Biruh Tesfa

Biruh Tesfa

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Biruh Tesfa, Health/Beauty, Dubai.

02/11/2025

ህብረ ብሄራዊነት፣ አሳታፊነት ፣ ብዝሃነት እና አቃፊነት የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ ነው ።

አቶ ትግሉ ገብሬ
የአዲስ ከተማ ወረዳ 4 ብልፅግና ፓርት ቅ/ጽ/ቤት

የብልፅግና ፓርቲ ዋና አላማ ህብረ ብሄራዊነቱን የጠበቀ እና የጋራ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያለው ማህበረሰብ መገንባት ነው።

ስለ ህብረ ብሄራዊነት ስናወራ ሁሉንም ብሔረሰቦችን ፣ ኃይማኖቶችን ወይም ማንነቶችን ያካተተ ነገር ግን የትኛውንም ብሔር የማያገለል ማለታችን ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሄራዊነት በአሳታፊነት ፣ ብዙሃነት እና አቃፊነት መገለጽ አለበት ብሎ ያምናል።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት ብዘኃነትን እንደ ልዩ ሥጦታ ይመለከተዋል። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የእርስ በርስ መተሳሰራችን መገለጫ እና የጠንካራ አንድነታችን ምልክት ነው። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም ፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት የጋራ የማንነታችን መገለጫ ፣ የአንድነታችን እና የጠንካራ ትስስራችን ምልክት ነው። የህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም ፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ብዙ ሆነን አንድ አንድ ሆነን ብዙ በመሆን ለጋራ ዓላማና ተልዕኮ የተሰባሰብንበት አንድነት ነው።

በብዝሃነታችን ውስጥ እየበራን በአንድነታችን ጠንክረን መገስገስ የውበታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው።
ፍትህ ከተረጋገጠ ሰብአዊ ክብር ከሰፈነ ብልፅግና ከመጣ እንደ ሀገር ቀጣይነታችን ይለመልማል። ነገር ግን የጋራ ህብረ ብሄራዊነት እነዚህ ምሰሶዎች ከተሳኩ ብቻ ሳይሆን ለዓላማው መሳካት የበኩላችንን ሚና እንድንጫወት ስለሚያስችሉን በጋራ ወደ ብልፅግና እንሄዳለን በሚለው መመሪያ መሰረት ፓርቲያችን ብልጽግና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

28/10/2025
Photos from Prosperity party -አዲስ ከተማ ወረዳ 4's post 21/10/2025
Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 15/10/2025
Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 13/10/2025
18/09/2025

የዘመናት ሕልም የአፍሪካ ተምሳሌት ኢትዮጵያ በብልፅግና ጎዳና!!

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ሀገራዊ ትንሳኤያችንንና የማንሰራራታችንን ዘመን ያመላክታል። ይህ ታላቅ ስኬት "ተጠናቋል! እንኳን ደስ አለን!" በማለት ብቻ የምንገልጸው ሳይሆን፣ የአባይ ግድብ ዳግማዊ አድዋ ሆኖ የኢትዮጵያን አንድነትና የመደመርን ሚስጥር ዳግም ያሳየበት ታሪካዊ ወቅት ነው።

ህዳሴ ልክ እንደ አድዋ ድል፣ አባይም የኢትዮጵያውያን ቆራጥነት፣ ጽናትና በጋራ ሲቆሙ ምንም ነገር ማከናወን እንደሚችሉ ዳግም ያስመሰከረ ሀገራዊ ኩራታችን ነው።

ይህ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የአባቶቻችን የዘመናት ምኞት፣ የእኛ ትውልድ ደግሞ ላብና ደሙን አፍስሶ እውን ያደረገው ታላቅ እውነታ ነው። ከሀሳብ ፅንስነቱ ጀምሮ በስንት መሪዎች አልፎ በስንት ውጣ ውረዶች ታጅቦ ዛሬ ለፍጻሜ በቅቷል። ይህ ግድብ ውሃ የሚቆልፍ ግድግዳ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንን የማይናወጥ ጽናት፣ አንድነት እና "ይቻላል" ባይነት ለዓለም ያወጀ ታሪካዊ ማህተም ነው።

የዘመናት ህልም የኛ ኩራት ይህም ግድብ የውሃና የሃይል ምንጭ ብቻ ሳይሆን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የማይናወጥ የሉዓላዊነትና የብልጽግና ተስፋ ምልክት ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።

#የመደመርመንግሥት
#መደመር

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Dubai?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Dubai