Ethiopia Hagere

Ethiopia Hagere

Share

news, entertement ,sport and poltics

17/03/2025
26/12/2022

መደማመጥ፣ መከባበር እና በሃሳብ ብዝሃነት ማመን የሰላም መሰረቶች በመሆናቸው ሁሌም ቢሆን ሳንሸራተት አጥብቀን ልንይዛቸው ይገባል፡፡

ሰላም ሁሉም ዜጋ በሚክፈለው አስተዋጽዖ ልክ ይረጋገጣል፡፡ በዙሪያችን ያሉን መልካም ነገሮች ሁሉ የሚመክኑት ሰላም ከእጃችን ስታመልጠን ነው፡፡

በአብሮነት በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሰላማችንን ጠብቀን መጓዝ እየቻልን በግትርነት እና ባለማስተዋል የምናጣው ሰላም ከእጃችን ከወጣ በኋላ መልሰን ለማግኘት ብዙ ድካም እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው፡፡ ሀገራችን ውስጥ በየትኛውም ጽንፍ የሚከሰት የሰላም መደፍረስ ለመዳረሻችን እንቅፋት ነው፡፡

ሁሉም ዜጋ ቆም ብሎ በማሰብ ችግርን ከመግፋትና ለችግሮቻችን ባለቤት እየሰጡ ከመዳከር ወጥተን ሁላችንም ከራሳችን ጀምረን የሰላም ሰው ልንሆን ይገባል፡፡

መልካም የፍሬያማነት፤የፍቅር፤ የሰላም ሳምንት እንዲሆንላችሁ ተመኘን 🌻🌻🌻

26/12/2022

በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና።

የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው።

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።
በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Photos from Ethiopia Hagere's post 04/10/2022

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል ?

በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ::

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

👉 ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

👉 ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

👉 የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

👉 ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

👉 ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።
(FM Addis 97.1)

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa