጉርህ ትጨነቃለህን?
በርካታ ሰዎች የፀጉራቸውን ሁኔታ በመስተዋት እያዩ በየቀኑ ብዙ
ሰዓት የሚያሳልፉ ሲሆን ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንተም
ትገኝበት ይሆናል። ስለ ፀጉር ማሰብ ወንድ ሴት የማይል
ከመሆኑም በላይ ትልቅ ጭንቀት የሚፈጥርበት ጊዜም አለ።
ስለ ፀጉርህ አንዳንድ ሁኔታዎችን እወቅ
በራስ ቅልህ ላይ ስንት ፀጉሮች እንዳሉ ታውቃለህ? በአማካይ
100, 000 ይደርሳሉ። አንድ ነጠላ ፀጉር የሚያድገው ዕድሜ
ልክ ሳይሆን ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ብቻ
ነው። ከዚያ በኋላ ይረግፍና ከጥቂት የሽግግር ጊዜ በኋላ ከዚያው
ቀዳዳ አዲስ ፀጉር መብቀል ይጀምራል። አንድ ነጠላ ፀጉር የራሱ
የሆነ የአስተዳደግ ኡደት አለው። (በገጽ 17 ላይ የሚገኘውን
ሣጥን ተመልከት።) በዚህ ኡደት ምክንያት ምንም ዓይነት የፀጉር
ችግር ከሌለበት ሰው እንኳን በእያንዳንዱ ቀን ከ70 እስከ 100
የሚደርሱ ፀጉሮች ይረግፋሉ።
የፀጉር ቀለም የሚለያየው በምን ምክንያት ነው? ዘ ወርልድ ቡክ
ኢንሳይክሎፒድያ እንዲህ በማለት ያብራራል:- “የፀጉር ቀለም
በአብዛኛው የሚወሰነው ሜላኒን የተባለው ጥቁር ቡናማ ቀለም
ባለው ሥርጭትና መጠን ነው።” ሜላኒን በፀጉር፣ በቆዳና በዐይን
ውስጥ የሚገኝ የተፈጥሮ ቀለም ነው። የቀለሙ መጠን በጨመረ
መጠን ፀጉርም ጠቆር እያለ ይሄዳል። የሜላኒን መጠን እያነሰ
ሲሄድ ደግሞ የፀጉር ቀለም ከጥቁር ወደ ቡናማነት ወይም ወደ
ቢጫነት ያደላ ይሆናል። ፀጉሩ ምንም ሜላኒን ከሌለው ግን ሙሉ
በሙሉ ነጭ ይሆናል።
ከፎረፎር ሌላ ብዙዎችን የሚያሳስባቸው የፀጉር መርገፍ
አለዚያም የፀጉር መሸበት ነው።

[11/29/16]   ሂናን ከእንቁላል እና ከሎሚ ጋር በመቀላቀል መጠቀም ለፀጉር
እድገት ፣ ፎሮፎርን ለማጥፋት እና የተፈጥሮ ቀለም ያለው
ውብ ፀጉር እንዲኖረን ይረዳናል

[11/29/16]   ፎሮፎር – Dandruff፡ የሚፈጠርበት ምክንያት፣ ህክምናውና
ጠቃሚ ምክሮች የጸጉር ጤና
በጭንቅላታችን ቆዳ ላይ የሚገኙ ሴሎች ተፈጥሮአዊ በሆነ ዑደት
በየጊዜው እየሞቱ በአዳዲስ ሴሎች እየተተኩ ይሄዳሉ፡፡ ይህ
የሴሎች የመተካከት ሂደት በጤነኛና የፎሮፎር ችግር በሌለባቸው
ሠዎች ላይ እስከ 1 ወር የሚደርስ ጊዜን ሊወስድ ይችላል በዚህ
ጊዜ ውስጥም የሞቱት ሴሎች ቀስ በቀስ ከቆዳ ላይ
እየተወገዱና እየተተኩ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን በተለያዩና
በእርግጠኛነት ይህ ነው በማይባል ምክንያት አዳዲስ የጭንቅላት
ቆዳ ሴሎች በብዛትና በፍጥነት እየተፈጠሩ ይሞታሉ እነዚህ
ሴሎች ከትክክለኛው ተፈጥሮአዊ የመተካከያ በጣም ባነሠ ጊዜ
ውስጥ ስለሚፈጠሩና ስለሚሞቱ እየተገፉ ወደ ላይኛው
የጭንቅላታችን የቆዳ ክፍል በብዛት ይወጣሉ በቆዳችን ላይ
ባለው ተፈጥሮአዊ ቅባት ምክንያትም እነዚህ የሞቱ ሴሎች እርስ
በእርሳቸው በመጠባበቅ በመጠን እያደጉ ነጫጭ ርጋፊዎችን
በመፍጠር በፎሮፎር መልክ ከፀጉራችን ላይ ይረግፋሉ፡፡ ይህ
የሞቱ ሴሎች ከጭንቅላት ላይ የመርገፍ ሂደት በጤነኛና ፎሮፎር
በሌለባቸው ሠዎችም ላይ የሚከሠተ ቢሆንም አዲስ
የሚፈጠሩና የሚሞቱት ሴሎች መጠን ተመጣጣኝ ስለሆነ
ሣይስተዋሉ ከፀጉር ላይ ይወገዳሉ፡፡ የፎሮፎር ችግር ባለባቸው
ሠዎች ላይ የሚስተዋለው በከፍተኛ መጠን የጭንቅላት የቆዳ
ሴሎች መፈጠርና መሞት እንዲከሠት ከሚያደርጉ ምክንቶች
ውስጥ Malassezia (ማላሴዚያ) የተባለው የፈንገስ አይነት
አንዱ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያሣያሉ ይህ ተዋህሣያን ጉዳት
ሳያስከትል በጭንቅላታችን ቆዳ ላይ የሚኖር ሲሆን በተለያዩ
ምክንያቶች ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ በመራባትና
ተፈጥሮአዊውን የቆዳችንን ቅባት በማብላላት የሚፈጥረው
ኬሚካል ቆዳችን እንዲቆጣና የተለያዩ ለውጦች እንዲከሠቱ
በማድረግ ከላይ ያየነውን ያልተመጣጠነነና ጊዜውን ያልጠበቀ
የሴሎች መተካካት እንዲኖርና ፎሮፎር እንዲፈጠር ምክንያት
ይሆናል፡፡
ፎሮፎር በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሠት ችግር ቢሆንም
በበለጠ መልኩ ግን ወጣቶችና ጐልማሶች ለችግሩ ተጋላጮች
ናቸው የተለያዩ ጥናቶች ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በፎሮፎር
እንደሚጠቁ አሣይተዋል፡፡
ፎሮፎር እንዲባባስ የሚያደርጉ ምክንያቶች
ፎሮፎር ከላይ ባየነው መልኩ መፈጠር ከጀመረ በኋላ በተለያዩ
ምክንያቶች አማካኝነት እየተባባሠ ሊሄድ ይችላል ከእነዚህም
ውስጥ
በተለያዩ የፀጉር መንከባከብያ ምርቶች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ
ኬሚካሎች በተለይም በጄሎች፣ እስኘሬዎች፣ ሻምፖዎችና
ቅባቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ከቆዳችን አይነት ጋር
ላይስማሙ ስለሚችሉ አለርጂኮችን ይፈጥራሉ በዚህም ምክንያት
የጭንቅላት ቆዳ ላይ መቅላት፣ መቁሠልና ማሣከክ የመሣሠሉት
ሁኔታዎች ይኖራሉ ይህም ፎሮፎርን ለማባባስ ከፍተኛ ሚና
እንደሚጫወት ይታወቃል በመሆኑም እነዚህን ምርቶች ስንጠቀም
እንደቆዳችን አይነት የሚስማማንን በአግባቡ መርጠን መሆን
ይኖርበታል
በተፈጥሮ የጭንቅላታችን ቆዳ በጣም ደረቃማ ወይም
ቅባታማ መሆን ችግሩን እንደሚያባብሠው የተለያየ ጥናቶች ያሣያሉ
በመሆኑም እነዚህን የቆዳ ችግሮች ለመቆጣጠር የቆዳ ህክምና
ባለሙያ በማማከር አስፈላጊውን ምክርና ህክምና ማግኘቱ
የፎሮፎር ችግር እንዳይባባስ ይረዳል፡፡
ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ ቀዝቃዛማ አየር ችግሩን
ሊያባብሠው ይችላል በተለይም በዚህ የአየር ንብረት ወቅት ፀጉርን
አጅለው የሚሸፍኑ ከፍያዎችና ስካርፎችን መጠቀም የችግሩን
መጠን ከፍ እንደሚያደርገው ጥናቶች ያሣያሉ፡፡ ከቀዝቃዛ አየር
በተጨማሪም ከፍተኛ ሙቀትም የችግሩን መባባስ ያስከትላል፡፡
የተለያዩ ከቆዳ ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ህመሞች
በተለይም seborrheic dermatitis (ሴቦሪክ ዳርማታይቲስ)፣
Eczema (ኤክዚማ)፣ Psoriasis(ሶሪያሲስ) የመሣሠሉት
ፎሮፎርን ያባብሣሉ
ከነርቭ ጋር ተያይዘው የሚከሠቱ ህመሞች እንዲሁም
ፖርኪንሠኒዝም (parkinsonism) ያለባቸው ሠዎች ከሌላው
በተለየ መልኩ ለችግሩ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው
በተጨማሪም የሠውነትን በሽታ የመከላከል አቅም (Immunity)
የሚጐዱ ህመሞች ያሉባቸው ሠዎችም ችግሩ ሊባባስባቸውና
ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡
ደካማና ተከታታይነት የሌለው የፀጉር ንፅህና አጠባበቅ
ለፎሮፎር መባባስ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በየጊዜው
በሚስማሙን የፀጉር ንፅህና መጠበቂያዎች አማካኝነት ፀጉራችንን
መታጠብና ማፅዳት ይኖርብናል በተለይም ከፍተኛ ላብን ከሚፈጥሩ
እንቅስቃሴዎች በኋላ በአግባቡ የፀጉርን ንፅህና መጠበቅ
ያስፈልጋል፡፡
አመጋገብ፡- በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ (Vitamin B
complex) እና ዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትሮ አለመመገብ
ችግሩን ሊያባብሠው ይችላል በአንፃሩ ስኳርን አብዝቶ መጠቀም
ደግሞ ፎሮፎርን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር
የተለያዩ ጥናቶች አሣይተዋል፡፡
ጭንቀት፡- ጭንቀት በጤናችን ላይ የተለያዩ ችግሮች
እንዲከሠቱ የሚያደርግ መሆኑ ይታወቃል ከዚህም ጋር ተያይዘው
በሚከሠቱ የተለያዩ ኬሚካላዊ ለውጦች ምክንያት ፎሮፎርን
እንዲባባስ የማድረግ አቅም አለው፡፡
ፎሮፎርን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መንገዶች
የፎሮፎር ችግርን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በተለያዩ
መንገዶች በደንብ መቆጣጠር ይቻላል የመጀመሪያው መንገድ
የፀጉርን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ ሲሆን ከፀጉራችን አይነት ጋር
ተስማሚ የሆኑ መታጠቢያ ሳሙናዎችና ሻምፖዎችን አንዲሁም
የፀጉር ቅባቶችን በመምረጥ መጠቀም ይኖርብናል ወዛም ቆዳና
ቅባትማ ፀጉር ያላቸው ሠዎች ደረቃማ ቆዳ ካላቸው ሠዎች
የተለየ የፀጉር ንፅህና መጠበቂያዎችን መጠቀም ያለባቸው
ሲሆን ለፀጉሬ አይነት የትኛው ይስማማኛል የሚለውን ለመምረጥ
በምርቶቹ ላይ የሚጻፈውን ማብራሪያ በደንብ ማንበብና መረዳት
ይኖርብናል ይህን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ
ባለሙያዎችን ጠይቆ መረዳትና መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ተጨማሪ
መዋቢያዎችን ለፀጉራችን የምንጠቀም ከሆነ ለተወሠነ ጊዜ
ማቆምና ለውጡን ማየት ይኖርብናል በተጨማሪም የሚከተሉት
ነጥቦች ተጨማሪ የመቆጣጠሪያ መንገድን ሊፈጥሩልን ይችላሉ።
• የምንወስደውን የዚንክ (Zinc) መጠን ከፍ ማድረግ፡- ዚንክ
ለፎሮፎር ምክንያት የሆነውን ፈንገስ ለማጥፋት ከማስቻሉም
ባሻገር የጭንቅላታችን ቆዳ የሚያመነጨው ቅባት ተመጣጣኝ
እንዲሆን በማድረግ ፎሮፎርን ይቆጣጠራል፡፡ ዚንክን ከአሣ፣ የስብ
መጠኑ ትንሽ ከሆነ ስጋ፣ ከስንዴ፣ ከለውዝ፣ ከዱባፍሬ፣ እንዲሁም
ከአጃ ልናገኘው እንችላለን
• በቫይታሚን ቢ ኮምኘሌክስ (vitaminB complex) የበለፀጉ
ምግቦችን አዘውትሮ መጠቀም ፎሮፎርን ለመቆጣጠር
እንደሚያስችል የተያዩ ጥናቶች ያሣያሉ
ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣
ጥራጥሬዎች እንዲሁም አሣ፣ ጉበት ጥሩ ምንጮች በመሆናቸው
በአመጋገባችን ውስጥ አካተን
መጠቀም ይኖርብናል በተጨማሪም በአሣ ውስጥ የሚገኘው
ኦሜጋ 3 (Omega 3) የተባለው ጠቃሚ የቅባት አይነትም
ተጨማሪ የመከላከል ጥቅምን
ያጐናጽፋል
• የምንጠቀመውን የስኳር መጠን መቀነስ ፡-ከፍተኛ መጠን
ያለው ስኳር መጠቀም የተለያዩ የፈንገስ አይነቶች እንዲራቡ ምቹ
ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል::
"ኤልያስ የወንዶች ቤተውበት"

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Dire Dawa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Dire Dawa
Melka Jebdu