Close up

Close up

Share

Infotainment and the ideology of winning mentality

24/02/2026
15/07/2025

በዓለም ላይ አራት ዓይነት ሰዎች አሉ''ሶቅራጥስ''
1,የሚያውቁ እና ማዎቃቸውንም የሚያውቁ:-ብርቱዎች ናቸው ።
2,የሚያውቁ እና ማዎቃቸውን ግን የማያውቁ:-ያልነቁ ናቸው ።
3,የማያውቁ እና አለማዎቃቸውን የሚያውቁ:-ቅኖች ናቸው ።
4,የማያውቁ እና አለማዎቃቸውነን የማያውቁ:-ሞኞች ናቸው ።

26/06/2025

በመጨረሻው ዘመን የሰዎች ክፉ ባህሪ ፣ የማህበራዊ እና የመንፈሳዊ ውድቀቶች ሲጨምሩ፣ የክርስቶስ ቤተክርስትያን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ታልፋለች።

ሃይማኖተኝነት እና አለማዊ ክህደት ሲበዙ፣ የሰው ልጅ አኗኗር በዓመፃ እየተሞላ ሲሄድ፣ አምላካችን ኢየሱስ በፅድቅ ሊፈርድ መምጣቱ አይቀርም።

በቅዱሳን መካከል የሚታየው ትግል ደግሞ ከውጫዊውም አለም የሚመጣ ብቻ ሳይሆን በመካከላችንም የሚከሰቱ ናቸው።

እግዚአብሔር ሰማያዊ መንግስቱን በምድር ሁሉ ላይ እንዳይተክል የጨለማው መንግስት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።ሆኖም አምላካችን በበቀል ሊሰራ ሲነሳ የሚቋቋመው የሚችል የለም።

የጌታ መምጣት በመቅረቡ ተያይዞ በዓለም ላይ ልዩ ልዩ የመጨረሻ ምልክቶች ቢታዩም በዚህ ውስጥ የጌታ ትኩረት የራሱ ህዝቡ ነው።

በዓለም ላይ ሊጀመር ካለው የፍፃሜ ጦርነት ና መከራ በፊት የሰማያዊ መንግስት አምባሳደር የሆነችው ቤተ ክርስትያን ወደ ሰማያዊው ቤት ትጠራለች።

ጌታ ሲመጣ እነማን ይነጠቁ ይሆን?

1)በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ የሚያምኑ ይነጠቃሉ።(ሮሜ 10:9)

2)በፀሎት ሁልጊዜ የሚጠባበቁ ይነጠቃሉ(ሉቃስ 21:36

3)በአገልግሎት በታማኝነት የቆሙ ይነጠቃሉ

4)ቅድስናቸውን የጠበቁ ይነጠቃሉ።

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ጌታ መምጣት ከተናገረ በኋላ በቅድስና እንዲኖሩ ይለምናቸዋል።
ዓለም በእርኩሰት ስታብድ የእግዚአብሔር ህዝብ (ቤተክርስትያን) ለመነጠቅ የምትናፍቅ ከሆነ ቅድስናን እንጠብቅ።

ይህ ዘመን የጌታ መምጣት በደጅ እንደሆነ ያሳያል።ዘመኑ ምንም የሚያስጨንቅ ቢሆንም፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ባገኘነው አዲስ ማንነት በቅድስና ጌታን ለመገናኘት እንዘጋጅ።

በዚህ ዘመን ቤተክርስትያን በተለያዩ ዓለማዊ ውጊያዎች ብታልፍም፣ ድል በመንሳት እግዚአብሔር ሊያየው የሚፈልገውን ሕይወት ይዘን በክብሩ ፊት መቆምን ይስጠን።

ፓስተር ሀንፍሬ አሊጋዝ

Photos from Close up's post 14/04/2023
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa