Ethio Bankers Association

Ethio Bankers Association

Share

Financing Matters

01/07/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወሰነ ።👏
🚩በዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጥል ተወስኗል ።


ሦስተኛ ስብሰባውን ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ዛሬ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውስኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው።

"አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል።

ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ሌሎች ለብሔራዊ ባንክ ቦርድ ቀርቦ መጽደቁንም መግለጫው አመልክቷል።

ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2022 ጀምሮ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ብድራቸው አምስት በመቶ የሚሆነውን ለዚህ የቦንድ ግዥ ሲያውሉ ቆይተዋል። በዚህ መመሪያ መሠረት የገዙት ቦንድ የሚመለሰው (ለቦንድ ግዢ ያዋሉት ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው) ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ሲሆን ፣ ባንኮቹ መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ወር አንስቶ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2024 ድረስ የገዙት የቦንድ መጠን 94 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት ዕዳ መግለጫ ያመለክታል።

በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ያሳለፈው ሌላኛው ውሳኔ በባንኮች ላይ የተጣለውን የብድር ዕቀባ የተመለከተ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት በባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጠል ኮሚቴው ወስኗል።

ለዚህም የሰጠው ምክንያት አሁን ላይ የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ እየተስተዋለ ቢሆንም ይህንን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕድገት ጣሪያ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጽ ነው።
Muktarovich Ousmanova

25/05/2023

አንድ ጓደኛዬ ስለ አንድ ባንክ የሰዉ ሀይል ቅጥር ሲያወራልኝ ባንኩ በቅጥር ላይ ያለዉን ብልሹ አሰራር ካላስቀረ አርሶ አደር እርፉን እየጣለ በሮቹን ሸጦ ይገባል እንጂ ዩኒቨርሲቲ ተምረዉ የመጡ ልጆቹ በእዉቀታቸዉ አይገቡም አለኝ። ይህ ባንክ ማን ነዉ?

01/11/2022

ሁሉም ሰዉ ሻጭ ነዉ

01/11/2022

ምርት እና አገልግሎትን እንዴት መሸጥ አለብን?

Photos from Ethio Bankers Association's post 06/07/2022

2021/2022 የባንኮች ሰርፕራይዝ ሚሞ

18/04/2022

WELL COME TO THIS PAGE

Photos from Banking Matters's post 10/03/2022
03/03/2022
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Abu Dhabi?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Ehiopia
Abu Dhabi
NICE