Eva organic
ተፈጥሮአዊ ምርቶችን እናቀርባለን ። በውበትና ጤና አጠባበቅ ዙሪያ እናማክራለን። ፎሎ ያርጉን 🙏🙏
27/05/2026
🌿ለሙስሊም ወዳጆቼ በሙሉ፡ እንኳን ለዒድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✨💚ለእናንተም ሆነ ለምትወዷቸው ሰዎች ሰላም፣ ደስታና በረከት ዛሬም ሁሌም እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።
ዒድ ሙባረክ! 🌙✨
24/05/2026
My dear Fam✨💚 ቆንጆ ፀጉር ያላቸው...እህቶቻችን፤ ውድ የሆኑ የኬሚካል ምርቶችን ሳይጠቀሙ ፀጉራቸው እንዴት እንደዚያ ጠንካራ፣ ያማረና አንፀባራቂ ሊሆን እንደቻለ አስባችሁት ታውቃላችሁ? 🌿✨
ብዙዎቻችን ትኩረት ያላደረግንባቸውን ነገር ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ተፈጥሯዊ ነገሮችን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ አጋርቻለሁ፤ እንዲያውም አንደኛው እያንዳንዳችን ቤት ውስጥ በቀላሉ የሚገኝ ነው!
ፀጉራችሁ የሚነቀል፣ የሚሰባበር አሊያም ደግሞ በጣም ደርቆ ካስቸገራችሁ ይሄ ቪዲዮ በፍጹም ሊያመልጣችሁ አይገባም። እነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ፀጉራችንን ከውስጥ ጀምሮ እንዴት እንደሚንከባከቡትና እንደሚያጠነክሩት በቪዲዮው ላይ በግልጽ አሳይቻለሁ 💚
ሙሉ ቪዲዮውን ከታች ባስቀመጥኩላችሁ ሊንክ ላይ ግቡና ተመልከቱት✨
👉ይህን ቪዲዮ ያዘጋጀሁት ዝም ብሎ እይታ (views) ለማግኘት ብቻ አይደለም። ከእናንተ መካከል ይሄ ነገር በእውነት የሚያስፈልጋቸው እህቶች እንዳሉ ስለምረዳ ነው 💚
🌿ቪዲዮውን ሳያዩት መውጣት የዩቲዩብ ቻናሌን በጣም ስለሚጎዳው፣ እባካችሁን ፍላጎቱ ካላችሁ ብቻ ሊንኩን ተጭናችሁ እስከመጨረሻው እዩት። የእናንተ ድጋፍ ለኔ ትልቅ ዋጋ አለው 🙏
👉እናንተስ እስካሁን ለፀጉራችሁ የተጠቀማችሁት የተፈጥሮ ውህድ አለ? ኮሜንት ላይ አጋሩኝ 👇
Like &Share Fam💚💚💚
18/05/2026
🌿 ከ Cream of Nature Argan Oil ሻምፖ ቀጥሎ… ይሄ Garnier Ultra Doux Avocado Oil ሰሞኑን በጣም ከወደድኳቸው ሻምፑዎች አንዱ ሆኗል 👀💚
የ 4C ፀጉሬ ብዙውን ጊዜ ከተታጠበ በኋላ በፍጥነት ስለሚደርቅ፣ ልክ በታጠብኩበት ቀን ፀጉሬ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚኖረው በጣም ነው የምከታተለው።
ይሄኛው ግን ፀጉሬን ልስልስ ያለ፣ የማይቋጠር እና በቀላሉ የሚታዘዝ (የሚበጠር) አድርጎታል።
የሆነ ፍፁም ተአምር ነው ማለቴ ባይሆንም 😊 ፀጉሬ ግን በእውነት ወዶታል።
እስኪ እውነቱን ንገሩኝማ 👇🏾 እናንተ ሞክራችሁት ወዲያውኑ “ይሄንማ ድጋሚ መግዛቴ አይቀርም!” ያላችሁት ያ አንድ ሻምፑ የትኛው ነው? 🤔
አሪፍ አሪፍ ጥቆማዎችን እፈልጋለሁ! 🤭💛
👉 like &share fam✨💚
No.shortcuts,Nochemicals,only Nature
#ጤናማፀጉር
16/05/2026
My dear fam✨💚....ጤናማ የፀጉር እድገት ሁልጊዜ ጭንቅላታችን ላይ ከምንቀባው ነገር ብቻ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ብዙ ጊዜ አውርተናል.. ለሰውነታችን የምንመግበው ነገርም ትልቅ ቦታ አለው! 👀
✨ 1) የዱባ ፍሬ (Pumpkin Seeds)
የዱባ ፍሬ ለፀጉራችን ጤናማ እድገት የሚረዱ በርካታ አልሚ ምግቦች (nutrients) አሉት። በተለይም በብዙዎቻችን ላይ የፀጉር መሳሳትን እና መርገፍን የሚያስከትለውን DHT የተባለውን ሆርሞን ከመጠን በላይ እንዳይመረት በመከላከል በሰፊው ይታወቃል።
✨ 2) የሱፍ ፍሬ (Sunflower Seeds)
እነዚህ ትናንሽ ፍሬዎች በቪታሚን ኢ (Vitamin E) እና በፀረ-ኦክሳይደንት (antioxidants) የተሞሉ ናቸው። የፀጉር ቀዳዳዎቻችን (follicles) በጭንቀት፣ ባልተመጣጠነ አመጋገብ እና በአካባቢ ብክለት ምክንያት እንዳይጎዱ እና እንዳይቆጡ ይከላከላሉ።
ጤናማ የፀጉር ቀዳዳዎች = ጠንካራ እና የሚያምር የፀጉር ስር! 🌿
👉 ፍሬዎቹ ትናንሽ ቢሆኑም ለፀጉራችሁ ውበት ያላቸው ጥቅም ግን በጣም ትልቅ ነው!
በቀላሉ በእነዚህ ምግቦች ላይ በትናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፡
• በአጃ (Oatmeal) ላይ
• በጁስ (Smoothies) ውስጥ
• በሰላጣ ላይ
• በእርጎ ላይ
• ወይም የራሳችሁን የእህል ዘር ድብልቅ በማዘጋጀት
🌿 አስታውሱ ፀጉራችሁ ለሰውነታችሁ የምትመግቡትን ነገር ሁሉ መጨረሻ ነው የሚደርሰው😭....የምንመገበው ምግብ ከአንጀት ተርፎ እዛ እንዲደርስ... አንዳንዴ ከኮስሞ ቀነስ በማድረግ በሃላፊነት🚗...i mean እንመገብ✌️
No shortcuts,Nochemicals...only Nature🌿
👉 ለሚስፈልጋቸው ይደርስ ዘንድ like&share አትርሱ.....Mydears✨❤
#ጤናማፀጉር
14/05/2026
My dear Fam ✨💚
ዛሬ አንድ ምርጥ ሚስጥር ላካፍላችሁ። አረንጓዴ ሻይ (Green Tea) መጠጣት ብቻ ሳይሆን ለፀጉራችንም ድንቅ ነገር እንደሆነ ታውቃላችሁ? በውስጡ ‘EGCG’ የሚባል ድንቅ አንቲኦክሲዳንት ስላለው የራስ ቅላችንን የማረጋጋት፣ የፀጉር ስሮችን የማጠንከር እና አላስፈላጊ ቅባትን የመቀነስ ትልቅ አቅም አለው።
በተለይ ደግሞ ፀጉራችሁ፦
የሚያሳክካችሁ ከሆነ 😖
በጣም ቅባታማ ሆኖ ክብድ የማለት ስሜት የሚሰማችሁ ከሆነ 🧴
ሽሩባ ወይም በዊግ...ተሰርታችሁ ምቾት ለሚነሳችሁ 💆♀️
ሁሌም ቅልል ያለ ንፁህ እና የቅዝቃዜ ስሜት ለራስ ቅላችሁ ለምትፈልጉ... ይሄን ሞክሩት!
አረንጓዴ ሻይ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ፀጉራችን እንዲያድግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
እንዴት እንጠቀም? 📝
መጠጣቱን አትርሱ፦ በየቀኑ በመጠኑ መጠጣት ለጤናችሁም ለፀጉራችሁም ቆንጆ ነው። ☕
ከእሬት ጋር ቀላቅሉት፦ የቀዘቀዘ አረንጓዴ ሻይ ከእሬት (Aloe vera) ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ማዘጋጀት። 🧴
በስኘሬ መርጨት፦ ያዘጋጃችሁትን ውህድ በሳምንት 2–3 ጊዜ የራስ ቅላችሁ ላይ ቀለል አድርጋችሁ እርጩት። 💦
ቆንጆ ፀጉር እንዲኖረን መጀመሪያ የራስ ቅላችንን መንከባከብ አለብን፤ ስለዚህ ራሳችሁን ከውስጥም ከውጭም ተንከባከቡ!
👉 እስቲ ሞክሩትና ለውጡን ንገሩኝ። ለሚያስፈልጋቸው ይደርስ ዘንድ Like &share ማድረግ አትርሱ Fam 🌱✨
#ጤናማፀጉር #ውበት
07/05/2026
🌿የሩዝ ውሃ ለብዙዎቻችን.... እንደ መፍትሄ ቢነገርም፣ ለእኛ ለ 4C ፀጉር ባለቤቶች ግን "ጥቅሙ ሳይሆን ጉዳቱ" ሊያመዝን ይችላል። 👀
ፀጉራችሁ ላይ እነዚህን ምልክቶች እያያችሁ ከሆነ አደራችሁን...አንዴ ቆም ብላችሁ አስቡ፡
❌ ፀጉሬ ድርቅ አለብኝ ካላችሁ
❌ በጣም ከመጠን በላይ ከጠነከረ (Hard)
❌ እና ካልተለመደ መሰባበር ጋር እየታገላችሁ ከሆነ...
ሳታውቁት ፀጉራችሁን እየጎዳችሁት ሊሆን ይችላል! 🛑 የያኦ (Yao) ሴቶች ፀጉር እና የእኛ 4C ፀጉር ለምን የተለየ ምላሽ እንደሚሰጥ እና መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ በአዲሱ ቪዲዮዬ በዝርዝር አቅርቤላችኋለሁ።
👉 ቪዲዮን ካያችሁት በኋላ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ በቪዲዮ ኮሜንት ሥር አስቀምጡልኝ.....አንዳንድ መልሶች ጥልቅማብራሪያ፤ስለሚያስፈልጋቸው...ሁሉኑምጥያቄዎቻችሁ እዛው በዝርዝር እመልሳለሁ ✨💚።
ፀጉራችሁ ላይ ጉዳት ሳይደርስ አሁኑኑ ገብታችሁ ተመልከቱት!ሊንኩን የመጀመሪያ ኮሜንት ላይ አድርጊላችኋለሁ 🎥👇
Noshortcuts,Nochemicals...only Nature🌿
#ጤናማፀጉር #ውበት
03/05/2026
🌿ዘይት... ማስክ... የተለያዩ ቅባቶች... ደጋግማችሁ ገዝታችሁ? 🧴✨
ግን አሁንም ፀጉራችሁ ማደግ እንቢ ብሎ ከገገመ? 🙅♀️
እስኪ... ዛሬ ትንሽ ወደ ውስጥ ጠለቅ ብለን...እንደ ተማረ ሰው እንነጋገር። 🔍
👉 ደማችን ለሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ኦክስጅን ያደርሳል... ለፀጉራችንም ጭምር። 🌬️
👉 ቫይታሚን B12 ደግሞ አንድ ትልቅ ኃላፊነት አለው፤ እሱም ሰውነታችን የቀይ የደም ሴሎችን እንዲያመርት መርዳት ነው። 🩸
በሰውነታችን ውስጥ የቫይታሚን B12 እጥረት ሲኖር → የቀይ የደም ሴሎች ቁጥር ይቀንሳል።
ኦክስጅን ለፀጉር ስሮች (Follicles) በበቂ ሁኔታ ካልደረሰ ደግሞ...
ሰውነታችን የፀጉር እድገትን በዝግታ ማቆም ይጀምራል። 🛑
ይህንን ችግር ደግሞ ማንኛውም አይነት ከውጪ የምንቀባው... ዘይት ወይም ቅባት ሊያስተካክለው አይችልም። 🧴🚫
ስለዚህ ፀጉራችሁ ላይ ከመፍረዳችሁ በፊት... ....በውስጥ በኩል ምን እየተካሄደ እንደሆነ...አረጋግጡ። 🩺✨
እነዚህን 3 አስፈላጊ ምርመራዎች በማድረግ ብትጀምሩ ደሞ የበለጠ አሪፍ ይሆናል፡
• የቫይታሚን B12 (Vitamin B12) ምርመራ 🧪
• የብረት (Iron) መጠን ምርመራ 🩸
• የቫይታሚን ዲ (Vitamin D) ምርመራ ☀️
ምክንያቱም እውነታው ይሄ ነው... 💡
ሰውነታችን ለፀጉር እድገት የሚያስፈልገውን ነገር ካላገኘ፣ ምንም አይነት ውጫዊ ምርት ለውጥ አያመጣም።
መጀመሪያ የችግሩን ምንጭ (ሥሩን) እናስተካክለው! ....ያኔ ፀጉሩ በራሱ ማደግ ይጀምራል። 🌱✨
No shortcuts,Nochemicals....only Nature🌿
👉 ለሚያስፈልጋቸው ይደርስ ዘንድ... like&Share ...My dears💚💚
#ፀጉርጉዳት #የፀጉርእንክብካቤ #ጤናማፀጉር
02/05/2026
🌿አንዳንዴ እንዲህ ገጥሟችሁ ያውቃል...ፀጉራችሁ እንደ አዲስ ሰው ሲሆንባችሁ 😊
ያ የለመደውን ቅባት፣ ውህድ....ያ ሁልጊዜ የሚስማማው ሻምፖ... በድንገት ....."አልቀበልም፣ አላውቃችሁም፣ ተዉኝ!" የሚል ስሜት።😔
ፀጉራችሁ ይደርቃል...
እምቢተኛ ይሆናል...
ለሁሉም ነገር ስሜታዊ ይሆናል።
ያንን የምትወዱትን ውህድ ትቀቡታላችሁ.... ምንም!
ትቀቡታላችሁ....አሁንም ያው ድርቅ እንዳለ ነው😔
ልትሰሩት ትሞክራላችሁ — አይታዘዝም።
እናም ማሰብ ትጀምራላችሁ..."ፀጉሬ ተበላሸ እንዴ🤔? ችግሩ ከእኔ ነው?"
ግን !..... አንዴ ቆይ✋....ሁልጊዜ መበላሸት ላይሆን ይችላል።
👉 ፀጉራችሁ "በዛብኝ" እያለ ሊሆን ይችላል።
⚠️የፕሮቲን መብዛት → (Protein overload)
⚠️የቅባቶች መከማቸት → (Buildup)
⚠️ሁልጊዜ መንካካት → (Stress)
ፀጉራችሁ ...👉 ተጨናንቋል!
እና ምን ያደርጋል?
ራሱን ይዘጋል። ሁሉንም ነገር ይገፋል።
ልክ "ትንሽ ሰላም ስጡኝ" እንደሚል ሰው ማለት ነው።
🌿 ታዲያ በዚያ ሰዓት ምን ማድረግ አለባችሁ?
ተጨማሪ ቅባቶችን በመቀባት አታስጨንቁት! ❌
አዳዲስ ሙከራዎችን ተውለት ! ❌
👉 ወደ መሠረታዊው ነገር ተመለሱ፦👇
🫧 ፀጉራችሁን በደንብ ታጠቡ (የተከማቸ ቆሻሻን አስወግዱ)
ፕሮቲን የተባለ ውህድ አስቁሙለት... ርጥበት (Hydration) ላይ አተኩሩ
🌸 ነገሮችን ቀለል አድርጉለት
⏳ ለፀጉራችሁ ራሱን የሚያድስበት ጊዜ ስጡት 💖
No shortcuts,Nochemicals...only Nature🌿
#ፀጉርጉዳት #የፀጉርእንክብካቤ #ጤናማፀጉር
29/04/2026
My dear fam✨💚.....ሁላችንም ፀጉራችን እንዲያድግ፣ ቆዳችን እንዲያበራ እና ሰውነታችን እንዲታደስ እንፈልጋለን። ግን ብዙ ጊዜ የምንሳሳተው አንድ ቦታ ላይ ነው... "ውበትን ከውጭ ብቻ" ፍለጋ መዳከራችን! 🏃♀️💨
🌿ነገሮችን በጥልቀት እንደሚያይ ሰው ለሁላችሁም የምነግራችሁ አንድ ትልቅ እውነት አለ....ጤናማ ፀጉር የሚጀምረው ከዘይት ወይም ከቅባት ብቻ....ሳይሆን ከደም ዝውውርና ከምግብ መፈጨት ነው። 🩸✨
ለዚህ ደግሞ እጅግ ቀላልና ተፈጥሯዊ መፍትሄው፦ የጥቁር ዘቢብ ውሃ ነው!
ለምን ? 🧐
🌱ለአይረን (Iron) እጥረት፦ ፀጉራችሁ እንዳይነቀልና ጉልበት እንዲኖረው ለሥሩ ኦክስጅን ያስፈልገዋል። ዘቢብ ይሄን ያሳካል።
🌱ለሰውነት ጥራት (Antioxidants)፦ በውስጡ ያሉት ንጥረ ነገሮች ቆዳችሁና የፀጉራችሁ ስር እንዲታደስ ያደርጋሉ። 🌟
🌱ለአንጀታችን፦ የምግብ መፈጨት ሲስተካከል፣ ሰውነታችሁ ለፀጉር የሚያስፈልገውን ምግብ በአግባቡ መውሰድ ይጀምራል (ሆድ ሲታከም ውበት ይፈካል!)።
አጠቃቀሙ (ለብርቱዎችብቻ!😊) 📋
1️⃣ ማታ ከ 8-10 የሚሆኑ ጥቁር ዘቢቦችን በአንድ ብርጭቆ ውሃ ዘፍዝፉ።
2️⃣ ጠዋት በባዶ ሆድ ውሃውን ጠጡ።
3️⃣ የዘፈዘፋችሁትን ዘቢብም ብሏቸው።
ይህንን በሳምንት 3-4 ቀን፣ ለተከታታይ 3 ሳምንታት አድርጉት። ውጤቱ የሚመጣው በወጥነት (Consistency) ስትጠቀሙት ብቻ ነው። ⏳💪
My dears✨💚....ሁልጊዜ የማወራው ሰውነታችሁን እንድታዳምጡት ነው። ውድ የሆኑ የውበት ምርቶች ላይ ብቻ ከማተኮር፣ እንዲህ ያሉ ተፈጥሯዊና ቀላል መንገዶችን ለሰውነታችሁ ስጡት።
🌱 ትንንሽ ለውጦች ትልቅ ውጤት ያመጣሉ!
እናንተስ ይሄን ቀላል መንገድ ለመጀመር ዝግጁ ናችሁ? ወይስ የተጠቀማችሁ ካላችሁ ውጤቱን ለቤተሰባችን አካፍሉን! 👇
👉 share &like fam💚💚💚
#ጤናማፀጉር #ውበት
27/04/2026
🌿 ያለ ዕድሜ ለሚመጣ ሽበት ማወቅ ያለብን ሳይንሳዊ ሚስጥር! ✨🌎
ሽበት ተፈጥሯዊ የእድሜ ፀጋ...ምልክት ቢሆንም፣ ገና በወጣትነት ዕድሜ "አለሁ አለሁ" ማለት ሲጀምር ግን ሰውነታችን የሆነ መልዕክት ሊያስተላልፍልን እየሞከረ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል!
🌿ብዙዎቻችን ሽበትን የምናየው ከላይ ብቻ ነው፤ ነገር ግን በፀጉር ሴሎቻችን ውስጥ ጥልቅ የሆነ ኬሚካላዊ ጦርነት ይካሄዳል፦
የሰውነታችን ህዋሳት በተፈጥሮ ሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ. ....የተባለ ኬሚካል ያመነጫሉ። ይህ ኬሚካል ልክ እንደ ፋብሪካ ቀለም "Bleach" ፀጉራችንን ከውስጥ የመለወጥ ባህሪ አለው።
👉 በወጣትነት ጊዜያችን ካታሌዝ (Catalase) የተባለ ኢንዛይም ይህንን ሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ
ሰባብሮ ወደ ውሃና ኦክስጅን በመቀየር ፀጉራችን ቀለሙን እንዳያጣ ይጠብቀዋል።✨💚
ነገር ግን...😔ሚዛኑ ሲዛባ፦ በጭንቀት፣ በበሽታ ወይም በንጥረ-ነገር እጥረት ምክንያት የዚህ ተከላካይ ኢንዛይም መጠን ሲቀንስ፣ ሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ በፀጉር ስር ይከማቻል፤ ይህም የፀጉርን ተፈጥሯዊ ቀለም (Melanin) በማጥፋት ፀጉርን ወደ አመዳማነት ይቀይረዋል። 🧪📉
ታዲያ ምን ማድረግ እንችላለን.... ሰውነታችንን ለማገዘዝ ካልን ፦
🌱ፀጉርን ከውስጥ መመገብ!
የሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ ክምችትን ለመቀነስና የፀጉርን ጤንነት ለመጠበቅ እነዚህ ምግቦች ወሳኝ ናቸው፦
🌱ስትሮበሪ 🍓፦ በፀረ-ኦክሳይድ (Antioxidants) የበለፀጉ ስለሆኑ የሴሎቻች መጎዳት ይከላከላሉ።
🌱አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች 🥬፦ ለፀጉር ጥንካሬ የሚሆኑ ቪታሚኖችንና ፎሌት ይይዛሉ።
🌱 የሚመረው ቾኮሌት (Dark 🍫)፦ ለፀጉር ቀለም (Melanin) ምርት አስፈላጊ የሆነውን ኮፐር ይዟል።
🌱ለውዝ እና ሽንብራ,ቴምር፦ ዚንክ እና ቪታሚን ኢ (E) ለፀጉር ስር ጤንነት ይሰጣሉ።
🌱እርሾ ያላቸው ምግቦች (እንደ እርጎ🥛 .....በተጨማሪም እንቁላል፣ ስኳር ድንች፣ አቮካዶ ለቪታሚን B12,D3 እንዲሁም አይረን አይረን ወሳኝ ምግቦች።
✨ ስለዚህ...
ያለ ዕድሜ ሽበት መታየት ሲጀምር አትደንግጡ! ይልቁንስ ለሰውነታችሁ የሚያስፈልገውን ፍቅር፣ ተገቢውን ዕረፍት እና ጥሩ አመጋገብ ስጡት። ጭንቀትን በመቀነስ ሰውነታችሁ ራሱን እንዲጠግን ዕድል ስጡት። 🤍💇♀️
ጤናማ ፀጉር፣ ጤናማ ማንነት! 😊🌷
#የፀጉርጤና #ሀበሻውበት #ሽበት #ጤናማፀጉር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Piassa, Near T/haimanot Hospital, Belay Teklu New Bldg, 1st Flr
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 19:00 |
| Tuesday | 09:00 - 19:00 |
| Wednesday | 09:00 - 19:00 |
| Thursday | 09:00 - 19:00 |
| Friday | 09:00 - 19:00 |
| Saturday | 09:00 - 19:00 |