Alta Medium Clinic
ሁሉንም የህክምና አይነት እንሰጣለን
01/02/2022
አንድ ሰዉ የስኳር ህመም አለዉ የሚባለዉ መቼ ነዉ?
አንድ ሰዉ የሚከተሉትን የህመም ምልክቶች ካሉት የስኳር ህመም ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡ እነሱም
1. ሽንት ቶሎ ቶሎ የሚሸና ከሆነ( በተለይ ማታ ማታ)
2. ዉሃ ቶሎ ቶሎ የሚጠማዉ ከሆነ
3. የሰዉነት ክብደት ለመቀነስ ሳይሞክር በራሱ ጊዜ እየቀነሰ ከመጣ
4. ከወትሮ የተለየ የረሃብ ስሜት የሚያስቸግረዉ ከሆነ
5. እይታ ላይ ብዥታ ካለዉ
6. የእጅና እግር መደንዘዝ ወይም መጠቅጠቅ ስሜት ካለ
7. ከፍተኛ ድካም ስሜት ካለዉ
8. የቆዳ ድርቀት የሚያስቸግረዉ ከሆነ
9. ቁስል ኖሮት ቶሎ የማይድን ከሆነ
10. ከተለመደዉ በተለየ በተደጋጋሚ በህመም መጠቃት ካለዉ
አንድ ሰዉ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በከፊልም ይሁን በአብዛኛዉ ካሳየ የደም የስኳር ምርመራ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ምርመራዉን አድርጎ የሚከተሉት መስፈርቶች ካሉት ወይም ካሟላ የስኳር ህመም አለዉ ይባላል፡፡ እነዚህም፡-
1. ተፁሞ የሚሰራ የስኳር ምርመራ(Fasting blood sugar test)፡- በዚህ ምርመራ መሰረት አንድ ሰዉ ቢያንስ ለ8 ሰዓታት ከፆመ በኃላ የደም ናሙና ተወስዶ ዉጤቱ ከ126 ሚሊግ/ዴሲሊና ከዚያ በላይ በሁለት ተለያዩ ምርመራዎች ከተረጋገጠ የስኳር ህመም መኖሩን ያሳያል፡፡
2. ሄሞግሎቢን ኤ ዋን ሲ ምርመራ( Glycated hemoglobin (A1C) test)፡- ይህ መፆም የማይጠይቀው የደም ምርመራ ላለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት ያለዎትን የደም ስኳር መጠን ያሳያል ፡፡ በዚህ ምርመራ መሰረት የምርመራዉ ዉጤት 6.5 ፐርሰንትና ከዚያ በላይ ከሆነና በሁለት የተለያዩ ምርመራዎች ከተረጋገጠ የስኳር ህመም እንዳሎት ያሳያል፡፡
ቅድመ ስኳር ህመም (Pre-Diabetes)
***********************
የሁለተኛዉ አይነት የስኳር ህመም ታማሚዎች ህመሙ እንዳለባቸዉ ሳያዉቁ እስከ 10 ዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የሰዉነታቸዉ አካላት ለከፋ ጉዳት ከተዳረጉ በኋላ ማወቃቸዉ ህክምናዉን ከባድ ያደርገዋል። ነገር ግን የስኳር ህመሙ ከመጀመሩ በፊት ሰዉነታችን ላይ የሚከሰተዉን ማስጠንቀቂያ ደወል ቅድመ ስኳር ህመም ብለን ልንከፍለዉ እንችላለን።
ቅድመ ስኳር ህመም ምንም ምልክት ላይኖረው ይችላል። ቅድመ ሰኳር ሁኔታው ደግሞ ወደ ስኳር በሽታ ከተሸጋገረ የሚታዩ ምልክቶችና ስሜቶች አሉ፡፡ እነሱም፣ የውሀ ጥም መጨመር፣ ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት፣ ድካም ስሜት፣ አይን ብዥ ማለትን ያካትታሉ፡፡
ለመሆኑ ለቅድመ ስኳር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች አሉ?
እነዚህን ሀኔታዎች በጥሞና መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ቤተሰበ ወይም ጓደኛን መምከርም አስፈላጊ ነው፡፡ ሁኔታዎቹ:-
👉የሰውነት እንቅስቃሴ የማያዘወትሩ ከሆነ
👉የሰውነት ክብደት ከመጠን በላይ ካለፈ
👉ዕድሜ ከ45 አመት በላይ ከተሻገረ
👉በቤተሰብዎ ውስጥ ዋናው የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ካለ
👉አፍሪካዊ ዝርያ ካለብዎት
👉በሴቶች በኩል፣ ከዚህ ቀደም ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የስኳር በሽታ ተከስቶ ከሆነ፣ ተወለደው ልጅ ከዘጠኝ ፓውንድ ወይም ከ4 ኪሎ ግራም በላይ ከሆነ
👉የደም ግፊት ካለብዎት
👉እንደገናም በሴቶች በኩል፣ polycystic o***y syndrome የሚባል ሁኔታ ካለባቸው፣ (ሁኔታው የውር አበባ መዛባት፣ በሰውነት ላይ ከሚገባው በላይና በሴቶች ላይ መብቀል የማይገባበት ቦታ ፀጉር ሲበቅል፣ ከመጠን በላይ ውፍረትን የሚያካትት ነው፡፡)
👉ኮለሰተሮል መጠን ደግሞ፣ ጤናማ (HDL) የሚባለው የኮለስትሮል መጠን ከፍ ማለት ሲገባው በማነስ ከ35 በታች ሲሆንና፣ ትራይግላይሰራይድ (Triglyceride) የሚባለው በደም የሚለካ የጮማ መጠን ከ 250 በላይ ሲሆን
👉እንቅልፍ ደግሞ ትንሽ ወይም ከመጠን በላይ ሲሆን፣ ማለትም፣ ከስድስት ሰአታት በታች የሆነ በቂ ዕንቅልፍ አለማግኘት፣ አለዚያም ከበቂ በላይ ወይም ከዘጠኝ ሰኣታት በላይ የሚተኙ ከሆነ፣
እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ካሉብዎት፣ ለቅድመ ስኳር አጋላጭ ሰለሆኑ፣ ለሁለተኛቀዉ አይነት የስኳር ህመም የመጋለጥ እድልዎን ስለሚያሰፉ መጠንቀቁ ይበጃል። ነገር ግን ህመሙ ካለብዎ ወይም ደግሞ አጋላጭ ሁኔታዎች ካለዎ በህመሙ የተሻለ ልምድ ባላቸዉ ባላቸዉ እና በህመሙ ስፔሺያሊስቶች ክትትልዎን እና ህክምናዎን ማድረግዎ የተሻለ ዉጤት ሊያስገኝሎዎ ይችላል።
በብዙዎች ዘንድ የተመሰገኑ የስኳር ህመም ስፔሺያሊስታችንን በቀጠሮ ለማግኘት በ 0920002180
02/02/2020
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Adama