Alemayehu Girma
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alemayehu Girma, Health/Beauty, Ahmedzake, Cairo.
31/03/2026
#ዛሬ በቀን 31/03/2026 እግዚአብሔር በወንድ ልጅ ባርኮናል ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን። #ዕዝራ #አለማየሁ እንኳን በሰላም መጣልን❤️
#እግዚአብሔርን
#ማመስገን
#መልካም
#ነው።
30/11/2025
#የአምላካችን #ክንዶች
━━━━━━━━━━━━━
📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል: ዘዳግም 32-34
"''ዘላለማዊ አምላክ መኖሪያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤ ‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል። ''
ዘዳግም 33:27"
ሙሴ በእግዚአብሔር ላይ ስንታመን፣ እርሱን መጠጊያችን ስናደርግና በእርሱ ጥላ ሥር መኖርን ስንመርጥ የምናገኘውን ታላቅ በረከት ሲገጽል የዚህ የዘላለም አምላክ ክንዶች ከእኛ በታች እንደሚሆኑ ይናገራል። ይህም ማለት ህጻናት ልጆቻችንን በክንዶቻችንን ላይ አድርገን እንደምንሸከማቸው፣ እነርሱም ሙሉ በሙሉ ክብደታቸውን በእኛ ላይ አድረገው በመታቀፍ፣ ፍጹም ደህንነትና ሰላም እንደሚሰማቸው፣ ልክ እንደዚሁ የእግዚአብሔር ክንዶች ከእኛ በታች ሆነው ይሸከሙናል። ይህ እንዴት ያለ ትልቅ እድል ነው! እስቲ ስለእነዚህ ክንዶች ጥቂት እንይ።
1 ብርቱ ክንዶች
ዳዊት ስለ እግዚአብሔር ክንዶች እንዲህ በማለት ይዘምራል:-
“ አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤
እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።” መዝ 89:13
በእርግጥም የአምላካችን የእግዚአብሔር ክንዶች ብርቱ ናቸው። ለእርሱ የሚሳነው አንዳች ነገር የለም። የእርሱ ብርቱ ክንዶች ለመሸከም የሚከብዳቸው ምንም አይነት ክብደት የለም።
2 የተዘረጉ ክንዶች
የእግዚአብሔር ክንዶች ብርቱ ብቻ ሳይሆኑ ደግሞ የተዘረጉ ክንዶች ናቸው።
“ በታላቁ ኀይሌና በተዘረጋው ክንዴ ምድርን፣ በላይዋ የሚኖሩትን ሰዎችና እንስሳት ፈጥሬአለሁ፤ ለምወደውም እሰጣለሁ።” ኤር 27:5
የእርሱ ክንዶች እኛን ለመፍጠር ተዘርግተዋል። እኛን ለማዳንም በመስቀል ላይ እንዲሁ ተዘርግተዋል። ዛሬም እለት እለት በእርሱ ላይ እንድንደገፍ፣ በክንዶቹም ሊሸከመን የሚወደው ይህ አምላክ ክንዶቹን ወደ እኛ ዘርግቶአል።
የእርሱ ክንዶች የታጠፉ ክንዶች ሳይሆኑ የተዘረጉ ክንዶች ናቸው። ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
3 ቅዱስ ክንዶች
"ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤
እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤
ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣
ማዳንን አድርገውለታል።" መዝ 98:1
የእግዚአብሔር ክንዶች ቅዱስ ክንዶች እንደሆኑ መዘንጋት የለብንም። ብዙ ጊዜ ብርቱና የተዘረጋው የእግዚአብሔር ክንድ የእኛን ያልተቀደሰ፣ በስስትና በስግብግበነት የተሞላ አላማ እንዲያስፈጽምልን ስንፈልግ እንስተዋላለን። የእግዚአብሔር ክንድ ግን ቅዱስ ክንድ ነው። የራሱን ፈቃድ የሚፈጽም፣ ከክፋት ጋር የማይተባበር፣ በጽድቅና በእውነት የሚሰራ ክንድ ነው። ይህንን በማስተዋል፣ የእኛን የረከሱ ምኞቶች ወደ ጎን ትተን የእርሱ ቅዱስ ፈቃድ በህይወታችን በቅዱስ ክንዱ እንዲፈጸም ፈቃደኞች ልንሆን ይገባል።
4 የዘላለም ክንዶች
የአምላካችን ብርቱ፣ የተዘረጉና ቅዱስ ክንዶች ደግሞ የዘላለም ክንዶች ናቸው። መቼም ቢሆን የማይጥሉን፣ እንደ ሥጋ ክንድ የማይሞቱ፣ የማይበሰብሱ የዘላለም ክንዶች ናቸው።
“የዘላለም ክንዶች ካንተ በታች ናቸው” ዘዳ 33:27
🙏 #ጸሎት:
አባት ሆይ፣ ያንተ ብርቱ፣ የተዘረጉ፣ ቅዱስና ዘላለማዊ ክንዶች እንዲሸከሙን እኛም ሁለንተናችንን ባንተ ላይ እንድንጥል በጸጋህ እርዳን። አሜን
28/11/2025
#የመታዘዝ በረከት
━━━━━━━━━━━
📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል: ዘዳግም 28-29
"''ለአምላክህ ለ እግዚአብሔር በፍጹም ብትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተል፣ አምላክህ እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርግሃል። እንቅብህና ቡሖ ዕቃህ ይባረካሉ። ''
ዘዳግም 28:1,5"
“እንቅብህና ቡሃቃህ ብሩክ ይሆንል” እነዚህ ቃላት ትኩረታችንን በቀላሉ የሚስቡ ናቸው። በእርግጥም ብዙዎቻችን ተግተን የምንሰራው ኑሮአችንን ለማሸነፍ የተሻለ ህይወት ብለን የሳልነውን ያንን ለመኖር ነው። በዚህ ረገድ ለስኬት ያበቁናል ብለን የምናስባቸውንም የተለያዩ ነገሮች እንሞክራለን። ታዲያ ይህንን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃልን ቃል መስማት እርሱም ያዘዘንን ትእዛዙን መፈጸም ለእውነተኛ ስኬት የሚያበቃ አስተማማኝ ቁልፍ መሆኑን ሙሴ ለእስራኤላውያን በመጨረሻ ንግግሩ ካስተላለፈው መልእክት እንረዳለን።
ሙሴ ለእኔ ገንዘብ ከከፈላችሁ፣ እኔ የምላችሁን ካደረጋችሁ፣ ከእኔ ጉባዔ ካልቀራችሁ፣ እኔ ያዘጋጀሁትን ዘይት ከተቀባችሁ ወዘተ አላለም። ይልቁንም “የእግዚአብሔርን ቃል ከሰማችሁና ትእዛዛቱንም ከፈጸማችሁ በማለት ሙሉ በሙሉ ወደ ቃሉና በቃሉም ወደ ሰፈሩት የጌታ ትእዛዛት ነበር ህዝቡን ያመለከተው። እኛም ዛሬ እውነተኛ ስኬት ከፈለግን ወደ እግዚአብሔር ቃል መመለስ፣ በዚያም ጌታ ለጥቅማችን ያሰፈረልንን የእርሱን ትእዛዛት የህይወታችን መመሪያ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጎዳና ሊሆንልን ይገባል።
የእግዚአብሔር ህዝብ ልቡ እጅግ በአምላኩ ላይ ሸፍቶ በጣኦት አምልኮ ውስጥ በተዘፈቀበት ጊዜ ኤልያስ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በመታዘዝ ህዝቡም ወደ እግዚአብሔር በእውነተኛ መታደስና መለወጥ እንዲመጣ ጸለየ። የህዝቡን ልብ ያሸፈቱትንም መሪዎች ፊት ለፊት ተጋፈጠ። እግዚአብሔርም በአስደናቂ ተአምሩ እንቅብና ቡሃቃውን ባረከለተ። ሊያልቅ የነበረውን ዱቄትና ዘይት አተረፈረፈው። በሌላ ጊዜ ደግሞ በሰማይ ቁራ መገበው። መጽሐፍ ቅዱስ ለጌታ ቃል በመታዘዝ በረከትን ስለተቀበሉ ብዙዎች ይዘረዘራል።
እዚህ ላይ ግን ልብ ልንል የሚገባን፣ የጌታን ቃል በመስማትና በመታዘዝ ስንኖር ሁልጊዜ መንገዳችን አልጋ ባልጋ ይሆናል ማለት አይደለም። ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በመታዘዝ ወንጌል እየሰበከ በኖረው ህይወት ስለገጠመው ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል:-
“ ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤ ብዙ ጊዜ ምግብ ሳልቀምስ ኖሬአለሁ፤ በብርድና በራቍትነት ተቈራምጃለሁ።” 2 ቆሮ 11:27
በዚህ ሁሉ ውስጥ ስናፍል ግን ጌታ በተለየ ጸጋው ከእኛ ጋር በመሆን በጥጋብና በመትረፍረፍ የማይገኘውን ሰላምና ደስታ ሊሰጠን ቃል ገብቶአል። በመጨረሻም ሁሉን ለበጎ እንዲሰራ አድርጎ ወደ ደስታው ሙላት ያስገባናል።
🙏 ጸሎት:
አባት ሆይ፣ ሁሉጊዜ ቃልህን ለመስማትና በትዛዝህም ለመራመድ ፈቃደኞች እንድታደርገን፣ በዚህም ለእኛም ያዘጋጀህልንን እውነተኛ በረከት ለመውርስ እንድንችል እንድትረዳን እንጸልያለን። አሜን።
26/11/2025
#ከርግማን ዋጀን
━━━━━━━━━
📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል: ዘዳግም 21-23
"''በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በ እግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ፣ በዚያ ዕለት ቅበረው።''
ዘዳግም 21:23"
አፍቃሪ አምላካችን ሁሉን ውብ አድርጎ በመፍጠር፣ በመልኩና በአምሳሉ ላበጀው ሰብ አዊ ፍጥረት “ብዙ ተባዙ” በማለት ባርኮቱን ሰጣቸው። የዚህ የበረከት አምላክ ዕቅድ ፍጥረተ ዓለም በእርሱ በረከት የተትረፈረፈን ሕይወት እንዲኖር ነበር። ይሁን እንጂ፣ ሰው በተሰጠው የምርጫ ነጻነት ዐመጽን ሲመርጥ፣ ያንን ተከትሎ እርግማን መጣ። ለዘላለም ሕይወት የተፈጠረው ሰው፣ “ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ” ተብሎ ተረገመ።
ይሁን እንጂ፣ አፍቃሪ አምላካችን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ይህንን እርግማን ከእኛ የሚያስወግድበትን አስደናቂ የድነት ዕቅድ አዘጋጀ። በዚህም መሠረት፣ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን የተዋረደ ሥጋ በመልበስ “በዕንጨት ላይ የሚሰቀል እርሱ የተረገመ ነው” በተባለው መሰረት ስለ እኛ እርግማን ሆኖ በመስቀል ላይ መስዋእት ሆነ።
ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ይህንን አስመልክቶ እንዲህ በማለት ጽፎላቸዋል፦
““በዕንጨት ላይ የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ፣ ክርስቶስ ስለ እኛ ርግማን ሆኖ ከሕግ ርግማን ዋጅቶናል፤” ገላ 3:13
ጴጥሮስም እንዲህ በማለት በመስቀሉ ላይ የተሰራውን ድንቅ ሥራ ተናግሮአል፦
“ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል።” 1 ጴጥ 2:24
በእርግጥም እጅግ የከፋውን የመስቀል ላይ ሞት በመሞት እርግማናችንን ተሸክሞ እኛን ከእርግማን ዋጀን። በእርሱ ቁስል ተፈውሰን የበረከቱ ወራሾች ለመሆን ብቁዎች ሆንን። በቃላት ሊገለጽ ስለማይችል ስለዚህ ታላቅ ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።
🙏 ጸሎት: አባት ሆይ፣ እርግማናችንን ለማስወገድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት ስለከፈልከው ታላቅ መስዋእትነት እያመሰገንህ፣ በዚህ ፍቅር የተማረከ ሕይወት እንድንኖር በጸጋህ እርዳን። አሜን።
24/11/2025
#ልብህን አታጨክንበት
━━━━━━━━━━━━
📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል: ዘዳግም 14-16
"''አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፣ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አታጨክንበት፤ ወይም እጅህን ወደ ኋላ አትሰብስብበት። ''
ዘዳግም 15:7"
ባለጠጋው አምላካችን “ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን የሚደግፍ” ( መዝ 146:9) ትልቅ ሆኖ ሳለ ትንሹን የማይንቅ የፍቅር አምላክ ነው። በባሪውያ በሙሴ በኩል ለሕዝቡ በሰጠው መመሪያ ላይም ስለ ድኾች የተናገረው ይህንን ባሕርይውን በግልጽ የሚያሳይ ነበር። በዘዳ 15፡ 7-10 ላይ ሰባት ጊዜ በተለያዩ መግለጫዎች ተመሳሳይ የልግስናን ጥሪ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ቅርቦአል፦
1. “በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አታጨክንበት፤
2. ወይም እጅህን ወደ ኋላ አትሰብስብበት።” ዘዳ 15:7
3. ይልቁንስ እጅህን ፍታለት፤
4. የሚያስፈልገውንም ሁሉ ቅር ሳይልህ አበድረው። ቁ 8
5. “በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፣ እርሱም በአንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!” ቁ. 9
6. በልግስና ስጠው፤
7. ስትሰጠውም ልብህ አይጸጸት፤
ከዚህም የተነሣ አምላክህ እግዚአብሔር በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል። ቁ 10
ልግስና የልብ ጉዳይ ነው። ከመስጠት እጃችን እንዳይጨበጥ “ልብህን አታጨክንበት” ተብለናል። ደግሞም ስንሰጥ በግድ ወይም በሃዘን እንዳይሆን “ልብህ አይጸጸት” ተብለናል።
🙏 ጸሎት:
አባት ሆይ፣ ቃልህ እንደሚለን ልችባንን ሳናጨክንና ደግም ሳንጸጸት ይልቁንም በልግስናና በደስታ የሰጠኸንን እንድናካፍል በጸጋህ እርዳን። አሜን።
#አንዳንዴ ሕይወት እንደ ነው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Ahmedzake
Cairo
ELMADDI