WanawTena

WanawTena

Share

Providing deep,detail & broad information in health issues

07/05/2022

የእናቶች እንግልት እና የጤና ባለሙያዎች ስቃይ በወላይታ ዞን ዉስጥ እንደቀጠለ ነዉ!

ከዚህ በፊት በወላይታ ኦቶና ሆስፒታል መድኃኒት መግዛት የማይችሉ እናቶች የራሳቸዉንም ሆነ የጽንሳቸዉን ህይወት እያጡ እንደሆነ በማስረጃ ተደግፎ በማህበራዊ ሚድያ ተዘግቧል፣ እኔም አቅርቤው ነበር።

እዉነትነቱም ተረጋግጦ የማስተካከያ እርምጃ የተባሉ ሙከራዎች ተደርገዉ ነበር። ግን የተባሉት እርምጃዎች ከ3 ቀን በላይ ዘለቄታ አልነበራቸዉም። አሁንም የገንዘብ አቅም የሌላቸዉ እየሞቱና 9 ወር የተሸከሙትን ጽንሳቸዉን እያጡ ይገኛሉ።

እጅግ በጣም የሚያሳዝነዉ የነገሩ እዉነትነት እንዳይመዘገብ ከፍተኛ ማስፈራሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስለተሰጠ የችግሩን ልክ ራሱ ማወቅ አይቻልም። ነገር ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ የእናቶች ህክምና ነጻ እየተሰጠ እንደሆነ ሁላችንም የምናዉቀዉ ቢሆንም የወላይታ እና አካባቢዉ እናቶች ለዚህ አልታደሉም።

ሌላዉ የጤና ባለሙያዎች የሰባት ወር duty ክፍያ አልተሰጣቸዉም። ሌሊት ያለ እንቅልፍ፣ ሰንበትንና በዓላትን ከቤተሰብ ተለይተዉ ደከመኝ ሳይሉ የሰሩትን የላባቸዉን ክፍያ አልተሰጣቸዉም። ይባስ ብሎ ይህን የጠየቀ ማንም ቢሆን የጁንታ ተላላኪ ነዉ የሚል ስም በመስጠት ባለሙያ እያሸማቀቁና ከስራም ለማባረር ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።

ኦቶና ብቻ ሳይሆን ወላይታ ዞን ዉስጥ ባሉ የጤና ተቋማት ለባለሙያ duty አለመክፈል፣ ከደመወዝ እንደፈለጉ መቁረጥ፣ለመጠየቅ የሞከረ ባለሙያ ማሰር፣ ማስደብደብ፣ የተለያዩ እርምጃዎችን መዉሰድ የተለመደ ሆኗል።

ይህ ብቻ አይደለም፣ የጤና ባለሙያ የመድኃኒት ሌባ በማለት ስም የማጥፋት ዘመቻ ተደርጎበታል። ከዚህ የተነሳ ታካሚዎች በተቋማት ያሉ ጤና ባለሙያዎችን ሌባ እያሉ ቁስላቸዉ ላይ እንጨት አየሰደዱ ሀኪሞችን እጅግ እያሳዘኑ ይገኛሉ።

መንግስት ይህንን ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ፈትሾ መፍትሄ ቢሰጥ መልካም ነው።

12/01/2022

በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል በአንድ እናት የወሊድ ወቅት የተከሰተ ድርጊትን በተመለከተ ትናንት ምሽት መረጃ አቅርቤ ነበር!

ይህን ተከትሎ የሆስፒታሉ ኃላፊዎች በቀኑ ስራ ላይ የነበሩት ሰራተኞች ጋር እየደወሉ "ለዚህ ዋጋ ትከፍላላችሁ" እያሉ እንደነበረ ዛሬ ሰምቻለሁ፣ "ሚድያ ላይ አወጣችሁ" ተብለው ማስፈራርያ የደረሳቸው በርካቶች ናቸው። እንደሰማሁት ምናልባትም አንዳንዶችን ከስራ ሊያባርሩ ወይም የሆነ ነገር ለጥፈዉ ሊያሳስሩ ይችላሉ።

እኔ ይህን መረጃ ስፅፈው እርግጠኝነቱን በደንብ አጣርቼ፣ ከዛ ደግሞ መረጃው ቢወጣ የዚህች እናት አሳዛኝ ክስተት ሌሎች ላይ እንዳይደገም ትምህርት ይሆናል በሚል እሳቤ ነበር።

ይህ በሆስፒታሉ ችግሮች እንዳሉ ማሳያ ነው። ሌላው ቀርቶ ትናንት (በቀን 3/5/2014) ሁለት የእናት ሞት ተመዝግቧል (ለዚህም ማስረጃ አለኝ)፣ ምክንያቱ ደግሞ ደም ባለመኖሩ እንዲሁም ኦክስጅን ባለመኖሩና ያለበት ቦታ ለመሄድ አቅም በማጣት ነበር። በተጨማሪም በሆስፒታሉ የባለሙያ የ5 ወር duty ክፍያ አልተፈፀመም።

የማዋለድ አገልግሎት በነፃ በመላው ኢትዮጵያ እየተሰጠ ባለበት ወቅት በዚህ ሆስፒታል እናቶች እንዲህ ሲሆኑ ማየት እና መስማት ይከብዳል። ከዛ ደግሞ አለ የተባለ ችግር ሲነሳ አጣርቶ መልስ ከመስጠት እና ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ የጤና ባለሙያዎችን ማስፈራራት ያልተገባ ድርጊት ነው።

07/12/2021

✍ #ጋንግሪን #ምንድነው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #ጋንግሪን አንድ የሰውነታችን ክፍል( ህዋሶች/ቲሹዎች ) እየሞቱ ሲሄድ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡ ይህም በተለያዩ አደጋዎች ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን በደም እጥረት፣ ምግብ እና ኦክስጅን በማይደርስ ወቅት ይፈጠራል፡፡

👉 #መንስኤዎቹ

🔺 የደም ዝዉዉር እጥረት
🔺 ኢንፌክሽን
🔺 አደጋ (ከፍ ያለ ቁስለት)

👉 #አጋላጭ #ሁኔታዎች

🔺 የስኳር ህመም
🔺 የደም ስር በሽታ
🔺 ከፍተኛ ጉዳት ወይም ቀዶ ህክምና
🔺 ሲጋራ ማጨስ
🔺 አንዳንድ መድሃኒቶች
🔺 በሽታ መከላከል አቅም አነስተኛ ከሆነ
🔺 ውፍረት
🔺 በኮቪድ ቫይረስ ምክንያት በሚመጣዉ ዉስብስብ ችግር
🔺 እንደ እጅ እና እግር ያሉ አካላትን አጥብቆ ለረጅም ሰአት ማሰር

👉 #የጋንግሪ #አይነቶች

⏩ #ደረቅ ጋንግሪን ፡-በአብዛኛው ሰዎች ላይ ትኩሳት የሚኖር ሲሆን የደም ስር ችግር ወይም ሌላ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችን ያጠቃል በአብዛኛው የሚያጠቃው እግር እና እጅን ነው፡፡

⏩ #እርጥብ ጋንግሪን ፡- ይህ የጋንግሪን አይነት የሚመጣው በኢንፌክሽን አማካኝነት ሲሆን በአብዛኛው በቃጠሎ እና በአደጋ አማካኝነት የሚጎዳ የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት የጋንግሪን አይነት ነው፡፡

⏩ #ውስጣዊ ጋንግሪ፡- የሚከሰተው ውስጣዊ የሰውነት ክፍላችን ላይ ሲሆን ወደ ውስጣዊ ሰውነታችን የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው፡፡

👉 #ምልክቶች

🔺 የመቀዝቀዝ እና የመደንዘ ስሜት መኖር
🔺 የደረቀ እና የተጨማደደ ቆዳ መኖር
🔺 የቆዳ ቀለም መቀየር (መጥቆር ሰማያዊ መሆን)
🔺 ማበጥ እና ባበጠው አከባቢ ህመም መኖር
🔺 ትኩሳት

👉 #ህክምና

🔺 እንደተጠቃው የሰውነት ክፍል ስፋት ሕክምናው ሊለያይ ይችላል፤ ሁኔታው በጊዜ ከተደረሰበት በሕክምና ሊድን ይችላል፤ ነገር ግን የተስፋፋ ከሆነ በሕክምናው አብዛኛውን ጊዜ የተጎዳውን በድን አካል ቆርጦ እስከ ማስወገድ ሊደርስ ይችላል።
🔺 የተለያዩ አንቲባዮቲክ መዳኒቶችን በመውሰድም ይታከማል በቶሎ ወደ ህክምና ከሄዱ

👉 #መከላከያ #መንገዶቹ

🔺 እንደ ስኳር ፣ግፊትና ተያያዥ የጤና ችግሮችን በአግባቡ መከታተል
🔺 ቁስል ሲኖረን ንጽህናውን መጠበቅና የህክምና እርዳታ ማግኘት
🔺 እግርና እጅን ከድርቀት መጠበቅ
🔺 የሰውነት ክብደትን ማመጣጠን
🔺 ሲጋራ አለማጨስ…

👉👉 #ትንሽም ቁስል በሰውነቶ ቢኖር በተለይ በእግርና በእጆ ችላ ሳይሉ ይንከባከቡ ምክንያቱም ለጋንግሪን መነሻ ምክንያት ነውና ፡፡ በዚህና ተያያዥ የጤና ችግር ዙሪያ ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ ፡፡ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!! ይደውሉ ይማከሩ!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን፡
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅ የዶክተር አለ 8809 የዩቱብ ቻነል፦ 👉
https://www.youtube.com/ / channel UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ

( #በጤና #ባለሙያ #ስጦታ)

30/11/2021
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa