Aster G

Aster G

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aster G, Health/Beauty, Addis abeba, Addis Ababa.

26/08/2023
10/08/2023

"አዲስ አበባ አለምአቀፍ የዲፕሎማቲክ ከተማ ናት!!

ይህ ወቅት ከምንጊዜዉም በላይ የአዲስ አበባን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትነት የምናሳይበት ፣ የሁላችንም ከተማ መሆኗን የሚያረጋግጥ ስራን የምንሰራበት መሆን አለበት!!"

:- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በከተማ አስተዳደሩ የ2015 እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ

10/08/2023

የምናተርፈው ከዘላቂ ሠላም እንጂ ከጥላቻና ቁርሾ አይደለም!!

ሠላም በጥላቻ፣በግጭትና በጦርነት ሲተካ ሀገራት በቀላሉ እንደሚፈርሱ ፣ ዜጎችም አገር አልባ ተሰዳጅ እንደሚሆኑ እነ ሊቢያና ሶሪያ የዛሬዎቹ አብነቶቻችን አይደሉምን?

ስለሠላም ሲባል ሁሉንም አማራጮች ማጤን ብልህነት ነዉ። ዘላቂ ሠላምን ማስፈን በራሱ የአንድ ሀገር ግንባታ ትልቁ አካል ነዉ ቢባል ትክክል ሊሆን ይችላል ።

ምክንያቱም የሠላም ግንባታዉ አስተማማኝ መሠረት ላይ ያልቆመ ሀገር አገራዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ይቸገራልና።

ስለዘላቂ ሠላም ሲታሰብ ስለዘላቂ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ማሰብ ነዉና ሠላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ማበርከት ይጠበቅበታል ።

የሠላም መደፍረስ የሥነ ልቦና ቀዉስን ሲያስከትል፣ ቁሳዊ ፣ ሰብአዊና ማህበራዊ ቀዉሶችን ሲያፈራርቅ ኖሯል።

የዛሬዉም ሆነ የነገዉ ትዉልድ የሚያተርፈው ከዘላቂ ሠላም ነዉ። ቂምና ጥላቻ ግጭትን ሲወልዱና ሲያዋልዱ እንጂ ለዘላቂ ሠላም መደላድል ሲፈጥሩ አልታዩም።

ዘላቂ ሠላም ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነዉ። በዚህም መነሻ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ጭምር በሀሳብና በንግግር ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ተነሳሽነት ወስዶ እየሠራ ይገኛል።

ይህን ዘላቂ ሠላምን የማረጋገጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ።ልዩነቶችን በሀሳብና በንግግር በማረቅ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሁሉም ኃይሎች የየበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው ።

በተዛባ ትርክት ወደ ተዛባ አቅጣጫ የሚነጉዱ ኃይሎች በዜሮ ድምር ፖለቲካ ዉስጥ ከመዳከር የተለየ ዉጤት ሊያመጡ አይችሉም።

ማናቸዉንም ጥያቄዎች ማንሳት፣ መጠየቅ የሚያስችል ግልጽ የዴሞክራሲ ስርዓት ባለበት አዉድ ኃይልና ነፍጥ መፍተሔ መሆን አይችሉም።

ወደስክነት፣ ወደ ሚዛናዊነት፣ ወደ ህገ መንግታዊነትና ወደ ህጋዊነት መርህ መመለስ ያሻል።

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 09/08/2023
09/08/2023

ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ እና ለዓለም ሰላም ከፍ ብሎ የሚበር ንስር ነው!!
-----
የአገሩን ሉዓላዊነት ሳያስደፍር ከኖረውና ከሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ ውስጥ የተገኘው ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ በተለያዩ ጊዜያት ከውስጥ ተላላኪዎችም ጭምር ለሚሰነዘሩበትን ትንኮሳዎች ቦታ ሳይሰጥ የዜጎችን ሰላም እና የሃገርን ክብር በማስከበር ላይ ይገኛል።

የለውጡ መንግስት መከላከያ ሰራዊት ከስርዓት ጋር ሳይጣበቅ ህዝብ በድምፁ የመረጠው መንግስት ስራውን በአግባቡ እንዲያከናውን፣ የተረጋጋች፣ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ኢትዮጵያን የመጠበቅ ሀላፊነቱን መወጣት እንዲችል ኢትዮጵያን በሚመስል የሰው ሀይል አደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ እንዲዘመን በትኩረት ሰርቷል።

በውጭ እና በውስጥ የተለያዩ ፈተናዎች ቢደቀኑም፣ ኢትዮጵያ አበቃላት የሚሉ ድምፆች ቢበራከቱም ደጀኑ የገዘፈ ታሪክ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነለት ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ህይወቱን ሰጥቶ ድቅድቁን ጨለማ ገፎ የሰላም ወጋገን እንዲመጣ ድርሻውን ተወጥቷል ፤ እየተወጣም ይገኛል።

ከጦርነት እንጅ ከሰላም ማትረፍ የተሰወረባቸው ሀይሎች መከላከያ የአገሩን ዳር ድንበር ከመጠበቅ ባሻገር ከዚህም ከዛም የሚነሳን እሳት በማጥፋት እንዲጠመድ አሰላለፋቸውን እንደ እስስት እየቀያየሩ ዛሬም በእኩይ ድርጊታቸው ቀጥለዋል።

በስሪቱ ህብረብሔራዊቷን ኢትዮጵያን የሚመስለውን እና ተልዕኮውም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ የሆነውን መከላከያ ሰራዊታችን ሲያሻቸው በራሳቸው ልክ ሰፈር አውርደው የሚስሉ ሲያሻቸው ደግሞ የሆነ አካል ጉዳይ አስፈፃሚ የሚያስመስሉ ፅንፈኛ ሀይሎች ትናንትም ነበሩ፣ ዛሬም አሉ፣ የሃሳብ የበላይነትን የማይቀበሉ ግለሰቦች ወደ ፊትም ከዚህ እሳቤያቸው ጋር እንደሚጓዙ ይጠበቃል።

ጀግናው የኢትዮጵያ ሰራዊት አገሩን ኢትዮጵያን ብቻም ሳይሆን ለወንድም እህቶቹ አፍሪካውያን የሰላም ዋስትና ሆኖ ለዓለም ሰላም እንደንስር ከፍ ብሎ መብረሩን ይቀጥላል!!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት!
የሃገር ኩራት የዜጎች ዋስትና!

09/08/2023

ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!!
--------

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡ የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው።

በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ የተማረረ በመሆኑ፣ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኮዋቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ አድርጓል። ጠቅላይ መመሪያ እዙም የክልሉ ህዝብ ላደረገለት ትብብር ምስጋናውን ያቀርባል።

በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከዘረፊዉ መንጋ ስጋት ነጻ ሆነዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት በየሥርቻው የተራረፈውን ዘራፊ በማጽዳት ላይ ናቸው። ማኅበረሰቡም መረጃ በመስጠት፣ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ለዚህ ስራ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሽንፈት የተከናነበው የፅንፈኞች ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ቅርስ ቦታዎችና የእምነት ተቋማት በመግባት ለመደበቅ እየሞከረ ነው።

የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት ህግ፣ ሥርዓትና ሞራልን ባከበረ መንገድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛል። በቀጣይም የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ዕቅድ የተያዘው ከተሞቹን ከዘራፊ የጥፋት ቡድን የማጽዳቱ ተግባር እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣
1. ከሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ ይጀመራል፤
2. ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፤
3. የመንግሥት፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚሁ አጋጣሚ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከዘራፊውና ከጽንፈኛው መንጋ በመነጠልና በመከላከል፣ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሰለፍ ላደረገው ተጋድሎ ዕዙ በድጋሚ ምስጋናውን ያቀርባል።

ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓም
አዲስ አበባ
የአስቸይኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ

08/08/2023

የዛሬ ስኬታችን እና የነገ ዕቅዳችን ዋናው አቅማችን ህዝባችን ነው!

ከዕቅድ ጀምሮ በሁሉም ተግባራት ህዝባችንን በማሳተፋችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመፈፀም አቅማችን ዳብሯል፤ በዚህም በርካታ ተግዳሮቶችን ተሻግረው የፈኩ አንፀባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል።

በህብረ ብሔራዊነት ሸማ በደመቀችው ከተማችን አዲስ አበባ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት በአብሮነት የተጋመደውን እና ፍፁም መለያየት በማይቻል መልኩ የተዋለደውን፣ እንደ ሰርገኛ ጤፍ የተሰባጠረውን ህዝባችንን ለመከፋፈል፣ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መናኸሪያ የሆነችውን ከተማችን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ፅንፈኞች ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

የከተማችን ህዝብ በየጊዜው ከውሸት ማሽን እየተፈለፈሉ የሚወጡ ጥሬ መረጃዎችን እንደወረደ ከመውሰድ በመቆጠብ እና ሚዛናዊ ሆኖ እውነትን በመፈለግ እንዲሁም በትዕግስት የፅንፈኛ ግለሰቦችንና ቡድኖችን የጥፋት ጥሪ አክሽፏል።

ስርዓት አልበኛነትን ለማስፋፋትና ህዝባችን ወጥቶ ለመግባት እንዲቸገር ሞባይል እና ንብረት ነጥቆ ከመሮጥ እስከ ህይወት መቅጠፍ ሲፈፅሙ የነበሩ ሌቦችን የሰላም አርበኛው ህዝባችን እጃቸውን ይዞ ለፀጥታ አካላት በማቅረብ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የማይተካ ድርሻውን እየተወጣ ነው።

በመኪና ውስጥ በተለምዶ "ሿሿ" የሚባለውን የለየለት የውንብድና ተግባር የሚፈፅሙ ነውረኞችን እና ሞባይል፣ ላፕቶፕ እና መሰል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከሌቦች እየተረከቡ በሚሸጡ በንግድ ስም ሌብነትን በሚያስፋፉ ባለሱቆች ላይ የፀጥታ አካሉ እየወሰደው ያለው የተጠናከረ እርምጃ በህዝባችን መረጃ ሰጭነትና ጥቆማ መነሻነት መሆኑን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።

የሰላም ዘብ ሆኖ 24 ሰዓት የአካባቢውን ሰላም በንቃት እየጠበቀ የሚገኘው ህዝባችን ማንኛውንም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ከፀጥታ ሀይላችን ጋር እያከሸፈ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ ተኪ የሌለው ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

የኑሮ ጫናውን ለማቃለል እሁድ ገበያ፣ ገበያ ማዕከል ግንባታ፣ ሌማት ቱሩፋት፣ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ ለአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና እድሳት እንዲሁም ምገባን የመሳሰሉ ሰው ተኮር ተግባራት ላይም በአንድም በሌላም ህዝባችን የማይደበዝዝ አሻራውን እያኖረ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት የማጠናቀቁ ባህል የፓርቲያችን የስራ መመሪያ ሲሆን በገንዘቡ፣ በእውቀቱ እና በጉልበቱ ዋነኛው ሞተሩ እና አንቀሳቃሹ እንዲሁም የሁሉም ስኬቶቻችን እና የነገ ዕቅዶቻችን ዋናዋ አቅም ደግሞ ህዝባችን ነው።

08/08/2023

"እኛ የምንሸነፈው በነፍሳችን ልናጸናት በቆምንላት ኢትዮጵያችን ፍቅር ብቻ ነው❗️"

የምንወጣ የምንወርደው፣ የነፍስ ዋጋ የምንከፍለው፣ የትኛውንም ፈተና የምንጋፈጠው ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ብቻ ነው።

አዕምሮውን በመንደር አጥብቦ፣ በዕውቀት ሳይሆን በስሜት ልቡን ያሳበጠ፣ የስህተቱ ምንጭ የሴረኞች "የጨፍን ላሞኝህ" ሀሳዊ ትርክት መሆኑ በደንብ ይገባናል። በሙያዊ ዲሲፕሊን በሰከነና ጥበብ በተሞላበት የግዳጅ አፈጻጸማችን ሁሉንም ወደ ትክክለኛው ቦታ መመለስ እንደሚቻልም እናውቃለን።

ማንም በነዳው ቁጥር በአጉራ ዘለልነት እኛ ላይ ቃታ ለመሳብ የሚዳዳው የትኛውም ሃይል በአሳፋሪ ድርጊቱ ብናዝንም የመጨረሻ ውጤቱ ምን እንደሆነ ከልምዳችን አሳምረን እናውቃለን።

አሳዛኙ ነገር ከትላንቱ ምስቅልቅል ቀውስ እና ኪሳራ ካተረፈልን ችግር መማር ያልቻሉ "ጦር አውርድ" ባዮች ምን ያህል ለህዝብና ለሀገር ግድ እንደሌላቸው እየታወቀ፤ የእነዚህ እኩያን ተከታይ ጋሻ ጃግሬ መኖሩ ነው።

የፈለገውን ዓይነት ጭምብል ይልበስ በሀገር ህልውናና በህዝብ ሰላም ላይ ተረማምዶ የፍላጎቱን ቅንጣት ማሳካት አይችልም።

እኛን በእጅጉ የሚያሳዝነን የውጭ ሃይሎች ተጋላቢ ፈረሶች፣ የስልጣን ጥማተኛ ጃስ ተብዬዎች ዓይናቸውን ጨፍነው በሚለኩሱት እሳት የህዝብን ሰላም ከማወክ አልፈው ማህበራዊ እረፍት ሲነሱት ነው። ያ እኛን ያመናል።

ምንም ሆነ ምን ግን በመስዋዕትነታችን ዋጋ የህዝባችንን ሰላም የሀገራችንን ህልውና አስጠብቀን ምርቱን ከግርዱ በለየ አስተውሎታዊ ግዳጅ አፈጻጸም ኢትዮጵያችንን አጽንተን ከነክብሯ እናስቀጥላታለን።

ለእኛ ከኢትዮጵያ የሚበልጥብን አንዳችም እሳቤ የለም። ሁሉም ነገር የሚያምረው በሀገር ነውና ስለሀገር መቤዛችን የማይቆም ግዴታችን ነው። ለማንኛውም ሁሉም በጎ ይሆናል። የሚያሳስበን የምንከፍለው ዋጋ አይደለም። የሀገርና ህዝብ ሰላም እንጂ።

በሀገርና በወገን ያሴረ ስሜት የሚነዳው አጉራ ዘለል ጊዜያዊ እውክታ ይፈጥር ይሆን እንጂ የትም እንደማያደርሰው ራሱም ጠንቅቆ ያውቀዋል።

"እኛን የሚያሸንፈን ማንም ሳይሆን በነፍሳችን ልናጸናት የቆምንላት ኢትዮጵያችን ፍቅር ብቻ ነው።"

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa