Flexy sanitary pad
The best sanitary pad for you
07/09/2023
If anyone interested to buy this original products inbox or call
11/09/2022
16/04/2022
ለምን በወር አበባ ወቅት ህመም ይከሰታል?
በወር አበባ ወቅት ምቾት የማይሰማቸው ሴቶች አሉ። አንድ ሦስተኛ ያህሉ ሴቶች ደግሞ ያማቸዋል። ከህመሞቹ ራስ ምታት፣ የጀርባ ህመም፣ ሆድ ቁርጠትና ማቅለሽ ይጠቀሳሉ። ለ24 ሰዓት ሊቆዩም ይችላሉ።
ምክንያቱን ለማብራራት ቢያስቸግርም አቅም ማነስ የሚከሰትበትም ጊዜ አለ።
የወር አበባ ህመም መጠን ያለፈ የማህጸን ውስጥ የደም እጢ ውጤት ነው። ይህም የማህጸን ጡንቻ መወጠርና መላላት የሆድ ቁርጠት ያስከትላል። ህመሙ ከወር አበባ አንድ ወይም ሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ ለቀናት ይዘልቃል። አንዳንድ ሴቶች ላይ ከቀናት ሊያልፍም ይችላል።
ዲስሜኖሪያ የተሰኘው ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ፍተኛ የሆድ ቁርጠት እድሜ ሲጨምር ሊከሰት ይችላል። በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው። በማህጸን ውስጥ መሆን ያለባቸው ህዋሶች ከማህጸን ውጪ ሲሆኑ ኢንዶሜትርዮሲስ ይባላል። ከአስር ሴቶች በአንዷ ሊከሰትም ይችላል።
ለሁሉም ሴቶች የተለየ ምቾት ያለው ሞዴስ FLEXY
05/04/2022
Flexy ሞዴስ በሁሉም መድሃኒት ቤቶች እና ሱፐር ማርኬቶች አንደምታገኙት ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው ::
01/04/2022
Congratulations all ladies Flexy sanitary pad is available on market.
12/03/2022
08/03/2022
መልካም የሴቶች ቀን🧑🦳👩🦰👩🦱👵🙍
Flexy የሁሉም ሴቶች ምርጫ
06/03/2022
ስለ የወር አበባ (ፔሬድ) ምን ያህል ያውቃሉ?
ሴቶች ስለ ወር አበባቸው ኡደት በደንብ ማወቃቸው ለራሳቸው ኖርማል የሆነውን፣ ለእርግዝና ምቹ የሆኑትን ቀናት፣ የወር አበባቸው ሳይመጣ ሲቀርና እንዲሁም ሲዘበራረቅ ለመለየት ይጠቅማቸዋል፡፡
የወር አበባ ኡደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ በየወሩ ኦቫሪ (የእንቁላል አቃፊ) ከተባለው የሰውነት ክፍል ኦቩሌሽን (ውጻት) በተባለ ስርአት አንድ እንቁላል ይወጣል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የተለያዩ የሆርሞን ለውጦች ማህጸንን ለእርግዝና ያዘጋጁታል፡፡ እርግዝና ሳይከሰት ከቀረ ግን ይህ የተደረገ ዝግጅት ፈርሶ በወር አበባ መልኩ ከሰውነት ይወገድና ለሚቀጥለው ኡደት ዝግጅት ይጀመራል፡፡
የወር አበባ ኡደት የሚባለው አንድ የወር አበባ ከመጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከሚቀጥለው ዙር የወር አበባ የመጀመሪያ ቀን ነው፡፡ የአንድ ኡደት ርዝማኔ ከ21 እስከ 35 ቀን ሊወስድ ይችላል፡፡ የወር አበባ መታየት እንደጀመረ (13 አመት አካባቢ) ረዘም ያለ ጊዜ ያላቸው ኡደቶች የተለመዱ ሲሆኑ በሂደት ግን ርዝመቱ እያጠረ ይመጣል፡፡
የወር አበባ ኡደት ከሴት ሴት፤ አንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ ከወር ወር የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ በየወሩ ያለው ርዝመት ተመሳሳይ የሆነ ለምሳሌ በየ 23፤ በየ 26 ወይ ደሞ በየ30 ቀኑ የሚመጣ አሊያም ደሞ ከወር ወር የተለያየ ርዝመት ያለው ለምሳሌ አንድ ወር በ30 ቀን በሚቀጥለው በ26 ቀን ከዛ በኋላ በ22 ቀን እያለ የሚቀጥል አይነት ሊሆን ይችላል፡፡ የወር አበባ የሚፈስበት ቀንም ከሴት ሴት የተለያየ ሲሆን ከ2 እስከ 7 ቀን ሊሆን ይችላል። የፍሰቱ መጠንም ከትንሽ እስከ ከበድ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡ ላንዳንድ ሴቶች ያለህመም ሲያልፍ ላንዳንዶች ደግሞ ህመም ይኖረዋል፡፡
በዚህ ሰፋ ባለ ማእቀፍ ውስጥ እያንዳንዷ ሴት የራሷ የሆነ ኖርማል ኡደት ይኖራታል፡፡ የኡደቱን ርዝመትና አካሄድ ለማወቅ ለተወሰኑ ወራት የወር አበባ የሚመጣበትን ቀን ካላንደር ላይ ምልክት በማድረግ መከታተል ይቻላል፡፡ ለእያንዳንዷ ሴት ኖርማል የሆነዉን የወር አበባ ኡደት (ርዝመት፣ የሚቆይበትን ጊዜ፣ ብዛት) በትክክል ማወቅ በዚህ ጽሁፍ መጀመሪያ ከተጠቀሱት ጥቅሞቹ በተጨማሪ በማንኛዉም ምክንያት መዘበራረቅ ቢያጋጥም ለሃኪሞች ለዉጡን ነግሮ ተገቢዉን የህክምና እርዳታ ለማግኘት ይረዳል።
የወር አበባ ኡደት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ከተለመደውና ለአንዲት ሴት ኖርማል ከሆነው ሊዛባ ይችላል፡፡ ይህን መዛባት ሊያመጡ ከሚችሉ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡
• እርግዝና ወይም ጡት ማጥባት
• ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መቀነስ
• የተለያዩ የመራቢያ አካላት በሽታዎች
• የማህጸን እጢ
• አንዳንድ መድሃኒቶች
• እድሜ ወደ 13-14 አካባቢ እና ከአርባዎቹ አጋማሽ በላይ ሲሆን። አንዲት ሴት እድሜዋ ወደ 45 ሲጠጋ የወር አበባ ኡደት ሊዘባረቅ ይችላል። ይሁንና እድሜ እየገፋ ሲሄድ የማህጸን ካንሰር የመያዝ እድል ስለሚጨምር እድሚያቸዉ ከ45 በላይ የሆኑ ሴቶች የወር አበባ ኡደት መዘባረቅ ካጋጠመ ወደ ጤና ባለሙያ በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ የታየዉ ለዉጥ መንሰኤ ካንሰር ይሁን የእድሜ መግፋት ለማወቅ ያስችላል።
• አንዳንድ የእርግዝና መከላከያዎች የወር አበባ ኡደትን ሊቀይሩ ስለሚችሉ ምን አይነት ለዉጥ ሊኖር እንደሚችል ከጤና ባለሙያ ጋር አስቀድሞ መመካከር ጥሩ ነው፡፡
• ጭንቀት
አንዲት ሴት ከታች የተዘረዘሩት ከፔሬድ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ካጋጠሟት ወደ ጤና ባለሙያ ሄዳ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ይገባታል፡፡ የወር አበባዋ፡
• ከ3 ወር በላይ ከቀረና እርግዝና አለመኖሩን እርግጠኛ ከሆነች
• ከ7ቀን በላይ ከፈሰሳት
• ብዛቱ ከተለመደው በላይ በጣም ከጨመረ
• የተስተካከለ የነበረው ኡደት የተዘባረቀ ከሆነ
• የኡደቱ ርዝመት ከ21 ቀን ካነሰ ወይም ከ35 ቀን ከበለጠ
• ከባድ ህመም ካለው፤ በወር አበባ መካከል ደም የሚፈሳት ከሆነ እና ታምፑን ከተጠቀመች በኋላ ትኩሳትና የህመም ስሜት ከተሰማት
****************
Flexy የ እርሶ ምርጫ
መልካም ምሽት ::
02/03/2022
Did you know?
That Sanitary Pad was developed by a black woman called Mary Beatrice Davidson.
Until sanitary pads were created, women used all kinds of reusable fabrics to absorb menstrual flows.
Mary's invention was initially rejected. The first company that showed interest rejected it because of racial discrimination. The world had no choice, her invention was too important to be ignored. It was later accepted in 1956, 30 years later.
She received five patents for her household and other personal items creations. One of her inventions is the bathroom tissue holder, which she co-invented with her sister. The patent number was US 4354643, dated October 19, 1882. 💚🖤💛❤✊🏾
01/03/2022
እንኳን ለ126ኛው የ አድዋ በዓል አደረሰን::
አድዋ የጥቁር ሕዝብ ድል ፣ የጥቁሮች ኩራት
01/03/2022
It makes all the ladies flexiable all the time.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 12:00 |