Amlaku Mebrat Ademasu
ኢትዮጰያ አሸንፍለች!!
እርስወ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ!!
ሰውን አትናቅ!
አልበርት አንስታይን በዩኒቨርሲቲዎችና በየምርምር ተቋም
እየዞረ ስለ ታወቂው አንፃራዊነት ቲዎሪ ሌክቸር ሲሰጥ
ሁሌም አብሮት የሚሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር ( cab driver ) ነበረው።
ሹፌሩ አነስታይን ሌክቸር ሲሰጥ በተደጋጋሚ ሰዎች በተመስጦ ሲያዳምጡ በማየቱ እሱም በትኩረት እና በተመስጦ እየተከታተለ ከሞላ ጎደል ፅንሰ ሐሳቡ በሚገባ ገብቶታል።
አንድ ምሽት የተለመደውን ሌክቸር እንዲሰጥ አንስታይንን
ይዞት እየሄደ ሳለ ባጋጣሚ አነስታይን ይታመማል ሹፌሩም "እንመለስና ወደ ሆስፒታል ልውሰድህ"
ቢለው አንስታይንም" በፍፁም አይሆንም ባይሆን ሌክቸሩን
ከሰጠሁ በኋላ ወደ ህክምና እሄዳለሁ" ብሎ እምቢ
አለው።በዚህ ግዜ ሹፌሩም "ይህን ያህል ጊዜ አብረን ስንውል የምታስተምረውን ሌክቸሮች ከመከታተሌ ብዛት ሀሳቡ በሚገባ ስለገባኝ አንተን ተክቼ መስጠት ስለምችል አንተ አረፍ በልና እኔ ሌክቸሩን ልስጣቸው " ይለዋል።
አንስታይንም በዛ ምሽት ሌክቸሩን በሚሰጥበት ቦታ በስም
እንጂ ማንም በአካል እንደማያውቀው በማወቁ በሹፌሩ
ሐሳብ ተስማማና ወደ ክፍሉ ገብቶ ጥጉን ይዞ ተቀመጠ።
ሹፌሩም ራሱን አነስታይን ነኝ ብሎ በማስተዋወቅ ወደ
ሌክቸሩ ገባ ጥሩም አድርጎ አስተምሮ ጨረሰ
ተሰብሳቢውና የሳይንስ ተማሪዎቹ መርካታቸውን በጭብጨባ ገለጹ እሱም አመስግኖ ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል አንድ ኘሮፌሰር ቀረብ ብሎ ፈታኝ የሆነ ነገር ግን ሆን ብሎ ለማሳጣት የፊዚክስ ጥያቄ ጠየቀው። ሹፌሩም ምንም ሣይደናገጥ ጥቂት አሰብ አደረገና" ይሄ እኮ በጣም ቀላል ጥያቄ ነው በእርግጠኝነት ሹፌሬን ብትጠይቀው በአጥጋቢ መልኩ አብራርቶ ይመልስልሀል "
በማለት በኩራት ለኘሮፌሰሩ መለሰለት ። ኘሮፌሰሩም ጥግ
ላይ ተኮራምቶ የተቀመጠውን ሹፌር በንቀትና ፌዝ
በተቀላቀለበት መልኩ ቢጠይቀው ሹፌሩም ( አነስታይን)
ከበቂ በላይ ሰፋ ባለ መልኩ አብራርቶ መለሰለት።ኘሮፌሰሩም በጣም በመደናገጥና በመሸማቀቅ ጭንቅላቱን ደፍቶ በአግራሞት ምንም ነገር ሳይናገር ወጥቶ ሄደ።እናም በማናለብኝነት ራስን አግዝፎና ሰቅሎ በማስቀመጥ ሌላውን ደግሞ ወዳጄ ሆይ ሰውን አትናቅ ማንንም ቢሆን !!
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጡ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።
በዚህ መሠረት፦
1. ወ/ሮ ሰላማዊ አለማየሁ በቀለ-የአብክመ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
2. አቶ ቀለሙ ሙለነህ አምሩ - የአብክመ ገጠር መንገዶች
ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
3. አቶ ዘውዱ ማለደ በላይ - የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
4. ዲ/ን ተስፋው ባታብል ቢታው - የአብክመ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር
5. ወ/ሮ ንጹሕ ሽፈራው ቸኮል - የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ
6. አቶ ወርቁ ያየህ ጨቅሌ - የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር
7. አቶ ማግኘት መልካሙ ሐበሻ - የአብክመ መሬት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
8. ዘውዱ ሙጨ አምባው(ዶ/ር) - የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
9. አቶ ሰለይማን እሸቱ ባሻ - የአብክመ ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
10. አየለ አናውጤ ገሰሰ (ዶ/ር)- የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ
11. ወ/ሮ የለምሽዋ በቀለ ወልዴ - የአብክመ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ
12. አቶ ጌትነት አማረ ገ/ህይወት - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለስልጣን ኃላፊ
13. አቶ ታደሰ ይርዳው ሞላ - የአብክመ መንገድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ
14. ዶ/ር ተስፋዬ ተገኘ ፈሩህ - በመምሪያ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ፕላን ኢኒስቲትዩት ባሕርዳር ቅርጫፍ አስተባባሪ
15. ወ/ሮ ኢሌኒ አባይ ጀምበሬ - የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ
16. አቶ ስማቸው ደምለው ከበደ - የአብክመ የወጣቶች ጉዳይ ረዳት አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥተዋል።
በእውነት እና በእውቀት የተመሠረተች ሀገር ውጤቱ እድገት, ብልፅግና ነው!
የሀገራችን ሰላም መስፈን በተመለከተ ሁላችንም ደስተኞች ነን። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ እርቁ ትክክል አይደለም የሚሉ በርካታ ሰውች አሉ። ጎበዝ ለመራመድ መጀመሪያ መዳረሻን መወሰኑ መልካም ነው የሚል እምነት አለኝ ። ትህነግ በርካታ የሆነ የሰው ህይወት, ሃብት እና የስነልቦና ጉዳት አድርሷል። ይህንን ሁሉ ጉዳት ያስተናገደው ግን እኔ ስልጣን ካልያዝኩ የሚለው ሰይጣናዊ እሳቤ ስላለው ነው። ይህ ሁሉ ከንቱ የሆነ ህልሙ ሳይሳካለት ቀርቷል ስለሆነም የህወሃት የመጨረሻው አማራጭ ህይወቱን ማትረፍ የሚለውን ሃሳብ በመፈበረክ ወደ ሰላማዊ ድርድሩ መጥቷል። አሁንም ቢሆን በተጠቀሱት ቀናቶች ሰምምነቶችን ተግባራዊ በማድረግ ወንድም የሆነውን የትግራይ ህዝብ ከወንድሞቹ ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ ሚናውን መጫወት አለበት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa