Amen Amen
ኦርቶዶክስ ህወቴ
20/10/2025
11/09/2025
እንኳን አደረሳችሁ!!
እንኳን ለብርሃን አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ውድ የሥራ ባልደረቦቼ፣ አዲሱ ዓመት ለሁላችንም በሥራችን የላቀ ስኬት፣ ትብብር እና ውጤታማነት የተሞላበት እንዲሆን እመኛለሁ። ከሁሉም በላይ፣ ደስታ፣ ጤና እና ሰላም አይለየን! መልካም አዲስ ዓመት!!
መስከረም 01/2018 ዓ.ም
27/04/2025
ዳግም ትንሣኤ - የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት
****************
ዳግም ትንሣኤ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የትንሣኤ በዓል በተከበረ በስምንተኛው ቀን የሚመጣ ኃይማኖታዊ በዓል ነው።
አስተምህሮቱ እንደሚለው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣበት ዕለት ደቀመዛሙርቱ (ተማሪዎቹ) ተሰብስበው ሳለ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ይህ ሲሆን ታዲያ የነበሩበት ቤት በሩም መስኮቱም ተቆልፎ ስለነበር ደቀ መዛሙርቱም በጣም ደነገጡ።
ኢየሱስ ክርስቶስም “አትፍሩ፣ እኔ አምላካችሁ ነኝ” ብሎ የተወጋ ጎኑን እና የተቸነከሩ እጆቹን አሳያቸው። እነርሱም ጌታ ከሞት መነሣቱን አመኑ።
ደቀመዛሙርቱም ያዩትን እንዲመሰክሩ እና ሕዝቡን እንዲያስተምሩ ላካቸው።
በዚያን ዕለት ከ12ቱ ደቀመዛሙርት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፤ ደቀመዛሙርቱ የጌታን መነሣት እና እነርሱም እንዳዩት በደስታ ሲነገሩት፣ እርሱ ግን “በዐይኔ ካላየሁ አላምንም” አለ።
ከስምነት ቀናት በኋላ እንደገና ቶማስ አብሯቸው ሳለ እንደ መጀመሪያው ቀን በሩ እንደተዘጋ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።
ቶማስም መጠራጠሩን ስላወቀ፣ “ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼን እና እግሮቼን፣ የተወጋ ጎኔንም ናና እይ” ብሎ አሳየው።
እርሱም ምልክቱን በማየቱ እና በመዳሰሱ ትንሣኤውን እና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ “ጌታዬ አምላኬ” ብሎ መስክሮ የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ።
ዕለቱ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመሆኑም የትንሣኤው ሳምንት እሑድ፣ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ መሰየሙን የኃይማኖቱ አባቶች ያስተምራሉ።
ከዚህም ባሻገር ዳግም ትንሣኤ በአከባበር እና በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ እንደሚመሳሰል እና በዕለቱ የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ በሙሉ እንደሚደገምም የኃይማኖት አባቶች ይገልጻሉ።
በቢታኒያ ሲሳይ
10/10/2024
23/09/2024
የማኅበረ ቅዱሳን መዝሙርና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ ከአሜሪካ ማእከል ሚዲያ፣ መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል ጋር በመተባበር ፍኖተ ያሬድ ልዩ መጽሔት አሳተመ።
መጽሔቱ በቅዱስ ያሬድ ሕይወትና ሥራዎቹ እንዲሁም መዝሙርና ሥነ ጥበባት አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል ያለውን ድርሻ በዝርዝር የሚተነትን ሲሆን በዚህም ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር፣ የዜማ መሳሪያዎችና ሥነ ጥበባት አገልግሎት ወቅታዊ ሁኔታዎችን (በጎ እድሎችና ተግዳሮቶች) እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በተለያየ ምዕራፍ አቅርቧል፤
ልዩ መጽሔቱ በየዓመቱ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብራትን በማከናወን ለምእመናን ይቀርቡ ከነበሩት የዐውደ ርእይና ሌሎችም ጽሑፎች በመነሳት በምእመናን አስተያየት መሠረት ለተሻለ ተደራሽነት በሁለት ቋንቋ ማለትም በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋ ሊታተም ችሏል። ማስተባበሪያው በ2016 ዓ.ም አኮቴተ ያሬድ በሚል ርእስ የመዝሙር መጽሐፍ አሳትሞ እያሰረጨ የሚገኝ ሲሆን ይህ ከአሜሪካ ማእከል ጋር በጋራ የታተመው መጽሔት ደግሞ በጽሑፍ ኅትመት ደረጃ የዓመቱ ሁለተኛ ሥራው ነው።
መጽሔቱ በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል 5ኛ ፎቅ በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ቢሮ እንዲሁም በአሜሪካ ማእከል ማግኘት እንደሚቻል ተገልጽዋል፡፡
25/07/2023
የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ስድስት ኤጲስ ቆጶሳትን ሾሙ
የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈውን የሰላም ጥሪ እና ማሳሰቢያ ባለመቀበል፣ በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ) ስድስት ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመዋል።
ባለፈው ሳምንት እሑድ ከተመረጡት 10 ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት፣ የቀሪዎቹ አራት አባቶች ሹመት ደግሞ፣ በቀጣይነት እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።
የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት፥ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና የጣሰ፣ ለመዋቅራዊ አንድነቷ እና ለሀገር አጠቃላይ ሰላም አደጋ እንደኾነ የገለጸው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ እና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ እንቅስቃሴው እንዲቆም ሲጠይቁ ቆይተዋል።
ሙሉጌታ ኣጽብሓ በላከው ዘገባ መሠረት፣ በርዕሰ-አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተካሔደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የተሾሙት አምስት በአገር ውስጥ እና አንድ በውጭ አገር የሚያገለግሉ አባቶች እንደኾኑ፣ በክልሉ የተቋቋመው፣ ‘መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት፣’ የተባለው ተቋም ጸሐፊ መጋቤ ብርሃናት ተስፋይ ሃደራ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ በአራቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የተሾሙት አባቶች፣ ቃለ መሐላ ፈጽመው፣ በይፋ ወደ ተመደቡበት የአገልግሎት ቦታ እንደሚሸኙ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ያካሔደውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ በጦርነቱ ወቅት ለነበረው የመዋቅራዊ ግንኙነት ጉድለት እና የሰብአዊ ድጋፍ እጥረት፣ በይፋዊ መግለጫ ይቅርታ ቢጠይቅም፣ ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ በእጅጉ እንዳሳዘነው አመልክቷል።
ከሹመቱ አስቀድሞ የተደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫም፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተቀባይነት የሌለው፣ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳ እንደኾነ በመጥቀስ እንዲቆም ወስኗል።
የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫም ይኹን ሹመት፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ እንዳልኾነ ገልጾ፣ ሿሚዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት፥ ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው ታቅበው ለሰላም ውይይት እንዲዘጋጁ የሚያሳስበውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ፣ በትግራይ የተቋቋመውና ራሱን “መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት” ብሎ የሚጠራው ክልላዊ ተቋም ጸሐፊ መጋቤ ብርሃናት ተስፋይ ሃደራ አይቀበሉትም፡፡ “በቤተ ክርስቲያኒቷ ሕግ መሠረት፣ በችግር ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ጳጳሳት፣ ዐዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ይሾማሉ፤” በማለት አስረድተዋል።
“በአሁኑ ጊዜ ትግራይ፣ ችግር ውስጥ ስለምትገኝና ሕዝቡም ተጨማሪ አባት ስለሚያስፈልገው፣ በቀኖናው መሠረት ሹመናል፤” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“በአሁኑ ጊዜ ከእነርሱ ተለያይተናል፤ ሕጋዊም ሕገ ወጥም ሊሉን አይችሉም፤” በማለትም የቅዱስ ሲኖዶሱን የሰላም ጥሪ እና ማሳሰቢያ ውድቅ ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በዛሬው ዕለት፣ በአክሱም የተሾሙት አባቶች ስድስት እንደኾኑ የገለጹት መጋቤ ብርሃናት ተስፋይ፣ በቀጣይ፣ ቀሪዎቹ አራት ተመራጭ አባቶችም ይሾማሉ፤ ብለዋል:: የሚሾሙበትን ቀን ግን ግልጽ አላደረጉም፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
23/09/2024