Etcare
An official page of Etcare, Etcare is a company that produces and sell beauty care products
10/09/2026
የከሰዓት ልዩ የበአል ፕሮግራማችን በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል!
የ2018 ዓ.ም የመጨረሻ ፕሮግራማችን የሆነው የከሰዓት ዝግጅታችን በውድ የምርት አስተዋዋቂዎቻችን ደማቅ ታዳሚነት በስኬት ተጠናቋል።
መድረኩን በታላቅ ብቃት ሲመራልን የቆየው፡ የኢቲኬር ማናጀር ግርማቸው አሻግሬ ሲሆን ፣ ልዩ የአዲስ አመት መልእክት እንዲሁም የተለያዩ መልእክቶችን ሲያስተላልፉ የቆዩልን የኢቲኬር ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሃይሉ እና የኢቲኬር ሪጅናል ዳይሬክተር እና ኤክስፐርት ትሬነር አሸብር ጉልላት ናቸው።
የ2018 ዓ.ም የመጨረሻውን ፕሮግራም በታላቅ ስኬትና አንድነት በማጠናቀቃችን ኩራት ይሰማናል።
ለአዲሱ ዓመት መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን!
መልካም አዲስ ዓመት!
ከኢቲኬር
10/09/2026
የአዲስ ዓመት ልዩ የዋዜማ ፕሮግራማችን በስኬት ተጠናቋል!
በዛሬው ዕለት ባካሄድነው ልዩ የዘመን መለወጫ በዓል ዝግጅት ላይ፣ የድርጅታችን መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ማቲዮስ መባ የማኔጅመንት አካላት፣ኤሊት አምባሳደሮች፣ ሪጅናል ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም የኢትዮጲያ ሊድ ቡድን እና አሶሼት ቡድን አባላት በጋራ በመታደም ይህንን ልዩ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ አጠናቀናል!
በመጨረሻም ዋና ስራ አስፈፃሚያችን ለመላው የኢቲኬር ቤተሰብ መልካም የአዲሱ ዓመት ምኞት እና መልእክት አስተላልፈዋል።
Etcare
የኤቲኬር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ማቴዎስ መባ የአዲስ አመት መልእክት!
09/09/2026
አምለሰት ገብረስላሴ(ኢቲኬር ማናጀር)
ይህ የስኬት ሽግግር ፣ የበለጠ የስራ ተነሳሽነቶን የሚያስቀጥሉበት እና በአስደናቂ ስኬቶችዎ ሌሎችን ማበርታትዎን ካለፈው በላቀ ሁኔታ የሚቀጥሉበት እንደሚሆን እናምናለን ። የእርስዎ ስኬት በትጋት፣ በፍላጎት እና በማያወላውል ቁርጠኝነት ምን ሊሳካ እንደሚችል አንጸባራቂ ምሳሌ ይሆናል፡፡ እንኳን ደስ አልዎት።
ኢቲኬር
Etcare
09/09/2026
New promoters training
ድንቅ የስልጠና መድረክ እሁድ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
የኢቲኬር የምርት አሰራር ኢንዱስትሪ እና መሰል ጉዳዮችን የሚዳስሰው አዳዲስ የኢቲኬር ምርት አስተዋዋቂዎችን በኢንዱስትሪው እና በአሰራር ለማብቃት የሚሰናዳው የኢቲኬር አዲስ ፕሮሞተሮች ስልጠና የፊታችን እሁድ በድምቀት ይከናወናል።
እሁድ መስከረም 3 ከታላላቅ አሰልጣኞች ጋር።
የኢቲኬር ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሃይሉ
ከኢቲኬር ሪጅናል ዳይሬክተር እና ኤክስፐርት ትሬነሮች ካሳሁን ሞሌ ፣ ንግስቲ ፍቅሬ ፣ ሽመልስ አበበ እንዲሁም ከኢቲኬር ፕሮፌሽናል ትሬነሮች ቀነኒ ቶሎሳ ፣ መለሰ ጎሹ እና ዮሃንስ ሲሳይ ጋር በጋራ በመሆን ለስልጠናው ዝግጁ ሆነዋል።
እሁድ መስከረም 3 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ እንገናኝ።
መግቢያ፡ 50ብር
መልካም አዲስ ዓመት!
09/09/2026
አዲሱ ዓመት ሁልጊዜም የአዲስ ህልም፣ የስኬት እና የእድገት መጀመሪያ ነው። እኛም በኢቲኬር ቤተሰብነታችን የነበረንን ጠንካራ ጉዞ እያሰብን፣ መጪውን አዲስ ዓመት ደግሞ በተሻለ ራዕይ፣ በበለጠ ጥንካሬ እና በአንድነት ለመቀበል ደማቅ የዘመን መለወጫ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።
ይህ ልዩ ዝግጅት አብረን ያለፍናቸውን የስኬት መንገዶች የምናከብርበት፣ እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ በፍቅር እና በጥንካሬ የምንገናኝበት እንዲሁም ለቀጣዩ ዓመት ትልቅ መነሳሳትን የምንሰንቅበት ልዩ አጋጣሚ ይሆናል።
ውድ የምርት አስተዋዋቂዎቻችን፣ በዚህ ታላቅና የማይረሳ ዝግጅት ላይ በሰዓታችሁ ተገኝታችሁ የዚህ ደማቅ ፕሮግራም አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የዚህን ታላቅ መድረክ በበላይነት የሚመሩልን እና የሚያደምቁልን፡
የኢቲኬር ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሃይሉ እና
የኢቲኬር ሪጅናል ዳይሬክተር እና ኤክስፐርት ትሬነር አሸብር ጉልላት ናቸው!
መልካም አዲስ ዓመት!
09/09/2026
ለስላሳ፣ ማራኪ እና የፈካ ቆዳ !
የቆዳዎን ተፈጥሯዊ እርጥበት እና ውበት ለመጠበቅ Ziva Lotion ሁልጊዜም ከእርስዎ ጋር ያድርጉ። ቆዳን በጥልቀት በመመገብ ቀኑን ሙሉ ድርቀትን የሚከላከል እና ልዩ ልስላሴን የሚሰጥ!
የአዲስ አመት መልእክት ከኢቲኬር ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ!
ቀን ተቆረጠ!
ለፕሮሞሽን አቺቨርስ በሙሉ ሻንጣችሁን ካሁኑ አዘጋጁ።
08/09/2026
የ2018 ዓ.ም የመጨረሻው የProduct ስልጠና ዛሬ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል!
ይህንን ስልጠና ያቀረበልን ፕሮፌሽናል አሰልጣኝ ታፈሰ ወዳጄ የኢቲኬር ምርቶችን በዋናነት መሰረት አድርጎ መድረኩን በስኬት መርቶታል!
ይህ ስኬታማ መርሃ ግብር የዚህ ዓመት የመጨረሻው የProduct ስልጠና ሲሆን ፤ ስለ ምርቶች አሰራር ፣ አመራረት ፣ ጥቅም እና የአሻሻጥ ክህሎቶች የተዳሰሰበት ይህ ስልጠና በርካታ ምርት አስተዋዋቂዎች ተገኝተውበታል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://maps. App. Goo. Gl/9awY8x3TpHfJixMi 9
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 07:00 |
| Tuesday | 08:00 - 13:00 |
| Wednesday | 08:00 - 13:00 |
| Friday | 08:00 - 13:00 |
| Sunday | 08:00 - 13:00 |