Bokku
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bokku, Health/Beauty, Nek'emte.
23/09/2026
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን አጥፊ መንገድ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገቡ
********************
የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ እና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገብተዋል።
ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃ እና ዘመቻ ዋና መምሪያዎች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ሕፃናትን አስገድዶ በመመልመል ለጦርነት በመማገድ፣ የትግራይ ሕዝብን ስቃይ እያባዛ ያለውን የህወሓት እኩይ ሴራ በመቃወም ጄኔራሉ ከድርጅቱ መለየታቸው የሕገ-ወጡን የህወሓት ቡድን ሕልውና ማክተሙን ያሳያል።
16/09/2026
በስልጠና ማዕከላት ገብተው ለሚሰለጥኑ የብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ ተሳታፊዎች የሚሰጥ ስልጠና የአዋቂዎች የስልጠና አሰጣጥ መርህን /Adult learning principles/ የሚከተል ሲሆን በሁሉም የስልጠና ሞጁሎች ላይ ሰልጣኝ ተኮር እና አሳታፊ የስልጠና አሰጣጥ ዘዴ ተግባራዊ ያደርጋል።
በዚሁ መሰረት እንደ የስልጠና ሞጁሎቹ የሰልጣኞችን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ የተለያዩ የስልጠና ዘዴዎች (የግል ንባብ፣ የቡድን ውይይት፣ ፅብረቃ እና የመስክ ምልከታ) በጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
ሰልጣኞች በቂ ጊዜ ተሰጥቷቸው በየስልጠና ጭብጦቹ፣ ጽንሰ ሃሰቦች እና ንድፈ ሀሳብ ላይ በቡድን እንዲወያዩ፣ እንዲከራከሩ እና ሀሳቦቻቸውን እንዲገልፁ ይደረጋል፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
16/09/2026
በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።
ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።
ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
Wishing our students across Ethiopia a successful new academic year!
Our young generation is Ethiopia’s greatest wealth. As the 2019 academic year begins, I encourage every student to learn with curiosity, pursue excellence, and develop the skills to shape our nation’s future. Much of what we are building today is for generations to come. As the beneficiaries and custodians of that future, your dedication is vital to carrying Ethiopia’s proud legacy of civilization forward.
To our teachers, your dedication is central to building a capable and confident generation. Continue inspiring our students, nurturing their potential, and equipping them with the knowledge and values to thrive.
To all stakeholders in our education sector, I wish you a successful and rewarding academic year.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
16/09/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
"በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።
ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።
ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።"
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
14/09/2026
ከንግስት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት የተወሰደ የሰላም መልዕክት! 🕊
ሰላም ለኢትዮጵያችን!